Uncategorized

1 መለኮት ሰው ሆነ የምንለው የቃልነቱ መለኮት ብቻ

ነው እንጂ ልብነቱ መለኮትና የእስትንፋስነቱ መለኮት ሰው አልሆኑም… አንደኛ  ንባብ ውስጥ “የቃልነቱ መለኮት ብቻ ነው” የሚለው በቤተ ክርስቲያናችን የምስጢረ ሥላሴና የምስጢረ ሥጋዌ ትምህርት መሠረት ስሕተት ሆኖ አግኝተነዋል ምክንያቱም የልብነቱ መለኮት ብቻ የቃልነቱ መለኮት ብቻ የእስትንፋስነቱ መለኮት ብቻ የሚል ትምህርት የለምና፣ መለኮትም ሦስቱ አካላት አንድ የሚሆኑበት እንጂ ሦስቱ አካላት ለየብቻ የሚከፋፈሉበት አይደለምና ቅዱስ አትናቴዎስ ተዋሕዶቶሙ ውእቱ መለኮት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ወበዝንቱ አእመርነ ከመ አሐዱ መለኮት ዘሠለስቱ አካላት፡፡?

ትርጉም

“መለኮት የአብ፣ የወልድ፣ የመንፈስ የባሕርይ አንድነታቸው ነው የሦስት አካላት መለኮት አንድ እንደሆነ በዚህ አወቅን” ሲል እንዳስረዳ ሃ/አበው ምዕ 25 ክፍል 4 ቁጥር 6 ?

የ፩ኛው መልስ

የእግዚአብሔር አንድነት

 • የእግዚአብሔር አንድነቱ በባሕርይ በመለኮት አንድ አምላክ ነው፡፡ በስመ እግዚአብሔር ዋሕድ በመለኮት ዘይሤለስ በአካላት ወበኩነታት ማለት በአካላት ሦስት በሚሆን በመለኮት አንድ በሚሆን በእግዚአብሔር እናምናለን፡፡ እንዳሉ ሠለስቱ ምእት፡  ፍትሐ ነገሥት ፩ኛ አንቀጽ፡፡

አንዱ በሚሆኑ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አምናለሁ እታመናለሁ እግዚአብሔርነቱ አንድ ጌትነቱም አንድ ሥልጣኑ አንድ በሚሆን በአንድ አምላክ በአብና በወልድ በመንፈስ  ቅዱስም እናምናለን፡፡

በአምላክነት አንድ ነው በአካል ፫ ይሆናል አንድ እግዚአብሔር የሚሆን  አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ያዕቆብ ዘእልበረዳኢ፡

ኩነታት የተባሉትም ልብነት ቃልነት ሕይወትነት ናቸው፡፡ እነዚህ ናቸው ማለት ሦስቱ ልብነት ቃልነት ሕይወትነት ወይም እስትንፋስነት ናቸው፡፡ የአብ ከዊንነቱ ልብነት ነው፤ የወልድ የመንፈስ ቅድስ ልባቸው እርሱ ነው፤ የወልድ ከዊንነቱ ቃልነት ነው፤ ለአብ  ለመንፈስ ቅዱስ ቃላቸው እርሱ ነው፤ የመንፈስ ቅዱስ ከዊንነቱ  ሕይወት ነው፤ የአብ የወልድ ሕይወታቸው እሱ ነው፡፡

አብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ልባቸው ነው በአብ ልብነት ያስባሉ፡፡

ወልድ ለአብና ለመንፈስ ቅዱስ ቃላቸው ነው በወልድ ቃልነት ይናገራሉ፡፡ መንፈስ ቅዱስም ለአብና ለወልድ እስትንፋሳቸው ነው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት ሕያዋን ይሆናሉ፡፡ ሃይማኖተ አበው አቡሊዲስ ዘሮሜ ክፍል ፪ኛ፡፡

አብ ልብ እንደ ሆነ ወልድም ቃል እንደ ሆነ መንፈስ ቅዱስም ሕይወት እንደ ሆነ እናገራለሁ አምናለሁም እታመናለሁም፡፡ ያዕቆብ ዘእልበ ረዳኢ፡፡

