Archives

All posts for the month August, 2017

  1. ጥያቄ ፈተና እና ተጋድሎ? በመነኮሳት እንዴት ይገልጣል? በመጽሐፈ መነኲሳት ማር ይስሕቅ ምፍ ፮ አንቅፅ ፴፫

በእንተ ሕሊናት እኩያት እለ ይመጽአ በግብር እመንገለ ሐኬት ዘይከውን እምቅድሜሆን።

አው ከክፉ ሕሊናት አስቀድሞ በሚደርስ ስንፋና ካለመጠበቅ የተነሣ  ተአቅቦን በማስረሳት ከገዳም ወይም ከበአት በመወጣት በተለያየ ሁኔታ ሰይጣን በግድ የሚያመጣውን የክፉ ሕሊናትን ሁሉ በመብል፣ በመጠጥ በፍቅረ ንዋይ፣ ፍቅረ ሢመት የሚመጣ ፈተና ወይም ፆር ነው።

ወኢንመጡ ነፍሰነ ኵለንታሃ ለሐኬት ወለጽርዓት።

ተዓቅቦን ለመተውና ከገዳም ለመውጣት ሕገ ገዳምን ለማፍረስ ሰውነታችንን ሁሉ ለመብል፣ ለመጠጥ ለሐኬት አሳልፎ መስጠት ትልቅ ፈተና ነው።

በዚህ ምክንያት የተሰናከሉት እንዲህ ያሉት ሰዎች በሚጸልዩበት የጸሎት ጊዜ ክፉ ሕሊናን ገንዘብ አድርገው እግዚአብሔርን እናስብ ባሉ ጊዜ መብል መጠጥ ሌሎችም ፍትወታት እኩያት በሕሊናቸው በአእምርቸው ያመ                                                                                                                   ጣባቸዋል።

 ወዛቲ ይእቲ እንተ አጥረይናሃ ጊዜ ሐኬትነ።

በስንፍናችን በሐኬታችን ተዓቅቦን ባፈረስን ጊዜ የገባነውን ቃል ኪዳን በዘነጋን ወቅት ገንዘብ የምናደርጋት ውጤት ኃጢአት ናት።

የሕሊና ሁከት ክፉ ሕሊና ማለት አብዝቶ ከመመገብና ከመጠጣት ስንፍናና አእምሮ ማጣትም ልክ መጠን ከሌላቸው አብዝቶ ከመናገር ለሕይወት የማይሆን ጭሆት  እንዲሁ አብዝቶ ዋዛ ፈዛዛ ሐሜትን አሉባልታ ቀልድ ከመጫወት የተነሳ ሕሊናን ታሰናክላለች ልቡናንም ከጸሎት፣ ከስግደት  ከምሥጢር ከእግዚአብሔር ፍቅር ይለየዋል፣ ተዓቅቦን ራስ መግዛትን ያፈርሳልና።

መፍትው ለመነኮስ ዘተዓርቀ እምግብር ሰማያዊ ከመ ይኩን ግኁሠ እምኵሉ ግብር ዓለማዊ።

ከጊዜያት የተለየ መነኩሴ ከዓለማዊ ግብር መለየት ይገባዋል። ማለትም ከዓለማዊ ሥራ የተለየ ከዘመድ አዝማድ የተለየ መነኲሴ ፈጽሞ ለምነና ሕይወት እንቅፋት ከሚሆኑ ሁሉ መለየት አለበት።

መነኲሴ ልቡናውን ከማየት ከመስማት መከልከል አለበት።

እለ ናሁ ይድኅፁ ውስተ ዛቲ ምግባራት

በነቢብ በገቢር ፈተና እንዳይሰናከሉ በገዳም በበዓት በመጽናት፣ በመጠበቅ የገቢረ ኃጢአት ሥራ ሰይጣን እንዳያሠራቸው ከሰው በመለየት ከማየት ከመስማት (በአርምሞ) ጸጥ በማለት ከሚገኝ ተዓቅቦን በማዘውተር ድል መንሳት ይገባል።

ከመ የኀልዩ ኅሊናተ ርሱሐተ

ሰይጣን ክፉ ነገርን ያስቡ ዘንድ ክፉ ሕሊና ለክፉ ሥራ ይታዘዙ ዘንድ ልባቸው ላይ ክፉ ነገራትን እንዲፈጽሙ በአእሙሯቸው ያሳስባቸዋል።

