Archives

All posts by admin

        ልዑል  ባሕርይ  እግዚአብሔር  አምላካችን  ከዘመነ  ሉቃስ  ወንጌላዊ  ወደ ዘመነ  ዮሐንስ               

           ፍስሐ ዜናዊ  በሰላም በሕይወት  በጤና  እንኳን  አደረስዎ!!

                            ወትባርክ አክሊለ ዓመተ መሕረትክ፣

                           ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም

                          ወይረውዩ አድባረ በድው

በቸርነትህ ዓመታትን ታቀናጃለህ፣ዘመናትንም ታበዛዋለህ። ገዳማት ልምላሜውን አግኝተው ደስ ይላቸዋል። በበረኃ ያሉት ተራራዎች ሁሉ ዝናሙን ይረካሉ። ኮረብታዎችም ደስ ብሏቸው ልምላሜውን እንደዝናር ይታጠቃሉ።መዝ.64፥11-12

ርትዕሰ እምድር ሠረጸት፣ ወጽድቅኒ እምሰማይ ሐወጸ፣ወእግዚአብሔርኒ ይሁብ ምሕረቶ።

እውነት ከምድር በቀለች፣ ጽድቅም ከሰማይ ተመለከተች፣ እግዚአብሔርም በጎ ነገርን ይሰጣል። መዝ 84፥10-11

“የዘመናት ባለቤት እግዚአብሔር አምላካችን ዘመናትን ጊዜያትን በሚመጡ ጊዜያት በሚመጡት ዘመናት እግዚአብሔር አምላክ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለጠግነት ይሰጠን ዘንደ ነው።” ኤፌ. 2፥6

ቸሩ አምላካችን ዘመኑን የሰላም፣ የጤና፣ የበረከት፣ የፍቅርና የሕይወት ዘመን ያድርግልን አሜን!!

 

                                           ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን !!

 

አባ ሳሙኤል

በኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ

 አዲስ አበባ

 

ስለ ሰላምና ዕርቅ እንዲሁም ግጭት አፈታ አስመልክቶ ከዚህ በታች የተገለጹትን በዚህ መነሻነት ከዚህ ቀጥሎ የተዘጋጀው ጽሑፍ እውነተኝነት ሃይማኖተኝነት ስለም እና ፍትሓዊነት አፈታትን ጥያቄዎች  ስለሆነ አንባቢ እያንዳንዱን ክፍል ከነበባ በኋላ  ስለዚህ እነዚህ

ጥያቄዎች  በአግባቡ የቤት ሥራዎች ይሠሩበት ከመጽሐፉ የተወሰዱ ጥቃዎች  በአግባብ ይሥሩ

1.     ሰላም በአያንዳንዳችን እጅ ነው ስንል ምን ማልታችን ነው?

2.    ቤተክርስቲያና ስለሰላም አጥብቃ እንድ ታሰተምር በተለይ ሰባኪያን ስለሰላም በአግባቡ እንዲያስተምሩ ምን ዝግጅት ማድረግ አለባት ?

3.    የሃይማኖት አባቶች በንስሐ ልጆቻቸው በኩል ሰላምን እንዲያስተምሩ የሰላም መመሪያ ቢዘጋጅ መልካምነቱን ይግለፁ ?

4.    ሰላም ከእምነት፣ ከመልካም አስተዳደር፣ ከዲሞክራሲ እና ከልማት ጋር እንዴት መጣጣም ይቻላል?

5.    ሰላምንና ግብረገብነትን በየደረጃው በትምህርት ቤቶች እንዴት ማስተማር ይገባል?

6.   ከመጽሐፉ በተገኘው ትምህርት በግልም ሆነ በቡድን ስለሰላም ምን መደረግ አለበት ይላሉ?

7.    የሃይማኖትና የመንግሥት ባለሥልጣናት ስለሰላም ጉዳይ አርአያ ሆነው ይታያሉ ወይ?

8.    መሪዎች ራሳቸውን የሰላም ሐዘዋርያ አድርገው ሌላውን ባገኙት አጋጣሚ ማስተማር ችሏል?

9.   ሰለሰላም ለማስተማር ከሚከተሉት እነማን በበለጠ ይሳተፉ?

                ሀ.  የደብር አስተዳዳሪዎ

                ለ.  ካህናት 

                .  ሰባክያነ ወንጌል

                .  የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች

                ሠ.  የእድር መሪዎች

                ረ. የቀበሌና የወረዳ አመራር አባላት

                ሰ. ሌሎች የመንግሥት አካላት 

10.  ከላይ የተጠቀሱት ሁሉም፣ ስለ ሰላም ጠቃሚነት ከ5 ገጾች ባልበለጠ አስተያየትዎን ያዳበሩ

1.     ሃይማኖቶች ስለ ሰው ተፈጥሮና ምንነት ሲገልጽ የሰው ልጅ ፈጣሪ ልዩ ትኩረት የሰጠውና በከንቱ  ያልተፈጠረ ፍጡር  ነው ስንልምን ማለት ነው?

2.    ሰው ሃይማኖተኛ ፍጡር እንደሆነ የሃይማኖት ሊቃውንተ ይናገራሉ ሃይማኖታዊ ዝንባሌም የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህርይ ነው ስንል ምን ማለት ነው?

3.    ሃይማኖት የሰዎችን አመለካካትና ጠባይ ለመለወጥና ለመቃኘት ጠንካራ መሳሪያ እንደሆነ የተለያዩ መረጃዎች ያመለክታሉእርሱሶስ የሃይማኖት አባቶ ምን ቢያደርጉ የተሻለ ነው ይላሉ?

4.    የሃይማኖት አባቶች ቸርነትና ለጋሽነት የበጎነትና የነፃ አገልገሎት በመስጠት በፍትሕ በሰላምና ዕርቅ ጉዳዮች በመሰማራት ጠንካራ ማኅበራዊ ትሥሥር በመፍጠርና በሰዎች መካካል ድንበር ተሻጋሪ ቤተሰባዊነት በመገንባትም አስተዋጽኦ አላቸው ይላሉ?

5.    የሃይማኖት መሠረታዊ የጋራ ዕሴት ለሰው ልጅ በሙሉ ለመንፈሳዊ ሕይወት ብቻ ሳይሆን  ለምድራዊ ሕይወት ጭምር በጣም አስፈላጊ ነው ታድያ እንዴት ማስተማር ይገባል?

6.   ለሰው ልጅ ሰላማዊ አኗኗር የሚጠቅሙ በርካታ የጋራ ማኅበራዊ  ዕሴቶች ውስጥ የተወሰኑትን የጋራ ዕሴቶች  በተጨባጭ ይጥቀሱ?

7.   ሃይማኖት የጋራ ዕሴት መሆኑን በማጠበቅ የሚገኘውን ግለሰቦዊ በማኀበራዊነት ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ፋይዳ ለትምህርት እንዲውል እነ ማን ይሳተፉ?

8.   ሃይማኖት የጋራ ዕሴት መሆኑን ባለማወቅና ባለመጠበቅ በግለሰቦች በማኅበረሰብ በሀገር እንዲሁም በመላው ዓለም ሰላምና የሰው ልጅ አብሮ የመኖር ባህርይ ላይ የሚያስከትለው ሁከት፣ ኢፍትሐዊነት፣ ጥላቻ ፣ማስገንዘብ መፍታት  እንዴት ይቻላል?

9.   ሃይማኖቶች የሰው ልጅ በመጨው ዓለም ከሚኖረው ዋጋ በተጨማሪ  በዚህ ዓለም   

 ሲኖር በሚኖረው የርስ በርስ ግንኙነት ወሳኝ ሚናዎች ምንና ምን ናቸው ይላል?

10.       ሰው በአምልኮት ከፈጣረው ጋር የሚገናኝባቸው በማኅበራዊ ኑሮው ሰው ከሰው ጋርና   

     ከተፈጥሮ ጋር በሰላም የሚኖርባቸው መሣሪያ  ምድን ናቸው ይጥቀሱ?

§  ከዚህ መሠረታዊ ግንዛቤ በመነሳት በሃይማኖቶች መካከል ያሉ ሃይማኖታዊ የጋራ ዕሴቶን ምንነት በአጭሩ ከላይ የተጠቀሱት  10 መጠይቆች ስለ ሃይማኖት እና

§  ሰላም ማለት በስምምነት፣ በፍቅር፣ በአንድነት፣ በተመሳሰብ፣ በመከባበር፣ የመኖር ውጤት ጠቃሚነቱን ከ5 ገጾች ባልበለጠ አስተያየቶትን ያዳብሩ

1.   እውነት የቃል (የንግግር) ነው?

2.   እውነት የሥራን (ተግባር)፣ የሐቀኝነት ነውን?

3.   እውነት ሐሳብን እና (ዕቅድን ) ይገልጻል?

4.   የእውነት ትክክለኝነት፣ ቀጥተኝነት፣ ሐቀኝነት፣ ታማኝነት፣ ተቀባይነትና እርግጠኝነት  እንዴት ይገለጽ?

5.   ትእውነት በሃይማኖት አስተምህሮ ከፍተኛ ቦታ ይሰጠዋል እርሶ እዴት እውነትን ይገልፁታል?

6.   እንደ ሃይማኖቶች አስተምህሮት እውነት በእራሱ የመጨረሻ ግብ ነው ብለው ያምናሉ እንዴት?

7.   እውነተኝነት በራሱ የመተማመን፣ የአዋቂነት፣ የቅንነት፣ የመልካም ሰውነት፣ የጀግንነት፣ የርኁርኁነት፣ አውንታዊነት፣ ሚዛናዊነትና የነፃነት  መገለጫ ነው ካሉ እንዴት ይገለጻል?

8.   እውነተኛ ሰው  በእውነት ላይ ከፍተኛ አመኔታ ስላላው እውነት ይናገራል፣ እውነትን ይሠራል እንጂ እውነትን በግድ ተቀበሉ አይልም፣ ስለእውነት አያታልልም ወይም አያስመስልም መልካምነቱ እንዴት ይገለጻል?

9.   ወሸተኛ ከንፈር በእግዚአብሔር ዘንድ አጸያፊ ነው፣ እውነትን የሚያደርጉ ግን በርሱ  

    ዘንድ የተወደዱ ናቸው” የሚለው በምን ላይ ነው?

10.       ፍትሕ ከእውነትኛነት ከሰላም ጋር ቁርኝነት እንዳለው የሃይማኖት ሊቃውን ያስረዱናል   

 ከቅዱሳት መጻሕፍት ይጥቀሱ? 

11.       እውነት ከተያዘ ፍትሕ አይጓደልም፣ እወነተኛ ሰውም ቅን ፈራጅ ሚዛናዊ ወይም ፍትሐዊ ነው ብለን ካልን በእነዚህ       ከላይ በተቀመጡ 11 ጥያቄ መሠረት መልሶት ከ5 ገጾች ባልበለጠ ይጻፉ?

1.     ፍትሕ ሲነሣ በአንተ ሊሆን የማትወደውን በሌላው ላይ አታድርግ የሚለው ፍትሐዊ ወርቃማ መመሪያ በሁሉም ቅዱሳት መጻሕፍት መገለጡ ልናስተውል ይገባል በዚህ መሠረት በየትኛው የመሐፍ ቅዱስ ምዕራፍና ቁጥር ነው የተጠቀሰው?

2.    ፍትሕ ከእውነተኛነትና ከሰላም ጋር ቁርኝነት እንዳለው የሃይማኖት ሊቃንት ያስረዱናል እንዴት ሆኖ?  

3.    ፍትሕ ካለ ሰላም አለ ፍትሕ ከሌለ ሰላም የለም ሰላም የፍትሕ ፍሬ ነው ይላሉ እርሶስ ምን ይላሉ?

4.    ይቅር ባይነት ጠባይም የአማኞች እንዲሆን ቅዱሳት መጻሕፍት ያስተምሩናል ይቅርታ ሰላም እንዳይደፈርስና ዕርቅ እንዳሰፍን ፍትሕ እንዳይጎድል ጥላቻና ልዩነተ ንዳይነግሥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ብለው ካሉ እንዴት?

5.    ይቅርታ በይቅርታ ጠያቄና በ-ይቅርታ ባይ መካከል ያለ ትልቅ ክፍተት ነው የሚሉትካለ?

6.   ይቅርታ ባዮች ፍትሐዊ፣ ቅን፣ የፍቅርና የሰላም ሰዎች ናቸው ሰዎች  ብለው ይላሉ ምክንያቱስ?

7.    ይቅርታ ካለ ጠበኝነት፣ ቂም፣ በቀል፣ ቅንዓት፣ የሉም ማለት ነው እንዴት ሆኖ ይግለፁ?

8.    እግዚአብሔር አምላክ ሰዎች የይቅርታ ባለቤቶች እንዲሆኑ ፈቃዱ ነው ግብዞችና ትምክህተኛች እንድንሆን ግን አይፈቅድምየሚለውን ከመጽሐፍ ቅዱ በማገናኘት ይብራሩት?

9.   ለሰዎች ስሕተታቸውን ይቅር ብትሉ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ኃጢአታችሁ ይቅር ይላችኋልና፣ ለሰዎች ግን ስሕተታቸውን ይቅር ባትሉ የሰማይ አባታችሁ ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም ይቅር የምንለው ማነው እንዴትስ ነው?

 

1.  ሃይማኖቶች ተከታዮቻቸው የሆኑ ምእመናንን ለበጎ ነገሮች ታዛዥ እንዲሆኑ ለክፉ ነገሮች ደግሞ እምቢተኛ እንዲሆኑ  ከአማኞች ምን ይጠበቃል ይላሉ?

2.  ከሃይማኖት ተቋማት ሰዎች ለቤተሰብ ታዛዥነት፣ መልካም ለሆኑ ለማኀበራዊ ሕግጋት ተገዥነት እንዲኖራቸው ከትምሕርት ቤቶች ምን ይጠበቃል?

3.  አባትህን እና እናትህን አክብር፣ አታመንዝር፣ አትስረቅ፣ በሐሰት አትመስክር፣ የባልጅራህን? አትመኝ፣ ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ የሚሉት ትእዛዞች ጥቅሱን በማስቀመጥ ይበራሩ?

4.  ሰላም፣ ፍቅር፣ ደስታ ፍትሕና ብልጽግና መከባበር ሰብዓዊነት ነው ብለው ያምናሉ?

5.  የሥነ ምግባር መርሆዎች የሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ዕሴቶች ምንጮች በመሆናቸው ጠቀሜታቸው ለማነው ለአገር ለቤተሰብ ለሁሉም ለተወሰኑ ?

6.  ሃይማኖታዊ የሥነ ምግባር መመሪያዎች በአብዛኛው እንዲተገብሩ የሚጠብቁት በግለሰብ ደረጃ፣ በሃይማኖት አባቶች በቤተ ሰብ፣ በወጣቶች በማህበረ ሰብ?

7.  በሥነ-ምግባር ዝርዝር ውስጥ የተጠቀሱት መመሪያዎች እንዲጠበቁ ምን መደረግ አለበት ይላሉ?

8.  ማንኛውም ግለሰብ ከሌላው ጋር በሚኖረው መልካም ግንኙነት ምክንያት የተሻለች አገር እንድትኖር የሥነ-ምግባር መርኅ ማለትም ሰላማዊነት ሰውን ማክበር፣ ለቤተሰብ ተገቢውን ትኩረትና ድጋፍ መስጠት የሚኖረበት አካባቢ ለሰብዓዊነት በአምላክ ለተፈጠሩ ሁሉ ምቹ ማን ምንመሥራት አለበት ይላሉ?

9.  በግለ ሰብ ወይም በህብረተሰብ ደረጃ መሆን የለባቸውም የሚሏቸውን ጠባዮች፣ እሴቶች፣ ልምዶች ይዘርዝሩ?

10.  በሕይወትዎ የይቅርታ ልምድ ተግባራዊ ለማድረግ ይሞክሩለጉድለታችንና ለችግሮቻቸን መፍትሔዎች ምን ሊሆን እንደሚችል ከ5 ገጽ ባልበለጠ ይጻፉ?

11.    በሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ዕሴቶች ተኮትኰተው ያደጉ ሕፃናት ለኅብረተሰብ ሁለንተና ደኅንነትና እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል በምንና በምን ይጠቅማል ይላሉ?

12.  በሃይማኖት እና የሥነ-ምግባር መርኆዎች ከተጠበቁ፣ ፈጣሪን የሚፈራ፣ ለሀገር የሚጠቅም፣ በማኅበሰቡ ውስጥም ታማኝና  አርአያ የሚሆን ትውልድ መፍጠር ይቻላል ካሉ እንዴት? ያብራሩ?

      ከላይ የተጠቀሱት ሁሉም ስለ መልካም ሥነ -ምግባር እና የግብረ ገብ ትምህርት 

     ጠቃሚነት ከ5 ገጽ ያልበለጠ አስተያየትዎትን ያዳብሩ

 

1.     ሰው ጥሩም ይሁን መጥፎ በነፃነቱ የመረጠው ምርጫ ነው?

2.    የሰው ልጅ የፈለገውን የማድረግ ነፃነት አለው ሲባል ገደብ የለሽ  ማለት  ነው?

3.    የሰው ልጅ ነፃነት በአቅሙ በማንነቱና በልዩ ልዩ ሰብዓዊ ሕግጋት የተወሰ ነው ብለው ያምናሉ እንዴት?

4.    ነፃነት የሚከበረውም የሌሎችን መብትና ነፃነት እስካከበሩ ድረስ ብቻ ነው  ካሉ ምክንያቱን ይግለፁ?

5.    ነፃነት ከተፈጥሮ ሕግ፣ ከማኅበረሰብ ሕግና ከእውቀት ጋር የጠበቀ ግንኙነት አለው ይላሉ ?

6.   ያለሕግና ገደብ የሚሰጥ ነፃነት ያልተገራ ፈረስን ያለልጓም እንደመጋለብ ይቆጠራል የሚለው ብሂላዊ አነጋገር እንዴት ይገለጻል?

7.    በፊታችሁ ሕይወትንና ሞትን በረከትንና መናገርም እንዳስቀመጥሁ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ አስመሰክራለሁ  በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍ ይገኛል?

8.    ከተፈጠሩት ፍጥረታት በሙሉ ሰው እጅግ በጣም የከበረ ነው ማረጋገጫው ምንድ ነው?

9.   የሰው ዘር በሙሉ ከአንድ ምንጭ የተቀዳ መሆኑን ቅዱሳን መጻሕፍት ያረጋግጣሉ በየትኛው የመጽሐፍ ክፍሎች ነው የተጠቀሱት?

10.  ሰው ሁሉ በተፈጥሮ እኩል ነው በቀለም፣ በቋንቋ፣ በፆታ፣ በዕውቀት፣ በእድሜ፣ ወዘተ ቢለያይም የሰው ዘር አንድ ነው ብለው ይምናሉ?

የሰው ልጅ ነፃነት ከሚለው ጽንስ ሐሳብ ያለዎትን ማንነት እንዴ ይመለከቱታል? ስለ ሕይወትዎ ምን ግንዛቤ ከመጽሐፉ ምን  አግኝተዋል? ከሌሎች ጋር ያወያዩበት

ከዚህች ትከክለኛውን  የአለመግባባት የግጭት አፈታት ጥያቄዎችን ይመልከቱ የመጣበትን ምንጭ ማጥናት ያስፈልጋል አንዳንዱ የሥራ አመራር ሊቃውንት ችግሩን ማወቅ ማለት የችግሩን መፍትሔ ለማግኘት ግማሽ መንገድ መሄድ ነው የሚሉት ለዚህ ነው በአብዛኛው አለመግባባትን የማቃለል ሥራ ላይ ሲውሉ የሚታዩት የሚከተሉት በአግባቡ ተረድተው ለመሥራት ይሞክሩ

1.     አመቻችነት ይህ ተግባር የተሰጠው ሦስት ወገን ያልተግባቡ ወገኖቸ እንዲገናኙ  

            አመቺ ሁኔታ ለምሳሌ ጊዜ ቦታ ሌሎች አስፈላጊ ነገሮች ከመፍጠር    

           ውጪ ሌላ ድርሻ አላቸው ይላ እንዴት? ያብሩት?

2.     ማስገደድ ማስገደድ ልዩነት ወይም አለመግባባት በተፈጠረ ጊዜ ያንዱን ወገን   

          ፍላጎት ወይም ውሳኔ በሌላው ላይ በግድ መጫን ይቻላልን?

3.    . የአብላጫ ውሳኔ መፈጸም የዚህ ዓይነት ዘዴ አለመግባባቱን አብዛኞች ድምፅ  

                                በሰጡበት መንገድ መፍታት ችግሩን ይፉቷዋል ብለው

                              ያምናሉ አው ካሉ እንዴት ?

4.    ዕርቅ ይህ ዘዴ ሁሉቱን ወገኖች ሊያግባባ የሚችለውን መፍትሔ ብቻ  

   በመውሰድ  ከሁለቱም ወገን የሚቀረው ቀርቶ ስጥቶ መቀበል በሚል   

    መርሕ ማለት ምን ማልት ነው?

5.    መቀላቀል ይህ ዘዴ የተቃራኒውን ወገን አመለካከት ወይም ዓላማን በመቀበል  

        መተባበር ማት ነው ከተቃራኒው ጋር መተባበር ያለ ምንም መርህ             

          ይቻላል ወይ እንዴት?  

6.   ማለሳለስ ሁሉት ተቃራኒ ወገኖች የልዩነት ነጥቦቻቸውን ሆን ብልው ችላ በማት

       የሚያግባባቸውን ንጥቦ ብቻ እየለዩ አብሮ ለመቀጠል መወሰን ሲባል   

         ምንያታዊነቱ ምድን ነው ይሉ?

7.    መራቅ ይህ ከነገር ጦር እደሩ በተሰኘው አባባል  የሚገለጽ ይመስላል፣ ይህ     

     ዘዴ አለመግባባት ሊፈጥር ከሚችል ሁኔታ ሆን ብሎ መሸሸ ማለት ነውን?

8.    አለመግባባትን ለማቃለል ሶስተኛ ወገን ምን ድርሻ እንደሚኖረው ያውቃሉ?

9.   አለመገባባትን ለማቃለል የሚያስችል ብቃት ምን እንደሆነ ግንዛቤ ወስደዋል ከተረዱት ምን ድን ነው ?

10.   አለመግባባትን ለማቃለል የሶስተኛ ወገን ሚና ምንድን ነው ይላሉ?

11.    አለመግባባትነ ማቃለል ከሁለቱ የማይግባቡ ወገኖች አልፎ የሦስተኛ ወገንን አስፈላጊነት ምንድን ነው

12.  ሁለት ሊግባቡ ያልቻሉ ወገኖች በራሳቸው ጥረት ችግራቸውን ማቃለል ካልቻሉ ወደባሰ ሁኔታ እንዳይሸጋገር በራሳቸው ጋባዥነት ወይም በሌላ ጠያቂነት ሦስተኛ ወገን ሊገባበት ይችላል? እንዴት?

13.  ደራዳሪነት የአደራዳሪነት ተግባር በአብዛኛው ሁለት ወገኖች ተገናኘተው

         እንዲወያዩ መርዳት ብቻ  ነው ወይስ?

14.  ገላጋይነት ገላጋይነት ወይም በእንግሊዝኛው አርቢትሬሽን የምነለው ሦስተኛ  

       ወገን የሁለቱንም ወገኖች የአለመግባባት መነሻ ምክንያቶች መከራከሪያ      

        ነጥቦች ወዘተ ካደመጠ በኃላ ምን ያደርጋልን?

15.  አለመግባባት በማቀለል ተግባር የሦስተኛ ወገን መግባት በሁሉቱ ወገኖች ውሳኔ     

              ወይም ከሁለቱ አንዱ በሚያቀርበው ሃሳብ ያለበለዚያም በሦስተኛ ወገን     

               ሊመጣ የሚችል ነው ለአንድ ያለመግባባት ሁኔታ የትኛው የሦስተኛ   

               ወገን  ዓይነት ነው የሚጠቅመው?