እነዚህ ሦስቱ ኩነታት በህልውና ሲገናዘቡ እንዲህ ነው፡፡ አብ ልባቸው ስለሆነ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ውስጥ አለ፤ ከቃሉ ከወልድ ከሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ አይለይም፤ ለምሳሌ የሰው ነፍስ ልብነቷ ከቃልነቷና ከሕይወትነቷ ሊለይ እንደማይቻል ነው፡፡ ወልድ ቃላቸው ስለሆነ በአብ በመንፈስ ቅዱስ ህልው አለ፤ ከልቡ ከአብ ከሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ አይለይም፣ የነፍስ ቃልነቷ ከልብነቷና ከሕይወቷ አይለይም፤ የነፍስ ቃልነቷ ከልብነቷና ከሕይወትነቷ ከመንፈስ ቅዱስ ሊለይ እንደማትለይ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሕይወታቸው ስለሆነ? አብና  በወልድ ውስጥ አለ፤ ከልቡ ከአብ፤ ከቃሉ ከወልድ አይለይም፤ የነፍስ  ሕይወትነቷ ከልብነቷና ከቃልነቷ ሊለይ እንደማይቻል ነው፡፡ ወልድና  መንፈስ ቅዱስ በነፍስ ቃልና እስትንፋስ ምሳሌ  ከአብ አለመለየታቸውንም አረጋዊ መንፈሳዊ እንዲህ ሲል ያስረዳል፡፡ ቃሏና ሕይወቷ ከነፍስ እንደማይለይ ወልድና መንፈስ ቅዱስ እንደዚኹ ከአብ አይለዩም፡፡ መጽሐፈ መነኮሳት አረጋዊ መንፈሳዊ፡፡     

ከዚህ በተለየ እንደተገለጸው ሥለሴ (፫ቱ አካላት) በልብ  በቃል በእስትንፋስ  በአንድ ልብ በአብ ያውቃሉ  በአንድ ቃል በወልድ ይናገራሉ በአንድ ሕይወት  በመንፈስ ቅዱስ ሕያዋን  ሁነው ይኖራሉ፡፡

በሕልውና (አንዱ በአንዱ መኖራቸውንም) ከ፫ቱ አንዱ ወልድ፣ በእኔ እመኑ እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ፤ ሲል ለሐዋርያት አስተምሯል፡፡ (ዮሐ.፲፬÷፲፩)፡፡

ቅዱስ ዮሐንስም ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፣ እግዚአብሔርም ቃል ነበረ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ ይህ አስቀድሞ አካላዊ ቃል ወልድ በአብ ህልው ነው ነበረ ሲል ገልጾልናል፤ (ዮሐ. ፩÷፩-፪)፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ ቃል በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ በማለቱ አካላዊ ቃል ወልድ በአብ ህልው ነው፡፡ ይህ አስቀድሞ በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ በማለቱ በመንፈስ ቅዱስ ህልው መኖሩን ያስረዳል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ከ፫ቱ አካላት አንዱ አካል ወልድ ቃልን በቃልነት በአብና በመፈስ ቅዱስ አለ በማለቱ ሁለቱን አብ በልብት በወልድ በመንፈስ ቅዱስ እንዳለ፤ መንፈስ ቅዱስ በሕይወትነት በአብና በወልድ እንዳለ ይታወቃል፡፡  

 • ፀሐይ አንድ ሲሆን ትነት አለው ይኸውም ክበቡ ብርሃኑ ሙቀቱ ነው፤ ፀሐይ ወጣ ሲባል ክበቡ ይታወቃል፤ የፀሐይ ብርሃን ታየ ሲባል ብርሃኑ ይታወቃል፤ የፀሐይ ሞቀ ሲባል ሙቀቱ ይታወቃል፤ ክበቡ አብ፤ በብርሃኑ ወልድ፤ በሙቀቱ መንፈስ ቅዱስ፤ ይመሰላሉ፡፡ እሳትም አንድ ሲሆን ሦስትነት አለው፤ ይኸውም ክበቡ ብርሃኑ ሙቀቱ ነው፡፡ ክበቡ እሳት ነደደ ሲባል ይታወቃል፤ ብርሃኑ እሳት በራ ሲባል ይታወቃል፤ ሙቀቱ እሳት ሞቀ ሲባል ይታወቃል፤ ክበቡ አብ፤ በብርሃኑ ወልድ፤ በሙቀቱ መንፈስ ቅዱስ ይመሰላሉ፡፡ ፀሐይና እሳት አንዳንድ ሲሆኑ ሦስትነት እንዳለቸው፤ ሦስትነት ሳላቸው አንድ እንደሆኑ ሥላሴም በአካል ሦስት ሲሆኑ በባሕርይ በመለኮት አንድ ናቸው፡፡
 • ሥላሴ በፀሐይና በእሳት መመሰላቸውንም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ለሐዋርያት እንዲህ ሲል ነግሯቸዋል፡፡ እኔና አባቴ መንፈስ ቅዱስም ፀሐይ /ክበብ/ ብርሃን ሙቀትም ነን፤ እኔና አባቴ መንፈስ ቅዱስም እሳትና ነበልባል ፍሕምም ነን፡፡ እሳት የተባለ ክበቡ ነው፤ ነበልባል ብርሃኑ፤ ፍሕም ሙቀቱ ነው፡፡ ጌታ ይህን የተናገረው ሐዋርያት ባሕርይህ አንድነትህ ሦስትነትህ እንዴት ነው? ብለው ጠይቀውት ሲያስረዳቸው ነው፤ ሐዋርያትም ይህን ጽፈውት ቀሌምንጦስ በተባለው መጽሐፍ ይገኛል፡፡ ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምዕት ተመልከት፡፡
 • ከዚህ በላይ በተነገሩት ምሳሌዎች እንደተገጸው ሁሉ ሥላሴ በአካላት ሦስት ሲሆኑ በባሕርይ አንድ ናቸው፤ አንድ እግዚአብሔር፤ አንድ አምላክ ናቸው፡፡ ይህን ሲያስረዱ መጻሕፍት እንዲህ ይላሉ፤ እስራኤል ሆይ ስማ እግዚአብሔር አምላካችን አንድ እግዚአብሔር ነው፤ ዘጸ. ፮÷፬፡፡ እግዚአብሔር አንድ ነው፤ ኤፌ.፬÷፭፡፡ ሦስት ስም ፩ዱ እግዚአብሔር ነው፡፡ ቅዳሴ ማርያም፡፡

