ልዑል ባሕርይ እግዚአብሔር አምላካችን ከዘመነ ሉቃስ ወንጌላዊ ወደ ዘመነ ዮሐንስ
ፍስሐ ዜናዊ በሰላም በሕይወት በጤና እንኳን አደረስዎ!!
ወትባርክ አክሊለ ዓመተ መሕረትክ፣
ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም
ወይረውዩ አድባረ በድው
በቸርነትህ ዓመታትን ታቀናጃለህ፣ዘመናትንም ታበዛዋለህ። ገዳማት ልምላሜውን አግኝተው ደስ ይላቸዋል። በበረኃ ያሉት ተራራዎች ሁሉ ዝናሙን ይረካሉ። ኮረብታዎችም ደስ ብሏቸው ልምላሜውን እንደዝናር ይታጠቃሉ።መዝ.64፥11-12
ርትዕሰ እምድር ሠረጸት፣ ወጽድቅኒ እምሰማይ ሐወጸ፣ወእግዚአብሔርኒ ይሁብ ምሕረቶ።
እውነት ከምድር በቀለች፣ ጽድቅም ከሰማይ ተመለከተች፣ እግዚአብሔርም በጎ ነገርን ይሰጣል። መዝ 84፥10-11
“የዘመናት ባለቤት እግዚአብሔር አምላካችን ዘመናትን ጊዜያትን በሚመጡ ጊዜያት በሚመጡት ዘመናት እግዚአብሔር አምላክ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለጠግነት ይሰጠን ዘንደ ነው።” ኤፌ. 2፥6
ቸሩ አምላካችን ዘመኑን የሰላም፣ የጤና፣ የበረከት፣ የፍቅርና የሕይወት ዘመን ያድርግልን አሜን!!
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን !!
አባ ሳሙኤል
በኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ
አዲስ አበባ