Archives

All posts for the month March, 2016

የ2008 ዓ.ም ከዘወረደ እስከ  ደብረ ዘይት የሚነበቡ ምንባባትና እና የሚሰበኩ ምስባኮች

ቀን ምንባብ ምስባክ የምስባክ ትርጉም
ዘወረደ

27/06/08

ዕብ. ም.13 $ Ì 7-17

ያዕ. ም. 4 $ Ì 6-ፍም

ግብ.ሐ ም. 25 $Ì 13-ፍ

ዮሐ. ም 3 $ Ì 10-25

ቅዳሴ እግዚእ

ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሀት፡፡

ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ፡፡

አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዐዕ እግዚአብሔር፡፡     መዝ.2 Ì 11

ለእግዚአብሔር በፍርሀት ተገዙ፡፡

በረዓድም ደስ ይበላችሁ፡፡ ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታእንዳይቆጣ፡፡

 

ሰኞ

28/06/08

ዕብ. ም. 14 $Ì8-22

ያዕ. ም. 3$ Ì 1ፍ.ም

ግብ.ሐ. ም.7 $Ì1-16

ሉቃ.ም.20 $Ì37 ፍም

ቅዳሴ እግዝእትነ

ዘሠርዓ ለአብርሃም፡፡

ወመሐለ ለይስሐቅ፡፡

ወአቀመ ስምዐ ለያዕቆብ፡፡

መዝ. 104 $ Ì 9

ለአብርሃም ያደረገውን፡፡

ለይስሐቅ የማለውን፡፡

ለያዕቆብ ሥርዐት እንዲሆን፡፡

ማክሰኞ

29/06/08

ሮሜ. ም.8 $Ì 3-12

ዮሐ. ም 4 $ Ì 7-18

ግብ.ሐ.ም. 9$Ì 20-32

ሉቃ. ም 2 Ì 1-21

ቅዳሴ እግዚእነ

እግዚአብሔር ይቤለኒ ወልድየ አንተ፡፡

ወአነ ዮም ወለድኩከ፡፡

ሰአል እምኔየ እሁበከ አሕዛበ ለርስትከ፡፡

መዝ. 2 $Ì 7

እግዚአብሔር አለኝ፡- አንተ ልጄ ነህ ፡፡ እኔ ዛሬ ወለድሁህ ፡፡ ለምነኝ አሕዛብን ለርስትህ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ፡፡

 

