Archives

All posts for the month September, 2015

ባሕታዊ  ዘበህድአት! ገዳማዊ ሕይወት በመነሳት

9-1አንድ ሰው ኅሊናውን ለምናኔ አነሣሥቶ ወደ ገዳም በሚገባበት ወቅት የሚያጋጥሙት ፈተናወች እጅግ በጣም ብዙዎች ናቸው፡፡ በዓለማችን እንደ ገዳም ያለ ፈተና የሚበዛባት ቦታ የትም የለም፡፡ ሰብአዊ ፈተናዎች በሙሉ ተሰባስበው የሚገኙት በገዳም ነው። ምክንያቱም ብዙኅ ሕማሞሙ ለጻድቃን ማለት የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው በተባለው መሠረት፣ በዚህ ዓለም ከሚኖሩ ሰዎች ይልቅ በምናኔ ወደ ገዳም በገቡ ሰዎች ላይ የሚደርሰው ፈተና የበለጠ ክብደት አለውና።

ገዳማውያን አበው መነኰሳትና እማት መነኰሳይያት  በገዳማዊ ሕይወታቸው የሚዋጉት ከዚህ ዓለም ካለው ከሚታየው፤ ከሚጨበጠው፤ ከሚዳሰሰውና ከሚሰማው ፈተና ብቻ ሳይሆን ከማይታዩ፤ ከማይዳሰሱ፤ ከማይጨበጡ ረቂቃን አጋንንት ጋርም  ከመዋጋት አቋርጠው አያውቁም። ውጊያውም እስከ ዕለተ እረፍተ ሥጋ ድረስ የሚያቆም ውጊያ አይደለም፡፡ ስለዚህ በገዳም በመናንያንና በመናንያት ላይ የሚደርሰው ፈተና ስፍር ቁጥር የለውም።

በመጀመሪያ ደረጃ በገዳማዊ ሕይወት የሥራን ክቡርነት መረዳት፤ የተለያዩ ፈተናዎች ሲያጋጥሙ መታገስን፣ ሲታዘዙ ያለማጕረምረምና ያለመታከት የታዘዙትን መፈጸም፣ ጾምን፣ ጸሎትን፤ ስግደትን፤ ሕርመትን መለማመድና ገንዘብ ማድረግ የግድ ነው። ምክንያቱም ገዳም የትጉሃን መናኸሪያ እንጂ የሰነፎች መኖሪያ፤ መጦሪያ ወይም መደበቂያ አይደለምና፡፡

ገዳማዊ መነኩሴ ወይም ገዳማዊት መነኩሲት በገዳማቸው ውስጥ በተለያዩ የሥራ ክፍሎች ሲመደቡ ማለትም አትክልትን መትከል፣ መኮትኮትና ውኃ ማጠጣትን፤ እርሻ ማረስን ሌሎችንም አስፈላጊና ተገቢ የሆኑ ተግባራትን ማከናወን፤ በገዳሙ ውስጥ ከሚኖሩ መሰሎቻቸው ጋር በመስማማትና ማንኛውንም ዓለማዊና ሥጋዊ  ፈቃድን በማስወገድ  ደከመኝ፣ ሰለቸኝ ሳይሉ ጸንቶ ማገልገል መንፈሳዊ ግዴታቸው ነው። ይህም ተግባርና አገልግሎት ደግሞ የአንድ ገዳማዊ ወይም ገዳማዊት ጠባይ፤ ችሎታ፤ ፍቅረ ቢጽነት የሚመዘንበት የምናኔ መስፈርት ነው። ልክ እንደ አባ ዮሐንስ ሐፂር ትዕግስትን መላበስ ይጠበቅባቸዋል።