‘‘ወይረክቡ ምትሐተ አባላቲሃ” በአእምሯቸው  የቀረጸውን  የተለያየውን  በዚህ ዓለም ያለውን ፍትወት ስስእት፣ ትዝሕርት፣ ትምክህት፣ በምትሐት ያገኛሉ። በዛን ጊዜ ወይርሕቅ እምኔሆም ዘይረድኦሙ።

 በዛን ጊዜ የሚረዳቸው የሚጠብቃቸው መልአክ ይለያቸዋል (እንደ ሙሴ ዘሴሐት ስንክሳር ዘመስከረም ፫)

ሙሴ ዘሴሐት ያልተማረ ጨዋ ምእመን ነበር። መንኖ ከሰው ተለይቶ ከበረሃ ወድቆ ይኖር ነበረ። ከብቃቱ የተነሣ አዕዋፍ እየመጡ ያጫውቱት ነበር። ሲፈልግም ለተለያዩ ተግባራት ይልካቸውና  እሺ በጀ ብለው ይላላኩት ነበር። ለምሳሌ ምግቡን ሳይቀር ከገነት የዕፁው ፍሬያት ያመጡለታል።

ከዕለታት በአንዱ ቀን ሰይጣን ሽማግሌ መነኲሴ መስሎ ታየው። ሙሴ ዘሴሐትም የወዴት ነህ ብሎ ጠየቀው። ሰይጣንም ሲመልስ ዓለማዊ ነበረኹ

አንዲት ልጅም ወልጄ አለሁ አሁን የሚረዳኝ አጥቼ ባስብ ባስብ አንተን አገኘሁ ስለዚህ እርዳኝ አለው።

ሙሴ ዘሴሐትም

መነኲሴ ሚስት ያገባልን አለው? ምነው እነ አብርሃም ሚስት በማግባታቸው ተጎዱ እንዴ አለው? ሙሴም

የእነ አብርሃምን ካገኘሁ ብሎ ከበአቱ ተከትሎት  ወጣ። ከዚህ በኋላ ከሰፊ ሜዳ ላይ ወስዶ ገሉን ጠጠሩን ወርቅ ብሎ አስመስሎ የዱር አራዊቱን ፈረስ፣ በቅሎ፣ ቅጠሉን፣ አበባውን ግምጃ አስመስሎ እሷን ከመጋረጃ ውስጥ አድርጎ አሳየው።

ወድያው እሱ ደግሞ የሞተ መስሎ ታይቶታል ይህስ የሚገርም ብሎ  ሙሴ ሰይጣኑን በሰው አምሳል የመጣውን ቀብሮ ወደሷ ተመልሶ ቢሄድ ምትሐት ሁና ጠፋችበት። ማርይሳ ምዕ. ፬፥

  1. ለመነኲሴ ሹመትና ሽልማለት!! ማለት ምን ማለት ነው። መልሱ ይህ ነው ማር ይሳ ምዕ.፩ ና በአንቀጽ ፴፫

ሰው ክቡር ነው እግዚአብሔርን ለማገልገል ብሎ በበአት በዋሻ በገዳም ደስ ብሎት መከራ መስቀል በማሰብ መከራ ለመቀበል ቢዘጋጅ  በነፍሱ  ከኀልዮ ኃጢአት ጽሩይ (የጠራ) ይሆናል።

 ጸጋ እግዚአብሔር ስለ አዱረበትም ማንን ማንንም ባይነቅፍ ባያማ

 ከፍትውት ከፆር የተለየ ከመከራ የራቀ ነው። ለእመ ኢመጽአ ኀበ   

 ክብራት መነኲሴ ተድላ ሥጋ ባይወድ። ወለእመኢተቈ ጥዐ በቅድመ እለ    ይሜንንዎ።በሚንቁት በሚጠሉት በሚያጥላሉት ሰዎች ዘንድ የማይቆጣ የማይቀየም

እስመ ናሁ ሞተ እምዛቲ ሕይወት

እነሆ እርሱ ከዚህ ዓለም የሚኖሩ ዓለማውያን ሥራ ተለይቷዋልና  አንድ ጊዜ ሞቷልና።

አባቶች ሌላው ገጽታቸው

ኢትመንኖዎ ለኃጥእ—- ይላሉ

በደል ያለበት ሰው እንኳን ቢኖር ኃጥኡን ኃጥእ ነው ብለህ አትንቀፈው

እስመ ኲልነ አባስያን

ሁላችንም ኃጥአን ነንና በእግዚአብሔር ፊት ማንም ጻድቅ የለም።

ሕገ እግዚአብሔር ስለ አፈረሰ ብለህ ለመገሠጽ ብትቆጣም በጥንቃቄ ይባስኑ እንዳይጠፋ

‘‘ብኪ በእንቲአሁ” ስለእሱ ብለህ አልቅስለት እዘንለት፣ ጾልይለት እንጂ አትጥላው። መሆን ያለበት መፍትው ለከ ከመ ትጽላእ ኃጣዊኢሁ።

