Archives

All posts for the month July, 2015

ወአጽዐንከ ሰብአ ዲበ አርእስቲነ፤ አኅለፍከነ ማዕከለ እሳት ወይማይ፤ ወአውፃእከነ ውስተ ዕረፍት፡፡

(መዝ. 65÷12-13)

“እውነት እላችኋሁ፣ ካልተመለሳችሁና፣ እንደ ሕፃናት ካልሆናችሁ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም፤ እንደዚህም ሕፃን ራሱን ዝቅ የሚያደርግ በመንግሥተ ሰማያት የሚበልጥ ይህ ነው፡፡” ማቴ. 18÷1-2፡፡

Abuneጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእስራኤል ምድር በሚያስተምርበት ወቅት ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀርበው “በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጥ ማን ነው?” ሲሉ ጠየቁት፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የምድራዊ ክብርና የሹመት ስሜት በልባቸውና በሐሳባቸው መኖሩን ስላወቀ ጌታችን ስለ ትሕትናና ራስን ዝቅ ዝቅ ስለማድረግ ያስተምራቸዋል፡፡ በአካባቢው ከነበሩት ሕፃናት መካከል አንድ ሕፃን ወስዶ በመታቀፍ “ካልተመለሳችሁና እንደዚህ ሕፃን ካልሆናችሁ ወደ መንግሥተ ሰማያ መግባት አትችሉም፤” አላቸው፡፡ እንደ ሕፃናት ካልሆኑ በመንግሥተ ሰማይ መብለጥ ሳይሆን መግባትም እንዳማይቻል ለደቀ መዛሙርቱ በአጽንኦት ገለጠላቸው፡፡ በጌታችን ትምህርት መሠረት ወደ መንግሥተ ሰማይ ለመግባት እንደ ሕፃናት መሆን አለብን፡፡ ይህ ምን ማለት ነው? መቼም ተመልሶ ሕፃን መሆን አይቻልም፡፡ ጌታም በዕድሜና በአካል እንደ ሕፃናት ሁኑ ማለቱ አይደለም፡፡ በጠባያችሁ እንደ ሕፃናት ሁኑ ማለቱ ነበር እንጂ፡፡ ሕፃናት የዋሆች ናቸው ቂም በቀል አያውቁም ቂም አይዙም ጸባቸውን ከጥቂት ጊዜ በኋላ ይረሱታል፡፡ ሕፃናት ሌላም በዐዋቂዎች ዘንድ የማይገኙ ብዙ ጥሩ ጠባዮች አሏቸው በወላጆቻቸው ላይ ከፍተኛ ፍቅርና እምነት አላቸው፡፡ ወላጆቻቸውን ማፍቀር ብቻ ሳይሆን በእነሱ ላይ ታላቅ እምነት አላቸው ሕፃናት ከወላጆቻቸው ጋር ከሆኑ ከምንም ነገር አይፈሩም፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ጌታችን ሁላችሁንም “እንደገና ካልተወለዳችሁ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት አትገቡም” ይለናል፡፡ እንደ ሕፃናት ካልሆናችሁ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት አትገቡም ይለናል ምናልባት ክፉ ሥራ በመሥራት የኃጢአት ሥራ በመሥራት እግዚአብሔርን አስቀይመነው ይሆናል ጎረቤቶቻችንን፣ ወንድሞቻችንን፣ እህቶቻችንን አስቀይመን ይሆናል፡፡ ቂም በቀልም ይዘን ይሆናል እንግዲህ ክፉ ሥራችንን እርግፍ አድርገን በመተው ያስቀየምነውንም ይቅርታ በመጠየቅ እኛንም ያስቀየሙንን ይቅር በማለት ወደ እግዚአብሔር ከተመለስን አዲስ ሰዎች አዲስ ልጆች ሆንን ማለት ነው፡፡ ይህን ከአደረግን ቸሩ እግዚአብሔር የምንጠይቀውን ሁሉ ይሰጠናል፡፡ እንግዲህ ጌታችን እኛ ሁላችንም እንደ ሕፃናት እንድንሆንና በማንም ሰው ላይ ቂም በቀል እንዳንይዝ ይጠይቀናል፡፡ ስንት ሰዎች ነን ከወንድሞቻችን ከእኀቶቻችን ከጎረቤቶቻችን ጋር የተቀያየምን? አባቶቻችን የሚሉትን ታውቃላችሁ? “ቂም ይዞ ጸሎት ሳል ይዞት ስርቆት” ፈጽሞ አይቻልም ይሉናል፡፡ ከወንድሞቻችን ጋር ከእኅቶቻችን ጋር ከጎረቤቶቻችን ጋር ተቀያይመን ሳንታረቅ ወደ ቤተ ክርስቲያን መምጣትና መጸለይ ዋጋ የለውም፡፡ ጸሎታችን ቅድመ እግዚአብሔር ፈጽሞ አይደርስም፡፡ የምንሰጠውም ስጦታ/ሙዳየ ምጽዋእት በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የለውም፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ይለናል፡- “መባህን (ስጦታህን በመሠዊያው ፊት በምታቀርብበት ጊዜ ያስቀየምከው ወይም የተጣላህ ወንድምህ መኖሩን ካስታወስክ መባህን ከማቅረብህ በፊት መጀመሪያ ሔደህ ከወንድምህ ጋር ታረቅ ከዚያም በኋላ ተመልሰህ መባህን አቅርብ” ይለናል (ማቴ. 5÷23-24)፡፡ Continue Reading