16.  እነዚህና ሌሎችም የሚጠቅሙ ጥያቄዎች በማዳበር አለመግባባትን በጠቃሚ ሁኔታ ማቃለል ይቻላል ለሀገር እድገትም ጠቃሚነቱ ከፍተኛ ነው ስለዚህ ከ5 ገጽ ባልበለጠ ለመመለስ ይሞክሩ

 

 

አባ ሳሙኤል

በኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ

                                                         አዲስ አበባ

በሰሙነ ሕማማት የጸሎት ምንባባት

ዘሰኑይ- የሰኞ ምስባክ

የምስባክ ትርጉም

ሰኞ በ1 ሰዓት ዘመዓልት

1ኛ. ምን. ዘፍ 1፥ 1-31፡፡
2ኛ. ምን. ኢሳ 5፥1-9፡፡
3ኛ. ምን. ሲራ. 1፡፡
ወንጌል ማር. 11፥ 13-26፡፡
ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ እስራኤል
ዘገብረ መንክረ ባሕቲቱ
ወይትባረክ ስመ ስብሐቲሁ
ምስባክ መዝ. 71 ፥ 18-19
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን
ብቻውን ድንቅ ሥራ ያደረገ
የጌትነቱም ስም ይክበር ይመስገን
ሰኞ በ3 ሰዓት ዘመዓልት

1ኛ. ምን. ኢሳ 5 ፥ 21-30፡፡
2ኛ. ምን. ኢዩ 2 ፥ 21-32፡፡
3 ፥ 1-21፡፡
3ኛ. ምን. ኤር 9፥ 12-19፡፡
ወንጌል ማቴ. 21 ፥ 18-22፡፡
ተፈሣሕኩ እስመ ይቤሉኒ ቤተ እግዚአብሔር ነሐውር
ወቆማ እገሪነ ውስተ አዕጻድኪ ኢየሩሳሌም
ኢየሩሳሌም ሕንጽት ከመ ሀገር

ምስባክ መዝ. 121፥1-3
ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂዳለን ባሉኝ ጊዜ ብለውኛልና ደስ አለኝ፡፡ ኢየሩሳሌም ሆይ እግሮችሽ በዓጸዶችሽ ቁመዋልና ደስ አለኝ፡፡ ኢየሩሳሌም እንደ ሀገርነቷ የታነጸች ናት
ሰኞ በ6 ሰዓት ዘመዓልት

1ኛ. ምን. ዘፀአ. 32፥ 7-15፡፡
1ኛ. ምን. ጥበብ 1 ፡፡
ወንጌል ዮሐ. 2፥ 13-17

እስመ ህየ ዐርጉ አሕዛብ
ሕዝበ እግዚአብሔር ስምዐ እስራኤል
ከመ ይግነዩ ለስምከ እግዚኦ
ምስባክ መዝ. 121 ፥ 3-4
የብዙ ብዙ የሆኑ እስራኤል ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተዋል፡፡ ለእስራኤል ምስክር የሚሆኑ የእግዚአብሔር ወገኖች ናቸው፡፤ አቤቱ ለስምሕ ይገዙ ዘንድ
ሰኞ
በ9 ሰዓት ዘመዓልት
1ኛ. ምን. ዘፍጥ 2፥ 15-23፡፡
3፥ 1-24 ፡፡
2ኛ. ምን. ኢሳ .40፥ 1-8፡፡
3ኛ. ምን. ምሳ. 1 ፥ 1-9፡፡
ወንጌል ማቴ.21፥ 23-27፡፡
ስምዐነ አምላክነ ወመድኃኒነ
ተስፋሆሙ ለኩሎሙ አጽናፈ ምድር
ብፁዕ ዘኀረይኮ ወዘተወከፍኮ
ምስባክ መዝ. 64፥5-6
ድኅነት የምታደርግልን ፈጣሪያችን ልመናችንን ስማን
በምድር ዳርቻ ላሉት ሁሉ አለኝታቸው
የምትሆን አንተ ነህ፡፡ የመረጥረከውና የተቀበልከው የተመሰገነ ነው፡፡
ሰኞ በ11 ሰዓት ዘመዓልት
1ኛ. ምን . ኢሳ. 50::
2ኛ. ምንኢሳ 26፥ 2-20::
3ኛ. ምን. ሲራ. 2::
4ኛ. ምን. ሆሴ 14፥ 2-10::

ወንጌል ዮሐ. 8፥ 51-59::
ምንባብ
ወትጼዕረኒ ልብየ ኩሎ አሚረ
እስከ ማእዜኒ ይትዔበዩ ጸላእትየ
ላዕሌየ ነጽረኒ ወስምዓኒ እግዚኦ አምላኪየ

ምስባክ መዝ. 12፥2

ልቡናየ ሁል ጊዜ ታስጨንቀኛለች
ጠላቶቸ እስከ መቸ ይታበዩብናል
አቤቱ ፈጣሪየ ስማኘረ ተመልከተኝም
ዘሰሉስ – የማክሰኞ

ማክሰኞ በ1 ሰዓት ዘመዓልት፡፡

1ኛ. ምን. ዘፀአ 19፥ 1-8፡፡
2ኛ. ምን. ኢዮ. 23፥ 24፡፡
3ኛ. ምን. ኢሳ 1፥ 21-31፡፡
4ኛ. ምን.ሆሴ. 4፥ 1-8፡፡
ወንጌልማቴ 26፥ 1-6፡፡
ለይትኀፈሩ ወይኅሰሩ እለ የኀሥሥዋ ለነፍስየ፤ ለይግብኡ ድኅሬሆሙ ወይትኀፈሩ እለ መከሩ እኩየ ላዕሌየ፤
ለይኩኑ ከመ ጸበል ዘቅድመ ገጸ ነፋስ፤
ምስባክ.መዝ. 34፥4
ሰውነቴን ለማጥፋት የሚሽዋት ሁሉ ይፈሩ፤ ይጎስቁሉም፤
በእኔ ክፉ ለአመጡብኝ የመከሩብኝ ሁሉ ወደኋላቸው ይመለሱ፤
ይፈሩ በነፋስ ፊት እንዳለ ትቢያ ይሁኑ፡፡

ማክሰኞ በ3 ሰዓት ዘመዓልት፡፡

1ኛ. ምን. ዘዳግ. 8፥ 11-19፡፡
1ኛ. ምን ሲራ. 3፡፡
ወንጌል ማቴ 23፥ 37-38፡፡
ፍታሕ ፍትሕየ ወባልሐኒ
ወበእንተ ቃልከ አሕይወኒ
ርኁቅ ሕይወትየ እምኃጥኣን
ምስባክ መዝ. 118፥ 154
ፈርደህ ከመከራ አድነኝ
ሕግህንም ስለጠበቅሁ አድነኝ
ሕይወት እግዚአብሔር ከኃጥኣን የራቀ ነው፡፡
ማክሰኞ በ6 ሰዓት ዘመዓልት፡፡

ኛ. ምን.ሕዝ. 21፥ 3-17፡፡
2ኛ. ምን. ሲራ .4፡፡
ወንጌል ዮሐ. 8፥ 12-20፡፡ አድኅነኒ እግዚኦ እምፀርየ፡፡
ወእምጸላትየ እስመ ይኄይሉኒ
ዘይባልሐኒ እምጸላጽየ ምንስዋን ወዘያዕሌኒ እምለቆሙ ላዕሌየ፡፡
ምስባክ መዝ.58፥-1
አቤቱ ከጠላቶቸ አድነኝ፡፡ ከሚበረቱብኝም ጠላቶቸ አድነኝ፡፡ ጥፋተኞች ከሆኑ ጠላቶቸም የሚያድነኝ እሱ ነው፡፡ በጠላትነት ከተነሱብኝ ጠላቶቸ በላይ ከፍከፍ የሚያደርገኝ እሱ ነው፡፡

ማክሰኞ በ9 ሰዓት ዘመዓልት፡፡

1ኛ. ምን. ዘፍጥ. 6፥ 5-22::
2ኛ. ምን. ዘፍጥ. 6፥ 21-24::
3ኛ. ምን. ዘፍጥ. 8፥ 9-22::
4ኛ. ምን. ዘፍጥ. 9፥ 1-7::
5ኛ. ምን. ምሳ. 9፥ 1-12::
6ኛ. ምን. ኢሳ. 20፥ 9-31፡፡
7ኛ. ምን.ዳን. 6፥ 2-28፡፡
ወንጌል.ማቴ 24፥3-35፡፡

ኀቤከ እግዚኦ አንቃዕዶኩ ነፍስየ አምላኪየ
ወኪያከ ተወከልኩ ወኢይትኀፈር ለዓለም፤
ወኢይሥሐቁኒ ጸላእትየ

ምስባክ. መዝ. 24፥1

አቤቱ ፈጣሪየ በአንቃዕድዎ ልቡና ወዳንተ መልሸ ለመንሁ፡፡ በመከራ ለዘላለሙ እንዳላርፍ ባንተ አመንሁ፡፡
ጠላቶቸም አይዘብቱብኝም፡፡

ማክሰኞ በ11 ሰዓት ዘመዓልት፡፡
1ኛ. ምን ኢሳ. 29፥ 5-21፡፡
2ኛ. ምን. ኢሳ. 28፥ 16-26፡፡
3ኛ. ምን. ምሳ 6፥ 20-35፡፡

ወንጌል ማቴ. 25፥14-46፡፡
46-54፡፡

በትረ ጽድቅ ወበትረ መንግሥትከ
አፍቀርከ ጽድቀ ወዐመፃ ጸላእከ
ብፁዕ ዘይሌቡ ላዕለ ነዳይ ወምስኪን

ምስባክ መዝ. 44፥ 6

የመንግሥትህ በትር የጽድቅ በጽር ነው፡፡
ጽድቅን ወደድህ፤ አመጽንም ጠላህ ፡፡
ለድኃና ለጦም አዳሪ የሚያስብ ንዑር ክቡር ነው፡፡

ዘረቡዕ – የሮብ ረቡዕ በ1 ሰዓት ዘመዓልት፡፡

1ኛ. ምን. ዘፀአ. 17፥ 1-7፡፡
2ኛ. ምን. ኢሳ. 2፥ 1-11::
3ኛ. ምን. ምሳ. 3፥ 1-15፡፡
4ኛ. ምን. ሆሴ. 5፥ 13-15፡፡
ወንጌል ዮሐ. 11፥ እስመ ተማከሩ ኅቡረ ወዐረዩ
ላዕሌከ ተሰካተዩ ወተካየዱ
ተዓይኒሆሙ ለኤዶምያስ ወለይስማኤላውያን፡፡

ምስባክ መዝ. 82፥ 5 አንድ ሁነው በአንድነት ተካክለው ተማክረዋልና
በአንተ ላይ ፈጽመው ተማማሉ
የኤዶምያስና የእስማኤላውያን ወገኖች

ረቡዕ በ3 ሰዓት ዘመዓልት፡፡

1ኛ. ምን. ዘፀአ. 13፥ 17-7፡፡
2ኛ. ምን. ሲራ. 22፡፡
ወንጌል ሉቃ. 22፥ 1-6፡፡

ይባዕ ወይርአይ ዘከንቶ ይነብብ
ልቡ አስተጋብአ ኃጢአተ ላዕሌሁ
ይወጽእ አፍኣ ወይትነገር ወየኀብር ላዕሌየ፡፡
ምስባክ መዝ. 40፥ 6
ከንቱ ነገርን የሚናገር ገብቶ ይይ፡፡ ልቡናው ዕዳ የሚሆንበትን ኃጢአት ሰበሰበ፡፡ ወደ ውጭ ወጥቶ ኃጢአትን ይናገራል በእኔ ላይም ያስተባብራል፡፡
ረቡዕ በ6 ሰዓት ዘመዓልት፡፡

1ኛ. ምን. ዘፀአ. 14፥13-31::
2ኛ. ምን. ሲራ. 23፡፡
ወንጌል ሉቃ. 7፥ 36-50::

ጸላእትየሰ እኩየ ይቤሉ ላዕሌየ
ማእዜ ይመውት ወይሠዐር ስሙ
ይባእ ወይርአይ ዘከንቶ ይነብብ
ምስባክ መዝ.40፥5
ጠላቶቸ ግን በእኔ ላይ ክፋትን ይናገራሉ፡፡
መቼ ይሞታል ስሙስ መቼ ይሻራል
ከንቱ የሚናገር ገብቶ ይመልከት

ረቡዕ በ9 ሰዓት ዘመዓልት፡፡

1ኛ. ምን. ዘፍጥ. 24 ፥ 1-9፡፡
2ኛ. ምን. ዘኁ. 20፥ 1-13፡፡
3ኛ. ምን. ምሳ. 1፥ 10-33፡፡
ወንጌል ማቴ. 26፥ 1-16፡፡

እስመ ናሁ ወውዑ ፀርከ
ወአንሥኡ ርእሶሙ ጸላእትከ
እስመ ተማከሩ ኅቡረ ወዐረዩ

ምስባክ መዝ. 82፥2
እነሆ ጠላቶችህ ደንፍተዋልና
ጠላቶችህ ራሳቸውን ነቅንቀዋልና
በአንድነት ተካክለው ተማክረዋልና፡፡
ረቡዕ በ 11 ሰዓት ዘመዓልት፡፡

1ኛ. ምን. ኢሳ. 58፥ 1-14፡፡
2ኛ. ምን. ኢሳ. 59፥ 1-8፡፡
ወንጌል ዮሐ. 12፥ 27-36፡፡

ወፈውሰኒ እስመ ተሀውካ አዕፅምትየ
ነፍስየ ተሀውከት ፈድፋደ
ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡፡
ምስባክ መዝ. 6፥2

አጥንቶቼ ታውከዋልና ፈውሰኝ
ነፍሴም እጅግ ታወከች
ፊትህ ከእኔ አትመልስ፡፡

 

ሐሙስ በ1 ሰዓት ዘመዓልት፡፡

1ኛ. ምን. ዘፀአ 17፥ 8-16፡፡
2ኛ. ምን. ግብ ሐ. ዘፀአ. 1፥ 15-20፡፡
ወንጌል ሉቃ. 22፥ 1-14፡፡
ዘሐሙስ- ዘሐሙስ

ወጽሕደ እምቅብ ነገሩ፤
እሙንቱሰ ማዕበል ያሰጥሙ፤
ዓዲ
ሶበሰ ጸዐለኒ እምተዓገሥኩ ፤
ወሶበ ጸላኢ አዕበየ አፉሁ፡፡
ምስባክ መዝ. 54፥ 21/12

ነገሩ ከቅቤ የለዘበ ሆነ ፡፡ እነሱ ማዕበል ናቸው ያሰጥማሉ፡፡
ወይም
ጠላት ሰድቦኝ ቢሆን በታገሥሁት ነበር ፡፡ ጠላትም በእኔ ላይ አፉን ከፍ ቢያደርግ በተሸሸግሁ ነበር፡፡

ሐሙስ በ3 ሰዓት ዘመዓልት፡፡

1ኛ. ምን. ዘፀአ. 32 ፥30-35፡፡
2ኛ. ምን. ዘፀአ. 33፥ 1-3፡፡
3ኛ. ምን.ሚክ 2 ፥3-13፡፡
ወንጌል ማቴ. 26 ፥ 17-19፡፡
ወይንዕዋ ለነፍሰ ጻድቅ
ወይንን ደመ ንጹሐ
ወኮነኒ እግዚአብሔር ጸወንየ፡፡

ምስባክ መዝ. 93 ፥ 21
የጻድቁን ሰውነት ለጥፋት ይሽዋታል፡፡
ንጹሕን ደም የሚያፈስ
አግዚአብሔር ግን አምባ መጠጊያ ሆነኝ

ሐሙስ  በ6 ሰዓት ዘመዓልት፡፡
1ኛ. ምን. ኤር. 7፥ 3-13::
2ኛ. ምን. ሕዝ. 20፥ 39-44::
3ኛ. ምን. ሚክ. 2፥ 7-13::
4ኛ. ምን. ሚክ 3፥ 1-8፡፡
5ኛ. ምን ሶፎ 1፥ 7-18 ፡፡
6ኛ. ምን. ሲራ. 12፡፡
ወንጌል.ማር. 14፥ 12-16::
እስመ ሰማዕኩ ድምፀ ብዙኃን እለ ዐገቱኒ ዐውድየ
ሶበ ተጋብኡኅቡረ ላዕሌየ
ወተማከሩ ይምስጥዋ ላዕሌየ፡፡

ምስባክ መዝ . 30፥ 13

በዙሪያየ የከበቡኝን የብዙዎችን ድምጽ ሰምቻለሁና
በእኔ ላይ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ
ሰውነቴን ሊጥቋት ተማከሩ፡፡
ሐሙስ በ9 ሰዓት ዘመዓልት፡፡

1ኛ. ምን. ዘፍጥ. 22፥ 1-19፡፡
2ኛ. ምን. ኢሳ. 61፥ 1-7፡፡
3ኛ. ምን. ኢዮ. 27፥ 1-23፡፡
4ኛ. ምን. ኢዮ. 28፥ 1-13፡፡
5ኛ. ምን ሚል 1፥ 9-14፡፡
6ኛ. ምን. ሚል. 2፥ 1-8፡፡
ወንጌል ሉቃ 22፥ 1-13፡፡
ትነዝሀኒ በአዛብ ወእነጽሕ
ተኀጥፅበኒ እምበረድ ወእጻዐዱ
ልበ ንጹሐ ፍጥር ሊተ እግዚኦ

ምስባክ መዝ. 50፥7

በአውባን /በሂሶጵ ቅጠል ትረጨኛለህ
እኔም ንጹሕ እሆናለሁ
ታጥበኛለህ እኔም እንደ ከበረዶ ይልቅ ንጹሕ እሆናለሁ
አቤቱ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፡፡

 

ሐሙስ ሐሙስ በ9 ሰዓት ውስጥ፡፡
ሀ.የኅፅበተ እግር ምንባብ
1ኛ. ምን. ዘፍጥ 18፥ 1-33::
2ኛ. ምን. ዘፀአ. 14፥ 29-34::
3ኛ. ምን. ኢያ. 3፥ 13-17::
4ኛ. ምን. ኢሳ 4፥ 2-7::
5ኛ. ምን. ኢሳ 55፥ 1-13::
6ኛ. ምን. ሕዝ. 11፥ 17-21::
7ኛ. ምን. ሕዝ 46፥ 2-9፡፡
8ኛ. ምን. ምዝ ፥ 51፡፡
9ኛ. ምን. መዝ ፥ 54፡፡
10ኛ. ምን. መዝ. ፥ 69፡፡
11ኛ. ምን. ጢሞ ቀዳ. 4፥ 9-16፡፡
12ኛ. ምን ጢሞ. ካል 5፥ 1-10፡፡
ወንጌል ዮሐ.13፥ 1-20::
ለ የኀዕበተ እግር መጨረሻ ምዕዛል፡፡
መዝሙር፥ 150

እግዚአብሔር ይሬእየኒ ወአልቦ ዘየጥአኒ
ውስተ ብሔር ሥዑር ህየ የኀድረኒ
ወኀበ ማየ ዕረፍት ሐፀነኒ
ምስባክመዝ . 22፥1

እግዚአብሔር ይጠብቀኛል፤ የሚያሳጣኝም ነገር የለም፡፡
በለመለመ መስክ በዚያ ያኖረኛል
ዕረፍት በአለበት ውኃም አነጻኝ፡፡

ሐሙስ ስለ ቁርባን፡፡

1ኛ. ምን ቆሮ ቀዳ. 11፥ 23-34፡፡
2ኛ. ምን ጴጥ ቀዳ 2፥ 11-25፡፡
3ኛ. ምን ግብ ሐዋ 8፥ 26-40፡፡
ወንጌል ማቴ. 26፥ 20-30፡፡

ምስባክ መዝ. 23፥5-6

ሐሙስ  በ11 ሰዓት ዘመዓልት፡፡

1ኛ. ምን. መዝ. 150፡፡
2ኛ. ምን. ኢሳ 52፥ 13-15፡፡
3ኛ. ምን. ኢሳ. 53፥ 1-12፡፡
4ኛ. ምን. ኢሳ. 54፥ 1-8፡፡
5ኛ. ምን. ኤር 31፥ 15-26፡፡
6ኛ. ምን. ኢሳ .31፥ 1-9፡፡
7ኛ. ምን. ኢሳ 32፥ 1-20፡፡
8ኛ. ምን. ኢሳ.33፥ 1-10፡፡
ወሠራዕከ ማእደ በቅድሜየ
በአንጻሪሆሙ ለእለ ይሣቅዩኒ
ወአጽሐድክዋ በቅብ ለርስየ

ምስባክ መዝ. 22፥ 4
ዘይሴሰይ እክልየ አንሥአ ሰኮናሁ ላዕሌየ
አንተ እግዚኦ ተሣሀሊ ወአንሥአኒ እፍድዮሙ
በእንተዝ አእመርኩ ከመ ሰመርከኒ፡፡
ምስባክ መዝ. 9 በፊቴ ማእድን ሠራህ
በሚያስጨንቁኝም ፊት
ራሴንም በዘይት አለዘብኽ(ቀባህ)

እንጀራየን የሚመገብ ( ግብረ በላየ) ተረከዙን በላዬ አነሣብኝ፡፡
አቤቱ አንተ ይቅር በለኝ
ፍዳቸውን እከፍላቸው ዘንድ አንሣኝ
በዚህ እንደ ወደድከኝ አወቅሁ፡፡

ዓርብ – ዘዓርብ

ዓርብ በ1 ሰዓትዘመዓልት (ዘነግህ)

1ኛ. ምን ዘዳግ. 8፥ 19-20::
2ኛ. ምን. ዘዳግ. 9፥1-24::
3ኛ. ምን. ኢሳ. 1፥1-9::
4ኛ. ምን. ኢሳ 33፥ 5-22::
5ኛ. ምን. ኤር. 20፥1-18::
6ኛ. ምን. ኤር. 12፥ 1-8::
7ኛ. ምን. ጥበብ 1፡፡
8ኛ. ምን.ዘካ. 11፥ 11-14፡፡
9ኛ. ምን. ሚክ. 7፥ 1-8፡፡
10ኛ. ምን. አሞ 2፥ 1-16፡፡
11ኛ. ምን. አሞ. 3፥ 1-7፡፡
12ኛ. ምን. ሆሴ. 10፥ 32-8፡፡
ወንጌል.ማቴ 27፥ 1-14፡፡
ማር .15፥ 1-5፡፡
ሉቃ. 22፥ 65-71፡፡
ዮሐ. 18፥28-40፡፡
ይበል መራሒ፡- ነአምን ነአምን ነአምን ሕማሞ ለዘኢየሐምም ርግዘተ ገቦሁ ነአምን ወቅንዋተ እደዊሁ ነአምን ዬ፡ ዬ፡ ዬ፡ ነአምን ሞቶ ወትንሣኤሁ፡፡ በመቀጠልም በግራና በቀኝ እየተቀባበሉ ይህን ይበሉ፡፡ ከዚያም ለከ ኃይል ይበሉ፡፡

እስመ ቆሙ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ፡፡
ወሐሰት ርእሰ ዐመፃ፡፡
ዓዲ
ተንሥኡ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ
ወዘኢየአምር ነበቡ ላዕሌየ
ፈደዩኒ እኪተ ህየንተ ሠናይት፤ ምስባክ. መዝ. 34፥ 11

1. ምራት፡- ወጸቢሖ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት ይስቅልዎ ለኢየሱስ ዲበ ዕፀ መስቀል፡፡
2. ምራት፡- ወጸቢሖ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት አውጽእዎ አፍአ ለኢየሱስ ውስተ ዓውደ ምኩናን፡፡
3. ምራት፡- ወጸቢሖ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት ሐመይዎ ለኢየሱስ ወመጠውዎ ለጲላጦስ፡፡
4. ምራት፡-ወጸቢሖ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት አውጽእዎ አፍአ ለኢየሱስ ወነበረ ዐውደ ሶቤሃ፡፡
በየምራቱ መጨረሻ ሁሉም ሰው በአንድ ላይ፡-

 ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል ተሣሃለነ እግዚኦ፡፡

 ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተጠምቀ በዮርዳኖስ ወተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል ተሣሃለነ እግዚኦ፡፡

 ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት፡፡

መሪው፡፡- የማይታመመውን ጌታ ሕማሙን እናምናለን እናምናለን እናምናለን ፤ የጎኑን በጦር መወጋት እናምናለን፤ እጆቹ በችንካር መቸንከራቸውን እናምናለን፡፡ ወዬው ወዬው ወዬው ሞቱንና ትንሣኤው እናምናለን በማለት ግራና እየተቀባበሉ ይበሉ፡፡
ከዚያም እንደተለመደው ለከ ኃይል ይበሉ

ምስባክ
የሐሰት ምስክሮች በጠላትነት ተነሥተውብኛልና
ሐሰትም የዓመፃ አበጋዝ ናት/
ወይም
የሐሰት ምስክሮች በጠላትነት ተነሡብኝ፡፡
በእኔ ላይም የማላውቀውን ነገር ተናገሩብኝ፡፡

1. ሊቃነ ካህናት ኢየሱስን በመስቀል ላይ ይሰቅሉት ዘንድ በጧት/በነጋ ጊዜ ተማከሩ፡፡
2. ሊቃነ ካህናት ኢየሱስን ወደ መስቀል አደባባይ ይወስዱት ዘንድ በጧት/በነጋ ጊዜ ተማከሩ፡፡
3. ሊቃነ ካህናት ኢየሱስን አስረው ለጲላጦስ አሳልፈው ይሠጡት ዘንድ በጧት/በነጋ ጊዜ ተማከሩ፡፡
4. ሊቃነ ካህናት ኢየሱስን ያን ጊዜ ወደ ውጭ አውጥተው በፍር አደባባይ ያቆሙት ዘንድ በጧት/በነጋ ጊዜ ተማከሩ፡፡
በየምራቱ መጨረሻ ሁሉም ሰው በአንድ ላይ፡-

 ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት የማይለወጥ ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደ አቤቱ ይቅር በለን፡፡
 ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት የማይለወጥ በዮርዳኖስ የተጠመቀ፤ በመስቀል የተሰቀለ፤ አቤቱ ይቅር በለን፡፡
 ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት የማይለወጥ፡፡ ብሎ ብቻ ያቆማል፡፡

ዓርብ በ3ኛ ሰዓት ዘመዓልት (ዘሠለስት)

1ኛ. ምን. ዘፍጥ. 41፥ 1-22::
2ኛ. ምን. ኢሳ. 63፥1-19::
3ኛ. ምን. ኢሳ. 64፥ 1-4::
4ኛ. ምን. ኢሳ. 4፥ 8-16::
5ኛ. ምን. ኢሳ. 50፥ 4-11::
6ኛ. ምን. ኢሳ. 3፥ 5-15::
7ኛ. ምን. ሚክ. 7፥ 9-20::
8ኛ. ምን. ኢዮ. 29፥ 21-25::
9ኛ. ምን. ኢዮ. 30፥ 1-14፡፡
10ኛ. ምን. መዝ. 35፡፡
ወንጌል ማቴ. 27፥ 15-26፡፡
ማር. 15፥ 6-15፡፡
ሉቃ. 23፥ 13-25፡፡
ዮሐ 19፥ 1-12፡፡

ይበል መራሒ፡- አርዑተ መስቀል ፆረ፤ አርዑተ መስቀል ፆረ፤ ይስቅልዎ ሖረ ፡፡ ዬ፤ ዬ፤ ዬ፤ ከመ ኪያነ ይቤዙ እግዚኦ ኮነ ገብረ፡፡
በጧት የተባለውን ምቅናይ ለከ ኃይልን ከዚህ በል፡፡
ዲያቆን፡- መዝ. 34 በውርድ ንባብ ይበል፡፡
ካህን፡- ግፍዖሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍዑኒ፤ ጽብኦሙ እግዚኦ ለእለ ይጸብኡኒ፤ነግፍዖሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍዑኒን በዜማ ይበል፡፡ ሕዝቡም ይቀበሉት፡፡

ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን፤
ወአኀዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን፤
ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን፡፡
ምስባክ መዝ. 21፥ 16
 ምራት፡- ጊዜ ሠለስቱ ሰዓት አኀዝዎ ለኢየሱስ ወወሰድዎ ይስቅልዎ፡፡
 ምራት፡- ጊዜ ሠለስቱ ሰዓት አሕየወ ሎሙ በርባንሃ ወወሀቦሙ ኢየሱስሃ ይስቅሉ
 ምራት፡- ጊዜ ሠለስቱ ሰዓት ወሰድዎ ለኢየሱስ ውስተ ምኩናን፡፡
 ምራት፡- ጊዜ ሠለስቱ ሰዓት ቀሰፎ ጲላጦስ ለኢየሱስ ወመጠዎሙ ይስቅልዎ፡፡

በየምራቱ መጨረሻ ሁሉም ሰው በአንድ ላይ፡-

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል ተሣሃለነ እግዚኦ፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተጠምቀ በዮርዳኖስ ወተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል ተሣሃለነ እግዚኦ፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ይበል፡፡

ዓርብ በ6 ሰዓትዘመዓልት (ዘቀትር)፡፡
1ኛ. ምን. ዘኊል. 21፥ 1-9::
2ኛ. ምን. ኢሳ. 53፥ 7-12::
3ኛ. ምን. ኢሳ. 13፥ 1-10::
4ኛ. ምን. ኢሳ. 50፥ 10-11::
5ኛ. ምን. ኢሳ. 51፥1-6::
6ኛ. ምን. አሞ. 8፥ 8-14::
7ኛ. ምን. አሞ 9፥ 1-15፡፡
8ኛ. ምን. ሕዝ. 37፥ 15-22::
9ኛ. ምን. ገላ. 6፥ 14-17::

ወንጌል ማቴ. 27፥ 27-45::
ማር. 15፥ 16-33፡፡
ሉቃ. 23፥ 27-44፡፡
ዮሐ. 19፥ 13-27፡፡

ይበል መራሒ፡- ተሰቅለ ፤ተሰቅለ፤ ተሰቅለ ወሐመ ቤዛ ኩሉ ኮነ፡፡ ዬ፤ ዬ፤ ዬ በመስቀሉ በዜወነ እሞት ባልሐነ እያለ ሲመራ በግራና በቀኝ ያሉ ሁሉ እየተቀባበሉ ይህን ይበሉ፡፡
በጧት የተባለውን ምቅናይ ለከ ኃይልን ከዚህ በል፡፡

ዲያቆን፡- በውርድ ንባብ ኦ መኑ ዝንቱን ያንብ፡፡
ካህን፡- ለመስቀልከ ንሰግድ ኦ ሊቅነ ወለትንሣኤከ ቅደስት ንሴብሕ ይእዜኒ ወዘልፈኒ የሚለውን ያዚም ሕዝቡም እየተቀባበሉ ይበሉ፡፡

ቀነውኒ እደውየ ወእገርየ፤
ወኁለ ኩሉ አዕፅምትየ፤
ቀነውኒ እደውየ ወእገርየ፤ ምስባክ መዝ. 21፥ 16
 ምራት፡- ጊዜ ስድስቱ ሰዓት አልበስዎ አልባሲሁ ለኢየሱስ ወወሰድዎ ይስቅልዎ፡፡
 ምራት፡- ጊዜ ስድስቱ ሰዓት ዐበጥዎ ለስምዖን ከመ ይፁር መስቀሎ፡፡
 ምራት፡- ጊዜ ስድስቱ ሰዓት ሰቀልዎ ለኢየሱስ በቀራንዮ መካን፡፡
 ምራት፡- ጊዜ ስድስቱ ሰዓት ቀትር ሶቤሃ ሊቃነ ካህናት ሰቀልዎ ለኢየሱስ መዕከለ ክልኤ ፈያት፡፡
በየምራቱ መጨረሻ ሁሉም ሰው በአንድ ላይ፡-

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል ተሣሃለነ እግዚኦ፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተጠምቀ በዮርዳኖስ ወተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል ተሣሃለነ እግዚኦ፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ይበል፡፡ መሪው፡- ተሰቀለ፤ ተሰቀለ፤ ተሰቀለ፤ ታመመም የሁሉ ቤዛ መድኃኒት ሆነ፤ ወዬው ወዬው ወዬው በመስቀሉ አዳነን ከሞትም አዳነን እያለ ሲመራ በግራና በቀኝ ያሉ ሁሉ እየተቀባበሉ ይህን ይበሉ፡፡
በጧት የተባለውን ምቅናይ ለከ ኃይልን ከዚህ በል፡፡

ዲያቆን፡- በውርድ ንባብ ኦ መኑ ዝንቱን ያንብ፡፡

ካህን ፡- ሊቅ ፈጣሪያችን ሆይ ለመስቀልህ እንሰግዳለን፡፡
ቅድስት የሆነች ትንሣኤህንም ዛሬም ዘወትርም እናመሰግናለን፡፡

እግሬን እጄን ቸነከሩኝ
አጥንቶቸንም ሁሉ ቆጠሩ
እግሬን እጄን ቸነከሩኝ
 ስድስት ሰዓት በሆነ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስን ልብሱን አልብሰው ይሰቅሉት ዘንደ ወሰዱት፡፡
 ስድስት ሰዓት በሆነ ጊዜ መስቀሉን ይሸከም ዘንድ ስምዖንን አስገደዱት፡፡
 ስድስት ሰዓት በሆነ ጊዜ ያን ጊዜ ቀትር ነበር፡፡ የካህናት አለቆች ኢየሱስን በቀራንዮ ሰቀሉት፡፡
 ስድስት ሰዓት በሆነ ጊዜ የካህናት አለቆች ጌታ ኢየሱስን በሁለት ወንበዴዎች መካከል ሰቀሉት፡፡
በየምራቱ መጨረሻ ሁሉም ሰው በአንድ ላይ፡-

 ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት የማይለወጥ ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደ አቤቱ ይቅር በለን፡፡

 ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት የማይለወጥ በዮርዳኖስ የተጠመቀ፤ በመስቀል የተሰቀለ፤ አቤቱ ይቅር በለን፡፡

 ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት የማይለወጥ፡፡ ብሎ ብቻ ያቆማል፡፡

በ9 ሰዓትዘመዓልት (የተሲያት)

1ኛ. ምን. ኢያ. 5፥ 10-12፡፡
2ኛ. ምን. ሩት. 2፥ 11- 14::
3ኛ. ምን. ኤር. 18፥ 18-23::
4ኛ. ምን. ኤር. 12፥ 1-13::
5ኛ. ምን. ኢሳ. 24፥1-23::
6ኛ. ምን. ኢሳ. 25፥ 1-12::
7ኛ. ምን. ኢሳ. 26፥ 1-8፡፡
8ኛ. ምን. ዘካ. 14፥ 5-11::
9ኛ. ምን. ኢዮ. 16፥ 1-22::
10ኛ. ፊልጵ. 2፥ 1-18::

ወንጌል ማቴ. 27፥ 46-50::
ማር. 15፥ 34-27፡፡
ሉቃ. 23፥ 45-46፡፡
ዮሐ. 19፥ 28-50፡፡ በዜማ ማኅዘኒ፡-
 አምንስቲቲ ብሂል በዕብራይስጥ ተዘከረነ በዓረብኛ በሥውር የነበርህ ማለት ነው፡፡
 ሙኪርያ ብሂል በዕብራይስጥ እግዚኦ በዓረብኛ ብሂል ነዳዊ ማለት ነው፡፡
 ሙዓግያ ብሂል በዕብራይስጥ ቅዱስ በዓረብኛ ብሂል እሳታዊ ማለት ነው፡፡
 ሙዳሱጣ ብሂል በዕብራይስጥ ሊቅ በዓረብኛ ብሂል ነበልባላዊ ማለት ነው፡፡
 አንቲ ፋሲልያሱ ብሂል በዕብራይስጥ በውስተ መንግሥትከ በዓረብኛ ብሂል ወዮ ጌታዬ እኔ ልሙትልህ ማለት ነው፡፡
ዲያቆን፡- በውርድ ንባብ ተዘከረነን ሲያነብ ካህናቱም ተዘከረነን ሲያዜሙ ሕዝቡ እተቀበለ አብሮ ያዜማል፡፡
ዲያቆኑ፡- በውርድ ንባብ ለትቅረብ ስእለትየን ሲያነብ ካህናቱም ኦ ዘጥዕመ ሞተን ሲያዜሙ ሕዝቡ ይቀበላል፡፡
ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ፤
ወአስተዩኒ ብሂአ ለጽምእየ፤
ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ፤
ምስባክ መዝ. 68፥21
 ምራት፡-ጊዜ ተሰዓቱ ሰዓት ጸርሐ ኢየሱስ በቃሉ ወይቤ ኤሎሄ ኤሎሄ
 ምራት፡-ጊዜ ተሰዓቱ ሰዓት ገዐረ ኢየሱስ በቃሉ ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ
 ምራት፡-ጊዜ ተሰዓቱ ሰዓት ከልሐ ኢየሱስ በቃሉ ወአማኅፀነ ነፍሶ ሶቤሃ
 ምራት፡-ጊዜ ተሰዓቱ ሰዓት አጽነነ ርእሶ ኢየሱስ ወይቤ ተፈጸመ ኩሉ፡፡
በየምራቱ መጨረሻ ሁሉም ሰው በአንድ ላይ፡-

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት … ብሂለከ ፈጽም፡፡

አሳዛኝ በሆነ ዜማ፡-
 አምንስቲቲ ማለት በዕብራይስጥ ተዘከረነ በዓረብኛ በሥውር የነበርህ ማለት ነው፡፡
 ሙኪርያ ማለት በዕብራይስጥ እግዚኦ በዓረብኛ ነዳዊ ማለት ነው፡፡
 ሙዓግያ ማለት በዕብራይስጥ ቅዱስ በዓረብኛ እሳታዊ ማለት ነው፡፡
 ሙዳሱጣ ማለት በዕብራይስጥ ሊቅ በዓረብኛ ነበልባላዊ ማለት ነው፡፡
 አንቲ ፋሲልያሱ ማለት በዕብራይስጥ በውስተ መንግሥትከ በዓረብኛ ወዮ ጌታዬ እኔ ልሙትልህ ማለት ነው፡፡
ዲያቆን፡- በውርድ ንባብ አቤቱ ይቅር በለንን ሲያነብ ካህናቱም አቤቱ ይቅር በለንን ሲያዜሙ ሕዝቡ እተቀበለ አብሮ ያዜማል፡፡
ዲያቆኑ፡- በውርድ ንባብ ልመናየን ተቀበልን ሲያነብ ካህናቱም ሞት የማይገባው አምላክ ምትን ቀመሰ እያሉ ሲያዜሙ ሕዝቡም ይቀበላል፡፡
በምግቤ ውስጥ ሐሞትን ጨመሩ፤
ጥማቴንም ለማርካት መፃፃውን አጠጠኝ፤
በምግቤ ውስጥ ሐሞትን ጨመሩ፡፡ ምስባክ መዝ. 68፥21
 በዘጠኝ ሰዓት ጌታ ኢየሱስ ቃሉን አሰምቶ ኤሎሄ ኤሎሄ አለ
 በዘጠኝ ሰዓት ጌታ ኢየሱስ ቃሉን አሰምቶ ጮኸ፤ ያን ጊዜ ነፍሱ ከሥጋው ተለየች፡፡
 በዘጠኝ ሰዓት ጌታ ኢየሱስ ቃሉን አሰምቶ ተናገረ፤ያን ጊዜ ነፍሱን አደራ ሰጠ፡፡
 በዘጠኝ ሰዓት ጌታ ኢየሱስ ራሱን ዘንብል (ዘለስ) አድርጎ ሁሉ ተፈጸመ አለ፡፡
በየምራቱ መጨረሻ ሁሉም ሰው በአንድ ላይ፡-

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት የማይለወጥ … ብሎ እንደላይኛው መድገም ነው፡፡

በተሰዓቱ ሰዓት
በዘጠኝ ሰዓት አምስት ልዑካን ልብሰ ተክህኖ ለብሰው በጥቁር መጎናጸፊያ ተሸፍነው በአንድነት የሐዘን ዜማ
አምንስቲቲ ሙኪርያ(ተዘከረኒ እግዚኦ) አንቲ ፋሲልያሱ (በመንግሥትከ)፣
አምንስቲቲ ሙዓግያ (ተዘከረኒ እሳታዊ) አንቲ ፋሲልያሱ (በመንግሥትከ) ፣
አምንስቲቲ ሙዳሱጣ (ተዘከረኒ ነበልባላዊ) አንቲ ፋሲልያሱ (በመንግሥትከ)፣
ይበሉ በዚህ ጊዜ በቤተ ክርስቲያንና ቅጥር ውስጥ ያሉ ሁሉ ይቀመጣሉ፡፡ ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ ካህናቱን ተከትለው ይበሉ፡፡
አምንስቲቲ ማለት ተዘከረኒ
ሙኪርያ ማለት ነበልባላዊ
ሙዓግያ ማለት እሳታዊ
ሙዳሱጣ ማለት ነበልባላዊ
አንቲ ፋሲልያሱ ማለት በመንግሥትከ ማለት ነው፡፡

ዘዐሠርቱ ወአሐዱ ሰዓት
በመጽሐፉ ትእዛዝ መሠረት ለሰዓቱ የታዘዘው ንባብ ይነበባል፡፡ ሥዕለ ስቅለቱ ይወርዳል፡፡ በቤተ መቅደስ ውስጥ ካህናቱ ከምዕራብ ወደ ምስራቅ ከምስራቅ ወደ ምዕራብ ከሰሜን ወደ ደቡደብ ከደቡብ ወደ ሰሜን መንበሩን እየዞሩ እግዚኦታ ያደርሳሉ፡፡ ሕዝቡም እንደ ካህናቱ እየዞረ እግዚኦታውን የቀበላል፡፡ እግዚኦታው ካለቀ በኋላ ሥርየት ይደረጋል፡፡ ሊቃውንት ካህናት ተሰባስበው ለሰዓቱ የተመደበውን መዝሙረ ዳዊት ካስተዛዘሉ በኋላ ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ስቡሐ ዘተሰብሐ የሚለውን በቁም፤ በመረግድ፤ በአመላለስ ካሉት በኋላ ካህናትና ምእመናን በአንድነት አሸብሽበውት የበዓሉ ፍጻሜ ይሆናል፡፡

ዘመነ ጽጌ  ከመስከረም   26  እስከ  ኅዳር  5 ቀን  ያሉት  40  ዕለታት  ሲሆኑ  ትርጓሜው  የአበባ  ጊዜ  ማለት  ነው። “ወይቤሎ  ለአዳም  ወሀብኩከ  ርስተ  ገነት  ትፍስሕት በፅጌ  ሥርጉተ ወበፍሬ ክልልተ  ዘፍ.2፥8 ” እግዚአብሔር  ጠፈርን በአድማስ ደግፎና በደመና ከፍክፎ  መባርቅትንና ዝናማትን በደመና ጭኖ ደመናውን በነፋስ አሽክሞ ዓለምን በፀሐይና በጨረቃ አብርቶ  በፅጌያት  አስጊጦ  ገነትን  በአዝርዕትና  በአትክልት  አዘጋጅቶ  መንግሥተ  ሰማያትን  ሠርቶ  የሰውን  ልጅ  ፈጠረው።

 አምሳላተ ጽጌ (የጽጌ ምሳሌዎች           )

 1. ጽጌ የጌታ ምሳሌ ነው

“ትወፅዕ  በትር  እምሥርወ  እሴይ  ወየዐርግ  ጽጌ  (ኢሳ. 11፥1 ) ትርጓሜ  ይእቲ በትር አምሳለ ማርያም  ቅድስት  ይእቲ  ወፅጌ  ዘወጽአ  እምኔሃ  አምሳሉ  ለወልድ ( ዮሐ. 1፥1- 14 ድጓ ዘጽጌ)ʼʼ

ከእሴይ  ሥር  በትር ትወጣለች።  ከእርሷም  አበባ ይወጣል፤  ይህችውም  በትር  የማርያም አምሳል ናት። ከእርሷ የተገኘው  አበባም የወልድ አምሳል ነው። በመሆኑም ጌታችን  መድኃኒታችን  ኢየሱስ  ክርስቶስ  ቅዱስ  ሥጋውንና  ክቡር ደሙን  እውነተኛ  መብልና እውነተኛ  መጠጥ  አድርጐ በመስጠቱ የፍሬ መገኛ በሆነው አበባ ተመስሏል። ቅዱስ ያሬድ                                                        ቡሩክ  ዕፅ ዘሠናየ  ይፈሪ ወኃጢአተ  ይሰሪ ( ድጔ ዘጽጌ ) የኃጢአት ማስተሥሪያ የሚሆን መልካም  ፍሬን  ያፈራ የበረከት እንጨት ክርስቶስ ነው። ለሕያዋን  ፍጥረታት  የሕይወት ምግብነት  ከሕቱም  ምድር በቅሎ አብቦና  አፍርቶ የተገኘው ክርስቶስ ከፍሬው  የበሉትን  ደቂቀ  አዳም   በሙሉ አድኗል።

 1. ፅጌ የቅድስተ  ቅዱሳን  ቅድስት ድንግል  ምሳሌ

እመቤታችን የእውነተኛው ፍሬ ክርስቶስ መገኛ በመሆኗ በአበባ ትመሰላለች፤ እመቤታችን የኃጢአታችን ክብደት ሳይሆን የግፋችን ብዛት የታየባት  እውነተኛ  ችሎት (ፍትሐ አምላክ) የተገኘባት  ናትና።  ትውልድ  ሁሉ ለዘላዓለም  ያመሰግኗታል።  “እስመ ርእየ  ሕማማ ለአመቱ ወገብረ  ኃይለ  በመዝራዕቱ   (ሉቃ. 1፥481)  መዝገቡ ለቃል  ፅጌ  እንተ ኢትትነገፍ መድኃኒተ ሕዝብ (ድጔ ዘጽጌ) ያገልጋዩን  መዋረድ  አይቷልና  በክንዱ  ታላቅ ሥራን አድረገ።  የቃል ማደሪያ  ( የፍሬ ሙዳይ ) የሆነችው አበባ ለዘለዓለም  አትረግፍም። ስለዚህ በፍሬዋ የሕዝብ መድኃኒት  በመዓዛዋ  የቅዱሳን የሕሊና እረፍት ናት።

‹‹ ዕፀ  ጳጣስ  እንተ  በአማን  ፅጌ  ደንጐላት  ሐረገ ወይን ዘእምነገደ ይሁዳ እንተ ሠረጸት ለሕይወት  (ዘፍ. 49፥1  ድጓ ዘጥቅምት  ማርያም) እመቤታችን ከይሁዳ ነገድ ለዘለዓለም መንግሥት የወጣች  የወይን ሐረግ በደብረ ሲና  በጳጦስ  እንጨት ላይ የታየውን ምሳሌ በእውነት ያሳያች ናት።››

 1. ጽጌ የመስቀል ምሳሌ

በማር  ሥራ  ላይ  የተሰማሩ  ሠራተኛ  ንቦች አንድ ሆነው በአበባ ላይ እንደሚሠፍሩ  ሁሉ ሕዝብና  አሕዛብ  በአንድነት የተሰበሰቡበት አበባ የዕለተ ዐርቡ  የክርስቶስ  መስቀል በመሆኑ መስቀል  አበባ  ይባላል። በከመ ይቤ ሰሎሞን በእንተ ማርያም ንዑ ንትፈጋዕ ወኢይኅልፈነ ፅጌ ደመና  መስቀል ዘዮም  አብርሃ በስነ  ማርያም። (ድጓ  ዘጽጌ ) ሰሎሞን ስለ ማርያም  ሲናገር  እነሆ ክረሞቱ፣  (ውርጩ፣ ውችንፍሩ፣ ጭቃው፣ ቁሩ ) አልፎ በረከት ተተካ እንዳለ። የክርስቶ መስቀል በማርያም  ባሕርይ ዛሬ አብቧልና የበረከት አበባ ሳያልፈን ኑ እንደሰት እንዲል።

በባሕርዩ  መወሰን  የማይስማማውን አምላክ ማርያም  በባሕርይዋ  ስለወሰነችው (ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ስለሆነ)  በተመረጠችው የማዳን ሰዓት / ዕለተ ዐርብ / መስቀል ያለባሕርዩ በማርያም ባሕርይ ተሸከመው።

 1. ጽጌ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ

የክርስቶስ ሥጋ የሚያፈራባት የአበባ እንጨት የሆነችው ቤተ ክርስቲያን አበባ ትባላለች። ቅዱስ ያሬድ በዝማሬው  “ወልድ እኁየ ጸዓዳ ወቀይህ ፀዓዳ ትቤሎ በእንተ ሥጋሁ ለክርስቶስ” ልጅ ወንድሜ መልከ መልካም ደመ ግቡ ቀይ ነው። ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን ስለለበሰው ሥጋ ቀይ ጐልማሳ አለችው ይላል። ቤተ ክርስቲያን  ምድራዊት  ስትሆን ሰማያዊት ናት። ለምድራዉያን ሰዎች የምትሰጠው ልጅነት የምታድለው ሰማያዊ ፀጋና ሀብት ነው።

‹‹ ሐረገ ወይን  እንተ  በሞድር  ሥረዊሃ  ወበሰማይ  አዕጹቂሃ››  ሥሯ በምድር ቅርንጫፚ በሰማይ የሆነች  የወይን  ሐረግ  በፈቃደ  ሥላሴ  ዛላዋ  የምትቆረጥ  ፍሬዋ  የምትለቀም የበረከትም  ፍሬ  የምታፈራልን  የወይን  ሐረግ  ቅዱስት  ቤተ ክርስቲያን ናት።

‹‹ቅዱስ ያሬድ  “ጽጌ ብሂል ቅድስት ቤተ ክርስቲያን››  ጽጌ ማለት  ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት ይላታል (ድጓ ዘጽጌ)

በጽጌ የተመሰሉ የጌታችንና የእመቤታችን ስደት  (ማቴ.  2፥13 -ፍ)

“እምግብፅ  ጸዋዕክዎ  ለወልድየ ” (ሆሴዕ. 11 ፥ 1) ልጄን  ከግብጽ  ጠራሁት  ለጊዜው የተነገረው  ለያዕቆብ  ሲሆን  ፍጻሜው ግን ለጌታ  ነው።  መልከ ጼዴቅም   ዘመዶቹን ማርልኝ  ቢለው ልጄን  በሥጋ  ሰድጄ  እምርልሀለሁ  ብሎ ቃል  ገብቶለት ነበርና ኪዳነ  መልከ ጼዴቅን  ለመፈጸም  ጌታ  ወደ ግብጽ ተሰደደ።

“መልአከ  እግዚአብሔር  አስተርአዮ  በሕልም  ለዮሴፍ”   ከእግዚአብሔር  የታዘዘ  መልአክ ለዮሴፍ በሕልም  ነገረው። “እንዘ  ይብል ተንሥእ ወንሣእ ሕፃነ  ወእሞ  ወጐየይ ውስተ  ሞድረ ግብፅ” ተነሥተህ እናቱንና ብላቴናውን  ይዘህ  ወደ  ግብጽ  ሂድ  ብሎ  ነገረው። እስመ  ሀለዎ  ለሄሮድስ ይኅሥሦ  ለሕፃን  ከመ ይቅትሎ ” ሄሮድስ ብላቴናውን  ሊገድለው ይሻው  ዘንድ  አለውና።

 • ወተንሥኦ ነሥአ  ሕፃነ  ወእሞ  በሌሊት ወሖረ ውስተ ብሔረ ግብጽ” ተነሥቶ ብላቴናውን እናቱን ይዞ በሌሊት ወደ ግብጽ ሂደ። ከላይ በመግቢያው እንደተገለጸው
 • ከመ ይትፈጸም ዘተብህለ  እም ኃበ  እግዚአብሔር  በነቢይ  እንዘ ይብል  እምግብፅ ጸዋዕክዎ ለወልድየ” እግዚብሔር በነቢይ አድሮ ነቢይ ከእግዚብሔር ተገልጾለት በነቢዩ

ቃል ልጄን ከግብጽ  ጠራሁት  ተብሎ  የተነገረው ይደርስ ይፈጸም ዘንድ፤ ወይወርድ እግዚእነ ውስተ ምድረ ግብጽ ዲበ ደመና  ቀሊል” በደመና ተላይ ሆኖ ወደ ግብጽ ይወርዳል ተብሎ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ።

 • “ወነበረ ህየ እስከ አመ ሞቱ” ለሄሮድስ” የተነገረው  ይፈፀም ዘንድ  ሄሮድስ  እስኪሞት ድረስ ሦስት ዓመት  ከመንፈቅ በግብጽ ኖረ።

ጌታ ለምን ተሰደደ?

