ወቅታዊ ጉዳዮች

ሕገ ወጥ ስደትን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መልዕክት

የሰዎች ዝውውር በአግባቡ ማለትም ሕጋዊውን መንገድ ከተከተለና መብትና ግዴታችንን በምናውቅበት መንገድ ሲካሄድ ለተዘዋወረው (ለተጓዡ) ለላኪ እና መዳረሻ ሀገሮች እንዲሁም  ለቤተሰብና ለአጠቃላይ ማኀበራሰቡ ሰፊ ጠቀሜታ አለው። ሕጋዊ መንገድን የተከተለ የሰዎች ዝውውር የሥራ የትምህርት፣የዕውቀትና፣ የልምድ፣ የቴክኖሎጂ፣ የባህል ልውውጥን የሚያመቻቹ እድሎችን ይፈጥራል።

በ2013 በዓለማችን የሰዎች ዝውውር ቁጥር 232 ሚሊዮን እንደደረሰ ጥናቶች ያመለክታሉ። ይህ ቁጥር በ2000 እ.አ.አ. 175 ሚሊዮን፣ በ1990 154 ሚሊዮን የነበረ ሲሆን ይህም ቁጥሩ በየጊዜው እየጨመረ ስለመምጣቱ የሚያመላክት ነው። ከዚህም በተጨማሪ የሰዎች የመዘዋወር ፍላጎት በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱ እና የሚቀጥል ሂደት ስለመሆኑ ያመላክታል። በተለይም በዘመናዊ የመገናኛ አውታሮች እና ቴክኖሎጂ መስፋፋት የሰዎችን የመዘዋወር ፍላጎት የበለጠ እንደሚያፋጥነው ይገመታል። Continue Reading

አንድ ታላቅ አባት አሉ፡፡ በኑሮአቸው ሁሉ ያሳለፏቸውን ተሞክሮዎች ሁል ጊዜ ለወጣቶች ማጫወት ያስደስታቸዋል፡፡ ታዲያ ወደ ወጋቸው ከመግባታቸው በፊት ‹‹እሰይ! እንኳን ተወለዳችሁ፤ እግዚአብሔር ያሳድጋችሁ!›› እያሉ ይመርቃሉ፡፡ እውነት ነው፡፡ ማንኛውም ወላጅ የወለደው ልጁ አድጐ ለቁም ነገር እንዲበቃ የዘወትር ምኞቱ ነው፡፡ አበ ብዙኃን አብርሃምም ልጁን ይስሐቅን ጡት ባስጣለበት ቀን ታላቅ ግብዣን ማድረጉ ለዚህ ምልክታችን ምስክር ነው፡፡ ‹‹አብርሃምም ይስሐቅን ጡት ባስጣለበት ቀን ትልቅ ግብዣን አደረገ›› እንዲል /ዘፍ. 21÷8/፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ አብርሃም ይስሐቅን ጡት እንዳስጣለ ይነግረናል እንጂ ይስሐቅ በራሱ ጡት አልጣለም፡፡ ከዚህ የምንረዳው ሥጋዊ ወላጆቻችን ለመውለድ ብቻ ሳይሆን ለማደጋችንም ጭምር እንደሚያስቡና ግድ እንደሚላቸው ሲሆን በመንፈሳዊው ዓለምም በጥንተ ተፈጥሮም ሆነ በዐዲስ ተፈጥሮ የወለደን እግዚአብሔር እኛን ለማሳደግ ከሕፃንነት ወራታችን ጀምሮ እንደሚደክምልን ነው፡፡ Continue Reading

ክፍል ሁለት

ጎጂ ባህልን በጠቃሚ ባህል እንከላከል፣

ማንኛውም ሕብረተሰብ በሚኖርበት አካባቢ የራሱ የሆኑ ባህልና ልማድ ወግና ሥርዐት አሉት። ዓይነቱና ይዘቱ ገቢሩም ይለያይ እንጂ ያለ ባህልና ልማድ የሚኖር ሕብረተሰብእ አለመኖሩ  የታወቀ ነው።

ሀገራችን ኢትዮጵያም ብዙዎች በሔሮችና ብሔረሰቦች ያሏት እንደመሆኗ መጠን ብዙና የተለያዩ ባህልና ልማድ የሚገኙባት ሀገር ናት። ቢሆንም ባህሎች ሁሉ ጠቃሚዎች አይደሉም፣ በሕብረተሰብኡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያመጡ ባህሎች መኖራቸው የታወቀ ነው። ደግሞም ባህሎች ሁሉ ጎጂዎች አይደሉም። የሀገርን ነጻነትና ሥልጣኔ  እምነትንና ታሪክን የሚያንፀባርቁ ባህሎች አሉ ለምሳሌ፡- Continue Reading

ክፍል አንድ

  1. መግቢያ

በሰው ልጆ ታሪክ ውስጥ ዓለማችን የስልጣኔ ጫፍ ላይ የደረሰችበት እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማዕበል የተጥለቀለቀችበት ዘመን ይህ እኛ የምንኖርበት ሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው። ሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን የመረጃ፣ የቴክኖሎጂ፣ የሉአላዊነት /Globalization/ ዘመን እየተባለ ይጠራል። ሥልጣኔው እና ቴክኖሎጂው የሰው ልጆችን አኗኗር ቀላል ከማድረጉ ባሻገር የተለያዩ እድሎች እና አማራጮች ተጠቃሚ አድርጓል። በዚህ የተነሳ የሰው ልጆች የአኗኗር ዘይቤ እጅግ በፍጥነት እየተለወጠ ሊሔድ ችሏል ።