       አባ አሞይ የደረቀ እንጨት ተክሎ ለምልማ እስክታፈራ ድረስ ውኃ እንዲያጠጣት ለአባ ዮሐንስ አዘዘው አባ ዮሐንስም ያለማጕረምረም በትሕትና በመቲረ ፈቃድ ዐሥራ ሁለት ምዕራፍ ያህል ከሚርቅ ቦታ በቀን ሁለት ጊዜ ውኃ እያመላለሰ ያጠጣ ጀመር፡፡ በሦስተኛው ዓመት ያች እንጨት ለምልማ አብባ ያማረ ፍሬ አፈራች። Continue Reading

በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሟል

5ነሥአ ደዌነ ወፆረ ሕማመነ የእኛን ደዌ ተቀበለ ሕመማችንንና ኃጢአታችንን ተሸከመ ስለ መተላለፋችን ሕጉንና ትእዛዙን በማፍረሳችን ስለ እኛ ቆሰለ፣ ስለ በደላችን ደቀቀ፣ ማለትም ሥጋውን ቆረሰ ደሙን አፈሰሰ በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደገነት ከውርደትና ከኃሳር ወደክብር ተመለስን፡፡ የዓለምን ሁሉ መድኃኒት የሁላችን ዕዳ፣ ፍዳና በደል በእርሱ ላይ አኖረ (ኢሳ. 53÷4-5)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመለኮቱ ስቃ ሳይኖርበት እኛን ከሥቃይ ለማዳን ሲል በለበሰው ሥጋ ተጨነቀ፣ ተሠቃየ፣ ለመታረድ እንደሚነዳ በግ (ጠቦት) በሽላቾቹም ፊት ዝም እንደሚል ይህ ሁሉ መከራ በእርሱ ላይ ሲፈጸም ስቃዩ በዛብኝ መከራው ፀናብኝ ብሎ አልተናገረም፣(አፉን አልከፈተም) ይልቁንም ስለሕዝቡ ኃጢአት ተገርፎ ተሰቅሎ ነፍሱን ከሥጋው ለየ፡፡

ይህን ከባድ ስቃይና መከራ ሲፈጽሙበት በሰውነቱ ስህተት በአንደበቱ ሀሰትና ተንኮል አልተገኘበትም (ኢሳ. 53÷7 ይህን መከራ ሲቀበል በሰውነቱ ስህተት በአንደበቱ ያልተገኘበት አምላክ ከመከራ ከፈተና ያድነን ዘንድ በጐ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡ አሜን 
Continue Reading

በድህነት ውስጥ ባለጠግነት፣ በመዋረድ ውስጥ ክብረት፣ በመሰደድ ውስጥ ዕረፍት እንዳለ ማመን ለአብዛኛዎቻችን ከባድ ነው፡፡ ነገር ግን በልቶ መራብ፣ ጠጥቶ መጠማት፣ ለብሶ መታረዝ ካለ እየተራቡ መጥገብ፣ እየተጠሙ መርካት፣ እየተዋረዱ መክበር፣ እየተሰደዱ ማረፍ፣ እየሞቱም መኖር እንዳለ እናስተውላለን፡፡ እኛ ክርስቲያኖች ስለሆን በመከራ ውስጥ ምቾት እንዳለ እንገነዘባለን፡፡ በዮፍታሔ ሕይወት ውስጥ የምናየው ተሞክሮ ይህን እውነት ያስረግጥልናል፡፡ ታሪኩ “…ዮፍታሔን የልዩ ሴት ልጅ ነህና በአባታችን ቤት አትወርስም ብለው አሳደዱት፡፡ ዮፍታሔም ከወንድሞቹ ፊት ሸሽቶ በጦብ ምድር ተቀመጠ፤ ምናምንቴዎችም ሰዎች ተሰብስበው ዮፍታሔን ተከተሉት” ይላል /መሳ.11፡2/፡፡

Continue Reading

ለጤናማ ግንኙነት ይቅርታ ወሳኝ ነው!