 1. ትንቢቱ  ይፈጸም  ዘንድ፤    ስደትን  ለመባረክ  3. በፈቃዱ  የሚሞትበት  ጊዜ  አልደረሰምና።  4.  አዳሞ  ከዚህ  ዓለም  አፍአ  ከምትሆን  ከገነት  ተሰዶ  ነበር።   5. ሰማዕትነት  በእሳት  በስለት ብቻ  አይደለምና  እኛን  ለማስተማር  ተሰደደ  ብለው  ሊቃውንት ይተርጉማሉ።  ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ  ተሳለቁበት ባየ ጊዜ  እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን ሁለት ዓመት  ከዚያም  የሚያንሱትን ሕፃናትን ሁሉ ግደሉ አለ። ቄሣር ሕፃናትን ሰብስበሕ ልብስ ምግብ እየሰጠህ በማር በወተት አሳድገህ ለእናት ለአባታቸው ርስት ጉልት እያሰጠህ ጭፍራ ስራልኝ  ብሎኛል ብሎ አዋጅ ነገረ። በዚያ ጌዜ ያላት ልጅዋን የሌላት ልብስ ምግብ ልቀበልበት ብላ  እየተዋሰች ይዛ ሂደላች። በዚያን ጌዜ 144.00 (አሥራ አራት እልፍ ከአራት ሺህ )ሕፃናት  ታርደዋል።

በባሕርየ መለኮቱ ስደት የማይስማማው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ  ወንጌል እንደ አስተማረው ሥጋዊ ስደቱ ፤

 1. ስደትን ለተከታዮቹ  ለማስተማር  በአንዲቱ  ከተማ  መከራ  ቢያደርሱባችሁ  ወደ ሌላይቱ ሽሹ  (ማቴ.  10፥23 )
 2. ሰው መሆኑን ለመግለጽ ከአዳም አካል አንድም ያልጐደለው ሙሉ ዳግማዊ አዳም መሆኑንና የለበሰው ሥጋ የሚደማ የሚቆስል በሰይፍም ሆነ በጦር ቢወጋ ጉዳት የሚደርስበት ሰብአዊ ባሕርይ ያለው መሆኑን ለማስረዳት
 3. ዲያብሎስን ለማሰደድ የጌታ ስደት በተዛዋሪ የዲያብሎስ ስደት ሆነ፤ ጌታ የሚቀበለው መከራ ሁሉ ዲያብሎስን በርቀት የሚመታ መሣሪያ ነው። በመጨረሻም በመስቀሉ ላይ የሆነው የጌታ ሞት የዲያብሎስ ሞት ሆነ።  የኢትዮጵያ ኦቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትም ይህን አጽንተው ያስተምራሉ ያምናሉ።

የጌታንና የእመቤታችን ጉዞ ከግብፅ  ወደ ኢትዮጵያ

እመቤታችን  ቅዱስት ድንግል  ማርያምና ጌታችን መድኃኒታችን  ኢየሱስ  ክርስቶስ አረጋዊ ዮሴፍና ሰሎሜ  በብሩህ  ደመና ላይ  ሆነው  ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ  ሲመጡ   ናግራን  ከተባለ ሀገር ደረሱ።  በናግራን ሳሉ ጌታ እንዲህ አለ። ከቀኝ ጐኔ  የሚፈሰው  ደሜ  በብርሃናት  አለቃ   በቅዱስ  ዑራኤል  እጅ  ተቀድቶ  በቅድሚያ በዚች ሀገር ይፈሳል፣ ይረጫል ። እመ ብዙኃን  ቅድስት ድንግል ማርያምን እንዲህ አላት፤ አንች  በድንግልና  ፀንሰሽ  በድንግልና  እንደወለድሽኝ  አምነው  የሚያከብሩሽ በእኔም  የሚያምኑ  ብዙ  የተቀደሱ  ሰዎች  በዚህች  ሀገር  ይወለዳሉ።  ከናግራን  ተነሥተው ለትግራይ  ትዩዩ  ከሚሆን  ሐማሴን  ከሚባለው  ሀገር ሲደርሱ በምሥራቅ በኩል ከፍተኛ ተራራ ተመለከቱና ወደ ተራራው ሄዱ። ጌታም በተራራው ላይ ሳሉ እመ ብዙኃንን እንዲህ አላት። ይህች ተራራ  ምስጋናሽ   የሚነገርባት ቦታ ትሆናለች። የተራራዋም ስም ደብረ ሃሌ ሉያ ወይም ደብረ ዳ  ይባላል። ትርጓሜውም የአምላክ ልጅ፣  የመስቀሉ፣ ቦታና የስሙ መገኛ ወይም  አደባባይ ማለት  ነው።

ከዚያም በኋላ ታቦተ ጽዮን ወደሞትኖርበት ወደ  አክሱም ደረሱ።  ታቦተ ጽዮን ባለቸበት ቦታ ሳሉ ባዚን የተባለው የኢትዮጵያ ንጉሥ ታቦተ ጽዮንን ለመሳለም መጣ።  የካህናቱ አለቃ አኪን  ለንጉሡ  የኢሳይያስን መጽሐፍ ድንግል በድንግልና ጸንሳ በድንግልና ትወልዳለች ስሙንም  አማኑኤል ትለዋለች የሚለውን አነበበ (ኢሳ 7 ፥ 14)

ስደተኞች  ግን ለንጉሡም ሆነ ለካህናቱ ሳይገለጡ የመጽሐፋን ቃል  ከሰሙ በኃላ በብሩህ ደመና ላይ ሆነው ወደ ደብረ ዐባይ ሄዱ።  ጌታም እናቱን እንዲህ አላት። ይህች ሀገር እንደ አክሱም  ለስምሽ መጠሪያ  ርስት ትሁን፣ በኋላ ዘመን በቀናች ሃይማኖት  ጸንተው ሕጌን የሚያስተምሩ አንችን የሚወዱ ሰዎች ይኖሩባታል አላት።

ከዚያም  ደብረ ዐባይ  ተነሥተው  ዋሊ  ወደሚባለው  ገዳም  ወደ ዋልድባ  ሄዱ። በዋልድባ በረሃም ሳሉ በራባቸው ጊዜ ጌታ በዮሴፍ በትር የአንድን ዕንጨት  ስር ቆፈረ። 318 ስሮችን አወጣና ለእናቱ ብይ  ብሎ ሰጣት። እናቱም ይህን የሚመር እንጨት አልበለም አላችው።  ጌታም በኋላ ዘመን ስምሽን የሚጠሩ አንችን  የሚያከብሩ ብዙ መናንያን ይህን እየበሉ በዚህ ቦታ ይኖራሉ አላት።  እንጨቱም የሚጣፍጥ ይሆንላቸዋል አላት።  ከዚህ በኋላ በብሩህ ደመና ላይ ሆነው   ከዋልድባ  ወደ ጣና  የባሕር  ወደብ  ሄዱ።  በጣና ደሴትም ደጋግ ሰዎች ተቀብለዋቸው 3 ወር  ከ10 ቀን ተቀመጡ። የኢትዮጵያ ሰዎች  በደስታ ተቀብለዋቸዋል። እንደ ግብፃውያን አላሰቃዮአቸውም።

በመሆኑም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን ተራራዎች ሁሉ ለስሞሽ መታሰቢያ ይሆኑሽ ዘንድ አሥራት አድርጌ ሰጥቼሻለህ አላት።  በብሩህ ደመና ላይ ተቀምጠው በጐጃም፣  በሽዋ ፣በጐንደር፣ በበጌ ምድር፣ በወሎ፣ በሐረርጌና  በአሩሲ ፣ በሲዳሞና  በባሌ፣  በጉራጌ፣ በከንባታ፣ በከፋና በኢሊባቡር፣ በወለጋና  በሌሎችም  ክፍላተ አኀጉር እየተዘዋወሩ  አስጉብኝቶ ኢትዮጵያን በሙሉ ለእመቤታችን  አሥራት በኩራት አድርጎ  ሰጥቷታል።  ይህ ሁሉ የሆነው በቅዱስ ዑራኤል መሪነት ነው።

 ከስደት መልስ

መልአኩ  ቅዱስ  ገብርኤል  ወደ  ግብጽ  ሄደና  የሄሮድስን  ሞት  ለእነዮሴፍ  ነገራቸው።

ሄሮድስም  ከሞተ በኋላ  እነሆ  የጌታ መልአክ  በግብፅ  ለዮሴፍ  በሕልም ታይቶ  የሕፃኑን  ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ  ሕፃኑንና እመ ብዙኃን እናቱን ይዘህ ወደ  እስራኤል ነገር ሂድ አለው (ማቴ. 2፥19-21 )

ስለዚህ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስተ ቅዱሳን ቅድስት ድንግል ማርያም ከአረጋዊ  ዮሴፍና  ከሰሎሜ  ጋር ከስደት በሚመለሱ  ጊዜ ወደ ደብረ ቁስቋም የገቡበት ዕለት በየዓመቱ ኀዳር 6 ቀን ይከበራል።

በዚህ መሠረት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶና እናቱ የእኛም እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም  ሊቀበሉት የማይገባውን  ሥጋዊ መከራ ለእኛ ሲሉ በመቀበላቸው  ምክንያት  ለእኛ እመቤታችንና  አምላክን  የምናመሰግንበት ክፍለ ዘመን ዘመነ ጽጌ ስለተባለ ኢትየጵያውያን ሌቃውንት አባ ጽጌ ብርሃንና አባ ገብረ ማርያም የተባሉ አበው መነኮሳት ማሕሌተ ጽጌን ደርሰውልናል።

  ይቆየን

ከብፁዕ አቡነ ሳሙኤል

 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ

አዲስ አበባ

 

 

 

 

ሰላም ማለት የሕሊና እረፍት ጸጥታ ማግኘት ከሁከት ከሽብርና ከሰቀቀን መራቅ፣ አንድነት ስምምነት ማለት ነው አንድ ሰው በውስጡ ያለው የእረፍት  ስሜት ሰላም ይባላል። ደግሞም ሰላም ማለት ከሌላው ሰው ጋር በፍቅር በአንድነትና በስምምነት መኖር ነው። ለሰው ልጅ ከሚያስፈልጉት ነገሮች አንዱ ሰላም ነው።

ለሰው ያለሰላም መኖር ትርጉም የለውምና። ስለዚህ ስለሰላም አስፈላጊነት የተረዱት ቀደምት ነቢያት በትንቢታቸው ሰላምን አስፍተው ይሰብካሉ። ኢሳ. 26፥3 መዝ. 28፥11. መዝ. 4፥8 ኤር. 29፥7 የሰላምና የደስታ ምንጭ እግዚአብሔር ስለሆነ የእግዚአብሔር መንግሥትም ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስ የሆነ ደስታ መሆኗ ተገልጿል፤ ሮሜ. 14፥17 በእግዚአብሔር አርአያና ምሳሌ ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ በዚህ ከመንፈስ ቅዱስ በሆነ ሰላም ይኖር የነበረው የሰው ልጅ በኃጢአት ምክንያት ለዘመናት ተጨንቆ ሲኖር በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ኃይል ሙሉ ሰላምን ሊያገኝ ችሏል።

የሰው ልጅ ከጌታው ይህንን ሰላም ሊያገኝ የቻለው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ እሱ ሰላማዊ የሆነ የሰላም አባት የሰላም አለቃ ለሰላሙም ፍጻሜ የሌለው በመሆኑ ነው። ኢሳ. 9፥6 የእግዚአብሔር አብ ልጅ እግዚአብሔር ወልድ ሰው ሆኖ በተገለጠ ጊዜ በመላእክት አንደበት ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ሰላምም በምድር ይሁን ተብሎ የተነገረው በሉቃስ ወንጌል 2፥14 በአዳም በደል ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ሰላም እንደገና እንዲቀጥል ከሦስት አካላት አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደ ጊዜ ሰላም ተመሠረተ በደላችንም በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የኃጢአት እዳ ለዘለዓለም ከፈለ።

በሰው ልጆች ላይ ለ5500 ዘመን ነግሦ የነበረው ሞት ድል ሆነ በመስቀሉ ኃይል በደላችን ተደመሰሰ በዓለም ላይ ሰፍኖ የነበረው የዲያብሎስ መንግሥት ፈረሰ ሰላማችንም ተመለሰ ኤፊ. 2፥11-17 ይህን ሰላም የተገኘው በመስቀል ላይ በፈሰሰው በኢየሱስ ክርስቶ ደም ነው ቆላ.1፥20 ስለዚህ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ ሊሚኖሩ ክርስቲያኖች በክርስቶስ ኢየሱስ ሰላምን እንያዝ  ሮሜ. 5፥12 ብሎ ስለ ሰላም እንዳስተማራቸው እንመለከታን። ስለዚህ በክርስቶስ የሚያምን ሰው ሁሉ ሰላም በዓለም ሰላም በሀገር፣ ሰላም በጎረቤት፣ ሰላም በቤተሰብ፣ እንዲሰፍን ስለሰላም ሊንቆምና ልንጸልይ ይገባል።

ክርስቲያኖችን ሰላም የሚነሱ ነገሮች ምን ምን ናቸው ብለን ራሳችንን ብንጠይቅ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አለመጠበቅ ከእግዚአብሔር ጋር በንስሐ አለመታረቅ፤ በአጠቃላይ ከመልካም ሥራ መለየት መጠራጠር ራስ ወዳድ መሆን አግዚአብሔር የማይወዳቸውን ነገሮች በውስጣችን እንዲኖሩ ማድረግና የመሳሳሉት ሁሉ ናቸው ከዚህ አንፃር ማንኛውም ክርስቲያን እግዚአብሔርን አላማው አድርጎ ከተጓዘ ሰላም ራሷ ትከተለዋለች ለዚህም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ዓለም በላካቸው ጊዜ የሰላም ልጆች ናቸውና ከሁሉ አስቀድመው ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ብለው እንዲያስተምሩ አምላካዊ መመሪያ ሰጥቷቸዋል ማቴ .10፥11።

ሐዋርያት ቅዱስ ያዕቆብ በተለያየ ምክንያት በዓለም ለተበተኑት ለአሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል መንፈሳዊ ጥበብን በሥራ ላይ እንዴት ማዋል እንደሚገባ ከመግለዕ ጋር ከእናንተ መካካል ጥበበኛና አስተዋይ ሰው ማነው? ብሎ ከጠየቀ በኋላ ለክርስቲያናዊ ኑሮ መመሪያ የሚሆኑ ዐበይት ነጥቦችን ግልጽ በሆነ ስእላዊ አገላለጽ በመልእክት ያስነብባል። እንዲህ በማለት ‹‹መራራ ቅናትና ራስ ወዳድነት በልባችን፤ ቢኖር አታታበዮ፤ በእውነትም ላይ አትዋሹ፤ ምከንያቱም እንዲህ ዐይነት ጥበብ የሚገኘው ከዓለም፣ ከሥጋ፣ ከሰይጣን ነው እንጂ ከእግዚአብሔር አይደለም፣ ቅናትና ራስ ወዳድነት ባሉበት ሥፍራ ከሁከትና ክፉ ሥራ ሁሉ ይኖራሉ። ነገር ግን ከእግዚአብሔር በሚገኘው ጥበብ የሚመራ በመጀመሪያ ንጹህ ነው፣ ቀጥሎም ሰላም ወዳድ፣ ደግ፣ ታዛዥ፣ ምሕረት አድራጊ ነው። ጥሩ ፍሬ የመላበት አድልዎና ግብዝነት የሌለበት ነው።

‹‹ሰላም ወዳድ ሰዎች ሰላምን ዘርተው የጽድቅን ፍሬ ይሰበስባሉ።›› እያለ ሐዋርያው የሰው ልጆች ሁሉንተናዊ ማኀበራዊ ኑሮ ያማረና የተዋበ እንዲሆን ከሰው ልቡና ቅናትና ራስ ወዳድነት እንዳይኖር፣ ወንድም በወንድሙ፣ ትልቁ በትንሹ፣ አዋቂው ባላዋቂው፣ ምሁሩ ባልተማረው፣ ባል በሚስቱ፣ ሚስትም በባሏ ላይ እንዳይነሳሱ በሚገባ አስተምሮአል። ለትውልደ ትውልድም ጽፎ አቆይቷል።

ታዲያ፣ እንደ ሐዋርያው ቃል ትምህርት ማነው ጥበበኛ? ማነው አስተዋይ ሰው? ማነው በሕግና በሥርዓት የሚኖረው? ማነው ለኑሮ ጓደኛው የሚታመነው? ማነው ለቤተሰቡ፣ ለኅብረተሰቡ የሚጠነቀቀው? መሠረቱ ጥበበኛና አስተዋይ ሰው የሚለውን አምላካዊ ሕግ ተላልፎ አይስርቅም አይዋሽም

ይህ የሰላም አምላክ በመለኮታዊ ሥልጣኑ ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ በእርሱ መሞት አዝነው የአይሁድን ዛቻ ፈርተው በዝግ ቤት ተሰብስበው ለነበሩት ደቀ መዛሙርት ሰላም ለሁላችሁ ይሁን በማለት ስለ ሰላም  ወሳኝነት በአንጽንኦት ይናገራል ከእርሱም የሚገኘው ሰላም የማያቋርጥ ዘለዓለማዊ ሰላም መሆኑን ነግሯቸዋል። ሉቃ. 24፥36 ዮሐ. 20፥19-23 ዮሐ.14፥17 ይህም ሰላም ለሐዋርያት ብቻ ሳይሆን በክርስቶስ ለሚያምን ሁሉ የተሰጠ ልዩ የፀጋ ሥጦታ መሆኑን በእምነት እናረጋግጣለን ቤተ ክርስቲያናችንም ከክርስቶስ የተቀበለችውን አደራ አጥብቃ በመያዝ ዘወትር ስለ ሰላም ታስተምራለች ትጸልያለች።  ማህበራዊ ሕይወታችንን ከቀውስና ከሁከት፣ ኅሊናችንንም ከጸጸት ይጠብቅልናል። ማስተዋል ይሏዋል ይህ ነው ልዑል እግዚአብሔር አስተዋይ ልቡና ይስጠን።

ይቆየን

 

 

ከብፁዕ አቡነ ሳሙኤል

 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀጳጳስ

  አዲስ አበባ

 

 

በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሟል

ነሥአ ደዌነ ወፆረ ሕማመነ የእኛን ደዌ ተቀበለ ሕመማችንንና ኃጢአታችንን ተሸከመ ስለ መተላለፋችን ሕጉንና ትእዛዙን በማፍረሳችን ስለ እኛ ቆሰለ፣ ስለ በደላችን ደቀቀ፣ ማለትም ሥጋውን ቆረሰ ደሙን አፈሰሰ በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደገነት ከውርደትና ከኃሳር ወደክብር ተመለስን፡፡ የዓለምን ሁሉ መድኃኒት የሁላችን ዕዳ፣ ፍዳና በደል በእርሱ ላይ አኖረ (ኢሳ. 53÷4-5)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመለኮቱ ስቃ ሳይኖርበት እኛን ከሥቃይ ለማዳን ሲል በለበሰው ሥጋ ተጨነቀ፣ ተሠቃየ፣ ለመታረድ እንደሚነዳ በግ (ጠቦት) በሽላቾቹም ፊት ዝም እንደሚል ይህ ሁሉ መከራ በእርሱ ላይ ሲፈጸም ስቃዩ በዛብኝ መከራው ፀናብኝ ብሎ አልተናገረም፣(አፉን አልከፈተም) ይልቁንም ስለሕዝቡ ኃጢአት ተገርፎ ተሰቅሎ ነፍሱን ከሥጋው ለየ፡፡

ይህን ከባድ ስቃይና መከራ ሲፈጽሙበት በሰውነቱ ስህተት በአንደበቱ ሀሰትና ተንኮል አልተገኘበትም(ኢሳ. 53÷7ይህን መከራ ሲቀበል በሰውነቱ ስህተት በአንደበቱያልተገኘበት አምላክ ከመከራ ከፈተና ያድነን ዘንድ በጐ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡ አሜን

ከእርሱ ጋር ሕይወትን ሰጠን (ቆላ. 2÷13)

አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ቀርባችኋል በአባታችን በአዳም በደል አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን የሰውና እግዚአብሔር ግንኙነት ተቋርጦ ስለነበረ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ሰውና እግዚአብሔር መታረቁን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ አስተማረ፡፡ ሐዋርያው ያስተማረው ይህን ብቻ አይደለም እርሱ ሰላማችን ነውና ሁለቱን ያዋሐደ የጥልንም ግድግዳ በምቱ ያፈረሰ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ ሁለቱንም በእርሱ አንድ ያደረገ ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን ቀርበው ለነበሩት ሰላምን የምስራችን ሰበከ፣ (ኤፊ. 2÷14–18)፡፡

እናንተም በበደላችሁና ሥጋችሁን ባለመገረዝ ሙታን በሆናችሁ ጊዜ ከእርሱ ጋር ሕይወትን ሰጣችሁ፣ በደላችሁን ሁሉ ይቅር አላችሁ፣ በእኛ ላይም የተጻፈውን የእዳ ደብዳቤ ደመሰሰው፣ እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል፡፡ (2ቆላ. 13÷15)፡፡

ከዚህ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉ እንደተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ ተጠማ በቸርነቱ የሚያጠጣ የደከመውን የሚያበረታ አምላክ ተጠማሁ አለ ለእሥራኤላውያን ከደረቅ አለት ውኃ ያጠጣ አምላክ መናን ከደመና አውርዶ የመገበ አምላክ ስለሰው ልጅ ብሎ ተጠማሁ አለ፡፡ በዚህም ሆምጣጤ የሞላበት መራራ ዕቃ “ተቀምጦ ነበር በሰፍነግ ሞልተው ወደአፉ አቀረቡለት ኢየሱስም ከርቤ የተቀላቀለበት ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ ተፈጸመ አለ፡፡ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ” (ዮሐ. 19÷28-31)፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ላይ ሳለ ሰባቱ (አጽርሐመስቀል) የተናገራቸው ቃላቶች

 1. ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ፡- ይህ አምላኬ አምላኬ ስለምን ተውኸኝ ማለት ነው፡፡ (ማቴ. 27÷46)
 2. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው (ሉቃ. 23÷34)፡፡
 3. እውነት እውነት እልሃለሁ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትሆናለህ (ሉቃ. 23÷43)፡፡
 4. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ (ሉቃ. 23÷46)
 5. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱን አንቺ ሴት እነሆ ልጅሽ አላት ደቀመዝሙሩን እነሆ እናትህ አለው (ዮሐ. 19÷27)፡፡
 6. ተጠማሁ (ዮሐ. 19÷29)፡፡
 7. ተፈጸመ አለ ራሱን አዘንብሎ ነፍሱን ሰጠ (ዮሐ. 19÷30)፡፡

ኦ አእዳው እለ ለሐኳሁ ለአዳም ተቀነዋ በቅንዋተ መስቀል አዳምን የፈጠሩ እጆች ወዮ በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ በገነት የተመላለሱ እግሮች ወዮ በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ፡፡ በአዳም ፊት የሕይወትን መንፈስ እፍ ያለ አፍ ወዮ ከሐሞት ጋር የተቀላቀለ መጠጥንና ከርቤን ጠጣ፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ በሰማይና በምድር የተፈጸሙ ሰባት ተአምራት፡-