አንተ መጥላት ያለብህ የሚሠራትን መጥፎ ሥራና ኃጢአትን ነው። ማለትም በግብር እንዳትመስለው መሆን ይገባሃል። አላ ሰአል በእንቲአሁ

ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታች ኢየሱስ ክርስቶስ ትመስለው ዘንድ። ‘‘እስመ ውእቱ ረፈቀ” ምስለ አባስያን እርሱ ሳይቀየማቸው ከኃጥአን ከመጸብሃን ጋር በልቷልና። ማቴ. 9፥10 (ሉቃ. 23፥4)

በእኛ በሰው ልጆች ከሚዘብት ከሰይጣን የተነሣ አንተን በሚመስል ሰው የሚዘብትን ለምን ትጠላው።

ፍቅር ከሌለህ ጻድቅነትህ ፍጹምትነህ ርትዕነትህ ወዴት አለ?

ኃጥኣን ከግብራቸው ተመልሰው በትሩፋት በመጽናትና በተአቅቦ ይኖሩ ዘንድ ኃጢአተኛ በደለኛ ብለህ ከመስደብ ይልቅ በቀቢጾ ተስፋ ከንስሓ እንዳይርቁ ማድርግ ግድ ነው።

  1. ለመነኮሳት ክብራቸውና ጽድቃቸው ወይም ማዕረጋቸው በምን ይገለጣል።

ለክብራቸው ፍጻሜ የለውም

እስመ ኲሎሙ ይከውኑ አማልክት ዘበጸጋ።የምንኲስና ሥርዓትና ሕይውት ጠብቀው በተባሕትዎ በተባሕትዎ በጽፁምነት የኖሩ አበው መነኲሳት

 

በፈጣርያቸው ቸርነት ሁሉም አማልክት ዘበጸጋ ይባላሉና። በሚያከብራቸው በጌትነቱ ብርሃን የተሰጣቸውን  የጽድቅ ክብር ያያሉና።

በአእምሮ በትሩፋት በተጋድሎ ፍጹማን የሆኑ ሁል ጊዜ የሚሰጥ መአርግ የጌትነቱ ክብር ይጨመርላቸዋል።

  • ወደ ፍጹም አንክሮም የምታደርስ ይህች ናት።
  • ልቡናቸውን ሰማያዊ ያደረጉ መናንያን አባቶቻችን ዓለምን ከነ ግንሣግንስ ጥለውታል ረስተውታል።
  • ለዚህም ነው ምንኲስና ወደ ፍጹም አንክሮ የምታደርስ ክብርት ናት። ለኖረበት ለተጠቀመበት።

“ ፍቃድህን ሁሉ ለእግዚብሔር ፈቃድ አስገዛ ማለትም ያንተን ፈቃድ

  ትተህ  የእግዚአብሔርን ፈቃድ ፈጽም”

በመዓልትም በሌሊትም በንጽሐ ልቡና ወደ እግዚአብሔር ለምን። ወደ

ንጽሐ ልቡና የደረሱ አባቶች እርሱን አይተውት ደስ ይላቸዋልና ለካ ይህን ያህል ለትሩፋት ለጾም፣ ለጸሎት፣ ለስግደት፣ ለተባሕትዎ ይተጉ የነበሩ ከዚሀ ለመድረስ ነው ብዬ አንክሮዬ በዛ።

ሶቦ ኀለየ ልብየ

ልቡናዬ የንጽሐ ነፍስን ነገር ባሰበ ጊዜ በንጽሐ ነፍስ ያሉ ጻድቃንን ባሰብሁ ጊዜ የንጽሐ ነፍስን ነገር እመረምር ዘንድ በንጽሐ ነፍስ ያሉት አይ ዘንድ

በወደድኊ ጊዜ ከንጽሐ ነፍስ ማዕረግ ደረስኩ እንደ አዳም በስምንተኛው ማዕረግ ደረስኩ

ዳግመኛ ከንጽሐ ነፍስ ወደ ንጽሐ ልቡና ወጣሁ ክንጽሐ ልቡና ለመድረስ ይተጉ የነበሩ ስለ ጻድቃን ነገር አንክሮዬ በዛ። የሥጋ ንጽሕና በሥጋ ከሚሠራ ኃጢአት መንጻት ነው።