ረቡዕ

30/06/08

ቆሮ. ም. 4$ Ì 7- ፍም

2ኛ.ጴጥ.ም1$Ì19-ፍም

ግብ.ሐ.ም.13 $Ì24-32

ማር.ም.6 $ Ì 21-34

ቅዳሴ ወልደ ነጎድጓድ

ገሥፆሰ ገሠፀኒ እግዚአብሔር፡፡

ወለሞትሰ ባሕቱ ኢመጠወኒ፡፡

አርኅው ሊተ አናቅጸ ጽድቅ፡፡

መዝ. 117$ Ì 18

መገሠጽስ  እግዚአብሔር ገሠጸኝ፡፡

ለሞት ግን አልሰጠኝም፡፡

የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ፡፡

ሐሙስ

01/07/07

ጢሞ. ም .2$ Ì 1- 17

ያዕ. ም 1$ Ì 5-15

ግብ.ሐ.ም.15 $ Ì1-13

ማቴ.ም.10 $ Ì 17-27

ቅዳሴ ግሩም

አንተ ውእቱ ዘታገብእ ሊተ ርስትየ፡፡

አህባለ ወረው ሊተ የአኀዙኒ፡፡

ወርስትየሰ እኁዝ ውእቱ ሊተ፡፡

መዝ. 15 Ì 5

እግዚአብሔር የርስቴ እድል ፈንታና ጽዋዕ ነው፡፡ ዕጣየንም የምታጠና አንተ ነህ፡፡ ገመድ ባማረ ስፍራ ወደቀችልኝ፡፡
ዓርብ

02/07/08

ሮሜ. ም. 1$ Ì 8-18

1ዮሐ.ም 1$Ì1-ፍም

ግብ.ሐ.ም.8 $Ì14-26

ማቴ.ም.5 $ Ì 20-31

ቅዳሴ ባስልዮስ

አፉሁ ለጻድቅ ይትሜሀር ጥበበ፡፡

ወልሳኑ ይነብብ ጽድቀ፡፡

ወሕገ አምላኩ ውስተ ልቡ፡፡

መዝ.36 Ì 30

የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል፡፡

አንደበቱም ፍርድን ይናገራል፡፡

የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው፡፡

 

ቅዳሜ

03/07/08

 2 ተሰሎ.ም.1$Ì 3- ፍ

2ኛ.ጴጥ.ም.3$Ì14-ፍም

ግብ.ሐ.ም.4$Ì13-27

ማቴ.ም.12 $ Ì 25-38

ቅዳሴ ግሩም

ወባሕቱ መከሩ ይስዐሩ ክብርየ፡፡

ወሮጽኩ በጽምዕየ፡፡

በአፉሆሙ ይድኅሩ ወበልቦሙ ይረግሙ፡፡ መዝ. 61 Ì 4

ነገር ግን ክብሬን ይሽሩ ዘንድ መከሩ፡፡ ሐሰትንም ይወዳሉ፡፡ በአፋቸው ይባርካሉ፤ በልባቸው ይረግማሉ፡፡

በኢትዮጵያ የሃይማኖት ለውጥ ለምን አስፈለገ?

በቅኝ ገዥዎች የተላኩ ሚሽነሪዎች አንዱ አላማቸው እያታለሉ የሕዝቡን ሃይማኖት ማስለወጥ ነው፡፡ እየንዳንዱ ሰው ያደገበትን ሃይማኖት ሲለውጥ አእምሮው ላይ የተለያየ የአእምሮ ግጭት ይፈጠራል፡፡ በዚህ ምክንያት ጭንቀት ይጀምረዋል፡፡ ከዚህ የተነሳ የአእምሮው ጤናማ አስተሳሰብ ፍጽም ይዛባል፡፡

ስለሆነም እንደበፊቱ ያለ ጤናማ ማስተዋል አይኖረውም፡፡ በዚህ ምክንያት ጤናማ የነበረው ባህሪው ይለዋወጣል፡፡ ይህ ሰው የጭንቀት በሽታ ሕመም ስለሚሰማው እራሱን ችሎ የመቆም አቅም ሞራል አይኖረውም፡፡

ስለዚህ ለመቃወምም ሆነ ለሃይማኖቱ ለነፃነቱ ለመቆምና ለመዋጋት አይችልም፡፡ ምክንያቱ መንፈሱ የተቃወሰ ሰው ከጭንቀቱ ሕመም የተነሳ የሚርበተበት እና በፍርሃት ስሜት የሚኖር ሰው በመሆኑ ነው፡፡ ይህን ቅኝ ገዥዎች ሃይማኖት ማስለወጥን ፕሮጀክት ቀርጸው የአጭርና የረጅም ብለው እንደ ጦር መሣሪያ አድርገው ሒደቱን እየተጠቀመበት ይገኛሉ፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ በግድ የለሽነት ሰው በማጣቱ ነው እምነቱን ጥሩ ባሕሉን እና መልካም ሥነ ምግባሩን እየለወጠ ያለው የጭንቀት በሽታ ተጠቂ እየሆነም ቨይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃይማኖቱን ትቶ የፕሮቴስታንትን እምነት እንዲቀበል የሚደረግበት ምዕራባውያን ዓላማ አላቸው፡፡ እርሱም ሰዎች ያደጉበትን ማንነታቸውን ሃይማኖታቸውን በሚለውጡበት ጊዜ በአእምሯቸው ውስጥ ግጭት ይፈጠራል፡፡ ይህ ወደ ጭንቀት ያመራል፡፡ ከዚያም የተለያዩ ደረጃ ያላቸው የተባባሰ የአእምሮ ሕመም ይፈጠራል፡፡