በሰማይ የተፈጸሙ ሦስት ተአምራት፡-

 • ከስድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ላይ ፀሐይ ጨለመ (ሉቃ. 23÷44)፡፡
 • ጨረቃ ደም ሆነ፣
 • ከዋክብት ረገፉ

በምድር የተፈጸሙ አራት ተዓምራቶች

 • የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከሁለት ተቀደደ
 • ዓለቶችም ተሰነጠቁ
 • መቃብሮችም ተከፈቱ
 • ሞተው ከነበሩት ከቅዱሳን ሰዎች ተነሡ (ማቴ. 27÷51)፡፡

ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ታረቅን (ሮሜ.5÷10)፡፡

እግዚአብሔር አምላክ የሰውን ልጅ አክብሮ በመልኩ ከፈጠረው በኋላ ሕግ ሠራለት፡፡ ሰውም የተሰራለትን ሕግ አፈረሰ፤ በዚህ ምክንያት በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ጥላቻዎች ተመሰረቱ፣ በሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ በርደተ መቃብር ርደተ ሲኦል ተፈርዶበት ሲኖር ይቅር ባይና ቸር አምላክ የሰውን ንስሓ ተቀብሎ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድያ ልጁን ወደዚህ ዓለም ላከው (ዮሐ. 3÷16-18) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስ ነስቶ ቅድመ ዓለም ከአብ ያለእናት ድኀረ ዓለም ከእመቤታችን ያለአባት ተወለደ በመወለዱ ጥልን አፈረሰ እርቅን መሠረተ፡- “ሐመ ከመ ሕሙማነ ያድኅን” የታመሙትን ያድን ዘንድ ታመመ፡- የተፍገመገሙትም ያጸናቸው ዘንድ የሞቱትንም ያድናቸው ዘንድ ሞትን ይሽረው ዘንድ የሰይጣንን  ማሰርያ ይቆርጥ ዘንድ በፈቃዱ ሁሉም ሆነ፡፡

 • በሰውና በእግዚአብሔር እርቅ ተመሠረተ (ዮሐ. 1÷14)፡፡
 • የሰውና የመላእክት ማኅበር ተመሠረተ (ሉቃ. 2÷8)፡፡
 • የሕዝብና አሕዛብ መገረዝና አለመገረዝን እርቅ ተመሠረተ (ቆላ. 2÷11-12)፡፡
 • ሕይወትን ሰጠ፣ ጠላታችን ዲያብሎስ ነፍስና ሥጋን ለያይቶ ሥጋን በመቃብር አበስብሶ ነፍስን በሲኦል ተቆራኝቶ ለማኖር አስቦ ሳለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን እነዚህን አንድ አድርጐ በመንግሥተ ሰማያት ለማኖር ፈቀደ (1ኛ. ተሰ. 4÷14)፡፡

“ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር በሌላ አልመካም/ገላ. 6÷14”

ትምክሕት፡- “ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር በሌላ አልመካም” ወይም “ከክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክሕት ከእኔ ይራቅ፤” የሚለው የቅዱስ ጳውሎስ አነጋገር አንድ ሀሳብና አንድ ግብ ብቻ ነው፡፡ ይኸውም በክርስቶስ መስቀል ብቻ መመካትና ደስታ ማድረግ ነው፡፡

በእርግጥ ቅዱስ ጳውሎስ በሌላ ቦታ በማንና በምን መመካት እንደሚቻል ተናግሯል፤ “በእግዚአብሔር ክብር ተስፋ እንመካለን፡፡” (ሮሜ. 5÷2) “መከራ ትዕግሥትን እንደሚያደርግ፤ ትዕግስትም ፈተናን፤ ፈተናም ተስፋን እንደሚያደርግ እያወቅን በመከራችን እንመካለን፡፡” (ሮሜ. 5÷3) “የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ፡፡” (2ኛ ቆሮ. 12÷9) “ትምክሕት የሚያስፈልግ ከሆነ እኔም በድካሜ እመካለሁ፡፡” (2ኛ. ቆሮ. 11 ÷30) “ተስፋችን ወይም ደስታችን ወይም የትምክሕታችን አክሊል ማን ነው? በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናንተ አይደላችሁምን?” (1ኛ. ተሰ. 2÷19)፡፡

ይሁን እንጂ ከላይ በተጠቀሱት ነገሮች መመካት በክርስቶስ መስቀል ከመመካት መራቅ አይደለም፡፡ ምክንያቱም የእግዜአብሔርን ክብር ተስፋ ማድረግ፣ መከራን መቀበልና በወንጌል አገልግሎት ሁሉን ትቶ መስቀሉን ተሸክሞ በእውነት መከተል ነው፡፡ በመስቀል ላይ የተፈጸመውን ድኀነት በአንድ ሐዋርያ ላይሊደርስ የሚችለው በመስቀል ላይየተሰቀለውን ክርስቶስ በሚሰብክበት ጊዜ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ሐሰተኞች መምህራንን ለማሳፈር እንደ ዓለማውያን በዓለማዊ ነገር ለመመካት የሞከረበት ጊዜ መኖሩ በሚከተለው አነጋገሩ ይታወቃል፡፡ ብዙዎች በዓለማዊ ነገር ስለሚመኩ እኔ ደግሞ እመካለሁ፡፡ (2ኛ ቆሮ.11÷18) ይህንንም በግልጥ ሲያስረዳ እንዲህ ይላል እነዚህ ዕብራውያንና እስራኤላውያን፣ የአብርሃም ዘሮች፡-

እንደዚሁ የተገረዙ ቢሆኑ እኔም እንደ እነርሱ ዕብራዊ፣ እስራኤላዊና የአብርሃም ዘር ነሀን፤ በስምንተኛ ቀን የተገረዝኩ ነኝ ከሁሉም እኔ እበልጣለሁ፤ ኦሪትን ጠብቄአለሁ፤ ለኦሪት ቀናተኛ ነበርሁ፤ በኦሪት ስለሚገኘው ጽድቅ ያለ ነቀፋ ነበርኩ፡፡ (ፊል. 3÷5-6)፡፡

ነገር ግን ይህ ዓይነቱ ትምክሕት ይላል ቅዱስ ጳውሎስ በተለይ ለመንፈሳዊያን ሰዎች ከእግዚአብሔር አይደለም፤ አይጠቅምም፤ ዕብደት ወይም ስንፍና ነው፤ ከንቱ ወይም ኢምንት ነው፤ እንደ ጉድፍም ነው፡፡ ስለዚህ ከመስቀሉ በቀር በሌላ አልመካም እናከብረው እና እንደፀጋው ባለጠግነት መጠን በደሙ የተደረገልን ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት ነው፡፡

 • በመስቀሉ ላይ በተሰቀለው በእግዚብሐር ወልድ ድነናል (ኤፌ. 1÷7፤ 1ኛ ጴጥ. 1÷19)
 • በመስቀሉ ክርስቶስ ወደ ራሱ አቅርቦናል፤

በሰማያት ወደ አባቱ አቅርቦናል፤ (ዮሐ. 12÷32፤ ኤፌ. 2÷13፤ ኪዳን፡፡)

 • አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በኃጢአት ምክንያት፣ በበደል ምክንያት በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል፡፡
 • በመስቀሉ ደም ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀናል፤ ሰላምን አግኝተናል፤ (ቆላስ. 1÷20-21፣ ሮሜ. 5÷10)፡፡
 • በጌታችን በአምላካችን ወደቆምንበት ወደዚህ ጸጋ በእምነት አግኝተናል
 • በመስቀል ላይ በፈሰሰው ደሙ ጽድቅን፣ ቅድስናንም ቤዛነትን አግኝተናል፤ (ሮሜ. 5÷2፣ 1ኛ ቆሮ. 1÷31፣ ዕብ. 10÷10፣ 13÷12)
 • በመስቀሉ ለዘለዓለም ፍጹማን ሆነናል፣ (ዕብ. 10÷14)
 • በመስቀሉ የዕዳ ደብዳቤያችን ተደምስሶአል፣ (ቆላስ. 2÷14)
 • በእኛ ላይ የነበረውን የተጻፈውን የእዳ ደብዳቤ ጽሕፈት ደምስሶ እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል፡፡
 • በመስቀሉ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ለመግባት ሞገስን አግኝተናል፤ (ዕብ. 10÷19)
 • በመስቀል ላይ በፈሰሰ ደሙ ከበደላችን ሁሉ ታጥበናል፣ (ራዕ. 12÷11)
 • በመስቀል አዲስ ኪዳን ተመስርቶአል፣ (ሉቃ. 22÷20)
 • ወይቤ ተፈጸመ ኩሉ፡፡
 • ጌታችን ሁሉ ተፈጸመ ብሎ እንደተናገረ ስለ ሰው ልጆች መዳን በመጻሕፍት የተነገረው ሁሉ በመስቀል ላይ ተፈጽሟል፣ (ዮሐ. 19÷18)፡፡
 • ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ ሁለቱን ወገኖች አይሁድና አሕዛብ አንድ አድርጐ ከራሱ ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው፡፡ (ኤፌ. 2÷16)
 • በመስቀል ላይ ስለተደረገልን ነገር የእኛ መልስ ምንድን ነው?

ከሁሉ በፊት ከእኛ የሚፈለገው በወደደንና ስለ እኛ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ በክርስቶስ በማመን በሃይማኖት መኖር ነው (ገላ. 2÷20) ምክንያቱም አሁን በሥጋ የምንኖርበት ጊዜ ስለእኛ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ነውና፡፡

 • ምንተኑ አዐስዮ ለእግዚአብሔር በእንተ ኩሉ ዘገብረ ሊተ
 • ስለ ተደረገልን ሁሉ እግዚአብሔርን ማመስገን፣ (መዝ. 115÷3-4)
 • ይህን ስለአደረገልን ምን ወረታ እንከፍለዋለን ጽናት አግኝተናልና፡፡
 • ከመስቀሉ በቀር በሌላ አለመመካት፣ (ገላ. 6÷14)
 • ከተሰቀለው ክርስቶስ በቀር ሌላ አዳኝ አለመኖሩን በእርግጥ ማመን፣ (1ኛ. ቆሮ. 2÷2)
 • ስለ እኛ በመስቀል ላይ መከራ የተቀበለውን የክርስቶስን ፍለጋ መከተል፣ (1ኛ. ጴጥ. 1÷21)
 • መንፈሳዊውን ነገር በሚያስተምረን የእግዚአብሔርን ቃል የተሰቀለውን ክርስቶስን መስበክ፣ (1ኛ. ቆሮ. 1÷13)
 • ሞቱን እስከ ዳግም ምጽአት ማወጅ፣ (1ኛ. ቆሮ. 11÷26)
 • በመስቀል ላይ ለድኀነት የፈሰሰውን ቅዱስ ምስጢር በእምነት መቀበል ከእኛ ይፈልጋል፡፡ (ማር. 14÷22-25)
 • በሰውና በእግዚአብሔር መካከል እርቅ ተመሰረተ (ዮሐ. 1÷14)
 • የሰውና የመላእክት እርቅ ተመሠረተ (ሉቃ. 2÷8)
 • የሕዝብና አሕዛብ መገረዝና አለመገረዝ እርቅ ተመሠረተ (1ኛ. ቆሮ. 6÷6፣ ሮሜ 8÷6)
 • ሕይወትን ሰጠ፣ ጠላታችን ዲያብሎስ ነፍስና ስጋን ለያይቶ ሥጋን በመቃብር አበስብሶ ነፍስን በሲኦል ተቆራኝቶ ለማኖር አስቦ ሳለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን እነዚህን አንድ አድርጐ በመንግሥተ ሰማያት ለመኖር ፈቀደ (1ኛ. ተሰ. 4÷14)
 • አቤቱ የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ! ካንተ ጋር በምንኖርበት ጊዜ ምን ያህል ደስተኞች ነን!
 • በዚህ ታላቅ ክብር ያሉ የእግዚአብሔር ልጆች ምንኛ ደስተኞች ናቸው!
 • አብሮን የሚኖር ክብርህ፣
 • የመለኮታዊ ክብርህ ተሳታፊነታችን፣ ደስታችንን ዕጥፍ ድርብ ያደርገዋል፡፡ ይህን የተናገርህ አንተ ነህ፡፡ “የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳን ሕያው ይሆናል ብለሀልና” ዮሐ. 11÷25፡፡
 • ስለዚህ አንተን በመጥራት እንከተልሀለን፡፡ “በዚህ ሁሉ በወደደን በእርሱ ከአሸነፊዎች እንበልጣለን፡፡” ሮሜ. 10÷32
 • “ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ፡፡ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም፡፡ ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፡፡” ገላ. 2÷20

በመስቀል ላይ በተደረገው የማዳን ሥራ ውስጥ መለኮትና ትስብእት በተዋሕዶ ባይገለጥ ኖሮ የተደረገው  የድኀነት ሥራ ከንቱ ይሆን ነበር፡፡ በድኀነት የመለኮትና የትስብእት ድርሻ በተዋሕዶ ምሥጢር ብቸኛ ነው፡፡ ዓለምን ለማዳን ከኀጢአተኞች ጋር ተሰቀለ፡፡ ኢሳ. 93 ሜቴ. 23÷38፡፡

ባለ ዘመናችን በደላችንና ኃጢአታችን ትዝ እያለን ንስሓ በመግባት የጌታችን ቅዱስ ሥጋውን በመቀበል ክቡር ደሙን በመጠጣት ከእርሱ ጋር ለመኖር ተጠርተናል፣ እርሱ “ሥጋዬን የበላ ደሜንም የጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ፡፡” ብሏል (ዮሐ. 6÷56)

“ከእግዚአብሔር አብ ከመድኃኒታችንና ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን፡፡” ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለደቀ መዝሙሩ ለቲቶ መልእክት ሲጽፍ በመግቢያው ላይ የሰጠው ቡራኬ (ቲቶ 1÷4-11)

እግዚአብሔር የሚለው የባሕርይ ስም ምንም እንኳ የሦስቱ የአብ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ ስም ቢሆንም አብዛኛውን ጊዜ በሐዋርያው በቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ለአብ ብቻ ተሰጥቶ ይገኛል፡፡ ስለዚህም መነሻ ጥቅስ በሆነው በዚህ ርእስ ሐዋርያው ለቲቶ ቡራኬ ሲሰጥ “ከእግዚአብሔር አብ” ከአለ በኋላ “ከመድኃኒታችን ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ” ብሏል፡፡ ጳውሎስ ይህን ሲጽፍ “ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር አይደለም” ሊል ፈልጎ አይደለም፡፡ ጌታ ማለት እግዚአብሔር ማለት ስለሆነ፤ እግዚአብሔር ማለትን ጌታ በማለት ስለተካው ነው፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሎ ሞቶ ዓለምን ያዳነ ስለሆነ፣ መድኃኒት፣ መድኃኔዓለም፣ ኢየሱስ ይባላል፡፡ ስለዚህም መድኃኒታችን ብሎ አዳኝነቱን በቅጽል ስም አንስቷል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ በባሕርዩ የሰማይና የምድር ንጉሥ ነው፤ ክርስቶስ ተብሏል ክርስቶስ የሚለውም ስም ንጉሥነቱን የሚገልጽ ስም ነውና እንደ ቅዱስ ጳውሎስ አጻጻፍ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚለው ቅጽል ስም መድኃኒትነቱን የዘለዓለም ንጉሥ መሆኑን የሚገልጥ ስም ነው፤ ጸጋና ምሕረት፣ ሰላምም ይሁን በማለት ቡራኬ ሲሰጥ ሦስት ቃላትን አስቀምጦአል፡፡ እነዚህን ሦስት ቃላት ነጣጥለን በማየት ምንነታቸውን እንረዳ፡፡

ሀ) ጸጋ፡- ጸጋ ማለት ቸርነት፣ ምሕረት፣ በጎነት፣ ያለ ብድርና ያለ ዋጋ የሚሰጥ ነጻ ስጦታ ማለት ነው፡፡ በተለይ ለሰው የሚሆን የእግዚአብሔር አስተያየት ነው፡፡ (ቲቶ 2÷11፣ ሉቃ. 1÷30፣ ኤፌ. 2÷4-5፣ ሮሜ 5÷6-8)፡፡ እግዚአብሔር በጸጋው ደኅንነትን ፈጽሞልናልና፤ (ኤፌ. 2÷6-8፣ 2ጢሞ. 1÷9)፡፡ የእግዚአብሔርን ጸጋ የምንቀበለው በእምነት ነው፡፡ (ዕብ. 4÷16፣ ኤፌ. 2÷8)፡፡ በሕግ ወይም በሥራ እንጸድቃለን ብንል የጸጋው ተቀባዮች ልንሆን አንችልም (ገላ. 5÷4-5፣ ሮሜ 8÷1-2፣ 5÷1፣ 15-17)፡፡ የእግዚአብሔር ጸጋ ምእመናንን ያጸናል (የሐዋ. 20÷32፣ 2ቆሮ. 9÷14፣ 12÷9፣ 2ጢሞ. 2÷1)፡፡ ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ስጦታን ይሰጣል፡፡ (ሮሜ 12÷6-8፣ ኤፌ. 3÷8) ይህን ጸጋ ቸል እንዳንለው መጠንቀቅ አለብን (ሮሜ 6፣ ይሁዳ 4)፡፡

ለ) ምሕረት፡– ምሕረት ቅጣት ለሚገባው ይቅርታ ማድረግ ነው (መዝ. 50፣ 129÷7-8)፡፡ ለደካሞች፣ ለበሽተኞች፣ ለድሆች ቸርነትና ርዳታ ማድረግ ነው፡፡ (ምሳ. 14÷21-31፣ ሆሴ. 14÷3፣ ሮሜ 5÷6፣ ማር. 10÷46-52)፡፡ እግዚአብሔር ከምሕረቱ የተነሣ ለእኛ ሲል በመስቀል ላይ እንዲሞት አንድ ልጁን ሰጠ (ኤፌ. 2÷4-5፣ 1ጴጥ. 1÷3)፡፡ ምእመናን ምሕረት እንዲያደርጉ ታዘዋል (ያዕ. 2÷1-13፣ ሉቃ. 6÷36፣ ማቴ. 5÷7፣ ሮሜ 12÷19)፡፡ እግዚአብሔር ከማናቸውም ነገር ሁሉ ይልቅ ምሕረትን ይወድዳል፣ (ሆሴ. 6÷6፣ ሚክ. 6÷8፣ ማቴ. 12÷7)፡፡

ሐ) ሰላም፡– ሰላም ስምምነትና አብሮ መኖር ነው፤ ዕረፍትና ጸጥታ ማግኘት ነው፡፡ ሰዎች ሲገናኙ የሚለዋወጡት የሰላምታ ቃል ወይም የንግግር መክፈቻ ቃል ነው፡፡ (ዮሐ. 20÷19)፡፡ እውነተኛ ሰላም የሚገኘው ሰው በክርስቶስ አምኖ፣ ከኃጢአቱ ነጽቶ ከእግዚአብሔር ጋር ሲታረቅ ነው፡፡ (ሮሜ. 5÷1፣ ኤፌ. 2÷14-17)፡፡ ሰላም የመንፈስ ፍሬ ነው (ገላ. 5÷22)፡፡ እግዚአብሔር ለሚታመኑበት የራሱን ሰላም ይሰጣቸዋል (ኢሳ. 26÷3-4፣ ዮሐ. 14÷27፣ ፊል. 4÷6-7)፡፡

አማኞች ከሰዎች ጋር በሰላም እንዲኖሩ ታዘዋል (ሮሜ. 12÷18፣ 1ጴጥ. 3÷11)፡፡ ክርስቶስ ሲመጣ ሰላም ይሰፍናል (ኢሳ. 9÷6-7፣ 11÷6-9)፡፡ ሰላም የእግዚአብሔር መንግሥት ራሱ ነው (ሮሜ 14÷17)፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔር ጸጋ ተሰጠን ማለት ዋጋ ሳንከፍል የብድር ምላሽ ሳንጠየቅ በእግዚአብሔር ቸርነትና ምሕረት ድኅነት ተሰጠን ማለት ነው፡፡

ከመስቀሉ በቀር ለኔ ሌላ ትምክሕት የለኝም

የሰው ልጅ ከግዙፍና ከረቂቅ ነገር የተገኘ ታላቅ ፍጥረት ነው፤ በግዙፍነቱ ይጨበጣል፣ ይታያል በርቀቱ ደግሞ እግዚአብሔር ሲፈቅድለት ለማመን የሚያስቸግሩ ብዙ አስደናቂ የፈጠራ ሥራዎችን በረቂቅ አእምሮው ሲሠራ ይታያል፡፡ ይሁንና በኃጢአት ምክንያት ከእግዚአብሔር ሲርቅ የረቀቀ አእምሮው በግዙፉ አካል እየተሸነፈና እየተዋጠ ወደ ግዙፉ ነገር ሲያመዝን ይታያል፡፡ በዚህ ምክንያት ብዙ ጊዜ የመንፈስን ሳይሆን የሥጋን ሥራ እየተከተለ ፈጣሪውን አሳዝኖአል፡፡ ራሱንም ጎልቶአል፣ (ዘፍ. 6÷6-23)፡፡ እግዚአብሔርም መሐሪ አምላክ ነውና በምሕረቱ እየጎበኘ ግዙፉን ሰው በግዙፍ ምልክት ሲያድነው እናያለን፡፡ ነገር ግን ሰው ዛሬም ድረስ የመስቀሉ ምልክት ተሰጥቶት እያለ በመከራ ሥጋ ተዘፍቆ ይገኛል፤ ለምን ይህ ሆነ? ያልን እንደሆነ መልሱ መስቀሉ እንደሚያመለክተው ሳይሆን በመቅረቱ ነው፡፡ መስቀሉ መዳን የተፈጸመበት ከመሆኑም በላይ በውስጡ ብዙ መልእክቶች አሉት፤ ክርስቶስ በመስቀሉ፣ ኃጢአትን ለማጥፋትና ለመደምሰስ ሞተ (ሮሜ 6÷3-14)፤

የእስራኤልን ሕዝብ ከግብጽ ባርነት ለማውጣት በግብጻውበያን ላይ ከታዘዘውም መቅሠፍት ለማዳን የደም ምልክት በቤቶቻቸው መቃን እንዲያደርጉ በማዘዝ ከመቅሠፍቱ አድኖአቸዋል፤ (ዘጸ. 12÷12-13)፡፡ እንደዚሁም እስራኤል በምድረ በዳ ኃጢአትን እየሠሩ ባስቸገሩ ጊዜ ተናዳፊና መርዛም እባብ በመልቀቅ ከቀጣቸው በኋላ ንስሓ ገብተው እንዲምራቸው በጠየቁ ጊዜ በሚታይ ቦታ ላይ የእባብ ምልክት በመስቀል እርሱን እያዩ እንዲድኑ አድርጎአል፤ (ዘኁ. 21÷5-9)፡፡ እነዚህ ነገሮች ለጊዜው ከመቅሠፍቱና ከእልቂቱ ለመዳን የተሰጡ ምልክቶች ሲሆኑ በኋላ ዘመን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና ደም ለሚፈጸመው ድኅነተ ዓለም እንደጠቋሚና አመላካች ቀስት ሆነው  የሚያስተምሩ ነበሩ፡፡ ጊዜው ደርሶ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ደሙን በማፍሰስ ሰውን ለፍጹም ድኅነት አብቅቶአል፣ በመሆኑም በመስቀሉ ላይ በፈሰሰው ደሙ አምነው ለሚፈሩትና ለሚያመልኩት መስቀሉ የመዳን ምክንያት ሆኖ ተሰጥቶአቸዋል፤ (1ቆሮ. 1÷18)፡፡ ቀድሞ እስራኤላውያን በደሙና በእባቡ ምስል ምክንያት ከመቅሠፍትና ከእልቂት እንደዳኑ ዛሬም ምእመናን ሥጋውንና ደሙን ተቀብለውና መስቀሉን ተሸክመው ከመከራ ሥጋና ከመከራ ነፍስ ይድናሉ፡፡

ስለዚህ በከበረ ደሙ የገዛን እኛ ሁላችን “ጌታችን በመከራው ከመሰልነው በክብር እንመስለዋለን በሞቱም ከመሰልነው በትንሣኤው እንመስለዋለን” (ሮሜ 6÷50) በሞቱ መስለነው በትንሣኤው እንድንመስለው የእግዚአብሔር ረድኤት አይለየን አሜን!!!

“ስብሐት ለእግዚአብሔር”

ከብፁዕ አባ ሳሙኤል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶቤተ ክርስቲያን

የልማትና ክርስቲያናተራድኦ ኮሚሽን ሊቀጳጳስ

አዲስ አበባ

 

 

ለመላው ኢትዮጵያውያን በሀገር ውስጥና በውጭ ዓለም ለምትገኙ ሁሉ

ልዑለ ባሕርይ ቸሩ እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ከማርቆስ ወንጌላዊ

 ወደ ዘመነ ቅዱስ ሉቃስ ዜናዊ 2011ዓ.ም በሰላም፤ በጤና፤ በሕይወት ሁላችንንም አደረሰን!!

