Archives

All posts for the month May, 2015

እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ አደረሳችሁ

“ወይቤሎሙ ከማሁ ጽሑፍ ከመይትቀተል ክርስቶስ ወይትነሣእ እምነ ምዉታን በሣልስት ዕለት፡፡ ወይሰብኩ በስሙ ለንስሓ ወለኅድገተ ኀጢአት ለኵሉ አሕዛብ እኂዞሙ እምኢየሩሳሌም፡፡ ወአንትሙሰ ሰማዕቱ ለዝንቱ ነገር፡፡ ወናሁ አነ እፌኑ ተስፋሁ ለአቡየ ላዕሌክሙ፣ ወአንትሙሰ ንበሩ ሀገረ ኢየሩሳሌም እስከ ትለብሱ ኀይለ እምአርያም፡፡ ክርስቶስ እንዲሞት በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ እንዲነሣ እንዲሁ ተጽፎአል አላቸው፡፡ ንስሓ እንዲገቡና ኀጢአታቸው እንዲሰረይላቸው፣ ከኢየሩሳሌም ጀምረው ለሕዝቡ ሁሉ በስሙ ያስተምራሉ፡፡ እናንተም ለዚህ ነገር ምስክሮቹ ናችሁ፡፡ እነሆ እኔ የአባቴን ተስፋ ለእናንተ እልካለሁ፣ እናንተ ግን ከአርያም ኀይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ተቀመጡ፣” (ሉቃ. 24÷46)፡፡ ሲል እርሱ መከራ መስቀልን ሊቀበል፣ ምስጢረ መስቀልን ሊፈጽም በመጻሕፍት እንደ ተገለጠና ያም እንደ ተፈጸመ፣ አሁንም መነሻው ከኢየሩሳሌም ኾኖ በኦሪት፣ በጣዖት  ተለያይተው፣ በኀጢአት ገመድ ታሥረው ለኖሩ ኹሉም ወደ ክርስቶስ እንዲመለሱ፣ የነበሩበትን ትተው፣ ተጠጥተው በጥምቀት እንዲታደሱ፣ የኀጢአታቸውን ሥርየት እንዲቀበሉ የወንጌል ትምህርት ለኹሉ እንደሚሰጥ፣ እርሱም ከአብ ዘንድ እልክላችኋለሁ ያላቸውን ተስፋ እንደሚያጸናላቸው፣ እነርሱም ባዩት፣ በሰሙት፣ በተማሩት ሊመሰክሩለት እንደ ተመረጡ ካስረዳቸው በኋላ ኀይልን ከአርያም እስኪለብሱ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ አዘዛቸው፡፡

Continue Reading


አመ ዐሥሩ ወአሚሩ ለሚያዝያ

ኮኑ ኢትዮጵያውያን ሰማዕታተ በሀገረ ሊብያ

Martyrሰማዕት ቃሉ የግዕዝ ሲሆን ከሁሉት ሥርወ ግሥ የተገኘ በመሆኑ ሁለት ትርጉም ይኖረዋል።

  1. ስማዕት የሚለው ቃል ሰምዐ መሠከረ ከሚለው ግስ ሲወጣ ሰማዕት ምስክር የሚል ትርጉም ይኖረዋል
  2. ስማዕት የሚለው ቃል ሶዐ አረደ ሠዋ ከሚለው ግስ ሲወጣ ደገሞ ሰማዕት የታረደ የተሰዋ መስዋዕት የሆነ ማለት ነው።

