Archives

All posts for the month August, 2015

በቅዱስ መጽሐፍ ሲነጻጸር

እግዚአብሔር ሰውን አክብሮና አልቆ በመልኩ በምሳሌው ፈጠረው፡፡ ሰው ግን እግዚአብሔር ባስቀመጠው የክብር ሥፍራ አልተገኘምና ተዋረደ፡፡፡ ከኃጢአቱም የተነሣ ደሃ ሆኗልና ሰው ሆኖ መፈጠር /መወለድ/ የምሬት ርእስ ሆነ፡፡ ሁሉን አይቶ ሁሉን ማጣት የሰው ልጅ የማይለምደው የኑሮ ጥቁር መልኩ ነው፡፡ ሁሉን ያጣ ሁሉን ሲያገኝ የዕድገት ሕግ ያለው፣ የሚናፈቅ ደስታና ሊተርኩት የሚያስቸኩል የኑሮ ገድል ነው፡፡ ሁሉን አይቶ ሁሉን ማጣት ግን የሚያንደረድር የቁልቁለት ጉዞ፣ ጉልበትን እያዛለ ከዕይታ የሚሠውር፣ ልታይ ልታይ ያለውን ሰብእና ደብቁኝ የሚያሰኝ፣ የማይለምዱትና የማይደፍሩት ሥፍራ ነው፡፡ ስለዚህ ብዙ ሀብት ጨብጣችሁ አግኝቶ እንደማያውቅ ብትቸገሩ ሌሊቱን ያመጣ ቀኑን ያመጣልና በርቱ፡፡ ሀብት በማጣታችሁ ስትበሳጩ ሀብት የማያመጣውን ጤና እንደምታጡ አስቡ፡፡ ወልዳችሁ ሞት ልጆቻችሁን ነጥቋችሁ ከሆነ ማዳን ብቻ ሳይሆን መግደልም የእግዚአብሔር ሥልጣን እንደሆነ በመረዳት ከከንቱ አእምሮ ራቁ፡፡ ሊነጋ የጨለመ እንጂ ጨልሞ ሊቀር የመሸ ሌሊት ስለሌለ በእምነታችሁ ጽኑ! ጌታችን ድል ለነሡ ሽልማት የሚሰጥ ንጉሥ ብቻ ሳይሆን ለወደቁትም ትንሣኤ የሚሆን አምላክ ነውና፡፡

በሥነ ፍጥረት ተመራማሪነቱ የሚደነቅ አንድ የሥነ ሕይወት ሊቅ በባሕር ዳርቻ ዳክዬዎችን እያየ ይመሰጥ ነበር፡፡ ሁል ጊዜ የሚያያቸው እነዚህ ዳክዬዎች በሽታ ገባባቸውና ማለቅ Continue Reading

“ጾም ትፌውስ ቊስለ ነፍስ”  ጾመ ድጓ ቅዱስ ያሬድ

 እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ በሰላም  አደረሳችው

በእየእለቱ የሚነበቡ ምንባባትና  የሚሰበክ ምስባክ ማውጫ (ዘቅዳሴ)

 

ቀን ምንባብ ምስባክ  ትርጉም
ነሐሴ 1 1ኛ ጢሞ 5፥1-1211ኛ ዮሐ 5፥1-6

የሐ.ሥራ 5፥26-34

ሉቃ.1፥39-57

በጽሑ መላእክት ወቦሙ መዘምራን፣ ማእከለ ደናግል ዘባጥያተ ከበሮ በማኀበር ባርክዎ ለእግዚአብሔር መዝ .67፥25  አለቆች  ቀደሙ መዘምራንም ለምስጋና ደረሱ መዘምራንም አሏቸው። ከበሮን በሚመቱ በደናግል መካከል። እግዚአብሔርን በማኅበር አመስግኑት።
ነሐሴ 2  1ኛ ጢሞ 2፥8-ፍም1ኛ ጴጥ 5፥1-7

የሐ.ሥራ 16፥13-19

ሉቃ 18፥1-15

ወይሰግዳ ሎቱ አወልደ ጢሮስ በአምኃ፣ ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር። ኵሉ  ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሀሴቦን፣ መዝ 44፥9  የጤሮስ  ሴት ልጆች እጅ መንሻ ይዘው ይሰግዱለታል። የምድር ባለጠጐች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ። ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብርዋ ነው።
ነሐሴ 3 1ኛ ተሰሎ 3፥1-ፍም1ኛጴጥ 3፥10-15