                                                    ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ፤

                                                  ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም፤

                                                  ወይረውዩ አድባረ በድው (መዝ. 64÷11-12)፡፡

በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃዋለህ፣ ምደረበዳውንም ገዳማት ልምላሜውን አግኝተው ደስ ይላቸዋል በበረኃ ያሉት ተራራዎች ሁሉ ዝናሙን ይረካሉ፡፡ ኮረብታዎችም ደስ ብሏቸው ልምላሜውን እንደዝናር ይታጠቃሉ፡፡ ቆላውና ደጋው ስንዴውንና የተለያየውን እህል ይሞላል፡፡

ወወሀብኮሙ ሲሳዮሙ ለሕዝበ ኢትዮጵያ (ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው) ተብሎ በነቢየ  እግዚአብሔር ቃል በተነገረው መሠረት ኢትዮጵያን በረድኤት ጐበኘሀት (ወአብዛኅኮ ለብዕላ) በሚመጡ ዘመናትም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለጠግነት ይሰጠን ዘንድ ነው፡፡ ኤፌ. 2፥6

ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ “አእትቱ እምላዕሌክሙ ግዕዘክሙ ዘትካት በእንተ ብሉይ ብእሲ ዘይማስን በፍትወተ ስሒት፤ ሐድሱ መንፈሰ ልብክሙ፡፡ ወልበስዎ ለሐዲስ ብእሲ ዘሐደሶ እግዚአብሔር በጽድቅ ወበርትዕ ወበንጽሕ” በተሳሳተ ምኞት የተበላሸውን አስቀድሞ ትኖሩበት የነበረውን አሮጌውን ሰውነት ከእናንተ አርቁ፡፡ ልቡናችሁን በእውቀት አድሱ፤ በእውነት፣ በጽድቅና በንጽሕና እግዚአብሔርን ለመምሰል የተፈጠረውን አዲሱን ሰውነት ልበሱ” (ኤፌ. 4÷22-24)፡፡

ይህ ዓመት በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር 2011 ዓ.ም ሲሆን በአውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር 2018 ነው፡፡ ይህ ልዩነት የመጣው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የምዕራብ አብያተ ክርስቲያናት የተለያየ የዘመን አቆጣጠር ስለሚከተሉ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሌላው የክርስትና ዓለም የተለየ የራስዋ ብቻ የሆነ የዘመን አቆጣጠር መንገድ አላት፡፡ ይህም የዘመን አቆጣጠር መጽሐፍ ቅዱስን በተለይም መጽሐፈ ሄኖክንና ኩፋሌን መሠረት ያደረገ ነው፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ታሪክ መረዳት እንደሚቻለው ጥንታዊው የጁሊያን የዘመን አቆጣጠር ከአሁኑ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የዘመን አቆጣጠር ተመሳሳይነት ነበረው፡፡ ሆኖም የምዕራብ ቤተ ክርስቲያን በ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ የጁሊያን የዘመን አቆጣጠር የተባለ ሌላ የዘመን አቆጣጠር ጀመረች፡፡ ይህም የግሪጎርያን የዘመን አቆጣጠር ሲሆን የ4 ዓመት የአቆጣጠር ልዮነት ስሕተት እንዳለው ራሳቸው አውሮፓውያን ያምናሉ፡፡

ያም ሆነ ይህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ በያዝነው እና

በምንጠቀምበት ባሕረ ሀሳብ በተባለው የዘመን አቆጣጠር ስልት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ታላቅ አገልግሎት እያቀረበች ትገኛለች፡፡ አሁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ዝም ቢሉ ለዓመቱ የዘመን መቁጠሪያ (ካሌንደር) ማዘጋጀት የሚችል ሰው ማግኘት ያስቸግራል፡፡ ለሚመጣው ዓመትም የዐቢይ ጾም፣ የሰኔ ጾም መቼ እንደሚገባ እንዲሁም የሆሳዕና፣ የስቅለት፣ የፋሲካና የዕርገት በዓላት መቼ እንደሚውሉ ለመናገር የሚችል ሰው አይኖርም፡፡ የእኛ ኦቶዶክሳዊ የተዋሕዶ ሊቃውንት የመሬትን፣ የፀሐይንና የጨረቃን እንቅስቃሴና ዑደት በልዩ የባሕረ ሀሳብ አቆጣጠር እያሰሉ የዕለታትን፣ የወራትን፣ የዓመታትንና የበዓላትን ቀናት መዋያ ለመናገር ጥልቅና ሰፊ የሆነ እውቀት አላቸው፡፡

‹‹የተመረጠችውን የእግዚአብሔርን ዓመት እሰብክ ዘንድ ላከኝ››

ይህ ቃል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረው ቃለ ወንጌል ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ  ክርስቶስ ለሰው ሲል ሰው የሆነ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደመሆኑ መጠን ይህን ቃል የተናገረው ሰው ሆኖ ወደዚህ ዓለም ለመምጣት የፈቀደበትን ምሥጢር ግልጽ በአደረገበት የትምህርት ክፍል ነው፡፡

በአንድ የሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ሲገባ ያነብ ዘንድ የቅዱስ ኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፡፡ መጽሐፉን ሲገልጥም ‹‹የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፡፡ ስለዚህ ቀብቶ (ማለት ከሥጋ ጋር አዋሕዶ) ለድሆች የምሥራችን እነግራቸው ዘንድ፤ ለተማረኩትም ነጻነትን እሰብከላቸው ዘንድ፤ ያዘኑትን ደስ አሰኛቸው ዘንድ፤ ዕውሮችም ያዩ ዘንድ የተገፉትንም አድናቸው ዘንድ፤ የታሰሩትንም እፈታቸው ዘንድ፤ የቆሰሉትንም እፈውሳቸው ዘንድ የተመረጠችውንም የእግዚብሔርን ዓመት እሰብክ ዘንድ ላከኝ›› የሚል ቃል አገኘ፡፡ ይህን የትንቢት ቃል የተናገረውም ነቢዩ ቅዱስ ኢሳይያስ ነበር፡፡ ኢሳ.61፥1-2፡፡ ጌታችን ይህን ቃል ከአነበበ በኋላም ‹‹የዚህ መጽሐፍ ቃል ዛሬ በጆሮዋችሁ ተፈጸመ›› ሲል እንደ ተናገረ፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት ስለሆነ በእሱ ትምህርትና ተአምራት፤ ስቅለትና ሞት በእርግጥ በኀጢአት ምክንያት ከሥጋዊና መንፈሳዊ በረከት ነዳያን የነበሩ በረከተ ሥጋንና በረከተ ነፍስን አግኝተዋል፡፡ በኀጢአት ምክንያት የዲያብሎስ ምርኮኞች የነበሩ ነጻ ወጥተዋል፡፡ በተፈጥሮ ያገኙትን ክብር አጥተው ኃዘንተኞቸ የነበሩ ያጡትን በማግኘታቸው ለዘለዓለማዊ ደስታ ዕድል ፈንታቸው ሁኗል፡፡ ቀን የጨለመባቸው ዕውራነ ሥጋና ዕውራነ ነፍስ የሆኑ መንፈሳዊና ሥጋዊ ብርሃንን አግኝተዋል፡፡ የዓለማዊና ሥጋዊ ፈቃድ ተቸናፊ የነበሩ አቸናፊ ሁነዋል፡፡ የኃጢአት እሥረኞች የነበሩ በይቅርታ ከእስራት ተፈትተዋል፡፡ በኃጢአት ደዌ የቆሰሉ ፈውስን አግኝተዋል፡፡ ይህ ሁሉ በረከት የተገኘው በክርስቶስ ስለሆነ ነቢዩ ቅዱስ ኢሳይያስ ‹‹የተመረጠችው የእግዚብሔር ዓመት›› ያላት ይህ ሁሉ ጸጋ የተገኝባት የድኅነት ቀን ናት፡፡ ዘመነ ድኅነት ማለት በግልጽ አነጋጋር ዘመነ ክርስትና ማለት ነው፡፡

የዘመን መለወጫን በዓል፣ የአዲሱን ዓመት በዓል የምናከረው

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንቶስ መልእክቱ ‹‹በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ፤ በመዳንም ቀን ረዳሁህ›› የሚለውን የነቢዩ ቅዱስ ኢሳይያስን ቃል ከጠቀሰ በኋላ ‹‹እነሆ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፦ የመዳን ቀን አሁን ነው›› 2. ቆሮ. 6፥2 ይላል፡፡  በቅዱስ መጽሐፍ የተመረጠች የእግዚአብሔር ዓመት፣ የተወደደ ሰዓት፣ የመዳን ቀን›› የሚል የተለያየ ስያሜ የተሰጠው አሁን እኛ ለምንኖርበት የክርስትና ዘመን መሆኑ ግልጽ ከሆነ ዘንድ በዚህ የድኅነት ዘመን ከሞተ ሥጋና ሞተ ነፍስ፣ ከደዌ ሥጋና ከደዌ ነፍስ፣ ከድቀተ ኃጢአትና ከአምላካዊ ፍርድ መዳን ካልተቻለ መኖር ትርጒም የለውም፡፡ ምንተ ይበቊዖ ለሰብእ ለእመ ኵሎ ዓለመ ረብኀ ወነፍሶ ኀጐለ (ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል) ማቴ.16፥26

አሁን ለዚህ ሁሉ ሐተታ መነሻ የሆነው  በዚሁ ጽሑፍ መግቢያ ላይ የተጠቀሰው ቃለ ወንጌል ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ የዘመን መለወጫ በዓልን የምታከብረው ይህን ቃል  በማስተማር  በመተግበር ነው፡፡ ‹‹የተመረጠችው የእግዚብሔርን ዓመት እሰብክ ዘንድ ላከኝ›› የሚለው ቃል ከክርስቶስ ልደት በኋላ ያለው እያንዳንዱ ዓመት የተመረጠ የእግዚአብሔር ዓመት መሆኑን የሚያረጋግጥ ኃይለ ቃል ነው፡፡ ይህም ማለት ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም ከመጣ በኋላ ቀኑም ሆነ ሰዓቱ የድኅነት ሰዓት ሁኗል ማለት ነው፡፡

በመሆኑም አዲስ ዓመት ብዙ ነገሮችን ያስታውሰናል፡፡ በዚህ በአዲሱ ዓመት እና ባለፈው ዓመት  የሠራነውን፤ የፈጸምነውን ነገር ሁሉ እናስታውሳለን፡፡ በአዲሱ ዓመት ባለፈው ዓመት የተሠራው ሥራ ሁሉ ይገመገማል፡፡ በአለፈው ዓመት ስለተሠራው ሥራ ሪፖርት (ዘገባ) ይቀርባል፡፡ እያንዳንዱም ሠራተኛ በአለፈው ዓመት ውስጥ ስለሠራቸው ሥራዎች ሁሉ ሪፖርት (ዘገባ) ለቅርብ አለቃው ያቀርባል፡፡ ይህ የሰለጠነው ዓለም አሠራር ነው፡፡ በዚህ ዓይነት የእያንዳንዱ ሠራተኛ ሥራ በአዲሱ ዓመት ይገመገማል፡፡

ባለፈው ዓመት መልካም ሥራ ከተሠራ፣ ይህ መልካም ሥራ በሚቀጥለውም ዓመት በተሻለና በበለጠ ሁኔታ እንዲቀጥል ይደረጋል፡፡

ባለፈው ዓመት 1ኛ) ስሕተት ከተሠራ፣

2ኛ) እንዲሠራ በታቀደው መሠረት ሥራው ካልተከናወነ፣

3ኛ) ሥራው ግቡን ካልመታ በአጠቃላይ ያለፈው ዓመት ስሕተትና ያለፈው ዓመት ድክመት በሚመጣው ዓመት እንዳይደገም ትኩረት ይሰጠዋል፡፡ ባለፈው ዓመት ስሕተት ወይም ጉድለት የሠሩ ሁሉ ያ ስሕተት፣ ያድክመት፣ ያጉድለት በአዲሱ ዓመት እንዳይደገም የሚመለከታቸው ሁሉ ታላቅ ጥንቃቄ ያደርጋሉ፤ ቃልም ይገባሉ፡፡ ሠራተኞች ሁሉ፣ አለቆችም ሆኑ የበታች ሠራተኞች እንደገና በአዲሱ ዓመት መልካምና የተሻለ ሥራ ለመሥራት አዲስ የሥራ ዕቅድና አዲስ የሥራ ፕሮግራም ያወጣሉ፡፡ እንዲሁም ለሥራ ማስኬጃ፣ ለወጭ መሸፈኛ የሚሆን በጀት ይዘጋጃል፡፡ ይህ እንግዲህ በሥጋዊ ሕይወታችን፣ በሥጋዊ ሥራችን የምንፈጽመው ተግባር ነው፡፡

በመንፈሳዊ ሕይወታችንስ ምንድን ነው የምናደርገው? መጀመሪያ ባለፈው ዓመት ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ምን ሠርተናል? ምን አከናውነናል? እያንዳንዳችን ባለፈው ዓመት ስለሠጠነው መንፈሳዊ አገልግሎት ለፈጣሪያችን ወይንም ለሕሊናችን ሪፖርት (ዘገባ) ማቅረብ አለብን፡፡ ለሚመጣውም ዓመት ዕቅድ ማውጣት አለብን፡፡ ምናልባት ባለፈው ዓመት በመንፈሳዊ ሕይወታችን ተገቢ አገልግሎት አልሰጠን ይሆናል፡፡ በእግዚአብሔር ሕግና ትእዛዝ አልሄድን (አልተጓዝን) ይሆናል፡፡ ይህንን ሁሉ ገምግመንና መርምረን ያለፈውን ዓመት መጥፎ ሥራዎቻችንን ሠርተንበት ከሆነ በአዲሱ ዓመት ደግመን እንዳንሠራ መጠንቀቅና ለእግዚአብሔር ቃል መግባት አለብን፤ ጥንቃቄም ማድረግ አለብን፡፡ በአዲሱ ዓመት መልካም ሥራና የጽድቅ ሥራ እንድንሠራና እግዚአብሔርን እንድናስደስት ዕቅድ ማውጣት አለብን፡፡ ከምናገኘውም ገቢ ሁሉ ለእግዚአብሔር አሥራት ለመክፈል እና ለተቸገረውም ለመርዳት ላዘነው ለማጽናናት ዕቅድ ማውጣት አለብን፡፡ ይህንንም ለማድረግ ለአምላካችን ቃል መግባት ይኖርብናል፡፡

ዘመኑ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፤ እድፈትም፤ ለሌለበት፤ ለማያልፍም ርስት እንደምሕረቱ ብዛት የመንፈሳዊ እውነተኛውን ሃይማኖት ለመጠበቅና ለማገልገል  ለሀገርና ለሕዝብ የሚጠቅም ሥራ እንሠራበት ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡

ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ቅዱስት ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ካህናት ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ “ኃረየ ፲ወ፪ተ ሐዋርያተ ሤሞሙ ኖለተ ወወሀቦሙ ሀብታተ ይስብኩ ቃለተ ሠለስተ አስማተ አሐደ መንግሥተ (አሥራ ሁለት ሐዋርያትን መረጠ፤ ለሕዝብ ጠባቂ አድርጐ ሾማቸው፤አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ (ሦስት ስሞችን) አንድ የእግዚአብሔርን መንግሥት ዐሠርቱ ቃላትን፤ ያስተምሩ ዘንድ እግዚአብሔር አምላክ አዘዘ በማለት በገለፀው መሠረት የተጣለብንን እና የተሰጠንን ሐላፊነት በሚገባ ተወጥተን የመንግሥቱ ወራሾች እንሆን ዘንድ ቅዱስ አምላክ ይርዳን፡፡

በየመሥራያ ቤቱ ሐላፊነት የተጣለባችሁና የተሰጣችሁ ክርስቲያኖች በሙሉ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ኢትኰንኑ ከመ ኢትትኰነኑ፡፡ እስመ በኵነኔ ዘኰነንክሙ ትትኴነኑ አንትሙ፡፡ ወበመስፈርት ዘሰፈርክሙ ይሰፍሩ ለክሙ፡፡ (እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈርድባችኃልና በምትሰፍሩበትም መስፈርያ ይሰፈርባቸኃል ማቴ.7፥1 በማለት አዟልና ፍርድ እንዳይጔል ደሀ እንዳይበደል በፍትሐዊነትና በቅንነት በታማኝነትና በትህትና በእኩልነት ሕዝብ እንድታስተዳድሩ በጐ ሕሊና ብሩህ አእምሮ ቀና አመለካከቱን እግዚአብሔር አምላክ ያድላችሁ፡፡

በመማርና በማስተማር ላይ የምትገኙ ሁሉ፦ ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ፡ በዮሐንስ ድጓው ጥበብ ትይኄስ እምብዘኅ መዛግብት፣ ኢወርቅ ሤጡ፣ ወኢብሩር ተውላጡ፣ ጥበብ ክቡራት ዕንቊ መሠረታ፣ አልቦ ለጥበብ ዘይመስላ (በዚህ ዓለም ዕውቀትን የሚስተካከላት የሚወዳደራት የለም፡፡ ስለዚህ ከብዙ ሀብት ዕውቀት ትበልጣለቸ፡፡ ወርቅም፣ ብርም፣ አልማዝም፣ቢሆኑ አይስተካከሏትም፡፡ የጥበብ መሠረቷ የከበረ ነው፡፡ ጥበብን የሚመስላት የሚስተካከላት የሚያክላት የለም እያለ በገለጸውና በአስተማረው መሠረት ለምታስተምሩትና ለምትማሩትም ቁሞ ነገር ትኩረት ሰጥታችሁ ተገቢውን የምርምር ውጤት በማስገኘት ሀገራችንና ሕዝባችን በተሻለ የኑሮ ደረጃ እንዲኖር እንድታደርጉ የፈጣሪያችን ትዕዛዘ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

በግብርና ሙያ ላይ ላላችሁ ገበሬዎች “እግዚኦ ባርክ ፍሬሃ ለምድር፡፡ መሐሪ ወጻድቅ መኑ ከማከ ዘታርኁ ክረምተ በጸጋከ፡፡ ነፍስ ድኅንት ወነፍስ ርህብት እንተ ጸግበት ተአኩተከ፡፡” አቤቱ የምድርን ፍሬ ባርክ፡፡ በስጦታህ ክረምትን መልሰህ የምታመጣው ሆይ! እንደ አንተ ያለ ጻድቅና ርኅሩኅ አምላክ ማን ነው? የታመመች ሰውነት በተፈወሰች ጊዜ የተራበች ሰውነት በጠገበች ጊዜ ታመሰግንሃለች እያላችሁ አመስግኑ፡፡

የዘመነ ኦሪት መጨረሻ የዘመነ ሐዲስ መነሻ፤ ነቢይም፣ ሰማዕትም፣ ሐዋርያም በአጥማቂነቱ ካህን፤ የዓለምን ኃጢአት ይቅር የሚል ከእኔ በኋላ ይመጣል በማለቱ ነቢይ፤ ስለ ክርስቶስ ሕይወቱን በመስጠቱ ሰማዕት ከሆነው ከቅዱስ ዮሐንስ በረከት ረድኤት እግዚአብሔር አምላካችን ሁላችንም ያድለን አሜን!!

ስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘአብጽሐነ እስከ ዛቲ ዕለት፤ ከዚህ ዘመን፣ ከዚህ ዕለትና ከዚህ ሰዓት ያደረሰን ልዑል እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን፡፡

ቸሩ ፈጣሪያችን መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዘመኑን የሰላም፣ የዕድገት፣ የጤናና የብልጽግና ዘመን ያድርግልን፡፡ ለሀገራችንና ለቤተ ክርስቲያናችን እንዲሁም ለመላው ዓለም በሙሉ እውነተኛውን ሰላምና ፍቅርን ያድልልን፡፡

 

 

አባ ሳሙኤል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀጳጳስ

አዲስ አበባ

 

 

 

“መኑ ይከልአነ ፍቅሮ ለክርስቶስ„ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል?
1. መከራ ወይስ ጭንቀት፣ ወይስ ስደት፣ ወይስ ረሃብ፣ ወይስ ራቁትነት፣ ወይስ ፍርሃት፣ ወይስ ሞት ነው። ሮሜ 8፥35

2. “ኢትፍርህዎሙ ለአለ ይቅትሉ ሥጋክሙ”
“ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል
የማይቻላቸውን አትፍሩ ፣ ይልቅስ ነፍስንም
ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ„ ማቴ 10፥28
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ ስንኖርና የምንቀበለው መከራ ሁሉ ቢበዛ ከሥጋ ያለፈ እንዳልሆነ ነገር ግን በነፍሳችን ላይ ጠላታችንን አንዳች ማድረግ እንደማይችል አረጋግጦልና።
3. ቅዱስ ጴጥሮስም “ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኳን መከራን ብትቀበሉ ብፁዓን ናችሁ። ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ አትናወጡም ብሏል። 1ጴጥ. 3-14 ከዚም የተነሣ ሰማዕታት ለሥጋቸው ሳይሳሱ “እስም በእንቲ አሁ ይቅትሉነ ኩሎ አሚረ ወኮነ ከመ አባግዕ ዘይጠብሁ።„ ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፣ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን እያሉ ስለ ክርስቶስ ፍቅር እራሳቸውን ለሞት አሳልፈው ሰጥተዋል። ሮሜ 8፥35
ሐዋርያትና አብዛኛው በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩት ጳጳሳት ሊቃውንት በሰማዕትነት አልፈዋል።
በድንጋይ ተወግረው ተፈተኑ ሞቱ፣ በመጋዝ ተሰነጠቁ፣ በሰይፍ ተገድለው በሰማእትነት ሞቱ፣ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፣ ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፣ በዋሻና በምድር ጉዳጓድ ተቅበዘበዙ። እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ ዕብ.11፥37
4. ጸርሑ ጻድቃን ወእግዚአብሔር ስምዖሙ። ጢሞ. 3፥11 ጻድቃን ወደ እግዚአብሔር ለመኑ እሱም ልመናቸውን ሰማ ካገኛቸውም መከራ ሁሉ ያድናቸው ዘንድ መልአኩ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ እሳቱን አጠፋው። የሚፍለቀለቀውም ውኃ እንደ በረዶ ቀዘቀዘ። ይህንን ተአምር ከተመለከቱት ብዙዎቹ ኢ አማንያን በክርስቶስ አመኑ። ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት
5. “ይትአየነ መልአከ እግዚአብሔር አውዶሙ፤ ለእለ ይፈርህዎ„
ወያድኅኖሙ። የእግዚአብሔር መልአክ እግዚአብሔር በሚፈሩት ዙሪያ ይሰፍራል፤ ያድናቸውማል መዝ. 33፥7
6. ቅዱስ ጳውሎስም ሲገልጽው፣ “እነርሱ በእምነት ሁሉንም ድል ነሡ፣
ጽድቅን አደረጉ፣ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ የአናብስትን አፍ ዙጉ የእሳትን ኃይል አጠፉ ከሰይፍ ስልት አመለጡ ከድካማቸው በረቱ
ዕብ.11፥33 ሠለስቱ ደቂቅን፣ ቅዱስ ቂርቆስን፣ እነ ቅዱስ አግናጤዎስ ሐዋርያ ቅዱስ እስጢፋኖስ ማለት መሆኑን ግድ ይላል።
7. “እሰመ ለመላእክቲሁ ይኤዝዞሙ በእንቲአክ„
በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስላንተ ያዛቸዋልና እግርህም
በድንጋይ እንዳትሰናክል በእጆቻቸው ያነሡሃል “መዝ. 90፥1
8. “ከመ ይዕቀቡከ በኵሉ ፍናዊክ„
በመንገድ ይጠብቅህ ወዳዘጋጀሁትም ሥፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ
መልአኬን በፊትህ እሰዳለሁ በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ስሜም
በርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት። ማቴ.
4፥7
9. “ብዙኅ ሕማሞሙ ለጻድቃን። የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው„ ሐሥ13፥50
የአባቶቻቸውን ርስት አሳልፈን ለባዕድ አንሰጥም በማለት የተገደሉትን መጽሐፍ ቅዱስ ክብር ሰጥቶ መዝግቧቸዋል። እስራኤላዊው ናቡቴ 1ኛ ነገ. 20፥1-15 ስለዚህ ቅዱስት ቤተ ክርስቲያን በሰማያት ያለውን ርስት በሚያሰጥ እምነትን መስክረው መሥዋዕት ለሆኑ ተከታዮቿ የቅዱስት ቤተ ክርስቲያን ሰማእታት ናቸው።
1.0 “ወእምኵሉ ያድኅኖሙ„ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ግን ካገኛቸው
መከራ ሁሉ ያድናቸዋል። 2ቆሮ. 1፥5
በዘመነ ሰማዕታት እንደ ወርቅ በእሳት፣ በመከራ ተፈትነው በሃይማኖት ነጥረው ከወጡ ሰማዕታት አንዱ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ነው። የዚህን ሰማዕት ገድልና ታሪክ ከሌሎች ለየት አድርጎ በአስደናቂ ደረጃ ላይ የሚያስቀምጠው የዕድሜው ሁኔታ ነው። ቅዱስ ቂርቆስ የሦስት ዓመት ሕፃን ነበር። ለነገሩ እነ ቅዱስ ጊዮርጊስም ስማቸውን ከፍ ከፍ አድርጎ የሚያስተጋባው ገድላቸውና የሰማዕትነት ታሪካቸው እንደሚገልጸው ተጋድሎውን የፈጸሙት በሃያ ዓመት የወጣትነት ዕድሜአቸው ነው።
ከእነ ቅዱስ ቂርቆስ ባነስ የዕድሜ ደረጃ ባሉ ሕፃናትም የተፈጸመ ብዙ የምስክርነትና የምስጋና ታሪክ በቅዱሳት መጻሕፍት ተጽፎዋል።
11. መጥምቁ ዮሐንስ ለልዑል እግዚአብሔር አምልኮትና ስግደት ያቀረበው ገና በእናቱ ማህፀን ሳለ ነው (ሉቃ.1፥40)። እንዲሁም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ በገባ ጊዜ ዝማሬና ምስጋና ያቀረቡለት ከሁለት እስከ አምስት ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የነበሩት ሕፃናት ነበር። ሆሣእና ለወልደ ዳዊት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለመንግሥተ ሰማያት ወራሽነት ምሳሌ አድርጎ ያስተማረባቸው ሕፃናትን ነበር (መዝ. 60፥61-2 ማቴ. 19፥14) እንደ ሕፃና ካልሆናች
12. “ቅሩብ እግዚአብሔር ለየዋሃነ ልብ„ እግዚአብሔር አምላክ ቅን ልቡና እና ሃይማኖት ላላቸው ሰዎች ቅርብ ነው ልመናቸውን፣ ጸሎታቸውን፣ ስዕለታቸውን፣ ፈጥኖ ያሰማል።