Aba Samuel-‹‹ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው እነዚያ አገልጋዮች ብፁዓን ናቸው እውነት  እላችዋኋሁ  ወገቡን ታጥቆ በማዕድ ያስቀምጣቸዋል፣ቀርቦም ያለግላቸዋል›› (ሉቃ 12፥37)
ይህ አገልግሎት በሚል ርእስ የተጻፈ ጽሑፍ የአገልግሎትን ምንነት፣ አገልግሎት በሰማያውያን ፍጥረታት በመላእክት እና በምድራውያኑ በደቂቀ አዳም ወይም በሰው ልጆች ዘንድ፣ የአገልግሎት ዓይነቶች፣ በአገልግሎት ወቅት የሚገጥሙ ፈተናዎች ሊኖር ስለሚገባው ጽናት፣ በአገልግሎት ወቅት በምእመናን በአገልጋዮች ሊኖር ስለሚገባው መጠኑን የጠበቀ ግንኑነት፣ ለአገልግሎት የሚሾም እግዚአብሔር ስለመሆኑ እና ተዛማጅ በአገልግልት ላይ የተቀመጡ መመሪያዎችን የሚያሳየን ጽሐፍ ነው።

ይህ ጽሑፍ የተጻፈበት ዓላማም ‹‹ከሌሊቱም በሁለተኛው ወይም በሦስተኛው ክፍል መጥቶ እንዲሁ ቢያገኛቸው እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው›› (ሉቃ 12፥38)ተብሎ እንደተጻፈ አገልጋዮች የአገልግሎት ጸጋ የሰጣቸውን እግዚአብሔርን እየተመለከቱ እንዲያገለግሉ ለማበረታታት ምእመናን ከአገልጋዮች ጋር ሊኖራቸው ስለሚገባው ግንኙነት ለመግለጽ በአገልግሎት ወቅት የሚገጥሙ ፈተናዎችን በመጠቆም አገልጋዮች በፈተና የጸኑ ይሆኑ ዘንድ ለመምከር ታስቦ ነው።