የነፍስ ንጽሕናም በልቡና ከምትኖር ከኅልዮ ኃጢአት መለየት ነው።

‘‘ንጽሐ ልቡናሰ ይከውን በርእየ ምሥጢራት”።

የልቡና ንጽሕና ግን ምሥጢር በማየት ይገኛል።

በነፍስ በሥጋ ከሚሠራው ኃጢአት በእግዚአብሔር አጋዥነት ንጹሕ ነውና።

“ነፍሶሙኒ ዘእንበለ ሕማም” ነፍሳቸውም ኀልዮ ኃጣውእ የለበትም። ከንጽሐ ልቡና ማዕርግ ደርሰዋል።

የልቡና ንጽሕና የነፍስ በሚሆን ዕውቀት ከክፉ ሕሊና ሲርቁ የሚሰጥ ሲሆን ከሕዋሳተ ሥጋ በልዩ ላሉ ለሕዋሳተ ነፍስ ሰማያዊ ምሥጢር በማየት ጊዜ ከፍጹምነት የተነሣ የሚሰጥ ነው። ለምን በብዙ ነገርና ወገን ለክርስቶስ ካለው ወይም መከራ መስቀሉን በማሰብ መከራን ተቀበሉ። በተለያየ ጊዜ ሰዎች በሚደርሱባቸው የተለያዩ የእድሜልክ ፈተናዎች ስለተፈተኑ ፈተናውን በትእግስት ድል ስለነሱ መነኲሳት። ከዚህ በኋላ “ዝ ውእቱ  መካነ ፍስሐ ኀበ አልቦቱ ጽላሎተ ሞት”።

የሞት ወሬ የማይሰማበት ቦታ ይህ ነው ይላቸዋል። አምላካቸው ምክንያቱ ስለ ጽድቅ ብለው ተርበዋልና፣ ተጠምተዋልና። የጨለማ ወሬ የሐሜት ወሬ  የማይሰማበት ራበኝ ጠማኝ የማይባልበት ቦታ ይህ ነው።

ከመ ትረሱ መንግሥተ ሰማያት ዘድልው ለክሙ”

 አስቀድሞ የተዘጋጀላችሁ መንግሥተ ሰማያት ትወርሱ ዘንድ።

ጽድቅን እንደ እህል የሚርባቸውና እንደ ውኃ የሚጠማቸው ጽድቅን አግኝተው ስለ ሚረኩ ደስ ይበላቸው። ማቴ. 5፥-5

ዝ ውእቱ ብሔረ ሕይወት!

በሕይወት በተድላ የሚኖሩበት ከተማ ይህ ነው።

ከጾም፣ ከጸሎት፣ ከስግደት፣ ትሩፋት ልሥራ ከማለት “ናሁ በጽሐ ይእዜ መዋዕለ ዕረፍት” እነሆ የሚያርፉበት ጊዜ ደረሰ ራእ፳፩፥፫

 

ከብፁዕ አቡነ ሳሙኤል

 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀጳጳ

 አዲስ አበባ

 

እግዚአብሔር የሚለው ስም የባሕርዩ ነው። ዓለምን ፈጥሮ የሚገዛ የማይታይና የማይመረመር  ሁሉን  ማድረግ የሚችል ሁሉንም የፈጠረ መጀመርያና መጨረሻ የሌለው ዘለዓለማዊ አምላክ መኖሩን  እናምናለን።

ከጌታችን ከመድኀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ከሐዋርያት ከሊቃውንት በሦስቱ ጉባኤዎች

፩ኛ. በ፫፻፳፭ ዓ.ም በ፫፻፲፰ ሊቃውንት በኒቅያ ጉባኤ የተወሰነውን

፪ኛ. ፻፶ በ፫፻፹፩  ዓ.ም  ሊቃውንት በቁስጥንጥንያ ጉባኤ የተወሰነውን

፫ኛ. በ፬፻፴፩ ዓ.ም በ፪፻ ሊቃውንት  በኤፌሶን ጉባኤ የተወሰነውን

በተወሰነው ውሳኔ መሠረት በምሥጢረ ሥላሴም ሆነ በምሥጢረ ሥጋዌ  ቤተ ክርስቲያናችን የምታስተምረው ትምህርት  የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ጠብቆ በማስጠበቅ ለማስተማር ነው።

ሀ. «ከሥጋዌ በፊት ቃለ አካል አልነበረውም» የሚሉትን እነ ጳውሎስ ሳምሳጢን እናወግዛለን

ቃልከሥጋዌም በፊት አካላዊ መሆኑን እናምናለን እናስተምራለን።

ለ. የስብአልዮስንም ያንድ ገጽ ትምህርት እናወግዛለን፤ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ፍጹማነ አካል