ደግሞም ሥጋ በተለየ አካሉ የቃልነትን መለኮት ?

የሚለውም ከቤተ ክርስቲያናችን የምሥጢረ ሥጋዌ ትምህርት ጋር የሚስማማ አይደለም ተቀባይነትም የለውም እኔም ሙሉ በሙ ተቀብየዋለሁ፡፡ እኔም ይህንን እላለሁ መለወጥ መበረዝ መንታነት በሌለበት በዚህ ተዋሕዶ ቃል ሥጋን ኾነ፣ ሥጋ ቃልን ኾነ፣ ወይም አምላክ ሰው ኾነ፣ ሰው አምላክ ሆነ፡፡…. እርሱም ሰው የሆነ እግዚአብሔር ነው፤ እርሱ አምላክ የሆነ ሰውም ነው… ሲል እንዳስረዳ ሃይማኖተ አበው፣ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ  ደግሞም ሥጋ በተለየ አካሉ የቃልነትን መለኮት የሚለውም ከቤተ ክርስቲያናችን የምሥጢረ ሥጋዌ ትምህርት ጋር የሚስማማ አይደለም፡፡ ተቀባይነትም የለውም ?

የ፪ኛው መልስ

በዚህ ተዋሕዶ የቃል ገንዘብ ለሥጋ የሥጋ ገንዘብ ለቃል ገንዘቡ ኾነ፡፡ ቃልና ሥጋ ወይም  መለኮትና ትስብእት ስለተዋሐዱ ቅድመ ዓለም ከአብ የተወደለው የቃል ልደት ለሥጋ ተነገረለት፡፡ ድኅረ ዓለም /ኑሮ ኑሮ/ ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው /የተገኘ/ የሥጋም ልደት ለቃል ተነገረለት፡፡ እንዲህ በማለት ቃል በሥጋ ድኅረ ዓለም ከአብ ተወለደ፡፡ ቅድመ ዓለም ከቅድስት ድንግል ማርያም የተገኘ ሥጋና ነፍስን ስለኾነ /ስለተዋሐደ/ አብ በአካላዊ ቃል ርስት ትስብእትን ልጄ አለው የኢየሱስ አባት ተባለ፤ አንተ ነህ ልጄ… እንዳለው፣ ራሱ (ሉቃ. ፫ ፥ ፳፪)፡፡

ድኅረ ዓለም  ከቅድስት ድግል ማርያም የተገኘ ትስብእት /ነፍስና ሥጋ ቅድመ ዓለም ከአብ የተገኘ ቃልን ስለኾነ /ስለተዋሐደ/ ቅዱስት ድንግል ማርያም በሥጋ አካላዊ ቃልን ወለደችው፣ የአምላክ እናት ተባለች፣…. እግዚአብሔር ልጁን ላከ ከቅድስት ድግል ማርያም ተወለደ  

 1. “የባሕርይ አንድነት ማለት ግን መመሳሰል ነው መመሳሰልስ እንዴት ነው ቢባል የአብ ባሕርይ፣ የወልድ የመንፈስ ቅዱስን ባሕርይ ይመብላል፤ የወልድ ባሕርይ የአብ የመንፈስ ቅዱስን ባሕርይ ይመስላል፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ባሕርይ የአብ የወልድን ባሕርይ ይመስላል” የሚለውም በቤተ ክርስቲያናችን የምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት አነጋገር ትክክል አይደለም፡፡ ምክንያቱም አይባልምና የሚመሳሰሉት በመልክ በገጽ ነው፡