በየትኛውም የኑሮአችን ክፍል ውስጥ ሰላም ያለውን ጤናማ ግንኙነት እስከ ሕይወታችን ፍጻሜ ድረስ ይዘን የምንዘልቀው ይቅርታ መድኀኒትን የምንጠቀም ከሆነ ብቻ ነው፡፡ በሰው ልጆች የዕለት ተዕለት ኑሮ ውስጥ ትልቁም ከባዱም ነገር ግንኙነት ነው፡፡ ብዙ ወገኖች በዚህ መንገድ ይፈተናሉ፡፡ በአንድ የጦር ሜዳ ላይ ከጠላት ትልልቅ ዒላማዎች መካከል የግንኙነት መስመሩን ማቋረጥ ቀዳሚ አጀንዳው ነው፡፡ እግዚአብሔር እንኳን በሰናዖር ሜዳ ላይ በጠላትነት በተነሡት ሕዝቦች ፊት የወሰደው እርምጃ ቋንቋቸውን መደባለቅ ነበር፡፡ በሌላ አነጋገር የግንኙነት መስመራቸውን አቋረጠው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ና የተባለው እየሔደ፣ ሒድ የተባለው እየመጣ፣ ውጣ የተባለው እየገባ፣ ቁም የተባለው እየተቀመጠ ጤናማ ግንኙነት ጠፋ፡፡ እናም መጨረሻቸው ጥፋት ሆነ፡፡በእውነት ከልቤ ልንገራችሁ ውጣ ውረድ በበዛበት፣ መውጣትና መግባታችን በብዙ  እንቅፋቶች በተሞላበት ዓለም ሰው በሰላም ለመገናኘቱ ዋጋ ቢሰጥ አይበዛበትም፡፡ ምክንያቱም መገናኘት ቀላል አይደለምና፡፡ እኛ ስንተያይ ሌሎች ጋ መለያየት፣ እኛ ሰላምታ ስንለዋወጥ ሌሎች ጋ መነካከስ፣ እኛ ጤና ይስጥልኝ ስንባባል ሌሎች ቀብር ላይ መሆናቸውን አንዘንጋ፡፡ ይህን እውነት የዘነጋ ሰው የኑሮ ምሥጢሩ አልገባውም ማለት ነው፡፡ እስቲ ሌሊት ስንት አንቡላንስ ጮዃል? ስንቶች ያለበደላቸው በሌሊት ሞተዋል? ስንቶች ከጨለማና ከሰው ጅብ ጋር ሲታገሉ አድረዋል? በሌሊት ለስንቶች ሲለቀስ ታድሯል? ተነፋፍቃችሁ በሰላም የተገናኛችሁ እንኳን ለዚህ አበቃችሁ፡፡ ወጥታችሁ የገባችሁ፣ ተሰማርታችሁ የተሰበሰባችሁ ሐሴት አድርጉ፡፡ ደግሞ ተከፍታችሁ ብቸኝነት የሚያሰቃያችሁ፣ የሰው ክፋት የወዳጅ ክህደት ያቆሰላችሁ፣ ሰው በነፍሱ ተወራርዶ ለሥጋው የተዋጋችሁ እና እንደ ድካማችሁ ያልተከፈላችሁ ተመስገን በሉ፡፡ ይህም የሆነው በሕይወት ስለኖራችሁ ነውና፡፡ Continue Reading

ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ፤

ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም፤

ወይረውዩ አድባረ በድው (መዝ. 64÷11-12)፡፡

New Year

“አእትቱ እምላዕሌክሙ ግዕዘክሙ ዘትካት በእንተ ብሉይ ብአሲ ዘይማስን በፍትወተ ስሒት፤ ሐድሱ መንፈሰ ልብክሙ፡፡ ወልበስዎ ለሐዲስ ብእሲ ዘሐደሶ እግዚአብሔር በጽድቅ ወበርትዕ ወበንጽሕ” በተሳሳተ ምኞት የተበላሸውን አስቀድሞ ትኖሩበት የነበረውን አሮጌውን ሰውነት ከእናንተ አርቁ፡፡ ልቡናችሁን በእውቀት አድሱ፤ በእውነት፣ በጽድቅና በንጽሕና እግዚአብሔርን ለመምሰል የተፈጠረውን አዲሱን ሰውነት ልበሱ” (ኤፌ. 4÷22-24)፡፡ ስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘአብጽሐነ እስከ ዛቲ ዕለት፤ ከዚህ ዘመን፣ ከዚህ ዕለትና ከዚህ ያደረሰን ልዑል እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን፡፡ እንኳን ከዘመነ … ወደ ዘመነ … በሰላምና በጤና ሁላችንንም አደረሰን፡፡ ፈጣሪያችን ቸሩ መድኃኔዓለም ዘመኑን የሰላም፣ የዕድገት፣ የጤናና የብልጽግና ዘመን ያድርግልን፡፡ ለሀገራችን ለቤተ ክርስቲያናችን እንዲሁም ለመላው ዓለም እውነተኛውን ሰላምና ፍቅር ያውርድልን፡፡ Continue Reading

ለሜዲካል መጽሔት አዘጋጆች አምደኞችና አንባቢዎች በሙሉ

በቅድሚያ ቸሩ እግዚአብሔር አምላክ በሰላም እንኳን ለ2008 ዓ.ም አደረሳችሁ!

ዘመኑን የሰላምና የሥራ፤የእድገት የብልጽግና፤ የጤና እና የሕይወት ያድርግላችሁ!!

እንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ እንኳን ለ2008 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ። ዘመነ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌልዊ የሰላም፣ የጤና የእድገት ዘመን እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን!!

 

ጥያቄ፡- በመጽሔታችን ዝግጅት ውስጥ ደካማና ጠንካራ ጎን እንዲሁም መታረም ወይም መቀጠል አለበት የሚሉን ነገር ካለ በሚል የተጠየቅሁት ጥያቄ መሠረት በማድረግ የሚከተለውን ሐሳብ እሰጣለሁ፡፡

በመጀመሪያ ሜዲካል መጽሔት ለምን አስፈለገ ? በሚል ጥያቄ እንነሳ፡- “በመሠረቱ ይህንን ጥያቄ ሰው ሁሉ ዘመኑን ባመጣው ዕድገት ከሜዲካልና ከላብራቶሪ ጤንነቱን ማወቅ ለሚፈልግ ሰው  ከነዚህ መራቅ አችልም ”

እንደ እኔ አመለካከት “በመጽሐፍ ያለ ይወረሳል በቃል ያለ ይረሳል” እንዲሉ አበው የሰው ልጅ የተሠጠውን ሙሉ የእውቀት ጸጋ በተሰጠው ሙሉ መብት መሠረት በአግባቡ ባለመጠቀሙ ተነሥቶታል፡፡ ከዚያ በኋላ ዓይነ ልቡናውና ዓይነ ሕሊናው ሁሉንም ነገር ማስታወስ ባለመቻሉ ብዕር መቅረጽ፤ ብራና መፋቅ፤ ቀለም መበጥበጥ ጀመረ፡፡ ይኸውም ያሰበውን፤ የተናገረውን፤ የሠራውን እንዳይረሳና ለወደፊት እቅዱም ምን ማድረግ እንዳለበት ንድፈ ሀሳብ የሚያስቀምጥበት ጥበብ፤ ሌሎችም እንዲረዱበት የሚያደርግ ተግባር በመሆኑ መጽሐፍትና መጽሔት እንዲሁም ጋዜጣ ማዘጋጀት ግድ ሆነበት፡፡ የሜዲካል መጽሔትም ለሕዝብ በወቅታዊ ጉዳይ ተደራሽ ለመሆን የጽሑፍ ዝግጅትንም ከዚህ ለይተን ልናየው አንችልም አስተማሪና መካሪ ነው በርቱ፡፡ Continue Reading