Archives

All posts for the month February, 2016

የሀገራችን ሕዝቦች የፕሮቴስታንታዊ መናፍቅነት የምዕራብ አውሮፓ ፕሮቴስታንቲዝምን ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኀበራዊ፣ ፍልስፍናዊ፣ ሥነ-ልቡናዊ፣ ሀገራዊ አመጣጥና መንስኤዎችን ሳያስተውሉ፣ ሊያስተውሉም ሳይፈልጉ፣ ለምን? ብለው ሳይጠይቁ፣ አንዳንዶቹ፣ ሀገራችን ውስጥ በአስከፊ ቁጣ ራሱን የገለጸው መንፈሳዊ ኪሳራ የፈጠረውን ባዶነትን ለመሙላት ቸኩለው፣ ሌሎች ደግሞ የራስ ሃይማኖትን መካድ የሚያስገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ሽተው፣ ግን ሁሉም በጸያፍ ፕሮፖጋንዳና የአዕምሮ ማንጠፍያ ዘዴዎች ተቆልምመው፣ ምርጫቸውን ተዘርፈው “መግቢያውን እንጂ መውጫውን ከማያውቁት” መጤ የጥገኝነት እምነት ውስጥ ዘው ብለው ገቡ፡፡

የምዕራብ አውሮፓ ፕሮቴስታንቲዝም፣ በጊዜው ጀርመንና ሌሎች ምዕራብ አውሮፓ ሀገሮች ውስጥ ለተነሱ ሥጋዊ ጥያቄዎች የሃይማኖት ሽፋን ያለው፣ ግን መንፈሳዊ ያልሆነ መልስ የሰጠ አመጽ/ተቃውሞ እንጂ፣ ዛሬ ለእኛ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ላይ ለምንገኝ ኢትዮጵያውያን ጥያቄው ከንቱ ነው፡፡ ምዕራባውያን በፍቅር፣ በእውነተኛ ሃይማኖት፣ በእድገት፣ በዲሞክራሲ… ሽፋኖች ጠቅልለው የሚሰጡን እርዳታዎች፣ ውስጣቸው፣ የስህተት ትምህርት፣ የጥገኝነት መንፈስ ማለትም፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኀበራዊ፣ ፍልስፍናዊ፣ ሥነ-ልቡናዊ… ሥርዓቶችንና እሳቦቶችን የያዙ፣ ምዕራባውያን የአንድን ሀገር ነጻነት የተለያዩ እንዱስትሪያዊ ልማቶች እንደሚያጸኑት ያውቃሉ፡፡ ይህን ግን ለእኛ አይሰጡንም፡፡ ይልቁንም የተለያዩ የእንዱስትሪያዊ እድገት ልማቶቻችን ከዚህም የሚገኝ የጸና ነጻነታችንን እንዳይቻል ለማድረግ፣ የተለያዩና መናፍቃዊ የሃይማኖቶች እንዱስትሪዎች በመላው ሀገራችን እየተከሉልን ነው፡፡

በካቶሊክ ቤተክርስቲያንና ከጉያዋ በወጣው ፕሮቴስታንታዊ እምነት መካከል በተፈጠረው (አሁን ምዕራባውያን በሚያፍሩበትና በሚጸጸቱበት) ፖለቲካዊ ማኀበራዊ ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊ፣ ዜግነታዊ፣ ሥነ-ልቡናዊ መሰል ክፍፍሎችና በተከተሉት ጦርነቶች የተነሳ፣ እርስ በርስ በተላለቁበት፣ እጅግ ተጋፊና ምዕራባዊ ወኔ፣ በመሰነቅ እኛንም ሊያጠፉን ተነስተዋል፡፡ ሚሲዮኖች የ500 ዓመታት የፕሮፓጋንዳና የጦርነት ልምድን በዶላርና በዘመናዊ የኀሊና መቆጣጠሪያ ሳይንስ በመታገዝ፣ አቅልጥ ፕሮቴስታንታዊ አንጃዎች በተሳሳቱ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን መንገድ መሪነት፣ ያለ ማንም ተው ባይነት፣ ያለ ምንም የረባ ተቃውሞ በቅድስት ሀገራችን ላይ ስኬታማ ወረራ በማድረግ ሊያድናቸው Continue Reading

ጥንታዊት ሐዋርያዊት በሆነች  በጌታችንና  በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ደም በተመሠረተችው በአንዲት ርትዕት ሃይማኖት  በአንዲት ጥምቅት  በአንዲት ቅድስት ተዋሕዶ ቤተ  ክርስቲያን እናምናለን  የሐ.ሥ. ፳፮፥፳፱ መዝ. ፺፭፥፯  ኤፌ.፬፥፭