የ፫ኛው መልስ

አንድነት በሦስትነት

 • የሥላሴ አንድነታቸው በባሕርይ በመለኮት በመንግሥት በአምላክነት ነው፣ ሥላሴ በአገዛዝ በባሕርይ በመለኮት አንድ ናቸው፡፡
 • ስለዚህ ሥላሴ በአምላክነት በባሕርይ፤ በመለኮት አንድ ናቸው፣ እግዚአብሔር በአካል ሦስት ነው፡፡ ወንጌላዊ ዮሐንስም ወእግዚአብሔር ውእቱ ቃል ሲል ጽፏል፡፡ ዮሐ. ፩፥ ፩፡፡

ሦስት የሚያደርጋቸው አካል ከሆነ፣ አንድ የሚያደርጋቸው ደግሞ ባሕርይና ፈቃድ ነው፡፡ ሦስትነት ያለበት አንድነት፣ አንድነት ያለበት ሦስትነት አብ፣ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ናቸው፤ እነርሱም አንድ አምላክ ይባላሉና፡፡ በአካል ሦስት ከሆኑ በፈቃድ በባሕርይ አንድ መሆን እንዴት ነው ያልን እንደሆነ አካል ህልውና ይገናዘባሉ በአንድ ልብነት ያስባሉ በአንድ ቃልነት ይናገራሉ በአንድ እስትንፋስነት ሕያዋን ሁነው ይኖራሉ፡፡ አብ በልብነቱ ዕውቀት ነው፣ ሌላ ልብ የለው “ ህየንተ ልብ ዘዝየ ነአምሮ ለአብ” ሲል ቴዎዶጦስ ዘእንቆራ ተናግሯል፡፡ ወልድም በቃልነቱ ነባቢ ቃል ነው፣ ሌላ ቃል የለውም ሲል ጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራት ተናግሯል፡፡   ዘዳ. ፮ ፥ ፬፡፡ መንፈስ ቅዱስም በሕይወቱ ሕያው ነው፣ ለሥላሴ ሌላ እስትንፋስ የላቸውም “ወአኮ ውእቱ ዘከመ ነፍስ ዘሀሎ ውስቴቴነ ዘንስሕቦ ኀቤነ እምነፋሳት ለቁመተ ሥጋነ፣ አላ ውእቱ መንፈሰ እግዚአብሔር ብሏል፡፡ ዲዮናስዮስ ዘአንጾኪያ፡፡”

 • አብ በልብነቱ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ህልው ነው፣ ወልድም በቃልነቱ በአብ በመንፈስ ቅዱስ ህልው ነው፣ መንፈስ ቅዱስ በእስትንፋስነቱ በአብ በወልድ ህልው ነው፡፡ “ አብኒ ህልው ውእቱ በወልድ ወበመንፈስ ቅዱስ፣ ወወልድኒ ህልው ውእቱ በአብ ወበመንፈስ ቅዲስ” ሲል ፈላታዎስ ዘእስክንድርያ መስክሯል፡፡ ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስ አብ ልባቸው ነው፡፡ ለመንፈስ ቅዱስና ለአብም ወልድ ቃላቸው ነው፡፡ ለወልድና ለአብ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ እስትንፋሳቸው ነው፣ ማለትም በአብ ልነት ሦስቱም ያስባሉ፣ በወልድ ቃልነት ሦስቱም ይናገራሉ፣ በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስነትም ሦስቱ ሕያዋን ሆነው ይኖራሉ፣ በጠቅላላም የህልውና ይገነዘባሉ ብለን እናምናለን፡፡
 • ነገር ግን ሦስትነትን ከአንድነት ጋር በማያያዝ እግዚአብሔር አምላክ ለአገልጋዩ ለሙሴ ሐመልማለን ከነበልባል፣ ነበልባልን ከሐመልማል ጋር አዋሕዶ “አነ ውእቱ እግዚአብሔር አምላክከ አምላከ አብርሃም ወአምላከ ይስሐቅ ወአምላከ ያዕቆብ” እያለ በእሳቱ መካከል አንድነቱን ሦስትነቱን በመግለጥ ተናግሯል፡፡ ማቴ. ፳፪፥፴፪፣ ዘፀ ፫፥፲፭፡፡ አምላክ አምላክ አምላክ በማለት ሦስት ጊዜ መናገሩ የሦስትነት መገለጫ ነው፣ እንዲሁም እግዚአብሔር ብሎ የተናገረውም አምላክ አምላክ አምላክ ያለው ቃሉ ያለመለወጡም አንድነትን የሚገልጥ ነው፡፡ እንደገናም ሙሴና አሮን የሕዝቡ መባረኪያ ቃል አድርጎ ሦስትነትንም አንድነትንም በሚገልጥ መልክ እንዲህ ሲል ይናገር ነበር፡፡ “እግዚአብሔር ይባርክህ፣ ይጠብቅህም፡፡ እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ፣ ይቅርም ይበልህ፡፡ እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሣ ሰላምም ይስጥህ፡፡” እንዲህ እያለ ሦስት ጊዜም መላልሶ መናገሩ የሦስትነት፣ በአንድ አንቀጽ (ቁጥር) መናገሩ ደግሞ የአንድት ማረጋገጫ ነውና፡፡

ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊትም በመዝሙሩ “ ዐቢይ እግዚአብሔር ወዐቢይ ኀይሉ፤ ወአልቦ ኊልቊ ለጥበቢሁ” እያለ አንድነትንም ሦስትነትንም ገልጦ ተናግሯለ፡፡ መዝ. ፻፵፭ ፥ ፭፡፡  ማለት ዐቢይ እግዚአብሔር ያለው እግዚአብሔር አብን ነው፣ ወዐቢይ ኀይሉ ያለው ደግሞ ኀያሉ እግዝአብሐር ወልድን ነው፣ ወአልቦ ኊልቊ ለጥበቢሁ ያለው ደግሞ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ነው፡፡ በድጋሜም “ሣህሉ ለእግዚአብሔር መልአ ምድረ፤ወበቃለ እግዚአብሔር ጸንዓ ሰማያት ወእምስትንፋሰ አፉሁ ኲሉ ኃይሎሙ”፡፡ በማለት አንድነትንም ሦስትነትንም ገልጧል፡፡ ሣህሉ ለእግዚአብሔር ያለው እግዚአብሔር አብን ነው፣ ወበቃለ እግዚአብሔር ጸንዓ ሰማያት ያለው ቃለ እግዚአብሔር ወልድን ነው፣ ወእምስትንፋሰ አፉሁ ያለው ደግሞ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ነው መዝ. ፭፪ ፥ ፭

 • ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኢሳይያስም ሱራፌል በሰማይ ሆነው “ቅዱስ፤ ቅዱስ፤ ቅዱስ እግዚአብሔር ጸባኦት ፍጹም ምሉእ ሰማያተ ወምድረ ቅድሳተ ስብሐቲከ፡ እያሉ ሲያመሰግኑ ሰምቷል፡፡ ኢሳ. ፮ ፥ ፫ ይኸውም ልዩ ሦስትነትን የሚያመለክት ነው፣ ሦስት ጊዜ ቅዱስ ማለቱ የሦስትነት፣ እግዚአብሔር ያለው እና ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ያለው ደግሞ የአንድነት አስረጂ ነው፡፡ ቃል አለመለወጡ ከዚህም ሌላ ልዑል እግዚአብሔር ሁል ጊዜ ለወዳጁ ምስጢርን መግለጥ ልማዱ ስለሆነ፣ በቃል ብቻ ሳይሆን በሥራም ለወዳጁ ለአብርሃም ሦስትነቱን ከአንድነቱ፣ አንድነቱንም ከሦስትነቱ ጋር በማያያዝ እንዲህ አድርጎ ገልጦለታል፡፡ “ዐይኑን አነሣና አየ፣ እነሆም ሦስት ሰዎች ወደርሱ ቀረቡ፣ ባያቸውም ጊዜ ከድንኳኑ ደጅ ሊቀበላቸው ሮጠ፣ ወደ ምድርም ሰገደ” ይህ የሦስትነቱ ምልክት ነው፡፡ የአንድነት ምልክት ደግሞ ከዚየ ደርሶ በነጠላ ቁጥር “አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ እለምንሃለሁ፣ ባርያህን አትለፈኝ” ማለቱ”” ዘፍ. ፲፰ ፥ ፪፡፡ ይኸውም እግዚአብሔር ሦስት ሲሆን አንድ፤ አንድ ሲሆን ደግሞ ሦስት መሆኑ የማያጠያይቅ ከፍተኛ ምስጢር ነው፡፡ ይህም ቅሉ ለአሁኑ ጊዜ ምሳሌው የጎላ መስሎ እንዲታይ ለዚያን ጊዜ ለእስራኤላውያን ረቂቂ ምሳሌ ሆኖባቸው ሲኖሩ ነበር፣ ሆኖም እግዚአብሔር ወልድ ወደዚሀ ዓለም መጥቶ ሲያስተምር “ኲሉ ተውህበኒ እምኀበ አቡየ” ወአልቦ ዘየአምሮ ለወልድ ዘእንበል አብ ወለአብኒ አልቦ ዘየአምሮ ዘአንበለ ወልድ ወለዘፈቀደ ወልድ ይከሥት ሎቱ ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጠኝ ማንም ወልድን ያለ አብ፣ አያውቀውም፤ አብንም ያለ ወልድ፣ ማንም አያውቀውም ወልድም ሲገልጥለት ከወደደው ሰው በቀር ሲል የራቀውን አቅርቦ፣ የረቀቀውንም ምስጢር አጉልቶ፣ አካለ አብን፣ አካለ ወልድን፣ አካለ መንፈስ ቅዱስን በመለየት አስተማራቸው ገለጠላቸው፡፡ ማቴ. ፲፭፥፳፯፡ እንዲሁም በጥምቀት ጊዜ ወልድ በማየ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ ሲጠመቅ ወናሁ መጽአ ቃል እምሰማይ ዘይብል “ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር ወሎቱ ሠመርኩ የምወደው ልጄ ይኸ ነው ብሎ አብ ሲያውጅ፤ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ በርግብ አምሳል ወርዶ ረብቦ ታይቷል፣ በዚህም ጊዜ ምስጢረ ሥላሴ የሥላሴ አንድነት ሦስትነት ተገለጠ፡፡ ማቴ. ፫፥ ፫.፪፡፡
 • ሐዋርያትም ይኸን ይዘው በመልእክታቸው በትምህርታቸው ምስጢረ ሥላሴን አምስጥረው አጉልተው አስፍተው ጽፈዋል፣ ለምሳሌ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በመልእክቱ ሲጽፍ እስመ ሠለስቱ እሙንቱ እለ ይከውኑ ስምዐ መንፈስ ወማይ ወደም ወሠለስቲሆሙ አሐዱ እሙንቱ “በሰማይ ምስክር የሚሆኑ ሦስት ናቸው” ብሎ ሦስት ሲሆኑ አንድ፣ አንድ ሲሆኑ ሦስት መሆናቸውን መስክሯል፡፡ ፩ኛ ዮሐ. ፭፥፰ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስም “ የእግዚብሔር ጸጋ፣ የወልድ ቸርነት የመንፈስ ቅዱስም ምሕረት ለእናንተ ይሁን” በማለት የሦስትነትን ትምህርት አስረድቷል፡፡ ፪ቆሮ ፲፫ ፥ ፫፫

እንዲህ ባለ ምልአት ስፋት ርቀት፣ እንዲህም ባለ አንድነት ሦስትነት ሥላሴ ሳይወሳሰኑ አንዱ ካንዱ መቅደም መቀዳደም ሳይኖርባቸው አንዱ ለአንዱ መገዛት ሳይኖር በአካል፤ በስም፤ በግብር፣ ሦስትነትን፤ በፈቃድ በህልውና በመለኮት አንድነትን ገንዘብ አድርገው ሥላሴ ቅድመ ዓለም ነበሩ፤ ዓለምን ፈጥረው አሉ፤ ዓለምን አሳልፈው ይኖራሉ፡፡

በሥላሴ ዘንድ አንድነት ካለ ብሎ ሦስትነትን፣ ሦስትነትም ካለ ብሎ አንድነትን ሊያፈርስ፣ ወይም ሊቀንስ የሚችል ከቶ የለም፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ትምህርት በዚህ የተመሠረተና በዚህም የጸና ነው፡፡ ስለ ሥላሴ የሚሰጠው ትምህርት በባሕርይ፣ በህልውና፣ በመለኮት አንድ የሆነውን በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት ነው፣ የማይሉ ክርስቲያኖች ክርስቲያን ነን ሊሉ አይችሉም፡፡

 • ለዚህ ለባሕርይ መመሳሰል ማስረጃ ይሆናል ተብሎ በጸሐፊው በአባ ገብረ እግዚአብሔር አብርሃም የቀረበው “አንሰ እብል እስመ ተብህለ በእንተ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ውእቱ አምሳለ እግዚአብሔር ይተረጐም ከመ ውእቱ እምኀላዌ መለኮቱ ለእግዚአብሔር ወይትማሰሎ ለእግዚአብሔር አቡሁ በዕበየ መለኮት ወበስነ ኂሩት በፍጹም ገጽ ወመልክእ፡

 “ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርሰቶስ እግዝአብሔርን ይመስላል ተብሎ የተነገረው ከእግዚአብሔር ከባሕርየ መለኮቱ እንደተገኘ በአምላክነቱ ክብር በቸርነቱ ሥራ አንድ የሚሆን በፍጹም መልክ በፍጹም ገጽ አባቱን እግዚአብሔርን ይመስላል ተብሎ እንደተተረጐመ እኔ እናገራለሁ”

ሃ/ አበው ምዕ ፴፪ ክፍል “ ገጽ 106 ተብሎ የሚተገረጐምና የባሕርይን አንድነት የመልክንና የገጽን መመሳሰል የሚያስረዳ እንጂ የባሕርይን መመሳሰል የሚያስረዳ አይደለም ባሕርይስ አንድ ነው፡፡

 1. መለኮት መንግሥት ሲሆን አንድነት ሦስትነት አለበት”?