ይቆየን

ከብፁዕ አቡነ ሳሙኤል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀጳጳስ
አዲስ አበባ

 

 

 

መግቢያ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሁለት ሺህ ዘመናት ያስቆጠረች ሐዋርያዊትና ጥንታዊት የሃይማሃት ተቋም ናት፡፡ በዚህም መሠረት የክርስትና እምነት እንዲስፋፋ፣ የሕዝቡን ሥነ ምግባር፣ አንድነትና ማንነት በመጠበቅ እንዲሁም ሥልጣኔን በመምራት ጉልህ ስፍራ ነበራት፡፡ ሆኖም ግን ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም ከባድ ፈተና ደርሶባታል፡፡
የቤተ ክርስቲያኒቱ ችግሮች ዘመናትን ያስቆጠሩ ቢሆኑም አሁን ካለው የዓለማችን ፈጣን የለውጥ እንቅስቃሴ አንጻር ሲታይ ችግሮቹ በጣም የተንሰራፉና የከፉ ሆነዋል፡፡ ይሁን እንጂ ለችግሮቹ መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ቤተ ክርስቲያኒቱ በበቂ ሁኔታ እየተጠናከረች ነው የሚለው አመለካከት እና መዘናጋት ችግሮች፡ ተባብሰው ቤተ ክርስቲያኒቱን ለውድቀት እየዳረጓት ይገኛሉ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ በታሪክ፣ በትውልድና በእግዚአብሔር ዘንድ ከሚያስጠይቀው ውድቀት ቤተ ክርስቲያኒቱን ማዳን፣ በመቀጠልም ተገቢውን እስትራቴጂና የማስፈጸሚያ ስልት በመንደፍ፤ የቤተ ክርስቲያኒቱን እምቅ ሀብት በመጠቀም ለሀገሪቱና ለዜጎቿ ተጨባጭ መንፈሳዊ እድገትን ማጎናጸፍና ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት አስተዋጽኦዎችን በብቃት እንድታበረክት ማድረግ ወቅቱ አበክሮ የሚጠይቀው እጅግ ወሳኝና መሠረታዊ ጉዳይ ነው፡፡
በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕልውና እየተፈታተነ ያለውን ችግር ለመፍታት ተቀዳሚው ተግባር ችግሩንና የችግሩን ምንጭ በማወቅ መለየት ነው፡፡ ስለሆነም ይህ ጽሑፍ በአሁኑ ሰዓት የሚታዩትን የቤተ ክርስቲያናችንን ዐበይት ችግሮችና መፍትሔውን በአጭሩ ይቃኛል፡፡
1. የቤተ ክርስቲያናችን የአስተዳደር ዐበይት ችግሮች
ቅዱስ ሲኖዶስ ቁልፍ ተግባራትን በማቀድ የማይመራበት፤ የወሰነውን ውሣኔ ማስፈፀም ያልቻለበትና ክትትልና ግምገማ የማድረግ ልምዱ ዝቅተኛ የሆነበት ነው፡፡
2. በቅዱስ ፓትርያርኩ ጽ/ቤት በእቅድና ፕሮግራም መሥራት ፈጽሞ የማይታወቅበት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሀብትና ንብረት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ዋና ዓላማ ማስፈጸሚያ ሳይሆን ውጤት ለሌላቸው ተግባራት የሚባክንበት፣ በሙያቸውና በችሎታቸው የተመረጡ አማካሪ ቡድኖች የሌሉበት፤ በአንጻሩ ቤተ ክርስቲያኒቱን የማያውቁ፣ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ምንም ግድ የሌላቸው ሰዎች በወሳኝነት የሚንቀሳቀሱበት ነው፡፡ በአጠቃላይ ቤተ ክርስቲያንን ስልታዊና ዘለቄታዊነት ባለው መልኩ ለመምራት የተዘጋጀ መሠረታዊ የአመራር ስልት የሌለና አካሄዱ በሙሉ በዘፈቀደ ግብታዊና ልማዳዊ የሆነበት ነው፡፡
3. የቤተ ክርስቲያኒቱ ዋነኛ ተልዕኮ የክርስቶስን ወንጌል በማስፋፋት የምዕመናንን ክርስቲያናዊ ሕይወት ማጽናትና ያላመኑትን በማሳመን ምዕመናንን ማብዛት መሆኑ እየታወቀ ይህን ተልዕኮ ለማሳካት የሚያስችል እቅድና ግብ እየተቀመጠ፤ ለዚሁ ተግባር ማስፈጸሚያ ተገቢው በጀት እየተመደበ የሚሠራበት ሁኔታ ባለመኖሩ ምዕመናን ለሌሎች ባዕድ ሃይማኖቶች ቅሰጣ ተጋልጠዋል፡፡ በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱን ተልዕኮ ማስፈጸም በእጅጉ ተዘንግቷል፡፡
4. በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የኃላፊዎች ምደባ በሞያ፣ በችሎታ ወይም በብቃት ሳይሆን በዝምድና፣ በሀገር ልጅነት፣ ለቤተ ክርስቲያኒቱ አገልግሎት ሳይሆን ለግለሰቦች ባለው ታማኝነት በመሆኑ፣ ለከፍተኛ የአመራር ችግር፤ ለሀብትና ንብረት ብክነትና ዝርፊያ፤ ለውዝግብና ለመልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት ሆኗል፡፡ በመሆኑም አብዛኛው የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ለብልሹ አመራርና አስተዳደር እንደ ጥሩ ማሳያ እየጠቀሰው ይገኛል፡፡
5. የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ለሁለት የተከፈለበት፤ በአንድነትና በሰላም ከመፈጸም ይልቅ የተከፋፈሉበት፣ ያልተረጋጉበት፣ ብሎም በሁከትና በግጭት ሰላማቸውን ያጡበት ሆኖ ይገኛል፡፡
6. የቤተ ክርስቲያናችን አጠቃላይ አወቃቀርና አደረጃጀት አሁን ካለንበት ሁኔታ፣ ከአገልግሎቱ ስፋትና ከልማትና ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎችን ጋር አብሮ የሚጓዝ ባለመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን ወቅቱን በመዋጀት ከጊዜው ጋር እንዳትራመድና ተከታዮቿን በአግባቡ እንዳትጠብቅ አድርጓታል፡፡
7. የወደፊቷ ቤተ ክርስቲያን ተረካቢዎች የሆኑ አገልጋዮችን የሚያፈሩት የአብነት ት/ቤቶችና የሰንበት ት/ቤቶች አደረጃጀት ተገቢ ትኩረት ተሰጥቶት በበቂ በጀትና ብቃት ባለው አመራር የተደራጀና የተደገፈ ባለመሆኑ ቤተ ክርስቲያኒቱን በሚረከቡ አገልጋዮች ዝግጅት ላይ ከፍተኛ ክፍተት ይታይበታል፡፡
8. የረጅም ጊዜ ግባችንንና ራዕያችንን የሚያመለክት ስትራቴጂክ ዕቅድ ባለመኖሩ አሠራሩ ሁሉ በእለት ተእለት ጉዳዮች እንዲሁም ጥቃቅንና ረብ የሌላቸው ተግባራት ላይ ብቻ በማተኮሩ ቤተ ክርስቲያኒቱን ራእይ የሌላት አስመስሏታል፡፡
9. በየዓመቱ ከሚደረገው የሥራ ፕሮግራም ጋር ተገናዝቦ የደመወዝ፣ የሥራ ማስኬጃና የካፒታል (የፕሮጀክቶች) በጀቶች የአዘገጃጀትና የአመዳደብ ሥርዓት ባለመኖሩ በተለይ የካፒታል በጀት የሚጠይቁ ፕሮጀክቶች ያለበቂ ጥናትና ዕቅድ እየተጀመሩ ለከፍተኛ የበጀት እጥረት፣ ለምዝበራና ለውዝግብ ምክንያት ሆነዋል፡፡
10. ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በቤተ ክርስቲያኒቱ ድርጅቶችና በሐዋርያዊ ተልዕኮ ስም በየደረጃው የሚሰበሰበው ሀብት ያለአግባብ ከዕቅድና ከፕሮግራም ውጭ ጥቅም ለማይሰጡ ተግባራት ይባክናል፡፡ በዚህም የተነሳ ለብዙ አብያተ ክርስቲያናት መዘጋት፣ ለካህናት መሰደድ፣ ለምዕመናን መፍለስ ምክንያት ሆኗል፡፡
11. ተጨማሪ የገቢ ምንጭ የሚያስገኙ ፕሮጀክቶች በማጥናት ተግባራዊ ለማድረግ ያለው አመለካከት እና ፍላጎት ዝቅተኛ በመሆኑ የቤተ ክርስቲያኒቱን የችግር ጊዜ መውጫ ጥሪት ከማባከን ውጪ ሌሎች አማራጭ የገቢ ምንጮችን አስፍቶ ማየት አልተቻለም፡፡ በዚህም የተነሳ በየጊዜው ለሚያጋጥመው የበጀት እጥረት ምላሽ መስጠት እጅግ ፈታኝ ሆኗል፡፡
12. ቤተ ክርስቲያኒቱ ለዘመናት ጠብቃ ያቆየቻቸው ቅርሶችና ንዋያተ ቅድሳት በከፍተኛ ሁኔታ እየተዘረፉና እየተመዘበሩ ያሉበት ወቅት ሲሆን ለችግሩም የቤተ ክርስቲያኒቱ አመራር ተገቢ ትኩረት አልሰጠውም፡፡
13. በአጠቃላይ በቤተ ክርስቲያኒቱ ማዕከላዊ የሆነ የሀብት አስተዳደር ባለመኖሩ አገልጋዮቿ ገጠሩን እየተው ገቢ ይገኝበታል በሚል ወደ ከተማ እንዲጎርፉ ምክንያት ሆኗል፡፡ ይህም በገጠር የሚገኙ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን ያለአገልጋይና ያለንዋያተ ቅድሳት በማስቀረቱ አብያተ ክርስቲያኗት እንዲዘጉ ሆነዋል፡፡
14. በደቡብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብና በመሳሰሉት የሀገሪቱ ክፍሎች ቤተ ክርስቲያን ወደ ሕዝቡ አልደረሰችባቸው ቦታዎች ትኩረት በመስጠት ልዩ የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ መርሐግብር በተጠና ሁኔታ በማካሔድ አገልግሎቱ ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ የየቦታውን ተወላጆች ከመነሻው ጀምሮ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በማስተማርና በማሰልጠን ለአገልግሎቱ ብቁ የሚያደርግ መሠረታዊ ሥራ አልተሠራም፡፡
15. ምንም እንኳን ቤተ ክርስቲያናችን ረጅም እድሜን ያስቆጠረችና እምቅ አቅም ያላት ቢሆንም በዋናነት በአስተዳደር ችግር ምክንያት በማኅበራዊ አገልግሎትና በኢኮኖሚያዊ ልማት ዘርፍ ያላት አስተዋጽዖ ከጊዜ ወደ ጊዜ በሀገሪቱ ካለው አጠቃላይ የልማት እንቅስቃሴ አንጻር እጅግ ውሱን ሆኗል፡፡
በአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያናችን አመራር ሠራተኛን፣ ገንዘብንና ንብረትን በአግባቡና ዘመኑ በሚጠይቀው የአሠራር ዘይቤ በማቀናጀት የቤተ ክርስቲያኒቱ ዋነኛ ዓላማ የሆነውን ሐዋርያዊ አገልግሎት ለማስፋፋትና ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አስተዋጽዖ ለማድረግ የሚያስችል ችሎታ ዕውቀትና ልምድ የሚጠይቅ፣ ከፍተኛ አደራና ኃላፊነት ያለባት ቢሆንም ያለው ተጨባጭ እውነታ ግን በዚህ መንገድ ኃላፊነቱን ለመወጣት እየተሠራ እንዳልሆነ የሚታይ እውነት ነው፡፡
በዚህም ምክንያት የቤተ ክርስቲያናችን መሠረታዊ ተልዕኮ የተደናቀፈበት፤ በማኅበራዊ አገልግሎትና በኢኮኖሚያዊ ልማት አስተዋጽዖ ማድረግ ይቅርና የራሷን አገልጋዮች በአመዛኙ ከችግር ማላቀቅ ያልቻለችበት ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ ይህም ቤተ ክርስቲያናችን በምዕመናን፣ በመንግሥትና በተለያዩ አካላት ያላትን አመኔታና ከበሬታ እያሳጣት ይገኛል፡፡
በመሆኑም በአደጋ ላይ ያለውን አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን ሕልውና ወደ መልካም ሁኔታ ለመመለስ ቤተ ክርስቲያናችን ውስጧን በአስቸኳይ በመፈተሽ ተገቢውን ወቅታዊ የማስተካከያ ሥራ በመሥራት ዘለቄታ ያለው መፍትሔ ለመስጠት መሠረታዊ የሆነ አስተዳደሩን የማስተካከል ውሣኔ በመስጠት በአስቸኳይ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል፡፡
ይህንን ውሣኔ ተግባራዊ በማድረግና እምቅ ሀብቷን በመጠቀም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነቷንና ሥርዓቷን፣ ታሪኳንና ቅርሷን መጠበቅና ማስጠበቅ ግዴታ አለብን።
2. ጠቅላይ ጽ/ቤቱን በተመለከተ
ቤተ ክርስቲያኒቱ የቤተ ክህነቱን ጠቅላይ ጽ/ቤት ያደራጀችበት ራሱን የቻለ መዋቅር ቢኖርም መዋቅሩን ሊያሠራ የሚችል እና ቤተ ክርስቲያኒቱንም የሚጠበቅባትን ተልዕኮ ለመወጣት የሚያስችል የሰው ኃይል አሰላለፍ እና አሠራር የውለም፡፡
1. በጠቅላይ ጽ/ቤት ደረጃ አብዛኛው የሰው ኃይል፣ ሙያን እና ችሎታን መሠረት ያደረገ ሳይሆን በዝምድና ወይም በቅርበት የተደረገ ምደባ ነው፡፡ ይህም የጠቅላይ ጽ/ቤቱ መምሪያዎች ስም ብቻ ተሸክመው ከዓመት ዓመት ከመሸጋገር ውጭ ስያሜያቸውን የሚገልጽም ይሁን የሥራ ዝርዝራቸውን በተግባር እንዳይተገብሩ ደካማ አድርጎ አስቀምጧቸዋል፡፡
2. የተማሩና ቤተ ክርስቲያኒቱን ከጊዜው ጋር እንድትራመድ ሊያግዙ የሚችሉ ባለሙያዎች አለማሳተፍና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማገልገል ገፍተው ሲመጡ በተለያዩ መንገዶች አማሮ ማባረር ደግሞ ሌላው በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ላይ የሚታይ ችግር ነው፡፡
3. መምሪያዎች በየዓመቱ የቤተ ክርስቲያኒቱን ዕድገት እና ጉድለት ለመገምገም የሚያስችል በዕቅድ እና ሪፖርት ላይ ያተኮረ አሠራር ስለሌላቸው ሥራቸው ሁሉ በልማድና በግብታዊነት ላይ የተመሠረቱ መሆናቸው የቤተ ክርስቲያኒቱን አገልግሎት ከማዳከሙ በተጨማሪ የወደፊት ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ ለመተለም አስቸጋሪ አድርጎታል፣
4. በስብከተ ወንጌል ተልዕኮ ክርስትናን ያላወቀውን ሕዝብ ቀርቶ የተጠመቀውን ሕዝብ እንኳን በወንጌል ኮትኩቶ ማሳደግ የሚችል ተግባር አለመኖሩ ቤተ ክርስቲያኒቱን የወላድ መካን እያደረጋት ያለ ጉዳይ ነው፣
5. በማዕከል ደረጃ የሚዘጋጁ በሕዝቡ ዘንድ ሰፊ ተቀባይነት ያላቸው ወቅታዊ መረጃዎችን የሚያቀርቡ እና የምዕመናንን ጥያቄዎች የሚመልሱ ጠንካራ ሚዲያዎች አለመኖራቸው ምዕመናን ቤተ ክርስቲያናቸውን በሚገባ እንዳያውቋት ሆነዋ፣
6. ቤተ ክርስቲያኒቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የማኅበራዊ አገልግሎት ተቋም በማቋቋም መሪ ብትሆንም የከፈተቻቸው ተቋማት በበቂ የማስፋፋት ሥራ አልተሠራባቸውም፡፡ እንደ ተከታዮቿ ብዛት እና በሀገሪቱ እንዳለ ድህነት ማኅበራዊ አገልግሎት በመስጠት ረገድ መሪ ፊት አውራሪ መሆን የሚገባት የኛ ቤተ ክርስቲያን ነበረች፡፡ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያኒቱ ያሏት ከጣት ቁጥር ያነሱ ተቋማት እንኳን የሚሰጡት አገልግሎት በራሱ የማያረካና አሠራሩም ብዙ ሳንካ ያለበት ነው፡፡
7. የገጠር አብያተ ክርስቲያናት በሰፊው ለችግር መጋለጣቸው በየመንገዱ ሥዕል እና ጃንጥላ ዘርግተው ሳንቲም የሚለምኑ ካህናትን አብዝቶአል፡፡ በዚህም ከለላ በርካታ ሕገወጦች ተግባሩን ገንዘብ እንደመሰብሰቢያ መንገድ እየተጠቀሙበት በመሆኑ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ከቁጥጥር ውጭ ከሆነ የማታለል ወንጀል እየተስፋፋ ይገኛል፡፡
8. ወጥ የሆነ የገንዘብ አስተዳደር አለመኖሩ የደመወዝ ክፍያ እንደ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑ አቅም እንዲወሰን አድርጎታል፡፡ ከዚህም የተነሳ በከተማ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት አንጻራዊ ገቢ ከፍተኛ ስለሆነ ድሀ በሆኑ አበብያተ ክርስቲያናት የሚኖሩ አገልጋዮች ገጠሩን እየተው ወደ ከተማ እንዲጎርፉ ምክንያት ሆኗል፡፡ ይህም የገጠሪቱን ቤተ ክርስቲያን በከፍተኛ ሁኔታ እያራቆታት ብሎም አገልጋዮቿ ለፍልሰት ዳርጓል፡፡
9. በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ባሉ መምሪያዎች በተለይም በሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ አስተባባሪነት በየጊዜው ጉባኤዎች ይካሄዳሉ፡፡ በጉባኤዎቹም ላይ ተግባራዊነታቸውን ለማየት የሚያጓጉ መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አንድምታ ያላቸው በርካታ ጠቃሚ ውሣኔዎች ይተላለፋሉ፡፡ ሆኖም ውሣኔዎቹ ከወረቀት ባለፈ ተግባራዊ ሲደረጉ አይታይም፡፡
በአጠቃላይ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለቀጣዩ ትውልድ ለማሸጋገር ከተለያዩ ፈተናዎችና ጥገኝነት ነጻ በማድረግ በገቢዋ ረገድ ራሷን ማስቻል ያስፈልጋል፡፡ አባቶችም ባለባቸው ኋላፊነት መጠን ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመምራትና ለማስተዳደር ይቸገራሉ፡፡ ስለዚህ አሁነ ያለውን በችግር የተተበተበ አስተዳደር፣ የዘፈቀደ አሠራር እንዲሁም አንድ በአንድ ችግሮችን በመፈተሽ ለማስተካከል ወቅቱ የሚጠይቀውን መፍትሔ ለማምጣት ጊዜው አሁን ነው፡፡
የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን ለመምራት ልዑል እግዚአብሔር ኃላፊነቱን በእኛ በአባቶች ትከሻ ላይ አስቀምጧል፡፡ ስለዚህ ትውፊቷንና ሃይማኖቷን በጠበቀ መልኩ በአስተዳደሯ ላይ መሠረታዊ የአሠራር ሒደት ለውጥ ለማድረግ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለተሻለ ተልዕኮ ማብቃት እግዚአብሔርና ሕዝበ ክርስቲያኑ ከእኛ የሚጠብቁት አስቸኳይ ተግባር ነው፡፡
ችግሩን ለመፍታት በቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ውስጥ ያሉ አካላት ሁሉ የበኩላቸው ሚና ቢኖራቸውም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከፍተኛውን ድርሻ መውሰድ ይጠበቅበታል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ የቤተ ክርስቲያኒቱ የመጨረሻ ወሳኝ አካል ሆኖ ሳለ ይህ ሁሉ ችግር በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ያለማቋረጥ እንደ ሐምሌ በረዶ ሲወርድባት በቂ የሆነ ትኩረት በመስጠት ተግባራዊ የመፍትሔ እርምጃ አልወሰደም፡፡ አልፎ አልፎ ለችግሮቹ መፍትሔ ሊያመጡ የሚችሉ አንዳንድ ጠቃሚ ውሣኔዎችን በተለያዩ ጊዜያት ቢያስተላልፍም የተላለፉ ውሣኔዎችን ተግባራዊነት ተከታትሎ ማስፈጸም አልቻለም፡፡ በዚህም ቤተ ክርስቲያኒቱ ያለምንም ማቋረጥ በችግር ቀጠና ውስጥ እንድትጓዝ ምክንያት ሆኗል፡፡ ስለሆነም የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ሁሉ በአንድ መንፈስ ሆነው ቤተ ክርስቲያኒቱን ከወደቀችበት አዘቅት ለማውጣት ጠንክረው ኃላፊነታቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡
በተለይም ችግሩ ጣሪያ በነካበት በዚህ ወሳኝ ጊዜ ቅዱስ ሲኖዶስ ነገሮችን በቸልታ መመልከቱን ትቶ አስቸኳይ የመፍትሔ እርምጃ መውሰድ ይጠበቅበታል፡፡ ይህን ለውጥና መልካም አስተዳደር ለማምጣት ጉዳዩን በጸሎት ከማሰብ ጋር በትኩረት መከታተል መሥራት ያስፈልጋል፡፡
የአጭር እና መካከለኛ ጊዜ የመፍትሔ ሐሳቦች
ቤተ ክርስቲያኒቱ አሁን ባለችበት የአስተዳደር ሁኔታ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ከፍተኛውን የተጠያቂነት እና ኃላፊነት ድርሻ ይወስዳሉ፡፡ አሁን በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የወደቀው ሸክም የተወሳሰበ እና ጠንካራ አመራር የሚያስፈልገው ነው፡፡ ሆኖም የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አውቀውም ይሁን ሳያውቁ በተፈጠረ ክፍተት ምክንያት ችግሮቹን መፍታት ስላልቻሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ ወርቃማ የሥራ ጊዜ እያመለጣት ነው፡፡ ጉዞዋም ወደ ኋላ ሆኖአል፡፡ አንገብጋቢ እና ፋታ የማይሰጡ ችግሮች በአደባባይ የተገለጡ ሆነው ሳለ ትኩረት እየተሰጣቸው ያሉት ጊዜያዊ በሆኑ መሠረታዊ ችግር የማይፈቱ በግርግር የታጀቡ ተግባሮች ናቸው፡፡ እንዲሁም እንደ ከፍተኛ የቤተ ክርስቲያኒቱ አስፈጻሚ አካል የቤተ ክህነቱ ጠቅላይ ጽ/ቤት በተለያዩ ምክንያቶች ውጤታማ አልሆነም፡፡ ይህንንም ግልጽ የሚያደርጉ መገለጫዎችን ቀደም ሲል አይተናል፡፡ ይህም የሚያሳየው ቤተ ክርስቲያኒቱ ስትሪቴጂያዊ ፖሊሲና ስልት እየተከተለች መሥራት እንዳልቻለች ነው፡፡ ስለሆነም ይህን የችግር ጅረት ገድቦ ለማቆም ብሎም ቤተ ክርስቲያኒቱ የምትፈልገውንና የሚጠበቅባትን አገልግሎት ለማበርከት እንድንችል ቀጥሎ ያሉት የመፍትሔ ሀሳቦች ተገቢ ናቸው ብዩ እናምናለን፡፡
የአጭር ጊዜ አስተዳደራዊ መፍትሔዎች
እነዚህ ተግባራት በከፍተኛ ርብርብ ወጥና ሁሉን አቀፍ በሆነ መልኩ ተግባር ላይ ሊውሉ የሚገባቸው ተግባራት ናቸው፡፡ የእነዚህን ተግባራት ዋና ዓላማና ግብ የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. የቅዱስ ሲኖዶስን ሥልጣንና ኃላፊነት ሕገ ቤተ ክርስቲያን በሚያዘው መሠረት ተፈጻሚ ማድረግ፣
2. ስለዚህም ቅዱስ ሲኖዶስ አስተዳደሩንና አሠራሩን አሻሽሎ አመራር በመስጠት በኩል መሠረታዊ ለውጥ የሚያመጣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን በጠበቀ መንገድ ቤተ ክርስቲያኒቱን ከችግር ቀጠና ማውጣት ወቅቱ የሚጠይቀው ተልእኮ ነው፡፡
3. ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና በአህጉረ ስብከቶች ያሉ አካላት ቤተ ክርስቲያኒቱ ያለችበትን ትክክለኛ ስዕልት ማየት እንዲችሉ ማድረግና የሀሳብ ልውውጥና ምክክር አድርገው ሊሠሩ ስለሚገባቸው ሥራዎች ተወያይተው አቅጣጫ እንዲተልሙና በቀጥታ ወደ ሥራ የሚገቡበትን መንገድ በመቀየስ ወደ ሥራ እንዲገቡ ማድረግ፣
4. በየአጥቢያው ላሉ ካህናት አንደኛ ወቅታዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ፤ ሁለተኛ እስከዛሬ በመደበኛ ሁኔታ እንደትምህርት የማይሰጡ የሕግ፣ የአስተዳደር እና ማኅበራዊ ጉዳዮችን፣ በሦስተኛ ደረጃ ደግሞ በአጠቃላይ ሊሠሩና ሊደረጉ ስለሚገባቸው ስልታዊና ዘለቄታዊ ሥራዎች ተከታታይና ጥልቀት ያላቸው ሥልጠናዎችን መስጠት፣
5. በቤተ ክርስቲያኒቱ አስፈላጊውን መሠረታዊ የአሠራር ሂደት ለውጥ በማድረግ የአስተዳደር ብቃት ያላቸውና የተማሩ ኃላፊዎችን፣ ሥራና ሠራተኞች ለማገናኘት በየዘርፉ መመደብ፣
6. በዘመድና በሙስና የሚፈጸሙ ቅጥሮችንና የተለየዩ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ሕገ ቤተ ክርስቲያን በሚያዘው መሠረት ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ በየደረጃው ተፈጻሚ እንዲሆኑ ማድረግ፣
7. በቅዱስ ሲኖዶስ የሚያዙ አጀንዳዎችና ውሣኔዎች ላይ ሁሉም ሊቃነ ጳጳሳት እኩል ሥልጣን እንዲኖራቸው እና የውሣኔዎቹን ተግባራዊነት የሚከታተሉበትን የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት፣
8. የሕትመት ውጤቶቹ ለምእመናን ተገቢውን ትምህርት የሚያስተላልፉና ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱ አስፈላጊውን መረጃ የሚሰጡ እንዲሆኑ በመንበረ ፓትርያርኩ ጠቅላይ ጽ/ቤት አስተዳደር ሥር ማደራጀት፤ እንዲሁም የተጠናከረ የኦዲቶሪያል ሂደቶችን እንዲያልፉ ማድረግ፡፡
9. የንብረት፣ የቤትና የገንዘብ አስተዳደር ሂደቱ በሕገ ቤተ ክርስቲያን እንዲከናወን ማስቻል፣
10. ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ቤተ ክርስቲያኒቱን ማዕከል ያላደረገ አስተዳደር እንዳይኖር አደረጃጀቱን ማስተካከል፡፡
4. በአጭር ጊዜ መተግበር ያለባቸው ሐዋርያዊ አገልግሎትን የሚያጠናክሩ መፍትሔዎች
1. የራሳቸውን እምነት ከማስተማር ይልቅ የቤተ ክርስቲያኒቱን ስም በማጥፋትና በማጥላላት በፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ላይ የተሰማሩትን ወገኖች ስህተታቸውና ማንነት ታቸውን በመግለጥና በማሳወቅ ምእመናን በሃይማኖታቸው ልበሙሉነት እንዲሰማቸው ማስቻል፣
2. ቤተ ክርስቲያኒቱ እያንዳንዱ ምእመን ዘንድ የሚደርስ መዋቅር ያላት በመሆኑ ካህናት ይህንን መልካም ሁኔታ በመጠቀም የንስሐ ልጆቻቸውን ተግተውና ነቅተው እንዲያስተምሩና እንዲጠብቁ ኃላፊነታቸውን ማሳሰብና ይህንን ለማድረግ እንዲችሉ አቅማቸውን ማሳደግና ማገዝ፣ ለዚህም መጠነ ሰፊ የሆነ የካህናት ሥልጠናዎች በየሀገረ ስብከቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ በተተለመና ስልታዊ በሆነ መንገድ በማዘጋጀት ስልጠና መስጠት፡፡
3. መሠረታዊ የሆኑ የቤተ ክርስቲያን ትምህርቶችንና በየጊዜው የሚነሱ ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ለእያንዳንዱ ምእመን ዘንድ ሊደርስ በሚችል መልኩ በራሪ ጽሑፎችን ማዘጋጀትና ማሰራጨት፣
4. የበራሪ ጽሑፎች ዝግጅትና ስርጭት ማዕከል (Tract Centre) በማቋቋም፣ የሚዘጋጁ ጽሑፎችም እያንዳንዱ ምእመን እጅ እንዲደርሱ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት፣
5. የቤተ ክርስቲያኒቱን ትምህርት ከጽሑፍ በተጨማሪ በተለያዩ መንገዶች በተለይም በEOTC TV ፕሮግራም በምስልና በድምፅ ለማሰራጨት እንዲቻል ይህንኑ ለመፈጸም የሚያስችል ከዝግጅቱ እስከ ስርጭቱ ያለውን ሥራ የሚሠራና ኃላፊነቱን የሚወስድ አንድ ማዕከል ወይም ክፍል ማቋቋም፣
6. በዚህ ላይ አስቀድሞ የአሰልጣኞች ሥልጠና መስጠትና ከዚህም ቀጥሎ በየአጥቢያው ላሉ ካህናት የመሠረታዊ ትምህርት ኮርስ መስጠት፣ እነዚህ ካህናትም ልጆቻቸውን የማስተማርና የመጠበቅ ተግባራቸውን በተጠናከረና ጥበባዊ በሆነ መንገድ በርትተው እንዲፈጽሙ ማድረግ፣
7. በየሀገረ ስብከቱ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ድረስ ምእመናን ሃይማኖታቸውን በሚገባ ማወቅ የሚያስችላቸው መሠረታዊ ትምህርቶችን የሚማሩባቸው ተከታታይነት ያላቸው የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብሮችን ማካሄድ፣
8. በቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ ላይ ተጽዕኖዎችና ፈተናዎች የበለጠም ጠንከር ያሉባቸውን ቦታዎች ለይቶ በማወቅ በእነዚህ ቦታዎች ላይ ሰፊና ተከታታይነት ያለው ጠንካራ ሐዋርያዊ ጉዞ ማድረግ፣ በቦታው ላይ በቋንቋቸው ሰባክያነ ወንጌል እንዲኖሩ የሥልጠናና ሌሎች ድጋፎችን ማድረግ፣
9. ከጠረፋማ ቦታዎችና የአካባቢው ነዋሪ ሕዝብ በአካባቢ ቋንቋ የሚሰብኩ መምህራን በጣም ጥቂት በሆኑበት ወይም በሌሉበት ቦታዎች መጠነኛ መነሻ ዕውቀት ያላቸውንና ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል ፈቃደኛ የሆኑትን አሰባስቦ በአዲስ አበባ ወይም በሚያመች አቅራቢያ ለተወሰኑ ወራት ያህል ጥሩ መረዳት ሊፈጥርላቸውና ለማስተማር የሚያስችላቸውን ትምህርት መስጠት፣
10. ለገዳማት አባቶች ግንዛቤ በማስጨበጥና በማወያየት በየአካባቢያቸው ያሉ ምእመናን በማስተማርና በመጠበቅ ቀጥተኛ ተሳታፊዎች እንዲሆኑ ማድረግ፡፡
5. የመካከለኛ ጊዜ ተግባራት
እነዚህ ተግባራት በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት (ከ2011 እስከ 2014 ዓ.ም) ድረስ የሚፈጸሙ ተግባራት ናቸው፡፡ የእነዚህ ተግባራት ዓላማዎች (ግቦች) የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. ምእመናን እምነታቸውን በሚገባ ከማወቃቸው በተጨማሪ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ ሙሉ ተሳትፎ ያላቸው እንዲሁም ለሌሎች መዳን የሚያስቡና የሚሠሩ እንዲሆኑ ማድረግ፡፡
2. ካህናት ራሳቸውን በዕውቀት ያበለጸጉ፣ በዘመኑ ካለው ሁኔታ አንጻር ምእመናንን እንዴት መጠበቅና መምራት እንዳለባቸው የሚያውቁና በተግባር የሚያውሉ እንዲሆኑ ማድረግ፣
3. ቤተ ክርስቲያን በዘለቄታዊነት ልትደርስባቸው ወደሚገቡ ግቦች ለመጓዝ ልጆቿ በተቀናጀ ሁኔታ የሚሠሩበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣
4. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በኢኮኖሚያዊ ልማት በኩል ጠንካራ መሠረት ያላቸው አሠራሮችና ተቋማት እንዲኖሯት ማስቻል፡፡ እነዚህን ግቦች ከዳር ለማድረስ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የመፈጸሚያ ስልቶች (ተግባራት) ማከናወን አስፈላጊ ነው፡፡
6. ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎትን በተመለከተ
1. የአብነት ት/ቤቶችን ሥርዓተ ትምህርት ለቤተ ክርስቲያኒቷ ስብከተወንጌል መሠረታዊ በቁዔት ያላቸውን ሰዎች ሊያፈራ በሚችል መልኩ መቅረጽና ተግባራዊ ማድረግ፣
2. የዕጩ ካህናት፣ የካህናትና የሰባክያነ ወንጌል ማሰልጠኛዎችን በየአህጉረ ስብከቱ በአግባቡ በማደራጀት አሁን ላሉትም ሆነ ወደፊት ለሚመጡት አገልጋዮች መሠረታዊና ጠንከር ያለ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት እንዲሰጥ ማድረግ፣
3. በሰንበት ትምህርት ቤቶች የሚሰጡ ትምህርቶች ወጥና ተከታታይነት ያላቸው እንዲሆኑ ሥርዓተ ትምህርት በመቅረጽ፣ የማስተማርያ መጻሕፍትን በማዘጋጀት ተግባራዊ ማድረግ፣
4. በየዓመቱ ባሉት የሁለት የክረምት ወራት የሰንበት ትምህርት ቤት መምህራን ሆነው ሊያገለግሉ ለሚችሉ መሠረታዊና ደረጃውን የጠበቀ ትምህርትና ሥልጠና በማዕከል መስጠት፣
5. ምእመናንን በሀገሪቱ የምጣኔ ሀብታዊና ማኅበራዊ እንቅስቃሴ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉና ለዚህም እርስበራሳቸው የመደጋገፍና የመረዳዳትን ባህል እንዲያዳበሩ ማስገንዘብና ማበረታታት፣ ይህም ለቤተ ክርስቲያንም ጠቃሚና አንድ የአገልግሎት ዘርፍ መሆኑን ማመልከት፣
6. በሀገራችን ቤተ ክርስቲያናችን ሕዝቡን ወዳልደረሰችባቸው ልዩ ትኩረት በመስጠት ልዩ የስብከተ ወንጌልና የሐዋርያዊ ተልዕኮ አገልግሎት በተጠና ሁኔታ በማካሄድ ይህም ቀጣይነት እንዲኖረው የየቦታውን ተወላጆች ከመነሻው ጀምሮ ማስተማርና ማሰልጠን፣
7. ቢያንስ በከተማ ያሉ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት በንግሥ ቀናትና በመሳሰሉት በዓላት ጥላ እያዞሩ መለመንን ሙሉ በሙሉ እንዲቀር ማድረግ፣
8. በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሊኖር የሚገባውን የአገልጋይ ብዛትና ዓይነት በጥናት ላይ ተመስርቶ ወጥ በሆነ ሁኔታ በመወሰን መገደብ፣
9. የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር በዓመት ቢያንስ ሁለት ጊዜ ወደ ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ኮንጎ እና ደቡብ ሱዳን በማድረግ ሕዝቡን ማስተማርና ማጥመቅ፣
10. በካሪቢያን አካባቢ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን ወገኖችን ቢያንስ አንድ ጊዜ በተቀናጀ መርሐ ግብር መጠየቅ፣
11. በአጠቃላይ በሕዝቡ ክርስቲያናዊ የሕይወት ጉዞ ላይ ሊገጥሙ የሚችሉ ቀኖናዊ ጉዳዮችን አስቀድሞ በመለየት አግባብነት ባለው አንድነትን በሚጠብቅ መንገድ መፍትሔ መስጠትና ሕዝቡ የክርስቶስ የማዳን ጥሪ ለሚሰጠው አወንታዊ ምላሽ እንቅፋት እንዳይገጥመውና ሸክም ከብዶት እንዳይቸገር መርዳት ናቸው፡፡