ከዚህ በመነሣት ሰማዕት ማለት ያመነበትን የክርስትና /ሃይማኖት እምነት መስክሮ ስለ እምነቱ መስዋዕት የሆነ፣ ሕይወቱን ለሃይማኖቱ ለእምነቱ መስዋዕት አድርጎ ያቀረበ የእምነቱ ምስክር ማለት ነው። ለዚህም ፍትሕ መንፈሳዊ ስለ ሰማዕታት በሚናገረው አንቀጹ 20፡ ቍ.744፡- ብፁዕ ኤጲስ ቆጶስ ያዕቆብና ቅዱስ እስጢፋኖስ በእኛ ዘንድ የከበሩ እንደሆኑ ሰማዕታት በእናንተ ዘንድ የከበሩ ይሁኑ፡፡ በማለት ሁለቱን በሐዲስ ኪዳን የተጠቀሱ የጌታችን ተከታዮችን ለሰማዕትነት ምሳሌ አድርጎ ጠቅሷል፡፡ እነሱም በእግዚአብሔር ዘንድ የተመሰገኑና ትሩፋታቸውም የማይገኝ ነው በማለት ተነግሯል፡፡ Continue Reading

ይህ መጽሐፍ ስለ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ትምህርተ ሐይማኖት፣ ስለ ቤተክርስቲያን ሕግ፣ ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ ኃላፊነት አካላት እና አሰራር . . . የመሳሰሉ ብዙ ቁምነገሮች ያሉበት ስለሆነ አውርደው ቢያነቡት ይጠቀሙበታል በሚል በዚህ ገጽ ላይ አስቀምጠንላችኋል። የህንን church law (YETRMEW) በመጫን ሙሉ መጽሐፉን ያገኛሉ።

በአሁን ዘመን የቤተክርስቲያን ወጣቶች ከራሳቸውም ከውጭም በሚመጣ ፈተና ሊኖሩ የሚፈልጉትን እና መኖር ያለባቸውን ክርስቲያናዊ ሕይወት እንዳይኖሩ እያደረጋቸው መሆኑ ይታወቃል።

በመሆኑም ወጣቶች ከተለያዩ ፈተናዎች እራሳቸውን እንዲጠብቁ እና መኖር የሚገባቸውን ክርስቲያናዊ ሕይወት ይኖሩ ዘንድ የሚረዳቸውን መጽሐፍ በማዘጋጀት ይጠቀሙበት ዘንድ በዚህ ገጽ ላይ አስቀምጠናል። ይህንን Wetatnet   በመጫንም ሙሉ መጽሐፉን ታገኛላችሁ።

የመጽሐፉን ይዘት፡ Continue Reading

ጌታችን የተናገረው የቅ/ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ

ገጽ ፪፻፬፮ አንቀጽ ፴፭

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ባሕርይ አባቱ ሊአቀርበን ኃጢአት ሳይኖርበት ለእኛ ለአመፀኞች ሰዎች  በኃጢአታችን ምክንያት የማይሞተው አምላክ ሞተ።

እኛን ለማዳን በለበሰው ሥጋ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቢሞትም በመለኮቱ ግን ሕያው ነው (፩ኛ ዼጥ ፫፥፲፫)

የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንና ኃጢአታችንን ተሸከመ፤ ስለ መተላለፋችን ሕጉንና ትእዛዙን በማፍረሳችን ስለ እኛ ቆሰለ፤ ስለ በደላችን ደቀቀ፤ ማለትም ሥጋውን ቆረሰ ደሙን አፈሰሰ በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፤ ከሲኦል ወደገነት፣ ከውርደትና ከኃሳር ወደክብር ተመለስን። የዓለም ሁሉ መድኃኒት የሁላችንን ዕዳ፣ ፍዳ በደል በእርሱ ላይ አኖረ (ኢሳ ፶፫፥፬-፭)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመለኮቱ ስቃይ ሳይኖርበት እኛን ከሥቃይ ለማዳን ሲል በለበሰው ሥጋ ተጨነቀ፣ተሠቃየ፣ለመታረድ እንደ ሚነዳ በግ (ጠቦት) በሸላቾቹም ፊት ዝም እንደሚል ይህ ሁሉ መከራ በእርሱ ላይ ሲፈጸም ስቃዩ በዛብኝ መከራው ፀናብኝ ብሎ አልተናገረም፣ (አፉን አልከፈተም)ይልቁንም ስለሕዝቡ ኃጢአት ተገርፎ ተሰቅሎ ነፍሱን ከሥጋው ለየ።