ስለዚህ አንባብያን ይህን ጽሑፍ በማንበብ ለአገልግሎት የበረታ ሰብእናን ገንዘብ እንዲያደርጉ፣ በአገልግሎት ወቅት የሚገጥሙ አንዳንድ ጥቃቅን ቀበሮዎችን አጥምዶ በመያዝ በፈተና ላለመሸነፍ መንፈሳዊ ወኔን መላበስ እና የምናገለግለው አምላክ የአገልግሎታችንን ዋጋ እንደማያስቀርብን በማመን ምድራዊውን ሳይሆን ሰማያውን ጊዜያዊውን ሳይሆን ዘላለማዊውን በመመልከት በተሰጠን ጸጋ ያለመሰልቸትና ያለማቋረጥ በጊዜውም ያለጊዜውም  በአገልግሎት ስንተጋ ልንገኝ ይገባል #ብፁዓን አግብርት እለ ይረክቦሙ እግዚአሙ መጺኦ እንዘ ይተግሁ፤ ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ ያገኛቸው እነዚያ አገልጋዮች ንዑዳን ክቡራን  ናቸው›› ተብሎ በቅዱስ ወንጌል እንደተነገረን በትጋታችን የምናኛውን ዋጋ እያሰብን ማገልገላችን ለራሳችንም ሆነ ለምናገለግላቸው ተገልጋዮች (ምእመናን) የሚጠቅም መሆኑን ልብ በማለት ማገልገል ይጠበቅብናል። Continue Reading

ምዕራፍ ዐሥራ ስድስት

በ9ኙ የመንፈስ ቅዱስ ተቃዋሚዎችና መናፍቃን መልሶቻቸው ላይ የተሰጠ ግልጽ መልስ

The Work of the Holy Sprit.pdf

Cover Page“ወበእንተሂ ዘመንፈስ ቅዱስ ኢንፈቅድ አኀዊነ ትኩኑ አብዳነ አላ ታእምሩ፡፡ ትካትኒ እንዘ አረሚ አንትሙ ተአምሩ ከመ አማልክተ በአማነ ታመልኩ ወአጣዖክሙ ወተጻእጻእክሙ ወተሐውሩ ኀበ ወሰዱክሙ፡፡ ወንድሞቻችን ስለ መንፈስ ቅዱስ በምታስቡትም አላዋቆች ልትሆኑ አንወድም እንድታውቁ እንጂ፡፡ ቀድሞም እኮ እናንተ አረማውያን ሳላችሁ ዲዳዎችን ጣዖታት ታመልኩ እንደ ነበር ታውቃላችሁ ጣዖትም አምልካችሁ ነበር ረክሳችሁም ነበር፤ ወደ ወሰዱአችሁም ትሔዱ ነበር፡፡” (1ኛ ቆሮ. 12÷1)፡፡

1. ቅዱስ ጳውሎስ ይህን ሲጽፍ፣ ሲናገር፣ ሲያስተምር ስለ መንፈስ ቅዱስ በምናስብበት፣ በምንናገርበት፣ በምንጽፍበት፣ በምናስተምርበት ጊዜ ሁሉ ጥንቃቄ እንድናደርግ ትምህርትና ምክር ይሰጣል፡፡ ቀደም ሲልም በቤተ ክርስቲያን ከተሰበሰቡት፣ ቤተ ክርስቲያን ከምታውቃቸው ታላላቅ ጉባኤያት አንዱ በ380 ዓመተ ምሕረት አካባቢ የሆነው በቁስጥንጥንያ የተሰበሰበውና መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ ያንሳል የሚል የኑፋቄ የክሕደት ትምህርት በቤተ ክርስቲያን የዘራውን የቁስጥንጥንያውን ሊቀ ጳጳሳት መቅዶንዮስን ለማውገዝ የተሰበሰበው የቁስጥንጥንያ ጉባኤ ነበር፡፡ መናፍቁን አውግዞ፣ ከሹመቱ ሽሮ፣ “ሕያው ማኅየዊ ጌታ በሚሆን በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን” የሚል የትምህርተ ሃይማኖት ውሳኔ ሰጥቶ ተነሥቶአል፡፡