በዚህ ዘመን የሚኖሩ ወጣቶች የስልጣኔው እና የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ መሆናቸው እንደ መልካም እድል ቢቆጠርም ለውጡ ያመጣቸው ችግሮች እና ፈተናዎች ደግሞ የወጣቶችን ሕይወት እጅግ ከባድ አድርጎታል። ወጣቶች ብዙ ግራ የሚያጋቧቸው፣ የሚያስጨንቋቸው እና ጫና የሚፈጥሩባቸው ከዘመኑ ጋር ተያይዘው የመጡ ችግሮች አሉ። ይህም በትምህርት ቤት፣ በወጣቶች መካከል ያለው ውድድር እና ፉክክር (በውጤት፣ በውበት፣በልብስ፣በሥራ)—– ወ.ዘ.ተ በዚህ ምክንያት አንዳንድ ወጣቶች የወደፊት ሕይወታቸው ጨለማ እና አስቸጋሪ እንደሆነ አስበው ከወዲሁ ተስፋ በመቁረጥ ይጨነቃሉ፣የመኖር ትርጉሙ ጠፍቷቸው በድብርት/ድብት/ ይሰቃያሉ። Continue Reading


አመ ዐሥሩ ወአሚሩ ለሚያዝያ

ኮኑ ኢትዮጵያውያን ሰማዕታተ በሀገረ ሊብያ

Martyrሰማዕት ቃሉ የግዕዝ ሲሆን ከሁሉት ሥርወ ግሥ የተገኘ በመሆኑ ሁለት ትርጉም ይኖረዋል።

  1. ስማዕት የሚለው ቃል ሰምዐ መሠከረ ከሚለው ግስ ሲወጣ ሰማዕት ምስክር የሚል ትርጉም ይኖረዋል
  2. ስማዕት የሚለው ቃል ሶዐ አረደ ሠዋ ከሚለው ግስ ሲወጣ ደገሞ ሰማዕት የታረደ የተሰዋ መስዋዕት የሆነ ማለት ነው።

ከዚህ በመነሣት ሰማዕት ማለት ያመነበትን የክርስትና /ሃይማኖት እምነት መስክሮ ስለ እምነቱ መስዋዕት የሆነ፣ ሕይወቱን ለሃይማኖቱ ለእምነቱ መስዋዕት አድርጎ ያቀረበ የእምነቱ ምስክር ማለት ነው። ለዚህም ፍትሕ መንፈሳዊ ስለ ሰማዕታት በሚናገረው አንቀጹ 20፡ ቍ.744፡- ብፁዕ ኤጲስ ቆጶስ ያዕቆብና ቅዱስ እስጢፋኖስ በእኛ ዘንድ የከበሩ እንደሆኑ ሰማዕታት በእናንተ ዘንድ የከበሩ ይሁኑ፡፡ በማለት ሁለቱን በሐዲስ ኪዳን የተጠቀሱ የጌታችን ተከታዮችን ለሰማዕትነት ምሳሌ አድርጎ ጠቅሷል፡፡ እነሱም በእግዚአብሔር ዘንድ የተመሰገኑና ትሩፋታቸውም የማይገኝ ነው በማለት ተነግሯል፡፡ Continue Reading

ሰላም በምድር ለሰው ልጅ ሁሉ!!

ሰላም፣ ፍቅር፣ ስምምነትና ዕርቅ እንደዚሁም እውነተኛ የማኅበረሰብእ እኩልነት ነው። ሰላም፣ሁለት ተቃራኒ ወገኖች የሚያገኙት እኩል ሚዛናዊ ፍትሕ ነው።

ሰላም የጦር መሣሪያን መቀነስና ጦርነትን ማቆም፡ ከሰዎችም መካከል የጥላቻ መወገድ ብቻ እንዳይደለ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ተናግሮአል።

ሰላም በየትኛውም አቅጣጫ የሕይወትን ሁለተንተናዊ ፍጹምነት የሚያመለክት ነው። የሀገርን ዕድገት ብልጽግና፣ትምህርትና ጤናን፣እንዲሁም ሕይወት በጠባይዓዊ ሞት እስኪፈጸም ድረስ ያለውን ረዥም ሕይወት ይገልጣል። ግላዊና ማኅበራዊ ደህንነትን ፀጥታና መረጋጋትንም ያሳያል። /ዮሐ. 20፥19/

ሰላም በምድር ለሰው ልጅ ከሚያስፈልጉ እጅግ የከበሩና የተወደዱ ከሁሉም ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ነገሮች ሁሉ በላይ ነው።

ቅዱስ ጳወሎስ “ያለ ሰላም እግዚአብሔርን ማየት የሚችል የለም” ይላል /ዕብ. 12፥14 /ሰው ያለ ሰላም ማየት የማይችለው እግዚአብሔርን ብቻ አይደለም። ባልንጀራውንም ያለሰላም ማየት አይችልም። ሰላም የሌላቸው ወገኖች ሊተያዩና  ሊነጋገሩ አይችሉም።

Continue Reading

Abune Samuel Speaking on  Contemporary Issues

ብጹዕ አቡነ ሳሙኤል በወቅታዊ ጉዳዮቸች ላይ ውይይት እያደረጉ

በመጋቢት 23 ቀን 2007 ዓ.ም በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ጥናትና ምርምር ክፍል ጋባዥነት፣ የኮሌጁ የበላይ ኃፊና ዲን ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፣ የኮሌጁ ደቀ መዛሙርት የቀንና የተከታታይ መርሐ ግብር ተማሪዎች፣ መምህራንና የአካዳሚክ ጉባኤ አባላት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተጋባዥ ምሁራን በተገኙበት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን አስተዳደራዊ፣ ጠንካራና ደካማ ጎኖች እንዲሁም የወደፊት ስጋቶች በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሑፍ አቅርበዋል፡፡

Continue Reading