የሆነው ሆኖ የሃይማኖት ለዋጮች ታማሚዎች ከምን እንደመጣ ሳያውቁት የአጋንንት መንፈሳዊ ውጊያ ነው ይላሉ፡፡ በዚህ በየጊዜው ለፈውስ ከመጸለይ በስተቀር ለነፃነታቸውና ተነሥተው በመቃወም አይዋጉም፡፡ በዚህ ደረጃ ላይ እያሉ በተፈጠረባቸው ጭንቀተ ምክንያት በጣም ድንጉጦች እና ፈሪዎች ናቸው፡፡ ይህን የአውሮፓ የቅኝ ገዥዎች ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ Continue Reading

ከባለፈው የቀጠለ

. ትክክለኛ እምነት ያላት ቤተ ክርስቲያን ፈተናዋ ለምን በዛ

ትክክለኛ እምነት ያላት ቤተ ክርስቲያን ማለት ከጥንት ጀምሮ በሕገ ልቡና በሕገ ኦሪት ማለትም በብሉይ ኪዳን እና በሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስን ሰማኒያ አሐዱን 81 በሙሉ የተቀበለች ሀገርና ሕዝብ ማለትም ታሪክና ሃይማኖት ያለው ስለሆነም ትክክለኛ እምነት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተፃፈው ሁሉ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ አምኖ የሚቀበል ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሕዝብ ነው፡፡

ይህንን በተመለከተ በ2ኛው የጢሞቴዎስ መልዕክት እንዲህ ይላል፣ ቅዱሳት መጽሐፍት ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው ናቸው ለማስተር ለመገሰፅ፣ ለማቅናት በጽድቅም መንገድ ለመምከር ይጠቅማሉ፡፡ ይኸውም የእግዚአብሔር ሰው ለመልካም ሥራ ሁሉ ብዙ ሆኖ እንዲያድግ ነው፡፡ (2ኛ ጢሞ. 3÷16)

ማርቲን ሉተር ከእግዚአብሔር ቃል ከመጽሐፍ ቅዱስ በላይ ራሱን አድርጎ የእግዚአብሔርን ቃል በራሱ ሥልጣን አስወግዶ፣ ሰርዞ እና ለውጦ 66 መጽሐፍ ቅዱስ ብሎ ጽፎ አሳትሟል፡፡ እንደዚሁም ማርቲን ሉተር ሲናገር የእኔ ቃል የክርስቶስ ቃል ነው የእኔ አፍ የክርስቶስ አፍ ነው ይል ነበር፡፡ ይህም ንግግር የተወሰደው ራሱ ከጻፈው መጽሐፍ ውስጥ ነው፡፡ (ኦ ሓሬ ፒኤፍ ዘፋክት አባውት ሉተር 1916-1987 እንደገና በታተመው ገጽ 203-204)

ማርቲን ሉተር በሮሜ መጽሐፍ ውስጥ የራሱን ቃል ጨምሯል

 

ማንም ሰው ሕግን በመፈጸም ሳይሆን በእምነት እንደሚጸድቅ እናረጋግጣለን፡፡ (ሮሜ 3÷28) ነገር ግን ማርቲን ሉተር በጀርመንኛ በተረጎመው መጽሐፍ የጨመረው በእምነት እንደሚጸድቅ የሚለውን ቃል እምነት ብቻውን ያጸድቃል ይላል፡፡ ሬስስ ሄረሲና ኦርቶዶክስ ኢን ዘሂስትሪ ኦፍ ዘቼርች ሄንድሪክሶን ፓፕሊሼር ፒቦዲ ኤም ኤ 1988 ገጽ 64-65)

እንደ ሉተር አባባል ማንም ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔር ቃል ጥሶ ብዙ የተለያዩ መጥፎ ወንጀሎችን እየሠራ ቢያምን እምነት ብቻውን ይበቃዋል ማለት ነው፡፡

