Archives

All posts for the month January, 2016

የጥምቀት በዓል ባሕረ ጥምቀት ታሪካዊ አመጣጥ

የጥምቀት  በዓል  ታሪካዊ አመጣጥ

15ለጥምቀት በዓል ታሪካዊ አመጣጥ መነሻ የሚሆነን በዋነኝነት የክርስቶስ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መሄድ ሆኖ ቅድመ በዓል ኤጲፋንያ (ከመገለጥ በዓል በፊት) እስራኤላውያን በብሉይ ኪዳን ወንዝ ወርደው፣ ዣንጥላ አስጥለው፣ ዳስ ሠርተው የመልካም ዛፍ ፍሬና የለመለመ ቅርንጫፍ ወስደው እያንዳንዱ አቅሙ የሚፈቅድለትን ስጦታ እየሰጠ በዓለ መጸለትን (የዳስ በዓልን) እግዚአብሔር ወደ መረጠው ስፍራ በመሄድ “አባቶቻችንን ባህር ከፍለህ ደመና ጋርደህ ያሻገርካቸው” አምላክ አንተ ነህ በማለት የተቀደሰ ጉባዔ በማድረግ በዓሉን ያከብሩ ነበር፡፡ ዘሌ 23፡1-44 ዘጸ 23፡14፣ ዘዳ 16፡16

በኢያሱ የምስፍንና ዘመንም የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙት ካህናት እግሮች በውሃ ዳር ሲጠልቁ (ወደ ውሃው ሲገቡ) ከላይ የሚወርድው ውሃ ቆሞ እስራኤል ዮርዳኖስን በደረቅ እንደተሻገሩና የእግዚአበሔር እጅ ጠንካራ እንደሆነች ወደፊት የሚነሳው ትውልድ እንዲያውቅ ከማድረግ ጋር በወንዙ ላይ የተደረጉትን ተአምራት የሚገልጽ የዘለዓለም መታሰቢያ (ምልክት) እንደነበራቸው በመጽሐፈ ኢያሱ (3፡14-17) ተጽፏል፡፡

የአረማውያን ቤተሰቦች አይሁድ ለመሆንና ሕገ ኦሪትን ለመጠበቅ ፈቃደኞች በሚሆኑበት ጊዜ ወንዶች የሚገረዙ ሲሆን አይሁድ በመንጻት ሥርዓት በውኃ ታጥበው ከርኲሰታቸው እንደሚነጹ ሁሉ መላው የአሕዛብ ቤተሰብም ከአረማዊነት አኗኗራቸው በውኃ እየተጠመቁ የመንጻት ሥርዓት ይፈጽሙ ነበር፡፡ ዘሌ 12፡8 Continue Reading

12ቅድመ ዓለም የነበረ፣ አሁንም ያለና ለወደፊቱም የሚኖር ሰማይንና ምድርን የፈጠረ አምላካች እግዚአብሔር ሰውን ከመሬት አፈር በእጁ የሠራው፣ በአርኣያውና በምሳሌው የፈጠረውም እርሱ ነው፡፡ (ዘፍ 1፡26)፡፡ እግዚአብሔር በአርዓያውና በአምሳያው የፈጠረውን ሰውም ከሌሎቹ ፍጥረታት በጸጋ አክብሮ በአእምሮ አልቆ በገነት እንደኖር አደረገው፡፡ Continue Reading

1ጐጂ ባሕልን አስመልክቶ በተደረገው የሁለት ቀናት ሰሚናር ከ8 አኅጉረ ስብከት የተወከሉ በተለያዩ ኃላፊነት ያሉና ከጠቅላይ ቤተ ክህንትም የተለያዩ የመምሪያ ኃላፊዎች በተገኙበት በፍሬንድሽፕ ሆቴል የተላለፈ መመሪያና ቃለ ቡራኬ ብፁዕነታቸው ተሰቶል።

የእግዚብሔር ፍጥረታት ሁሉ ምንም ምን ሕፀፅ እንደሌለበት በጎ እንደሆነ የሚጣልም እንደሌለ እንናገራለን በማለት ይህን ቃል ሐዋርያትም አስተምረውታል ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ግሩምና ድንቅ ሆኖ በአርአያ ሥላሴ የተፈጠረው ሰው አናጺው (ፈጣሪው) ሁሉንም አሟልቶ እጅግም መልካም አድርጎ ፈጥሮታልና በድጋሚ በፍጡር እርማት ሊደረግበት እንደማይገባ ገልጿል። ነገር ግን ሰዎች በዓለማችን ብሎም በሀገራችን ኢትዮጵያ በተሳሳተ አስተምህሮ እየተመሩ ክቡርና ድንቅ ሆኖ የተፈጠረውን የሰው ልጅ አካል በማጉደል ላይ ይገኛሉ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና አስተምህሮ መሠረት ጐጂ ባሕል መጽሐፍ ቅዱሳዊና ሃይማኖታዊ የሆነ መሠረት የሌለው መሆኑን አጥብቃ ታስገነዝባለች። ለዚህም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች በጻፈው መልዕክቱ “በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝንቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምም” (ገላ 6፥15) በማለት ያስረዳናል። በሌላ መልኩ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ጾታን መሠረት ያደረግ የሴት ልጅ ጥቃት በሃይማኖትም ሆነ በሰው ልጅ ሕግ የማይደገፍ ተግባር መሆኑን ታስተምራለች።

በዘመነ ኦሪት አንድ ወንድ አንዲትን ሴት በተለይ ልጃገረድ የሆነችውን የደፈረ እንደሆነ በሞት መቀጣት እንደሚገባው በኦሪት ዘዳግም ተጽፎ እናነባለን። Continue Reading

Lidetልዑለ ባሕርይ ቸሩ እግዚአብሔር ፈጣሪያችን

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም፣በጤና እና በሕይወት አደረስዎ

 

“እስመ ናሁ ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘውእቱ ክርስቶስ እግዚእ ቡሩክ በሀገረ ዳዊት”

   ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋል፡፡ ሉቃ 20

     “For unto you is born this day in the city of David a Saviour, which is Christ the Lord” (Luke 2:1)

 

         “ወአመ በጽሐ ዕድሜሁ ፈነወ እግዚአብሔር ወልዶ ”

የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን ላከ  ገላ ፬፥፬

“When the fullness of time was come, God sent forth His Son” Gal. 4፥4

                                                                

    “ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ለእጓለ እመሕያው ሥምረቱ”

ምስጋና ለእግዚብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጐ ፈቃድ

Glory to God in the highest, and on earth peace, good will to ward Amen

 

 ቸሩ እግዚአብሔር አምላካችን በዐሉን የሰላም፣ የጤና፣ የበረከት ያድርግልን!!!

 

          

                                     

                                  ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላች ጋር ይሁን!!