ከላይ ያለውን የሚለው አገላለጽ ከቤተ ክርስቲያናችን የምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት ፈጽሞ የራቀ ነው፡፡ ምክንያቱም ሥላሴ በመንግሥት አንድ እንጂ ሦስት አይባሉምና፡፡

የ፬ኛው መልስ

 • ሊቁ ቅዱስ አግናጥዮስ በሃ/አበው ምዕ ፲፩ ክፍል ፩ ገጽ ፲፩ “ አሐቲ ምልክና፣ ወአሐቲ ሥምረት፣ ወአሐቲ ኀይል፣ ወአሐቲ መንግሥት፣ አሐቲ ስግደት፣ ወአሐቲ አኰቴት ወአሐዱ ስብሐት ይደሉ ለሥሉስ ቅዱስ አሐቲ ምክር፣ ወአሐቲ ሥልጣን ወአሐዱ ክብር ወአሐቲ ጽንዕ ወአሐዱ ህሉና ወአሐዱ ፈቃድ፤ አንዲት አገዛዝ አንዲት ፈቃድ፣ አንዲት ኀይል አንዲት መንግሥት አንዲት ስግደት አንዲት ምስጋና አንዲት ክብር አንድ ጽንዕ ለሥላሴ ይገባል፣ አንዲት ምክር አንዲት ሥልጣን አንድ ክብር አንድ ጽንዕ አንድ አኗኗር፣ አንድ ፈቃድ ለሥሉስ ቅዱስ፡፡

ሠለስቱ ምእትም ም. ፲፱ ፥ ፭ አሐዱ እግዚአብሔር ወአሐቲ መንግሥት እንተ ኢትትከፈል ወእንተ ኢትትፋለስ።

የ፬ኛ ተጨማሪ መልስ

አንድነት በሦስትነት

 • የሥላሴ አንድነታቸው በባሕርይ በመለኮት በመንግሥት በአምላክነት ነው፣ ሥላሴ በአገዛዝ በባሕርይ በመለኮት አንድ ነውና፡፡

ስለዚህ ሥላሴ በአምላክነት በባሕርይ፣ በመለኮት አንድ ናቸው፣ እግዚአብሔር በአካላት ሦስት በመለኮት አንድ ነው፣ ይላልና፡፡ ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስም ወእግዚአብሔር ውእቱ ቃል ሲል ጽፏል፡፡ ዮሐ. ፩ ፥ ፩፡፡

