Archives

All posts for the month July, 2016

ወደ ዓለም ሁሉ ሒዱ፣ለፍጥረትም ሁሉ ወንጌልን ስበኩ፤ማር.1615

‹‹በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና›› እንዳለው ዮሐ 3፥16 በዚህ አምላካዊ ፍቅር ሁላችንም በመስቀሉ ተሰባስበን ለእኛም ያለውን ፍቅሩን ማሳየት ብቻ ሳይሆን ስለሰጠን ዛሬም ማንኛውም ክርስቲያን የቀለም፣ የቋንቋ፣ የነገድና የጾታ ልዩነት ሳያደርግ ሁሉንም በክርስቶስ ፍቅር አንድ አድርጐ ይመለከታል፣ ሥርዓቱም ትምህርቱም ይህ ነው። 1ኛ ጴጥ 4፥7/ ዮሐ 15፥12

የክርስትና ሃይማኖት ሰውን በሰውነቱ የማክበር ሥርዓት ያለው ሃይማኖት ነው

ክርስቲያናዊ ሃይማኖታችን ለሰዎች ሁሉ ትልቁ አክብሮትን ይሰጣል ከምናውቃቸው ይልቅ የማናውቃቸውን /አንዳችን/ ከፍ ከአሉት ይልቅ ችግር ዝቅ ያደረጋቸውን ዋጋና ሥጦታን ከሚመልሱት ይልቅ ምንም የሌላቸውን የማሰብና የማሳብሰብ በአጠቃላይ ከሚቀርቡን ይልቅ የሚያሳድዱን ከሚመርቁን ይልቅ የሚረግሙንን በጸጋ የመቀበል ነገር ግን ሰውን በሰውነቱ የማክበርና የመወደድ ሥርዓት ያለው ነው። በማይመች አካሄድ /2.ቆሮ 6፥14 / ከአልሆነ በቀር አብሮ የመኖርን የመቻቻልን ትዕግሥት የሚያላብስ ነው። ‹‹ለማንም ስለክፉ ፈንታ ክፉ አትመልሱ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ›› ተብሎ በታዘዘው መሠረት በተለይ ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያን በዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትእዛዝ መሠረት ልዩ ያደርጋታል።  በአጠቃላይ ሃይማኖታችን በእነዚህ ዓይነት በጐ ሥራዎች ላይ ቆም ብሎ ወርቅነቱ የሚታይ ዕሴታዊ ሃይማኖት ነው (ሮሜ 12፥17)

ክርስትና ለአዲስ ኪዳን አማኞች በሙሉ የተሰጠ ሹመት ነው በብሉይ ኪዳንም ቢሆን እግዚአብሔር ሕዝብ እስራኤል በሙሉ እንዲያገለግለው ወዶ ሳለ ሕዝቡ ለካህናት መንግሥትነት በሚበቁበት መታመን ውስጥ ስላልተገኘ የክህነት አገልግሎት የሌለው ሆነ፤ በአዲስ ኪዳን ግን እያንዳንዱ ክርስቲያን በአዲስ ሕይወት ተወልዷል። (1ኛ.ጴ¬ጥ .ምዕ 2፥9፣ ራእይ፡ ምዕ.1፥6) Continue Reading

“ይትዐየን መልአከ እግዚአብሔር ዓውዶሙ ለእለ ይፈርህዎ ወያዳኅኖሙ” እግዚአብሔርን ለሚፈሩት ለሚያመልኩት ሰዎች ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ በዙርያቸው ይከትማል ያድናቸዋል፡፡

መዝ. 33÷7

St Gebrielበዛሬው ዕለት ቤተ ክርስቲያናችን ወደምታከብረው ወደ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስና ወደ እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ በዓል ይወስደናል፡፡ ከክርስቶስ ልደት በኋላ በሦስተኛ መቶ ዓመት ላይ ክርስቲያኖች እየታደኑ በሚሠቃዩበትና በሚገደሉበት በዘመነ ሰማዕታት ጊዜ ቅድስት ኢየሉጣና ልጅዋ ሕፃኑ ቂርቆስ በአንድ እስክንድሮስ በተባለ ዐላዊ (ከሀዲ) መኰንን ልዩ ልዩ ሥቃይና መከራ ደርሶባቸው ነበር፡፡ ቅድስት ኢየሉጣ ከሦስት ዓመቱ ሕፃን ልጅዋ ጋር የምትኖረው በሮም ከተማ ነበረ፡፡ በዚያ አገር በክርስቲያኖች ላይ የተነሳው ስደት እጅግ ከባድ ስለነበር እሷንም ሃይማኖቷን እንድትክድና ጣዖት እንድታመልክ ይህ መኰንን ተጽእኖ ስላበዛባት ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሸሽታና ተሰዳ በመሄድ በዚያ መኖር ጀመረች፡፡ ያም መኰንን ወደዚያው አገር ተዛውሮ በመሄድ ቅድስት ኢየሉጣን ሃይማኖቷን ለውጣ ለጣዖት መሥዋዕት እንድታቀርብ ይጠይቃታል እሷም መኰንኑን “ስለ ሃይማኖት ጉዳይ ይህን የሦስት ዓመት ሕፃን ጠይቀው እርሱ ሁሉን ያስረዳሃል፤” አለችው፡፡ መኰንኑም የሦስት ዓመት ሕፃን ምን መናገር ይችላል በማለት ንቆት ዝም አለ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን ወዲያውኑ መኰንኑ ፊት ቀርቦ ስለ ክርስቶስ አምላክነትና የዓለም ሁሉ አዳኝ መሆኑን አብራርቶ ከመናገሩም ባሻገር፣ የመኰንኑ ጣዖት የሰው ሥራና ከንቱ መሆኑን በድፍረት ነገረው፡፡

መኰንኑም በዚህ እጅግ ተቈጥቶና ተናዶ በሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስና በእናቱ ኢየሉጣ ላይ ብዙ መከራና ሥቃይ አደረሰባቸው፡፡ የደረሰባቸው ስቃይ ግን በእግዚአብሔር ኃይልና ረድኤት ምንም ጉዳት ስለ አላደረሰባቸው የተለየ ከባድ ሥቃይ ሊያደርስባቸው አሰበ፡፡ በአንድ ትልቅ የናስ ብረት ጋን (በርሜል) ውስጥ ውኃ እንዲሞሉና በእሳት እንዲያፈሉት፣ እንዲሁም በውስጡ ሰም፣ ጨው፣ ባሩድ፣ ሙጫ፣ ቅንጭብና ቁልቋል እንዲጨምሩበት አዘዘ፡፡ ውኃውም ሲፍለቀለቅ ድምፁ እንደ ክረምት ነጐድጓድ ከሩቅ ይሰማ ነበር፡፡ Continue Reading