መሆናቸውን እናምናለን እና ስተምራለን።

ሐ. «ወልድ ፍጠር ነው»  የሚሉ አርዮሳውያንንም እናወግዛለን። አብ ልጄ  ይህ ነው ብሎ  የመሰከረውን

ተቀብለን አብ የወልድ አባት መሆኑን እናምናለን አባት ልጄ ነው  ካለ ለልጅ  ከአባት የበለጠ

ምስክርየለውምና። ወልድም« እኔን ያየ አባቴን አየ እኔና አብ አንድ ነን»(ዮሐ.፲፬ ፥ ፱-  ፲፥፴)  ባለው

መሠረት   ወልድ የአብ የባሕርይ ልጅ መሆኑን እናምናለ  እናሳምናልን። በዚህም የኒቅያ ጉባኤ  ወሳኔ

እንቀበላለን። ዘተወልደ ወአኮ ዘተገብረ ወልድ  የተወለደ  እንጂ ያልተፈጠረ መሆኑን እናምናለን

እናስተምራለን።

መ. መንፈስ ቅዱስም ከአብ የሠረጸ ከአብና ከወልድ የተካከለ መሆኑን እናምናልን (ማቴ ፫ ፥ ፲፮

የሐዋ ሥራ ፪፥፫) በ ፫፻፹፩  በቁስጥንጥንያ ከተሰበሰቡት አንድ መቶ ሃምሳ አባ ቶች ጋር ሆነን

መንፈስ ቅዱስን ሐጹጽ ያለ   መቅዶንዮስን እናወግዛለን።

ሠ. በምሥጢረ ሥጋዌም  የእግዚአብሔር ልጅ ቃል

ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ  ከንፍሷ ነፍስ ነስቶ መዋሐዱን እናምናልን  ስለዚህም

«ሥጋ እነጂ ነፍስ አልነሳም» ለሚሉ   መናፍቃን እናወግዛለን።

ረ. እመቤታን ድንግል ማርያም ወላዲተ እግዚአብሔር መሆኗን እናምናለን። ስለዚህም« አምላክ እሷ

በወለደችው አደረ የሚሉ ትን እነ ንስጥሮስ በ፬፻፴፩ በኤፌሶን ከተሰበሰቡት ፪፻ አበው ጋር

ሁነን  እናወግዛለን።

ሰ.  ወላዲተ እአምላክ ቅዱስት ድንግል ማርያም ቅድመ ፀኒስ፤ ጊዜ ፀኒስ፤ ድኀረ ፀኒስ፤ ቅድመ ወሊድ፤ ጊዜ

ወሊድ፤ ድኀረ ወሊድ፤ ድንግልናዋን እናምናለን።  በአማላጅነቷም እናምናልን። ስለዚህም

«ተደመረት ድኀረ ወሊያድ» የሚሉ መናፍቃን (ዘውእቱ ጸረማርያም ብሂል) እናወግዛለን።

ሸ. በቅዱሳን መላእክትና በቅዱሳን ሰማእታት በቅዱሳን ጻድቃን አማላጅነት እናምናለን ተሐድሶ

መናፍቃንን  እናወግዛለን ።

ቀ.  እመቤታችን የወለደችው ሥግው ቃል ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ

መሆኑን እናምናለን ስለዚህም «ሁሉት አካል ሁለት ባሕርይ»  የሚሉ እነ ንስጥሮስ እናወግዛለን።

በ. በተዋሕዶ የሥጋ ገንዘብ ለቃል የቃል ገንዝብ ለሥጋ ስለሆነ ሥግው ቃል አንድ አካል አንድ ባሕርይ

አንድ ግብር አንድ ፈቃድ መሆኑን እናመናለን። ስለዚህም «መለኮት ይገብር  ግብረ መለኮት

ወትሰብእት ይገብር ግብረ ትስብእት» የሚሉ ልዮንንና በኬልቄዶን ፬፻፶፩ ዓ /ም የተሰበሰቡት

፮፻፴፮ መናፍቃንንና  ተከታዮቻቸውን እናወግዛለን።

ተ. በመጨረሻ በምሥጢረ  ተዋሕዶ ውላጤን ሚጠትን ቱሳሔን የሚያስተምሩ እነ አወጣኪን

እናወግዛለን።

 

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

 

 

ከብፁዕ አቡነ ሳሙኤል

      በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

       የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀጳጳስ

  አዲስ አበባ