Archives

All posts for the month June, 2015

“ሑሩ ውስተ  ዂሉ ዓለም ወስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ጥፍረት

ወደ ዓለም ሁሉ ሒዱ፣ለፍጥረትም ሁሉ ወንጌልን ስበኩ፤”

ማር.16፥15።

‹‹በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና›› እንዳለው ዮሐ 3፥16 በዚህ አምላካዊ ፍቅር ሁላችንም በመስቀሉ ተሰባስበን ለእኛም ያለውን ፍቅሩን ማሳየት ብቻ ሳይሆን ስለሰጠን ዛሬም ማንኛውም ክርስቲያን የቀለም፣ የቋንቋ፣ የነገድና የጾታ ልዩነት ሳያደርግ ሁሉንም በክርስቶስ ፍቅር አንድ አድርጐ ይመለከታል፣ ሥርዓቱም ትምህርቱም ይህ ነው።

1ኛ ጴጥ 4፥7/ ዮሐ 15፥12

የክርስትና ሃይማኖት ሰውን በሰውነቱ የማክበር ሥርዓት ያለው ሃይማኖት ነው Continue Reading

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተ ክርስቲያን ገዳማት

ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ሊቃውንት፣ መነኵሳት ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ በዱር በገደል፣ በእሳት፣ በስለት፣ በረሀብ፣ በእርዛት፣ በጾም፣ በጸሎት፣ በምናኔ እየተንገላቱ መከራ ተቀበሉት ለሃይማኖታቸው ለምግባራቸው፣ ለሥርዓታቸው፣ ለሀገራቸውና ለወገናቸው ነው ለእምነታቸው፣ የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት በማስተማርና በማስከበር ሁሉን የእግዚአብሔርን ስም ይጥራ፣ ሁሉም ከእግዚአብሔር የተገኘነውና በእግዚአብሔርም የሚረዳ ነው፣ በማለት ነው።

እነ ኤልያስ፣ እነ ኤርምያስ፣ እነ ኢሳይያስ በድንግልና በብሕትውና በማስተማር፣ ነገሥታት ነን ባዮችን፣ ድሀ አትበድሉ፣ ፍርድ አታጓድሉ፣ ጣዖት አታምልኩ፣ በእግዚአብሔር እመኑ በማለት የሰውን ነጻነት የእግዚአብሔርን ቸርነት ለመመስከር የአመቻቸው ብቸኝነታቸው ነው። ያስተማሯቸውም ለሰው ሕይወት ለሀገር ደኀንነትና ነጻነት ነው። Continue Reading

ሙሴ ጸሊም

Moses the Ethiopian

Moses the Ethiopian

አባ ሙሴ ጸሊም ይባላሉ፣ ሙሴ ኩሻዊ፣ ሙሴ ኢትዮጵያዊ ለማለት ነው፡፡ በግሪክ ቋንቋ ኢትዮጵያዊ ማለት ጠይም ገጽ ማለት ነው፡፡ ሙሴ ጸሊም ማለት ሙሴ ኢትዮጵያዊ ማለት ነው፡፡ ሰኔ 24 ቀን የሚነበበው የግእዝ ስንክሳር እና በርካታ ዓለም አቀፍ ታሪክና የሥርዓተ ምንኵስና መጻሕፍት ስለ አባ ሙሴ ጸሊም ብዙ መረጃዎችን ጽፈዋል፡፡

ስንክሳር ዘሰኔ 24 በዚህች ቀን ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አባ ሙሴ ጸሊም አረፈ፡፡ አስቀድሞ ሽፍታ፣ ወንበዴ፣ ዘማዊ ፣ጣኦት አምላኪ ነበር፤ በኃላ እንደ አብርሃም አምላኬ ማን ነው? ብሎ ተመራመረ፤ ወደ አስቄጥስ ገዳም ብትሄድ አምላክህ ማን እንደሆነ የበረሐ መነኰሳት ይነግሩሃል የሚል ራዕይ አየ፣ ተመለከተ፤ ተነስቶም ሄደ፡፡