የሐ.ሥራ 14፥20-ፍም

ማቴ 25፥1-14

አዋልደ ንግሥት ለክብርከ፣ ወትቀውም ንግሥት በየማንከ፣ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት፣ መዝ.44፥9  የንግሥቲቷ ልጆች ለክብርህ ናቸው። በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍናንግሥቲቷ በቀኝህ ትቀመጣለች።
ነሐሴ 4 ሮሜ 12፥16-ፍም 1ኛ ጴጥ 5፥5-12የሐ.ሥራ 17፥23-28

ዮሐ. 12፥24-26

ወይወስዱ ለንጉሥ ደናግለ ድኅሬሃ፣ ወቢጻሂ ይወስዱ ለከ፣ ወይወስድዎን በትፍሥሕት ወበሐሤት መዝ .44፥14 በኋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ ባልንጀሮችዋንም ወደ አንተ ያቀርባሉ በደስታና በሐሴት ይወስዷአቸዋል።
ነሐሴ 5 2ኛ ቆሮ 12፥10-171ኛ ዮሐ 5፥14-ፍም

የሐ.ሥራ 5፥14-ፍም

ሉቃ 13፥10-18

እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ፣ወየሐውር እምኀይል ውስተ ኀይል ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን።መዝ 83፥

 

 

የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳል የአማልክት አምላክ በፅዮን ይታያል
ነሐሴ 6 1ኛ. ቆሮ 3፥10-221ኛ.ጴጥ 3፥1-7

የሐ.ሥራ 16፥13-19

ማቴ. 2፥9-16

ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ሀገእግዚአብሔር፣ እዜከሮን ለረዐብ ወለባቢሎን እለ የአምራኒ፣ ወናሁ ኢሎፍሊ ወጢሮስ ወሕዝበ  ኢትዮጵያ መዝ 86 ፥3 እግዚአብሔር ከተማ ሆይ ባንቺ የተደረገው ነገር ድንቅ ነው።የሚያውቁኝን ረዓብንና ባቢሎንን አስባቸው እነሆ ኢሎፍሊን ጢሮስን የኢትዮጵያንም ሕዝብ አስባቸዋለሁ።
ነሐሴ 7 ዕብ 9፥1-112ኛ ጴጥ 2፥6-18

ዮሐ ሥራ 10፥1-30

ማቴ 1፥1-17

መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፣ ያበድሮን እግዚአብሔር ለአናቅጸ ጽዮን፣ እምኵሉ ተዓይኒሁ ለያዕቆብ መዝ 86፥1 መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው። ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል።
ነሐሴ 8 ሮሜ 9፥24-ፍም1ኛ ጴጥ 4፥12-ፍም

የሐ.ሥራ 16፥35-ፍም ሉቃ 10፥38 -ፍም

ዕግትዋ ለጽዮን ወሕቀፍዋ፣ ወተናገሩ በውስተ ማኅፈዲሃ፣ ደዩ ልበክሙ ውስተ ኃይላ፣መዝ 47-12 ጽዮንን ክበብዋት በዙሪያዋም ተመላለሱ። በቤቷ ሁናችሁ ጸልዩ። ልባችሁም በእሷ ላይ አድርጉት።
ነሐሴ 9 ፊልጵ 1፥12-242ኛ ዮሐ 1፥6-ፍም

የሐ.ሥራ 15፥19-25

ሉቃ 23፥26-31

እስመ ኀረያ እግዚአብሔር ለጽዮን፣ ወአብደራ ከመ ትኩኖ ማኅደሮ፣ ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም፣መዝ 131፥13 እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና፣ ማደሪያው ትሆን ዘንድ ወዷታልና እንዲህ ሲል፦ ይህች ለዘለዓለም ማሪፊያዬ ናት
ነሐሴ 10 ዕብ 12፥22- ፍም1ኛ ጴጥ 1፥6-13

የሐ ሥራ 4፥31-ፍም

ሉቃ 16፥9-17

ተዘከር ማኅበረከ ዘአቅደምከ ፈጢረ፣ ወአድኀንከ በትረ ርስትከ ፣ደብረ ጽዮን ዘኀደርከ ውስቴታመዝ 73-2 አስቀድመህ የፈጠርሃትን ማኅበርህን። የተቤዥሃትንም የርስትህን በትር። በእርስዋ ያደርህባትን የጽዮንን ተራራ አስብ።
ነሐሴ 11 1ኛ ቆሮ 5፥11-ፍም1ኛ ዮሐ 2፥14-20

