Archives

All posts for the month December, 2015

‹‹ከእናንተ ወገን በእውነት የተፈተነ ብልህና ዐዋቂ ማነው?››ያዕ 3፥13-18
ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ በተለያየ ምክንያት በዓለም ለተበተኑት ለዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል መንፈሳዊ ጥበብን በሥራ ላይ እንዴት ማዋል እንደሚገባ ከመግለጽ ጋር ከእናንተ መካካል ጥበበኛና አስተዋይ ሰው ማነው? ብሎ ከጠየቀ በኋላ ለክርስቲያናዊ ኑሮ መመሪያ የሚሆኑ ዐበይት ነጥቦችን ግልጽ በሆነ ስእላዊ አገላለጽ በመልእክቱ ያስተላልፋል። እንዲህ በ
ማለት ‹መራራ ቅናትና ራስ ወዳድነት በልባችን፣ ቢኖር አትታበዩ፣ በእውነትም ላይ አትዋሹ፣ ምክንያቱም  እንዲህ ዐይነት ጥበብ የሚገኘው ከዓለም፣ ከሥጋ፣ ከሰይጣን ነው እንጂ ከእግዚአብሔር አይደለም፣ ቅናትና ራስ ወዳድነት ባሉበት ሥፍራ ሁከትንና ክፋ ሥራ ሁሉ ይኖራሉ። ነገር ግን ከእግዚአብሔር በሚገኘው ጥበብ የሚመራ በመጀመሪያ ንጹህ ነው፣ ቀጥሎም ሰላም ወዳድ፣ ደግ፣ ታዛዥ፣ ምሕረት አድራጊ ነው። ጥሩ ፍሬ የመላበት አድልዎና ግብዝነት የሌለበት ነው።

‹‹ሰላም ወዳድ ሰዎች  ሰላምን ዘርተው የጽድቅን ፍሬ ይሰበስባሉ።›› እያለ ሐዋርያው የሰዎች ልጆች ሁሉንተናዊ ማኅበራዊ ኑሮ ያማረና የተዋበ እንዲሆን ከሰው
ልቡና ቅናትና ራስ ወዳድነት እንዳይኖር፣ወንድም በወንድሙ፣ ትልቁ በትንሹ፣ አዋቂው ባላዋቂው፣ ምሁሩ ባልተማረው፣ ባል በሚስቱ፣ ሚስትም በባሏ ላይ እንዳይታበዩ በሚገባ አስተምርል። ለትውልደ ትውልድም መመሪያ እንዲሆን ጽፎ አስተላልፍል። Continue Reading

ለሰው ልጅ ከፈተናዎቹ ሁሉ ረኃብ ይከፋል!!

ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ አኮ መፍትው ይሑሩ ርኁባኒሆሙ ሀብዎሙ አንትሙ ዘይበልዑ/ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እናንተ የሚበሉትን ስጧቸው እንደተራቡ ሊሔዱ አይገባም አላቸው፡፡ ማቴ 1416

ሕይወት ያለው ፍጥረት በሙሉ  ሊቋቋመው የማይችል  ጠላት ቢኖር ረኃብ ነው፡፡ በሥነ ፍጥረት እንደሚታወቀው ሁሉ ሰዎች   በዐራቱ ባሕርያተ ሥጋ ለሁሉም ፍጥረታት አንድ አይነት ነው፡፡ በመሆኑም ከዚህ ከዐራቱ አንዱ ሲጎድል ወይም ሲጠፋ በፍጹም  በሕይወት መኖር አይቻልም፡፡

IMG_1061እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ፈጥሮ በገነት ምግቡን (ዐራቱን ባሕርያተ ሥጋ) ምሉእ በምሉእ  አዘጋጅቶ እንዳኖረው በስነ ፍጥረት መጽሐፍ ላይ ተገልጾዋል፡፡ ነገር ግን የሰው ልጅ የተሰጠውን ሙሉ መብት በአግባቡ ባለመጠቀሙ ምክንያት የተለያዩ ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች ሲፈራረቁበት ይታያል፡፡ በእነዚህም ሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት (climate change) የአካባቢ አየር ለውጥ/መዛባት፤ የሙቀት መጨመር ወይም መቀነስ፤ የዝናብ እጥረት ወይም ያለ ወቅቱ መዝነብ፤ መጠኑ ያነሰ ወይም የበዛ ዝናብ፤ የጎርፍ መጥለቅለቅ፤ ድርቅና  ደዌያት ሁሉ ይከሰታሉ፡፡ የፋብሪካ ጭስና ዝቃጭ፤ የደን መመናመን፤ የጦር መሣሪያና የጦርነት ውጤቶች፤ የመሬት ለምነት መቀነስና መራቆት፤ የመሬት በውኃ መሸርሸር፤ እፅዋትን አለመትከልና አለመንከባከብ፤ ማኅበራዊ ችግሮች ወዘተ ሰው ሰራሽ ችግሮች ለድርቅ መከሰት ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸው፡፡ ድርቅ ኢትዮጵያን ብቻ አይደለም የሚያጠቃው፡፡ የሌሎች አህጉራትና ዓለማትም የዚሁ ችግር ሰለባዎች መሆናቸው የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ በclimate change ምክንያት በረዶው ሲቀልጥ፤ ተራራው ሲናድ፤ መሬቱ ሲሸሽ፤ ውኃው ከመጠን አልፎ  የሰዎችን መኖሪያ ሲያጥለቀልቅ፤ ጦርነት የተካሄደበት ሀገርና ቦታ ወደ በረሃነት ሲቀየር ማየት የተለመደ ነው፤ በመሆኑም ተፈጥሮ እንዲከፋ የሰው አስተዋፅኦ ያለበት መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ Continue Reading