አባ ኤስድሮስን አገኛቸው፤አጽናንተው አረጋግተው ወደ አባ መቃርስ ወሰዱት አባ መቃርስም ንሥሓውን ተቀብለው ቀኖና ሰጡት ኋላም አመነኰሱት ፤ የሽፍቶች አለቃ የነበረው የመነኮሳት አለቃ እስከመሆን ደረሰ፡፡ ሰይፉን ወርውሮ ከፍቅር ጋር ተወዳጀ፤ሌሊት እየተነሣ ለሁሉም መነኮሳት ውኃ ይቀዳላቸው ነበር፤ ለሁሉም ይታዘዛቸው ነበር ትንሹም ትልቁም ሙሴ ይህን አድርግልኝ ይሉታል አርሱም ሁሉንም እሺ ይላል፤ ራሱን ዝቅ አደረገ ትሁትም ሆነ፤ በጸሎቱ ዝናብ ያዘንም ነበር፡፡ Continue Reading

ክፍል ሁለት

ጎጂ ባህልን በጠቃሚ ባህል እንከላከል፣

ማንኛውም ሕብረተሰብ በሚኖርበት አካባቢ የራሱ የሆኑ ባህልና ልማድ ወግና ሥርዐት አሉት። ዓይነቱና ይዘቱ ገቢሩም ይለያይ እንጂ ያለ ባህልና ልማድ የሚኖር ሕብረተሰብእ አለመኖሩ  የታወቀ ነው።

ሀገራችን ኢትዮጵያም ብዙዎች በሔሮችና ብሔረሰቦች ያሏት እንደመሆኗ መጠን ብዙና የተለያዩ ባህልና ልማድ የሚገኙባት ሀገር ናት። ቢሆንም ባህሎች ሁሉ ጠቃሚዎች አይደሉም፣ በሕብረተሰብኡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያመጡ ባህሎች መኖራቸው የታወቀ ነው። ደግሞም ባህሎች ሁሉ ጎጂዎች አይደሉም። የሀገርን ነጻነትና ሥልጣኔ  እምነትንና ታሪክን የሚያንፀባርቁ ባህሎች አሉ ለምሳሌ፡- Continue Reading

ክፍል አንድ

  1. መግቢያ

በሰው ልጆ ታሪክ ውስጥ ዓለማችን የስልጣኔ ጫፍ ላይ የደረሰችበት እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማዕበል የተጥለቀለቀችበት ዘመን ይህ እኛ የምንኖርበት ሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው። ሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን የመረጃ፣ የቴክኖሎጂ፣ የሉአላዊነት /Globalization/ ዘመን እየተባለ ይጠራል። ሥልጣኔው እና ቴክኖሎጂው የሰው ልጆችን አኗኗር ቀላል ከማድረጉ ባሻገር የተለያዩ እድሎች እና አማራጮች ተጠቃሚ አድርጓል። በዚህ የተነሳ የሰው ልጆች የአኗኗር ዘይቤ እጅግ በፍጥነት እየተለወጠ ሊሔድ ችሏል ።

በዚህ ዘመን የሚኖሩ ወጣቶች የስልጣኔው እና የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ መሆናቸው እንደ መልካም እድል ቢቆጠርም ለውጡ ያመጣቸው ችግሮች እና ፈተናዎች ደግሞ የወጣቶችን ሕይወት እጅግ ከባድ አድርጎታል። ወጣቶች ብዙ ግራ የሚያጋቧቸው፣ የሚያስጨንቋቸው እና ጫና የሚፈጥሩባቸው ከዘመኑ ጋር ተያይዘው የመጡ ችግሮች አሉ። ይህም በትምህርት ቤት፣ በወጣቶች መካከል ያለው ውድድር እና ፉክክር (በውጤት፣ በውበት፣በልብስ፣በሥራ)—– ወ.ዘ.ተ በዚህ ምክንያት አንዳንድ ወጣቶች የወደፊት ሕይወታቸው ጨለማ እና አስቸጋሪ እንደሆነ አስበው ከወዲሁ ተስፋ በመቁረጥ ይጨነቃሉ፣የመኖር ትርጉሙ ጠፍቷቸው በድብርት/ድብት/ ይሰቃያሉ። Continue Reading