የሐ.ሥራ 121ኛ ዮሐ 12፥18-ፍም

ሉቃ 61ኛ ዮሐ 2፥20-27

ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ፣ወትሠይሚዮሙ መላእክተ  ለኵሉ ምድር፣ወይዘክሩ ስመኪ በኵሉ ትውልደ ትውልድ መዝ 44፥16 በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተወለዱልሽ። በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ።ለልጁ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ።
ነሐሴ 12 1ኛ ቆሮ 9፥17-ፍምይሁዳ 1፥8-14

የሐ ሥራ 24፥1-22

ማቴ 8፥10-15

ወይሰግዱ ሎቱ ኵሎሙ መላእክቲሁ፣ ሰምዐት ወተፈሥሐት ጽዮን፣ ወተሐሥያ አዋልደ ይሁዳ መዝ 96፥8 መላእክቱ ሁሉ ይሰግዱለታል አቤቱ ስለፍርድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት። የይሁዳ ሴት ልጆች ደስ አላቸው።
ነሐሴ 13 ዕብ 11፥23-302ኛ ጴጥ 1፥15-ፍም

የሐ.ሥራ 7፥44-51

ማቴ. 17፥1-19

ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአክ ይትፌሥሑ፣ ወይሴብሑ ለስምከ፣ መዝራዕትክ ምስለ ኀይል  መዝ 88፥12  ታቦርና አርሞንኤም በስምህ  ደስ ይላቸዋል። ስምህን  ያመሰግናሉ። ስልጣንህ ከኃይልህ ጋር ተደረገላቸው።
ነሐሴ 14 1ኛ ቆሮ 1፥10-19ያዕቆብ 1፥12-22

የሐ. ሥራ10፥31-44

ሉቃ 1፥39-57

ትሴብሖ ኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር፣ ወሰብሒዮ ለአምላክኪ ጽዮን፣ እስመ አጽንዐ መናሥግተ ኆኃትኪ መዝ 147፥1 ኢየሩሳሌም እግዚአብሔርን ታመሰግነዋለች ጽዮን ሆይ ለአምላክሽ እልል በይ። የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና።
ነሐሴ 15 1ኛ ቆሮ 1፥18-ፍምይሁዳ 1፥17-ፍም

የሐ.ሥራ 1፥12-15

ማቴ 10፥1-15

ውስተ ኵሉ ምድር ወጽአ ነገሮሙ፣ ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ፣ ወውስተ ፀሐይ ሤመ ጽላሎቶ፣ መዝ 18፥4 ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ። በእነርሱ ውስጥ የፀሐይን ድንኳን አደረገ።
ነሐሴ 16 ሮሜ 8፥31-ፍም2ኛ ዮሐ 1፥1-7

የሐ.ሥራ 1፥12-15

ማቴ 26፥26

ቀደሰ ማኅደሮ ልዑል፣ እግዚአብሔር ውስተ ማእከላ ኢትትሀውክ፣ ወይረድኣ እግዚአብሔር ፍጽመ መዝ 45፥4 ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ። እግዚአብሔር በመካከልዋ ነው አትናወጥም። እግዚአበሔር ፈጥሮ ይረዳታል።

                                           

 ስብሐት ለእግዚአብሔር

ለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!

ከአባ ሳሙኤል

 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

               የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ

አዲስ አበባ

ሕገ ወጥ ስደትን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መልዕክት

የሰዎች ዝውውር በአግባቡ ማለትም ሕጋዊውን መንገድ ከተከተለና መብትና ግዴታችንን በምናውቅበት መንገድ ሲካሄድ ለተዘዋወረው (ለተጓዡ) ለላኪ እና መዳረሻ ሀገሮች እንዲሁም  ለቤተሰብና ለአጠቃላይ ማኀበራሰቡ ሰፊ ጠቀሜታ አለው። ሕጋዊ መንገድን የተከተለ የሰዎች ዝውውር የሥራ የትምህርት፣የዕውቀትና፣ የልምድ፣ የቴክኖሎጂ፣ የባህል ልውውጥን የሚያመቻቹ እድሎችን ይፈጥራል።

በ2013 በዓለማችን የሰዎች ዝውውር ቁጥር 232 ሚሊዮን እንደደረሰ ጥናቶች ያመለክታሉ። ይህ ቁጥር በ2000 እ.አ.አ. 175 ሚሊዮን፣ በ1990 154 ሚሊዮን የነበረ ሲሆን ይህም ቁጥሩ በየጊዜው እየጨመረ ስለመምጣቱ የሚያመላክት ነው። ከዚህም በተጨማሪ የሰዎች የመዘዋወር ፍላጎት በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱ እና የሚቀጥል ሂደት ስለመሆኑ ያመላክታል። በተለይም በዘመናዊ የመገናኛ አውታሮች እና ቴክኖሎጂ መስፋፋት የሰዎችን የመዘዋወር ፍላጎት የበለጠ እንደሚያፋጥነው ይገመታል። Continue Reading