ማርቲን ሉተር በጀርመንኛ ቋንቋ የተረጎመው በሮሜ መጽሐፍ ውስጥ የራሱን ቃል በመጨመር ብቻ የሚል ቃል ተጠቅሟል፡፡ (ሮሜ 4÷15)፡፡ ይህ የተወሰደው በጀርመንኛ ቋንቋ ከታተመው መጽሐፍ ነው (ኦ ሄሪ ከገጽ 201) ነገር ግን የሮሜ መጽሐፍ የሚለው ሕግ ቁጣን ያስከትላል ሕግ በሌለበት ግን መተላለፍ አይኖርም፡፡ (ሮሜ 4÷15)

. ፕሮቴስታንት መጽሐፍ ቅዱስ ትንታኔ ወይም ሔርሜኔ ዩቲክ

እ.ኤ.አ. በ1442 ዓ.ም ጉተንበርግ በተባለ ቦታ በጀርመን የፕሮቴስታንት አተረጓጐም ትንታኔ ወይም ሔርሜኔ ዩቲክ ተጀመረ፡፡ ከዚያም የፕሮቴስታንት ሥራዎች ሲያስተምሩ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር የሚነግርን የመጀመሪያው የእውቀት ምንጭ ነው፡፡

ስለዚህ የየቃሉ አተረጓጎም ትንታኔ ለቤተ ክርስቲያን ሕይወት በጣም ጠቃሚ ነው ብለው የራሳቸውን ሃሳብ አስፋፍተው እየፃፉ አሳትመው አሰራጩ የመጀመሪያው ትንታኔ ወይም ሔርሜኔ ዩ ቲክ ሲመራ የነበረው በማርቲን ሉተር ነበር፡፡ ስለሆነም የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታዮች በሕይወታቸው መከተል የሚገባቸው መሆኑን መመሪያ ሰጠ፡፡ ከዚያም የፕሮቴስታንት መሪዎች ማርቲን ሉተር የተረጎመውን እየተነተኑ ሲያስተምሩ ነበር፡፡

በቅኝ ግዛት ዘመን ያለው መጽሐፍ ቅዱስ

በሚሽነሪዎች አማካኝነት የፕሮቴስታንትን እመነት የተቀበሉ በአፍሪካ ውስጥ የፕሮቴስታንት አማኞች በየጊዘው በሀገራቸው ላይ እያዩት ያለው የቅኝ ግዛት እንቅስቃሴ ስላሳሰባቸው ጥያቄ ለተላኩላቸው ለሚሽነሪዎች አቅርበው ነበር፡፡

ነገር ግን የተሰጣቸው መልስ መንፈሳዊነት ይጎድላችኋል መጸሐፍ ቅዱስን በደንብ ስላልተረዳችሁ ነው፣ ስለዚህ ብዙ መማር ያስፈልጋችኋል አሏቸው፡፡ ወይም ሚሺነሪዎቹ 66 መጽሐፍ ቅዱስን ሰጧቸው እናም እንዲማሩ ተደረገ እነርሱም እንዳዘዟቸው ተማሩ፡፡ ነገር ግን ያገኙት ለውጥ የለም፡፡ ከዚህ የባሰ መሬታቸው በቅኝ ገዥዎች ቁጥጥር ሥር ዋለ ምንም ማድረግ ስላልቻሉ በባርነት ስር ወደቁ በሥጋዊም በመንፈሳዊም ተስፋፊዎች ወይም የቅኝ ገዥዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትንታኔ ወይም ሔርሜኔ ዩቲክ ያስፈለጋቸው አፍሪካ ለጥቁር ሕዝብ እምነት አስበው ሳይሆን በቅኝ ግዛት ለመያዝ እቅዳቸው ስለነበረ ነው፡፡ በዚህ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አፍሪካን በቅኝ ግዛት ጌታን ተቀበሉ በማለት ይዘው በመግዛት ላይ ለረጅም ዘመናት ይገኛሉ፡፡