Continue Reading

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

‹‹… ለዘለዓለም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ የሠራኸውን ቤት ቀድሻለሁ። ዓይኖቼና ልቤም በዘመኑ ሁሉ በዚያ ይሆናሉ›› (ቀዳማዊ ነገሥት ፱፥፫)።

በአ/አበባ ሀ/ስብከት እስካሁን ከተሠሩ ዘመናውያነ አብያተ ክርስሪያናት ሊጠቀሰ የሚችለው የአየር ጤና ኪዳነ ምሕረት ቅዳሴ ቤቱ በሚከበርበት ዕለት ይህን መልክት ሳለተላልፍ የሚሰማን መንፈሳዊ ደስታ እጅግ ከፍ ያል ነው።

በሕዝበ ክርስቲያኑ አማካይነት ምን ያህል እንደተደከመበት እናውቃለንና ምእመናን ቤታችን፣ ንብረታችን፣ ትዳራችን፣ ሀብታችን ሳይሉ በከፍተኛ ትዕግሥትና ተአማኒነት፣ ጥበብና አስተዋይነት ይህን ታርክ፣ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ለቅዳሴ ቤቱ ላበቁት ምእመናን፣ ምእመናን በተላበሰ የኮሚቴው አባላት እግዚአብሔር አምላክ ዋጋቸውን ይክፈላቸው ዘንድ ከልብ እንጸልያለን፣ ሥራቸውንም እናደንቃልን።

Continue Reading

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!!

ከዚህ በፊት በሜዲካል መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥር 2007 በወጣው እትም ላይ ከአዘጋጁ ጋር ቤተ ክርስቲያን ስለምትደግፋቸውና ስለምትቃወማቸው ሳይንሳዊ ጉዳዮችን ያደረኩትን ቃለ ምልልስ ተከትሎ ሦስት አንባብያን ጥያቄዎችን በዚሁ የሜዲካል መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 11 ጥር 2007 እትም ላይ አቅርበዋል፡፡ እነዚህም፡-

  • “ብዙ ተባዙ” የሚለው ቃል ከድህነት አንጻር ምን ያህል ተለይቷል?
  • ቤተ ክርስቲያኗ የደም ዝውውርን ከፈቀደች ስለምን የማህፀን ኪራይን ተቃወመች?
  • ማንን ልከተል አቡነ ሳሙኤል ወይስ ሂፓክራተስን? የሚሉ ናቸው፡፡ የሰው ልጅ እንድሚታወቀው ሁልጊዜ ጠያቂ ነው፡፡ ይህም ተፈጥሮአዊና ተገቢም ነው፡፡ ሰው ጥያቄዎችን በመጠየቅ በርካታ ጠቀሜታዎችን የሚያገኝ ሲሆን በጥቅልል ግን ጥያቄዎችን በመጠየቅ በሚያገኘው ምላሽ 1. የማያውቀውን ያውቅበታል 2. ያልገባውን ይረዳበታል 3. የተጠራጠረውን ያረጋግጥበታል፡፡ 4. ባለው ዕውቀትም ላይ ጭማሪ እውቀት ይገኛል፡፡ በመሆኑም ጥያቄውን ያቀረባችሁት ሁላችሁንም ለጠየቃችሁት ጥያቄ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮና እንዲሁም አሁን ካለው የዓለማችን ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ምላሽ እሰጣለሁ፡፡ የምሰጠው ምላሽም እንደ ሃይማኖት አባት መጽሐፍ ቅዱስ ላይ መሰረት ያደረገ ይሆናል፡፡