‹‹ኢትክልእዎሙ ለሕፃናት ይምጽኡ ኃቤዬ››

‹‹ሕጻናትን ወደኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው (ማር 9፥36) ››

222111

 

 

 

 

 

 

 

ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታዎች ናቸው የነገም የሀገርና፣ የታሪክ፣ የእምነት፣ ተረካቢዎች ናቸው በስነ አእምሮ ጎልምሰው እንዲያድጉ አቅም የሌላቸውን መደጋገፍና ማስተማር ይገባል።

እግዚአብሔር አምላክ ከአማኝ የሆኑ ወላጆች ጋር ቃል ኪዳን ሲመሰርት ከልጆቻቸውም ጋር መስርተዋል (ዘፍ 17፥10 – ሐዋ 2፥29 መዝ 127፥3)  ኮሚሽነር  ጸሐፊ

ልጅ የሚለው ቃል ከአንድ ሰው በሥጋ የተወለደው ብቻ ሳይሆን፣ የሥራ ወይም የትምሕርት ተከታይ፣ በሃይማኖት፣ የተወለደ፣ በእድሜ ትንሽ (ሕፃን) የሆነ፣የአገር ልጅ (በዜግነት) ተወላጅ የሆነ፣በሌላ አስዳጊ ስር ያለ ነው።

123ስለሆነም እነዚህን ወላጅ የሌላቸው ህፃናት እንደ ሃይማኖትም እንደ ሀገርም በጥበብ ማሳደግና ማስተማር ግዴታ አለብን። በማስተዋልም እንዲያድጉ ታዟል ይህ የማድረግም ከእምነት ሰዎች ያጠበቃል። ኤፌ 6፥4 -መ. ምሳ 1፥8 ለህፃናቱ መልካም የትምህርት ጊዜ ይሁንላችሁ እግዚአብሔር ይባርካችሁ!!

አባ ሳሙኤል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀጳጳስ

አዲስ አበባ

“ነገር ግን ገና ኀጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሙቷልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል (ሮሜ 5፥8-21)

በኀጢአት ብዛትና ክፋት ምክንያት ሰውን በመፍጠሩ መጻጸቱን የገለጸው እግዚአብሔር (ዘፍ 6፥1-8)። የሰው ልጅ ገና ኀጢአተኛ ሳለ ራሱ ታራቂም አስታራቂም ሆኖ በልጁ በጌታችን  በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት የሰውን ልጅ ማዳኑንና ይህም ስለ ሰው ልጅ ያለው ፍቅር ምን ያህል የረቀቀና የጠለቀ ምሥጢር ያለው መሆኑን ነው። ሐዋርያው ዮሐንስ ስለ ፍቅር ምሥጢር ሲናገር እንዲህ ይላል፦

“ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፤ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፤ በእሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና፤ ፍቅር እንደዚህ ነው። እግዚአብሔር ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኀጢአታችን ማስተሥርያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደላከ እንጂ እኛ እንደወደድነው አይደለም። ወዳጆች ሆይ! እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ ርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል። እግዚብሔርን ማንም ከቶ አላየውም፤ ርስ በርሳችን ብንዋደድ እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል፤ ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ይሆናል። (1ኛዮሐ. 4-8-2)

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በቆሮንቶስ መልእክቱ “እምነት፥ ተስፋና ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው፤” ይላል። (1ቆሮ 13፥13) በዚህ ምንባብ “እግዚአብሔር ፍቅር ነው” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ፍቅር በርግጥ የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘብ መሆኑን ነው። ፍቅረ እግዚብሔርና ፍቅረ ሰብእ ከሌለ በእምነት ብቻ ምድራዊና ሰማያዊ ሕይወትን ተስፋ ማድረግ  ስለማይቻል ከእምነትና ተስፋ ፍቅር ይበልጣል ይላል። ሐዋርያው ቅዱዱስ ጳውሎስ እንዳስተማረው። የፍቅር ምሥጢር በቃላት ሊገለጽ የሚችል አይደለም፤ ምሥጢሩ ግልጽ ሊሆን የሚችለው በሥራ በተግባር ሲተረጐም ነው( 1ቆሮ.13፥4-7)። Continue Reading