  • የጌታችንና የአምካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት በሚሆን ፍጥረቱን

ሁሉ በፈጠረ በአንድ አምላክ እናምናለን በባሕርዩ ምክንያት የለበትምና ዘፍ ፩፥፩

  • አስቀድመን እንደ ተናገርን በዘመኑ ሁሉ ይኖራል እንጂ ጥንት ወይም ፍጻሜ የለው ምና ኢሳ ፵፬፦፮ የማይጠፋ ብርሃን አለው ወደርሱም መቅረብ የሚቻለው የለም  ፩ኛ ጢሞ.፮፥፲፮
  • ሁለተኛ አይደለም ሦስተኛም አይደለም አይጨመርበትም ብቻውን ለዘለዓለሙ የሚኖር አንድ ነው እንጂ᎓᎓ ዘዳ ፮፥-፬ -ማር ፲፪፥፳፱ ፩ኛ ጢሞ ፪፥፭ የማይመታወቅ የተሰወረ አይደለምና ሁሉን የያዘና ከፍጥረቱም ሁሉ በላይ የሠለጠነ መሆኑን በኦሪትና በነቢያት ፈጽመን አውቅነው እንጂ᎓᎓
  • ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር አንድ አምላክ ነው᎓᎓ ዓለም ሳይፈጠር የተወለደ ከርሱ ጋራ የተካከለ የሚሆን አንድ ልጅ ሠራዊትንና ሢመታትን ሥልጣናትንም ሁሉ የፈጠረ᎓᎓
  • በኋለኛው ዘመን ሰው ይሆን ዘንድ የወደደ ቁላስ.፩፥፲፭-፲፰ ያለ ዘርዐ ብእሲ ቅድስት ከምትሆን ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ሥጋን ነሣ᎓᎓ ሉቃ.፪፥፴-፴፱

ያለ ኃጢአትና ያለ በደል እንደ ሰው አደገ᎓᎓ በአንደበቱም ሐሰት የለበትም᎓᎓

፩ኛ ጴጥ ፪፥፳፪

  • ከዚህ በኋላ በሥጋ ታመመ ሞተም በሦስተ ኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ

፩ኛ ቆሮ ፲፭፥፳ ወደ ላከውም ወደ አብ ወደ ሰማይ ዐረገ  ማር. ፲፮፥፲፱  ኃይል ባለውም ቀኝ ተቀመጠ ከአብ የሠረፀ ጰራቅሊጦሰ መንፈስ ቅዱስን ሰደደልን ዓለሙንም ሁሉ አዳነ ከአብና ከወልድ ጋራ ህልው የሚሆን᎓᎓ ግብ.ሐ. ፪፥፩-፪

  • እንግዲህ የእግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ በጎ እንደ ሆነ የሚጣልም እንደ ሌለ እንናገራለን᎓᎓ ፩ኛጢሞ ፬፥፬ የሥጋ ሕይወት የምትሆን ነፍስ ግን ንጽሕት ቅድስት ናት᎓᎓ ዘፍ.፪፥፯
  • እኛስ ጋብቻ ንጹሕ እንደ ሆነ ልደትም ርኵሰት እንደሌለበት እንናገራለን᎓᎓

ዕብ ፲፫፥፬ ሕዝብ ይበዙ ዘንድ እግዚአብሔር አዳምንና ሔዋንን ፈጥሮዋቸዋልና᎓᎓ ዘፍ. ፩፥፳፯ ከሥጋ ጋራ የማትሞትና የማትበሰብስ ነፍስ  በሥጋችን እንዳለን እናስተውል᎓᎓ Continue Reading

«መነሻዬ ከገዳም ነውና በገዳም ጸንተው ለሚኖሩ አባቶች ትልቅ አክብሮት አለኝ፡፡»

ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀጳጳስ ወደ መናገሻ አምባ ማርያምና የጋራው መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም በመመላለስ፤ በግላቸውና በልማት ኮሚሽኑ ለገዳሙ እጅግ ብዙ አስተዋጽኦ ያበረከቱ በመሆናቸው፤ የጋራው መድኃኔዓለም ሕንፃ ቤተክርስቲያን አሠሪ ኮሚቴ በዚህ መጽሔት ብፁዕነታቸው ወደዚህ ገዳም ለመምጣት ምክንያት የሆናቸውን ምን እንደሆነ? በመጡበት ወቅት ገዳሙን እንዴት? እንዳገኙት፤ የነበራቸውን ትዝታዎቻቸውን፣ ወደ ገዳሙ ተመላልሰው ብዙ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ የጋበዛቸውን ምክንያት እና አሁን ገዳሙ የደረሰበትን የዕድገት ደረጃ ፤ እንዲሁም የልማት እንቅስቃሴውን እንዲያስተላልፉልን ስለፈለግን፤ አባታዊ ምክር እንዲሰጡን፤ጥያቄ አቅርበንላቸው እንደ ሚከተለው ነግረውናል፡፡

13

የመናገሻ መድንኔ ዓለም ገዳም ቤተ ክርስቲያን ሥራ ተጠናቆ ተመረቀ ቤተ ክርስቲያኑ በልዩ ሆኔታ የተሠራ ነው᎓᎓

መልካም ንባብ!!