የሃይማኖት መሪዎች በቅኝ ገዥዎች ሰልጥነው ወደ አፍሪካ የሚላኩ በሃይማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀሱ እና የእያንዳንዱን ሀገር መረጃ እየሰበሰቡ ለሀገራቸው መንግሥት በሰላይነት ወሬን የሚያቀባብሉ ናቸው፡፡ ስለዚህ ለቅኝ ገዥዎች እንደመሸጋገሪያ ድልድይ ሆነው የሚያገለግሉ እንጂ ትክክለኛ ሃይማኖተኞች አይደሉም፡፡

ሚሺነሪዎች የማርቲን ሉተርን 66 መጽሐፍ ቅዱስን ይዘው አፍሪካ ገብተው የሕዝቡን ሃይማኖት እና ባህሉን በማስለወጥ የራሳቸውን ቋንቋ እና ባህል ለመጫን ነበር፡፡ እንዲሁም በዚህ የማስተማር ተግባር ውስጥ ሆነው ሕዝቡን ሲከፋፍሉት ኑሯል፡፡ አሁንም በማንነቱ ላይ ገብተው እየከፋፈሉት ይገኛሉ፡፡ ስለዚህም ሚሺነሪዎች ለቅኝ ገዥዎች የሚያመቻቹ ከፍተኛ የመገልገያ መሳሪያዎች ነበሩ አሁንም ናቸው፡፡

ይቆየን ይቀጥላል

 

አባ ሳሙኤል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ  ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀጳጳስ

አዲስ አበባ

ከባለፈው

. የፕሮቴስታንቶችመጽሐፍ ቅዱስ ሉተራዊ ትርጉም

በሉተር አንደበት በአሥራ አምስተኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የተነገረውና ዛሬ ጦሱ ለሀገራችን የተረፈው የፕሮቴስታንቶች መከራከሪያ ነጥብ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ እንጂ በጎ ሥራ ወዘተ. የክርስትናና የክርስቲያን መመሪያ ሊሆን አይገባም የሚል ነው፡፡ ይህ Sola Scripture መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ የእምነት መገለጫ ምንጭ ነው፣ የሚለው ድርቅና፣ በመሠረቱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ፣ እንዲያውም ከመጽሐፍ ቅዱስና ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ አንጻር ስናየው ትርጉም የለሽ የሆነ ነገር ነው፡፡

ይሁንና ይህ ዋጋ ቢስ ክርክር ለሕዝባችን አንድነት ማጣት መሠረት የጣለ፣ ፈረንጆች በአጼ ንብለ ድንግል ጊዜ የጀመሩትን የሕዝባችን መከፋፈል ጉጉት አሁን በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ላይ ያሳካ እንቆቅልሽ ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ የማይችል ሰውም በመስማት ብቻ ክርስትናን ሊቀበል ይችላል፡፡ ጥንት የክርስቶስ ወንጌል የተሰበከውም በአብላጫው በቃል ነበር፡፡

በመለያየት እምነት እጅግ የተሳከሩ የፕሮቴስታንት ጽንፈኞች፣ ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት “ልዩ” ወይም “የበላይ” የሚያደርጋቸውን የሚመስላቸውን ሲፈልጉም የራሳቸው ትርጉም በመስጠት ሁሉ እየመረጡ፣ “ይህን መጽሐፍ ቅዱስ አለ”፣ “ይህን መጽሐፍ ቅዱስ አይልም” “መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሌለ አመላለክ ሁሉ ከኢየሱስ አይደለም ወዘተ. በማለት ልዩነትን ያሰፋሉ፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የነበሩ የክርስቶስን ተከታዮች፣ መጽሐፍ ቅዱስን ራሳቸው አንብበውና አምነውበት አልነበረም ክርስቶስን የተቀበሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውቀት ባላቸው የሃይማኖት አባቶች፣ እንዲሁም ነቢያት ሐዋርያትና ፃድቃን በራዕይ የተገለጸላቸውንና በቃል በመስማትም እንጂ”፡፡ Continue Reading