ሙሉ መጽሐፉን እዚህ በመጫን ያውርዱና ያንብቡ Leadership

የብፁዕነታቸው መልእክት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጠቅላይ ቤተ ክህነት መምሪያ ኃላፊዎች፣ የአኅጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችና ዋና ጸሐፊዎች የልማት መምሪያ ኃላፊዎች  እንዲሁም  በማንኛውም ደረጃ የምትገኙ የቤተ ክርስቲያኒቷ የሥራ አስፈጻሚዎች በሙሉ ይህች ሐዋርያዊት፣ ታሪካዊትና ዓለም አቀፋዊት የሆነችው ቤተ ክርስቲያን በዚህ ረጅም የታሪክ ኩነቶች ውስጥ በሃይማኖት መሪዎቿ ጥበብና የመንፈስ ብርታት፣ ብቃትና ጽናት እንዲሁም በጠንካራ አገልግሎትና ጸሎት፣ በየዘመናቱ የሚገጥማትን እጅግ ፈታኝና አስቸጋሪ ፈተናዎችን አልፋ ለዚህ አሁን ላለችበት እንድትበቃ የበኩላቸውን አስተዋጽኦና ድረሻ ተወጥተው እምነታቸውንና፣ ታሪካቸውን ለሀገርና ለእኛ አስረክበዋል፡፡

አሁን ያለንበት ዘመን እጅግ ፈጣን ለውጦች የሚካሄዱበት ጊዜ ብቻ ሳይሆን ውስብስብ ችግሮች አብሮ የሚፈጠሩበት በመሆኑ ዘመኑ የሚጠይቀውን የአመራር ጥበብና ክህሎት  በራሱ እጅግ የጠለቀ እውቀትና ብልሀት እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ መታገዝን የሚጠይቅ በመሆኑ የመሪነትን ተግባር አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡

በዚህ ደግሞ ቤተ ክርስቲያኗ በዘመናት ውስጥ አልፋ የመጣችበት ጥንካሬዎቿ ዛሬ ዛሬ በፈታኝ ሁኔታ ውስጥ እንደምትገኝ ነባራዊው ገጽታ የሚያሳየው እውነታ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ ፈታኝ ወቅት እኛ መንፈሳዊ መሪዎች አውንታዊውን ሆነ አሉታዊውን ተግባር በማከናወን ረገድ የራሳችን ሚና በመጫወት ላይ እንገኛለን፡፡ Continue Reading

የቴክኖሎጂ ውጤቶችና ዘመናዊ የመገናኛ አውታሮች ባልተስፋፋበት ዘመን የዓለማችን ሕዝብ የተለያዩ አመለካከት ነበረው፡፡ ሰዎች መሠረታዊ ፍላጐታቸውንና ማኀበራዊ ግንኙነታቸውን የሚገልጹት በዛ ቢባል በስልክ ብቻ ነበር፡፡ በስልክ የሚደረገውም ግንኙነትና የሐሳብ ልውውጥም ከሞላጎደል ነበር፡፡ ስልክ ለማግኘት የሚችሉት በጣት የሚቆጠሩ የኀብረተሰብ ክፍሎች እንደነበሩም የቅርብ ጊዜ ትውስታዎች ናቸው፡፡

ይህን የጠበበውን አስተሳሰብና ዓለማቀፋዊ ይዘት ያልነበራቸው አስተሳሰቦች በመስበር የሰዎችን ማንነት በውል ለማወቅ የሚያስችል ዘመናዊ የማገናኛ መንገዶች ተፈጥረዋል፡፡ እነዚህም አውታሮች ሰዎች ከነበራቸው ውስን እውቀትና የተሳሳተ ግንዛቤ በመላቀቅ ዓይናቸውን እንዲከፍቱ አድርጓቸዋል፡፡ ኢንተርኔት፣ ፌስቡክ፣ ድሕረገጾችና ቲዎተሮች ሰዎች በዓለም ውስጥ የሚያደርጉትን ሁለንተናዊ ክስተቶች ለማጤንና ለመረዳት አስችሏቸዋል፡፡ ኢንተርኔትን መሠረት ያደረጉት እነዚህ መግባባቶች በድሆችና በባለፀጎች እንዲሁም በጨቋኞችና በተጨቋኞች መካከል ያለውን አመለካከት ለማወቅና ለመስበር እድል ፈጥሮላቸዋል፡፡ የሰው ልጆች እነዚህን የመገናኛ አውታሮች ለመጠቀም የሚያደርጉትን የዕለት ከዕለት ግንኙነት ለሰላም፣ ለፍትሕ ለእኩልነትና ለጋራ ብልጽግና በጋራ እንዲሠሩ ከፍተኛ እገዛ እያደረከተላቸው ይገኛል፡፡ Continue Reading