በመጀመሪያ ብዙ የደከማችሁበት ሕንፃ ቤተክርስቲያን ሥራው ተፈጽሞ ለምርቃት በመድረሱ እንኳን ደስ አላችሁ! ማለት እፈልጋለሁ፡፡ ሰው የሠራው ሥራ ከፍጻሜ ሲደርስለት ይደሰታል፡፡ እናንተ ደግሞ እግዚአብሔር የሚመሰገንበትንና ሕዝበ ክርስቲያኑ የሚገለገሉበትን፤ በዚያውም ላይ በታላቁ መናገሻ አምባ ማርያምና የጋራው መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም በመሆኑ ደስታችሁን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል፡፡ በሥራችሁ መካከል የገጠማችሁን ችግር ሁሉ ተቋቁማችሁ በመጪው ትውልድ ስትታወሱ፤ የምትኖሩበትን ትልቅ ሥራ ሠርታችኋልና ልትመሰገኑ ይገባችኋል፡፡ ወደ ጥያቄው ስመለስ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደዚህ ገዳም የመጣሁት፤ የጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለት ለማክበር ፣ ከአባቶች መነኮሳት ጋር ለመስገድና ለመጸለይ ነበር፡፡ ገዳሙ በደን የተሸፈነ ተራራ ላይ ያለ በመሆኑ መንፈስን  ደስ የሚያሰኝ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ ነገር ግን  ቤተክርስቲያኑ ጠባብ መሆኑ ፣ የአባቶች መነኮሳት በዓት ለቤተክርስቲያኑ የቀረበና ለአባቶች መኖሪያነት የማይመጥን መሆኑን፣ ቤተምርፋቅ አለመኖሩን፣ የገዳሙን ጥንታዊነት የሚገለጹ ነገሮች በተደረጀ መልኩ አለመቀመጣቸውና ቤተ መዘክር ( ሙዚየም) አለመኖሩን በማየቴ በጣም አዝኛለሁ፡፡ በተለይም ለአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ በመገኘቱ ጎብኝዎችን በሚስብ መልኩ አለመደራጀቱ ቁጭት ፈጥሮኛል፡፡ እናንተ እንደምትሉት በግሌ ብዙ አስተዋፅዖ አድርጌአለሁ ለማለት አልችልም ፡፡ ቢሆንም እንኳን መነሻዬ ከገዳም ነውና በገዳም ጸንተው ለሚኖሩ አባቶች ትልቅ አክብሮት አለኝ፡፡ ስለሆነም “በርቱ ጽኑ” ለማለት ከጎናቸው እንዳለን ለመግለጽ በልማት ኮሚሽኑ በኩል ትላልቅ ብረት ድስቶች፣ የሹራብ መሥሪያ ማሽኖች ሲንጀሮች ፣ ለቢሮ መገልገያ ኮምፒውተሮች  ከነፕሪንተራቸው ፣ ቶዮታ ፒካፕ መኪና ሠጥተናቸዋል፡፡ የቦታው ትልቁ ችግር ውሃ ስለሆነ ጋራው ላይ ከቤተክርስቲያኑ በስተምሥራቅ  ረግረግ ስላለ የከርሠ ምድር ውኃ ልናገኝ እንችላለን ብለን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምሁራንን ጋብዘን በባለሙያ ሲጠና ውሃ ቢኖርም ከተራራው እግር ሥር ይወጣል እንጂ እዚህ ሊቆም አይችልም ስላሉን ያ ጥረት ተቋርጧል፡፡ ነገር ግን የታችኛው ገዳምና የአካባቢው ሕዝብም የውሃ ችግር ስላለበት ከተራራው ግርጌ በመነኮሳቱ እርሻ መሬት ላይ የከርሠ ምድር ውሃ እንዳለ ስለተጠቆምን በባለሙያ አስጠንተን ከማስቆፈሩ ጀምሮ ከ 500,000.00 ( አምስት መቶ ሺህ ብር) በላይ ወጪ በማድረግ ውሃውን አውጥተን  ለአገልግሎት እንዲውል በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡  መነኮሳቱ እኛም ረድተናቸው ውሃውን ጥራት እና የማዕድን ይዘቱን አስጠንተው የታሸገ ውሃ ለገበያ ቢያቅርቡ የገቢ ምንጭ ይፈጥራል፡፡ ከገዳሙ የተገኘ በመሆኑም ከመጠጥነት ባሻገር እንደጠበል ስለሆነ ተፈላጊነት ይኖረዋል ብዬ አምናለሁ፡፡

ጥንታዊው ቤተ ክርስቲያን የነበረበት ስውር ተብሎ የሚጠራው ላይ የተሠራ የተለየ ቤተ መቅደስ ነው᎓᎓ Continue Reading