2. ትምህርቱም ቀደም ብሎ በ328 ዓመተ ምሕረት በኒቅያ ጉባኤ ከተወሰነው፤ ወልድ ዋሕድ፤ ከሚለው ትምህርት ጋራ በቤተ ክርስቲያን ጸንቶ እስከ ዛሬ አለ፡፡ በኒቅያ ጉባኤ፤ ወልደ አብ ዋሕድ፤ አንድ የአብ ልጅ፤ ተብሎ ወልድ ከአብ መወለዱ እንደ ተገለጠ፤ በቁስጥንጥንያ ጉባኤም ዘሠረጸ እምአብ ከአብ የሠረጸ ተብሎ ስለ መንፈስ ቅዱስ ተነግሯል፡፡ ይህ ውሳኔ “መንፈሰ ጽድቅ ዘይወፅእ እምኀበ አብ ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ፤” ባለው በጌታ ቃል ላይ የተመሠረተ የጸና እንጂ ልብ ወለድ አነጋገር አይደለም፡፡ (ዮሐ. 15÷26)፡፡ “ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር የምወደው ልጄ ይህ ነው” የሚለው የአብ ምስክርነት ወልድ ከአብ መወለዱን እንደሚያስረዳ (ማቴ. 17÷5)፡፡ “ከአብ የወጣ የእውነት መንፈስ፤” የሚለው የጌታ ምስክርነትም መንፈስ ቅዱስ ከአብ ብቻ መሥረጹን ለቤተ ክርስቲያን ሲያስረዳ ሲመሰክር ሲያስተምር የሚኖር ቀዋሚ ምስክር ነው፡፡ ማንም ሊቃወመው ሊያስተባብለው አይችልም፡፡ Continue Reading

ብፁዕ አባታችን አቡነ ሳሙኤል የሀዋሳ ደ/ሰ/ቅ/ሥላሴ  ቤተ ክርስቲያን ሲመርቅ ያስተላለፉት መልእክት

ዘፍ 18፥1 ወአስተርዮ እግዚአብሔር ለአብርሃም በኀበ ዕፀ ምንባሬ

ብጹእ አቡነ ሳሙኤል በዓሉ ላይ ሲያስተምሩ

ብጹእ አቡነ ሳሙኤል በዓሉ ላይ ሲያስተምሩ

እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ስር ለአብርሐም ተገለጠለት የአብርሃም  አምልኰ የሕይውት ጉዞ የሚጀመረው በመገለጥ ነው። አብርሃም ከጣኦት አምላኪያን ቤተሰበ የተገኘ ሰው ነው እንዲሁም አባቱ ታራ ጣኦት እየቀረፀ  የሚተዳደር ሰው ነበር በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነው አብርሃም በሥነፍጥርት ተመራምሮ ህያው ያለ እና የሚኖር ፈጣሪውን አምላክ ለማምለክ የተጠራው።

እግዚአብሔርም አለው ዘርህን አበዛዋለሁ ታላቀ ሕዝብም ይሆናል እባርክሃለሁ። ስምህንም ገናና አደርገዋለሁ ለሌሎችም በረከት ትሆናለህ

ዘፍ 12፥1-2

አብርሃም የማያውቀው እግዚአብሔር እርሱን የሚያውቀው ይህ የመለየት ጥሪ ከዘመድህ ከቤትህ ተለይ የሚል መልእክት በዚያን ዘመን እና ጊዜ ይቅርና ዛሬም በእኛ ዘመን እንኳን ቢሆን በጣም አስጨናቂ ነበር በመንፈሳዊ ሕይወት መጀመሪያ  የሚቀድመው መለየት ነው የምንለየውም ከዝሙት፣ከሱስ፣ከሀሰት፣ከስካር፣ ከሙስና በአጠቃላይ ከኃጢአት ሥራ ነው። አብርሃምም በአምነ የእግዚአብሔርን ቃል ወደ አብርሃም መጣ ከዚህ በኋላ አብርሃም ራዕይ አየ እግዚአብሔርም አብርሃም አትፍራ እንደጋሻ ሆኜ ከአደጋ እጠብቅሃለሁ አለው።