Continue Reading

በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሟል

ነሥአ ደዌነ ወፆረ ሕማመነ የእኛን ደዌ ተቀበለ ሕመማችንንና ኃጢአታችንን ተሸከመ ስለ መተላለፋችን ሕጉንና ትእዛዙን በማፍረሳችን ስለ እኛ ቆሰለ፣ ስለ በደላችን ደቀቀ፣ ማለትም ሥጋውን ቆረሰ ደሙን አፈሰሰ በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደገነት ከውርደትና ከኃሳር ወደክብር ተመለስን፡፡ የዓለምን ሁሉ መድኃኒት የሁላችን ዕዳ፣ ፍዳና በደል በእርሱ ላይ አኖረ (ኢሳ. 53÷4-5)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመለኮቱ ስቃ ሳይኖርበት እኛን ከሥቃይ ለማዳን ሲል በለበሰው ሥጋ ተጨነቀ፣ ተሠቃየ፣ ለመታረድ እንደሚነዳ በግ (ጠቦት) በሽላቾቹም ፊት ዝም እንደሚል ይህ ሁሉ መከራ በእርሱ ላይ ሲፈጸም ስቃዩ በዛብኝ መከራው ፀናብኝ ብሎ አልተናገረም፣(አፉን አልከፈተም) ይልቁንም ስለሕዝቡ ኃጢአት ተገርፎ ተሰቅሎ ነፍሱን ከሥጋው ለየ፡፡

Continue Reading

አማን ተንሥአ እግዚአብሔር

ጌታ በእውነት ተነሥቷል

The Lord is risen in deed   ሉቃ ፳፬፥፴፫ / Luke 24-34

ቸሩ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር አምላክ በሰላም በጤና በሕይወት ለ፳፻፯ ዓ.ም እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረስዎ!

‹‹ኦ አቡነ ዮም ፍስሓ ኮነት ለነ››

አባታችን ሆይ ዛሬ ለእኛ ደስታ ሆነችልን!

ደዌ ነፍስ፣ ደዌ ሥጋ፣ ሞተ ሥጋ፣ ሞተ ነፍስ፣ ጠፋ። መቃብር ተዘጋ፣ ሞት ድል ተነሣ፣ መበስበስ ቀረ፣ሐዘን ተሻረ፣መከራ ተዘነጋ፣ የሕይወት መገኛ መንግሥተ ሰማያት ተገለጠ። የሁሉ ቤዛ ጌታ ያድነን ዘንድ በእኛ ኃጢአት ተሰቅሎ ሞቶ ሞትን ድል አድርጎ ተነሥቶአልና  (ዕዝ ሱቱ ፯፥፶፫)

Continue Reading

ሰላም በምድር ለሰው ልጅ ሁሉ!!

ሰላም፣ ፍቅር፣ ስምምነትና ዕርቅ እንደዚሁም እውነተኛ የማኅበረሰብእ እኩልነት ነው። ሰላም፣ሁለት ተቃራኒ ወገኖች የሚያገኙት እኩል ሚዛናዊ ፍትሕ ነው።

ሰላም የጦር መሣሪያን መቀነስና ጦርነትን ማቆም፡ ከሰዎችም መካከል የጥላቻ መወገድ ብቻ እንዳይደለ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ተናግሮአል።

ሰላም በየትኛውም አቅጣጫ የሕይወትን ሁለተንተናዊ ፍጹምነት የሚያመለክት ነው። የሀገርን ዕድገት ብልጽግና፣ትምህርትና ጤናን፣እንዲሁም ሕይወት በጠባይዓዊ ሞት እስኪፈጸም ድረስ ያለውን ረዥም ሕይወት ይገልጣል። ግላዊና ማኅበራዊ ደህንነትን ፀጥታና መረጋጋትንም ያሳያል። /ዮሐ. 20፥19/

ሰላም በምድር ለሰው ልጅ ከሚያስፈልጉ እጅግ የከበሩና የተወደዱ ከሁሉም ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ነገሮች ሁሉ በላይ ነው።

ቅዱስ ጳወሎስ “ያለ ሰላም እግዚአብሔርን ማየት የሚችል የለም” ይላል /ዕብ. 12፥14 /ሰው ያለ ሰላም ማየት የማይችለው እግዚአብሔርን ብቻ አይደለም። ባልንጀራውንም ያለሰላም ማየት አይችልም። ሰላም የሌላቸው ወገኖች ሊተያዩና  ሊነጋገሩ አይችሉም።

Continue Reading