ሐራሲ በዕርፈ መስቀል፤ ሰባኬ ወንጌል አባ ሳሙኤል ብፁዕ ብእሲ ብእሴ እግዚአብሔር ወሊቀ ጳጳስ

IMG_0270ቸሩ አምላካችን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነበረ ያለና ይህንም ዓለም አሳልፎ ለዘለዓም የሚኖር ዓለማትን እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ አምጥቶ የፈጠረ፤ እምኀበ ቦ ኀበ አልቦ የሚያሳልፍ ከእሑድ እስከ ሐሙስ ምሴት ድረስ በሰማይና በምድር ያሉ ፍጥረታትን ከፈጠረ በኋላ ዐርብ በጽባሕ (በነግህ) ግብር እምግብር ከዐራቱ ባሕርያተ ሥጋ አምስተኛ ባሕርየ ነፍስ ሰጥቶ ንጉሠ ምድር፤ እግዚአ ምድር፤ አምላክ ዘበጸጋ፤የሆነ ሰውን በአካሉና በአምሳሉ ፈጥሮ  ከሰማይ በታች ከምድር በላይ ያሉ ፍጥረታትን በሙሉ ያስተዳድርና ዓለማትን በአግባቡ ይገዛ  ዘንድ ሙሉ ስልጣን ሰጥቶ ከሃያው ዓለማት አንዷ በሆነችው በገነት አኖረው፡፡

በዚያም ጊዜ ለአዳም የተሰጠው ትእዛዝ ገነትን ይንከባከበትና ይኮተኩታት፤ ያበጃጃት ዘንድ እንጂ እንዲሁ በስንፍና እንዲኖር አልነበረም፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት ኢነሥኦ ለዘነሥኦ  እመላክት እንበለ ዳዕሙ እምዘርዐ አብርሃም እንዲሉ  የሰውን የበላይነት ጥንቱ ይህ ነው በማለት ያረጋግጣሉ፡፡ ማለትም መላእክት የተፈጠሩት በእለተ እሑድ  እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ ሲሆን ሰው ግን በአርአያውና በአምሳሉ ስለተፈጠረ ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል አካላዊ ቃል ቃለ እግዚአብሔር ወልድ  የመላእክትን ባህርይ ባህርይ ሳደርግ የሚበላውን የሚጠጣውን የሚያረጀውን የሚያፈጀውን የሰውን ደካማ ሥጋ ተዋሐደ፡፡ በዚህም ጊዜ አብ ለአጽንዖ፤ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ ፤ ወልድ በተለየ አካሉ ከቅድስተ ቅዱሳን ቅደስት ድንግል ማርያም ከነፍሷ ነፍስ  ከሥጋዋ ሥጋ ነሥቶ አምላክ  ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ፡፡ (እንቲአሁ ለቃል ኮነ ለሥጋ ፤ ወዘዘዚአሁ ለሥጋ ኮነ ለቃል) የማይታይ የማይዳሰስ የማጨበጥ ምሉዕነት የቃል ገንዘብ ለሚበላ፤ለሚጠጣ፤ለሚደክም፤ለሚሞት፤ለሚዳሰስ ለሥጋ ገንዘቡ ሆነ እንዳለው ሊቁ፡፡ ከዚህያም በኋላ እነ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርዊ “አንቲ ውእቱ ገራህት ዘኢተዘርዐ ውስቴታ ዘርዕ፤ወፅአ እምኔኪ ፍሬ ሕይወት” በማለት የሐራሲውን እና የገራህቱን ሕይወት አስገኝነት ያመሰጥራሉ፡፡ ካልበሉ ሬሳ ካለበሱ እንስሳ እንዲሉ አበው በገበሬ ድካምና ጥረት ጠቢቡ ሰሎሞን እንደገለጸልን “ቀዳሜ ሕይወቱ ለሰብእ እክል ወማይ ወይን ወስርናይ” የሆነው ምግብና ልብስ በአራሹ ከመሬት ይገኛሉ፡፡ ገበሬው ፈጣሪውን በማመን በጠራራው ፀሐይ ምርቱን ከጎተራው አውጥቶ ወፍ አእላፍ አብላኝ ብሎ እጁ ሳይሣሣ እኩል ከማሳው ላይ ሲዘራው ተመጋቢ ፍጥረታት በሙሉ አሜን ወአሜን፤ ለይኩን ለይኩን በማለት ፈጣሪያቸውን ያመሰግናሉ፡፡ Continue Reading