ዘፍ. 15፥1-2

አብርሃም በሕይወት ዘመኑ እግዚአብሔርን በማምለክ እንዲኖር እንዳይፈራ እግዚአብሔር ጋሻ እንደሆነ የሚያስረዳ ነበር ነው። አብርሃም የዘለዓለም ቃል ኪዳን ከተቀበለ በኃላ በመልካም ሥራ ተጠምዶ መኖር የጀመረው አባታችን አብርሃም ከሚታወቅበት መልካም ሥራዎቹ ውስጥ አንዱ እንግዳ ተቀባይነቱ ነው። በዚህም ሰዓት ሰይጣን ይቀናበት እና ይበሳጭበት  ነበር አብርሃም ግን በበረከት እየበዛ በሄደበት ሁሉ የእግዚአብሔርን ስም እየጠራ የሚኖር አባት ነበር /ዘፍ 13፥1-5 / Continue Reading

“የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች” /ዮሐ.12÷24/

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ ማርያምን ነሥቶ ፍጹም ሰውነታቸንን  የተዋሐደው ስለ  ስለ እኛ ለመሞት መሆኑን ለደቀ መዛሙርቱ በተለያየ ጊዜያትና ምሳሌያት ይገልጽላቸው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ሞት የሰው ሁሉ ፍርሃት በሆነበት ሁኔታ የቃሉ ምሥጢር ለብዙዎች እንቆቅልሽ ሲሆን ደቀ መዛሙርቱንም ተስፋ ያስቆርጣቸው ነበር፡፡ ሞት በሁሉ ላይ ነግሦ ሲገዛ እንደ ነበር ተጽፏል፡፡ /ሮሜ.3÷14/ መቼም “ነበር” ብሎ ለመናገር የተለወጠ  ነገር መኖር አለበትና ሞት ሁሉን ሲገድል ክርስቶስ ሞትን በሞቱ ድል ነሳው፡፡ በመሆኑም “ሞት ሆይ፣ መውጊያውስ የት አለ?  ሲዖል ሆይ ድል መንሣትህ የት አለ?” ተብሎ እንደ ተጻፈው የትንሣኤው ኃይል ሞትን ታሪክ አደረገው፡፡ “ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ ሞቼም ነበርሁ፣ እነሆም ለዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፤ የሞትና ሲዖል መክፈቻ አለኝ”  /ራእ.1÷13/ ፡፡ Continue Reading

አንድ ታላቅ አባት አሉ፡፡ በኑሮአቸው ሁሉ ያሳለፏቸውን ተሞክሮዎች ሁል ጊዜ ለወጣቶች ማጫወት ያስደስታቸዋል፡፡ ታዲያ ወደ ወጋቸው ከመግባታቸው በፊት ‹‹እሰይ! እንኳን ተወለዳችሁ፤ እግዚአብሔር ያሳድጋችሁ!›› እያሉ ይመርቃሉ፡፡ እውነት ነው፡፡ ማንኛውም ወላጅ የወለደው ልጁ አድጐ ለቁም ነገር እንዲበቃ የዘወትር ምኞቱ ነው፡፡ አበ ብዙኃን አብርሃምም ልጁን ይስሐቅን ጡት ባስጣለበት ቀን ታላቅ ግብዣን ማድረጉ ለዚህ ምልክታችን ምስክር ነው፡፡ ‹‹አብርሃምም ይስሐቅን ጡት ባስጣለበት ቀን ትልቅ ግብዣን አደረገ›› እንዲል /ዘፍ. 21÷8/፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ አብርሃም ይስሐቅን ጡት እንዳስጣለ ይነግረናል እንጂ ይስሐቅ በራሱ ጡት አልጣለም፡፡ ከዚህ የምንረዳው ሥጋዊ ወላጆቻችን ለመውለድ ብቻ ሳይሆን ለማደጋችንም ጭምር እንደሚያስቡና ግድ እንደሚላቸው ሲሆን በመንፈሳዊው ዓለምም በጥንተ ተፈጥሮም ሆነ በዐዲስ ተፈጥሮ የወለደን እግዚአብሔር እኛን ለማሳደግ ከሕፃንነት ወራታችን ጀምሮ እንደሚደክምልን ነው፡፡ Continue Reading