7. የገንዘብ አስተዳደር እና ኢኮኖሚያዊ ልማትን በተመለከተ
ቤተ ክርስቲያኒቱ በገንዘብ አስተዳደር ከመቸውም ጊዜ በከፋ መልኩ የገንዘብ ብክነት ውስጥ ትገኛለች፡፡ ይኸም የሆነበት ምክንያት በዋናነት ቤተ ክርስቲያኒቱ በእቅድና በህግ የማትመራ መሆኑን ያሳያል በዕቅድና በጥናት ያልተመሠረተ ከፍተኛ ምዝበራዎች እየተፈጸሙ ነው። የቤተ ክርስቲያኒቱ ገንዘብ ብቻ ሳይሆን አስተዳደሯም በቤተ ዘመዳዊ በአካባቢ በጥቅም ስለለትን በመዘርጋት በሚፈጸም አድሎ ለሙስና መጋለጡ እንዲሁም ተጨማሪ የገቢ ምንጭ የሚያስገኙ ፕሮጀክቶች ላይ ያለው ፍላጎት ደካማ በመሆኑ እና ሁል ጊዜም የሚጠበቀው ከታወቁት (ቋሚ ከሆኑት) የገቢ ምንጮች ብቻ በመሆኑ ነው፡፡
ከላይ በተገለጹት ምክንያቶች ዛሬ ቤተ ክርስቲያኒቱ ለከፍተኛ የገንዘብ ችግር በመጋለጡዋ በተለያዩ ጊዜያት በስጦታና በስዕለት የገቡ ወርቆች እየተሸጡ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ መፍትሔ ሳይሰጠው ከቀጠለ የቤተ ክርስቲያኒቱ መሬት ሕንጻዎች ንብረቶች መሸጣቸው አይቀሬ ነው፡፡ በመሆኑም ይህ በዚህ እንዲያበቃ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን የኢኮኖሚ አቅም ለማሳደግ፤ ብሎም በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ በመሳተፍ ለሀገሪቱ ልማት አስተዋጽኦ እንዲኖራት የሚከተሉት መፍትሔዎች በአስቸኳይ መወሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
ሀ. የንዋያተ ቅድሳት ኢንዱስትሪ
ቤተ ክርስቲያ የምትገለገልባቸው ንዋያተ ቅድሳት ማምረቻ ፋብሪካ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ መክፈት አስፈላጊ ነው፡፡ በዚህም ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ ልብሰ ተክህኖ፣ ጧፍ፣ ሻማ፣ እጣን፣ ወይን (ዘቢብ)፣ መስቀሎች (አርዌ፣ ብርት፣ ጽንሐ) እና ሌሎች ንዋያተ ቅድሳት እንዲመራት ማድረግ ይህም ቤተ ክርስቲያኒቱ የራሱዋን አስተምህሮ የሚያስረዱና ትውፊትዋን የጠበቁ ንዋያተ ቅድሳትን ማምረት ከማስቻሉም በላይ ለኢኮኖሚያዊ ዕድገትዋ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያደርጋል፡፡
ለ. ማተሚያ ቤት
ቤተ ክርስቲያኒቱ በሕትመቱ ኢንዱስትሪ ተሳትፎዋ በዕድሜ ቀዳሚ ብትሆንም ኢንዱስትሪውን አሳድጋ እና አስፋፍታ ጊዜያችን የሚጠይቀው ደረጃ ላይ ማድረስ አልቻለችም፡፡ ስለሆነም በዘመናዊ መልኩ የተቀናጀና በባለሙያ የሚመራ ማተሚያ ቤት ቢኖራት በዚህም ውስጥ ጋዜጦችን፣ መጻሕፍትን፣ የተለያዩ ሰነዶችን፣ የተለያዩ ፖስተሮችን፣ ወዘተ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ብቻ ሳይሆን ከሌላውም ጋር ተወዳድሮ ማሸነፍ የሚያስችል በጥራት የሚያትም እንዲሆንና ገቢ ሊያስገባ እንዲችል ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህም በቤተ ክርስቲያኒቱ በኩል የሚታተሙ ሕትመቶችን በፍጥነት እና በጥራት ማተም ከማስቻሉም በላይ በሀገሪቱ ያለውን የማተሚያ ቤት እጥረት በማቃለል በኩል ቤተ ክርስቲያን የበኩልዋን እንድትወጣ ያደርጋታል፡፡
ሐ. ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት
ዛሬ በሰለጠነው ዓለም ላሉ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች መሠረታቸው የሃይማኖት ተቋማት ናቸው፡፡ በኛ ሀገር ግን በዚህ በኩል የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዋጽዖ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ ሆኖም አሁንም ቢሆን ከተሠራ በቂ ጊዜ እና ሀብት አለ፡፡ ስለሆነም በነገረ እግዚአብሐር፣ በቀለምና በቴክኒክ ሙያ ሚያሰለጥኑ በተመጣጣኝ ክፍያ አገልግሎት የሚሰጡ ደረጃቸውን የጠበቁ ኮሌጆችን በመክፈት በሥነ ምግባርና በሙያ የታነጹ ዜጎችን ማፍራት ከቤተ ክርስቲያኒቱ የሚጠበቅ ወቅታዊ ጉዳይ ነው፡፡ ይህም መንፈሳዊና ማኅበራዊ ኃላፊነቷን እንድትወጣ የሚያደርጋት ተግባር ነው፡፡ በሁሉም አህጉረ ስብከት ያሉ አድባራትና ገዳማትን እንደ ቦታው ሁኔታና ኢኮኖሚ በማጥናት የአደኛ ደረጃ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መሥራት ግድ ይላል በአለንበት ክፍል ዘመን ትውልዱን የምናገኝበትና የምንቀርጽበት ብቻ አማራጭ ነው።
መ. የጤና ተቋማት
በጤናው ረገድ ከከፍተኛ ሪፈራል ሆስፒታሎች እስከ ክሊኒክ በመክፈት ኅብረተሰቡን ከማገልገል በተጨማሪ ከፍተኛ ገቢ ማግኘት ይቻላል፡፡ በተያዥነትም የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮችና አቅም የሌላቸውም በነጻ ሕክምና እንዲያገኙ ያስችላል፡፡

ሠ. የሕትመት ውጤቶች
ቤተ ክርስቲያኒቱ የራሷን ፍልስፍናና የሊቃውንቶቿ ውጤት የሆኑ ትምህርቶቿን በማሳተም ከፍተኛ ገቢ የሚያገኙ ግለሰቦች ከቁጥር በላይ ናቸው፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ቤተ ክርስቲያኒቱ በዘረፈ በኪሣራ እየተንቀሰች ትገኛለች፡፡ በቤተ ክርስቲያኒቱ አንድ አሳታሚ ድርጅት ቢኖርም በሚፈለገው መጠንና ጥራት ማሳተም ባለመቻሉ ለሊቃውንትና የምእመናንን ፍላጎት ማርካት አልቻለም፡፡ የሕትመት ሚዲያዎቹም ቢሆኑ ማስተማሪያ ሳይሆኑ መሳደቢያና የግለ ሰዎችን ዝና ብቻ የሚያወሩ በመሆናቸው በአንባቢውና በኅትመት ዓለም ተቀባይነታቸው ዝቅተኛ ሆኗል፡፡ በገበያም አይፈለጉም፡፡ ይህም የሆነው የተቀላጠፈና ማዕከላዊነቱን የጠበቀ አፈጻጸም ባለመኖሩ ነው፡፡ ስለዚህ አደረጃጀቱንና አሠራሩን አስተካክሎ የተለያዩ የሕትመት ውጤቶችን በጥንቃቄ ለሕጻናት፣ ለወጣቶች፣ ለአረጋውያን በተለያዩ ቋንቋዎች ወቅቱን በጠበቀ መልኩ ቢታተሙ የስብከተ ወንጌል አድማስ ይሰፋል፡፡ በተጨማሪም የቤተ ክርስቲያኒቱን ገቢ በከፍተኛ መጠን ማሳደግ ይቻላል፡፡
ረ. ግብርና እና መሬት አስተዳደር
የሀገራችን የገቢ ምንጭ በከፍተኛ ደረጃ የተመሠረተው በግብርና ነው፡፡ ይኸውም 85 በመቶ የሚሆነው ሕዝባችን የሚተዳደርው በግብርና ስለሆነ ነው፡፡ በተለይም በአሁኑ ወቅት እየታየ ያለውን በግብርና ላይ የተመሠረተ መጠነ ሰፊ የልማት ዘመቻ ሥራ ለማጠናከር ቤተ ክርስቲያኒቱ በየአህጉረ ስብከቱ ባሏት መሬቶች ላይ ወይም ለዚሁ ሥራ መሬት በመቀበል የግብርና ሥራ መሥራት አለባት፡፡ የግብርና ምርት ሽያጩንም ለሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ በገበያ ላይ ማቅረብ ይጠበቅባታል፡፡ ይህም የካህናቷን ገቢ ማሳደግና ለሀገሪቱ ትርጉም ያለው የልማት አስተዋጽዖ ከማበርከተ አንጻር ትክክለኛ አቅጣጫን መንደፍ ያስችላታል፡፡

ሰ. የቤቶች አስተዳደር
ቤተ ክርስቲያናችን ከቁጥር በላይ የሆኑ የኪራይ ቤቶች አሏት፡፡ ነገር ግን ቤቶቹ በብልሹ አሠራር የተነሳ የተፈለገውን ያህል ገቢ እያስገኙ አይደለም፡፡ እንዲሁም ሆኖ የሚሰበሰበው ገቢ ዝቅተኛ አይደለም፡፡ ይህን የበለጠ ለማጠናከር፡-
1. ወቅቱን ያማከለ የኪራይ አከፋፈል እንዲኖረው በማድረግ ገቢውን ማሳደግ፣
2. አዳዲስ ቤቶችን ባሉን የከተማ መሬቶች ላይ እንደየቦታዎቹ አቀማመጥና ሁኔታ የተለያዩ ሕንጻዎችን በማስገንባት ማከራየትና በሪል እስቴት ኢንዱስትሪ ተሳታፊ መሆን አስፈላጊ ነው፡፡
ሸ. ቱሪዝም
ቤተ ክርስቲያኒቱ የዘረፋ ብዙ ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ባለሀብት ስትሆን በዘርፉ ያላት ጥቅም ዝቅተኛ ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ ዘርፍ አስጎብኚ ተቋማት በመክፈት እና በማስጎብኘት ከፍተኛ ገቢ ማግኘት ይቻላል፡፡ እንዲሁም በቱሪዝም ቦታዎች ላይ ለጎብኚዎች አስፈላጊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን በመክፈት በሀገሪቱ ቱሪዝም ኢንዱስትሪ ከፍተኛ አወንታዊ ሚና መጫወት አላስፈላጊ ነው፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ የቱሪስት መስህቦች በአብዛኛው በቤተ ክርስቲያኒቱ ስር እንደመሆናቸው ከዘርፉ መንግሥት ከሚያገኘው ገቢ የባለቤትነት ገቢ እንድታገኝ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ከብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀጳጳስ
አዲስ አበባ