 • ሦስት የሚያደርጋቸው አካል ከሆነ፣ አንድ፣ የሚያደርጋቸው ደግሞ ባሕርይና ፈቃድ ነው፡፡ በሦስትነት ያለ አንድነት፣ ያለበት ሦስትነት፤ አብ፣ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ናቸው፣ እነርሱም አንድ አምላክ ይባላሉና፡፡ በአካል ሦስት ከሆኑ በፈቃድ በባሕርይ አንድ መሆን እንዴት ነው ያልን እንደሆነ አካል በአካል ህልው ሆኖ በአንድ ልብነት ቃልነት እስትንፋስነት ስለሚኖር ነው፡፡ አብ በፍጹም አካሉ ልብ ነው፣ ሌላ ልብ የሌለው “ ህየንተ ልብ ዘዝየ ነአምሮ ለአብ” ሲል ቴዎዶጦስ ዘእንቆራ ተናግሯል፡፡ ወልድም በፍጹም አካሉ ቃል ነው፣ ሌላ ቃል የለውም ሲል ጎርጎርዮጽ ገባሬ መንክራት ተናግሯል፡፡ ዘዳ. ፬፡፡ መንፈስ ቅዱስም በፍጹም አካሉ እስትንፋስ ነው፣ ለሥላሴ ሌላ አስትንፋስ የላቸውም “ወአኮ ውእቱ ዘከመ ነፍስ ሀሎ ውስቴትነ ዘንስሕቦ ኀቤነ እምነፋስ ለቁመተ ሥጋነ፣ አላ ውእቱ መንፈስ እግዚአብሔር (ብሏል) ዲዮናስዮስ ዘአንጾኪያ፡፡”
 • አብ በልብነቱ በወልድ በንፈስ ቅዱስ ህልው ነው፣ ወልድም በቃልነቱ በአብ በመንፈስ ቅዱስ ህልው ነው፣ መንፈስ ቅዱስም በእስትንፋስነቱ በአብ በወልድ ህልው ነው፡፡ “ አብኒ ህልው ውእቱ በወልድ ወበመንፈስ ቅዱስ፣ ወወልድኒ ህልው በአብ ወመንፈስ ቅዲስ፡ ሲል ፈላታዎስ ዘእስክንድርያ መስክሯል፡፡ ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስ አብ ልባቸው ነው፡፡ ለመንፈስ ቅዱስና ለአብም ወልድ ቃላቸው ነው፡፡ ለወልድና ለአብ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ እስትንፋሳቸው ነው፣ ማለትም በአብ ልቡናነት ሦስቱም ያስባሉ፣ በወልድ ቃልነት ሦስቱም ይናገራሉ፣ በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስነትም ሦስቱ ሕያዋን ሆነው ይኖራሉ፣ በጠቅላላም ይገነዘባሉ ብለን እናምናለን፡፡ ይላል፤ ሠለስቱ ምእትም በምዕ ፲፱ ቊ ፭ “አሐዱ እግዚአብሔር ወአሐቲ መንግሥት እንተ ኢትትከፈል ወበእንተ ኢትትፋለስ”
 • አንድነት በሦስትነት አይከፈልም፣ ሦስትነትም በአንድነት አይጠቀለልም ነው፤ ምሥጢርም የሚያሰኘው ይኸ ሁሉ ሲገናዘብ ነው፡፡ እግዚአብሔር አብ ፈጣሪ ነው፣ ዘፍ. ፩ ፥ ፩፡፡ እግዝአብሔር ወልድም ፈጣሪ ነው፣ መጽ.ምሳ. ፰፥፴ ዮሐ. ፩፥፩ ዕብ. ፩፥፫፡፡ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ፈጣሪ ነው ኢዮ. ፴፫፥፬ መዝ. ፴፫፥፮፡፡ ነገር ግን ሦስቱም በአምላክነት አንድ ሰለሆኑ አንድ አምላክ አንድ ፈጣሪ ይባላል እንጂ ሦስት  አማልክት ሦስት ፈጣሪዎች አንልም፣ አይባልም፡፡ እግዚአብሔር አብ አምላክ ነው፣ እግዚብሔር ወልድም አምላክ ነው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም አምላክ ነው፡፡

ዘፍ. ፩ ፥ ፩ እንዲህም ስለሆነ አነድ አምላክ እንጂ ሦስት አማልክት ከቶ አንልም፤ አይባልም፤ እንግዲህ እግዚአብሔር አንድ ሲሆን በንድነቱ ውስጥ እንዴት ልዩ ሦስትነት እንዳለ እንመልከት፡፡

ሦስትነት በአንድት፣

 • እግዚአብሔር አንድ ሲሆን ልዩ በሦስትነቱ ይኖራል በስም በግብር በአካል ነው፡፡ ለሥላሴ የስም ሦስትነት አላቸው፣ ይኸውም አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ መባል ነው፡፡ ምንም ስምን ለይተን ሦስት ብንልም ቅሉ ሦስት አማልክት አንልም አንድ አምላክ እንጂ፡፡ ስማቸውም ከቶ አይፋለስም፣ አይለወጥም፤ በየስማቸው ሲመሰገኑ ጸንተው ይኖራሉ እንጂ፣ ይህም ማለት አብ በተለየ ስሙ አብ ይባላል እንጂ ወልድ ወይም መንፈስ ቅዱስ አይባለም፣ ወልድም ወልድ ቢባል እንጂ አብ ወይም መንፈስ ቅዱስ አይባለም፣ መንፈስስ ቅዱስም እንዲሁ መንፈስ ቅዱስ ቢባል እንጂ አብ ወይም ወልድ አይባለም፡፡
 • ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስትስ “ ወእንዘ ታጠምቅዎሙ በሉ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዲስ” ብሎ በስም ሦስትነታቸውን ጠርቶ ተናግሯል፡፡ ማቴ.፳፰ ፥ ፲፱ ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ሊቃውንትም ንባርኮ እናመሰግነዋልን ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ሃይማኖተ አበው ንባርኮ ብለው አንድነቱን፣ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብለው የስም ሦስትነታቸውን መስክረዋል፡፡ እኔም ይህንን እመሰክራለሁ አምናለሁ፡፡

እግዚአብሔር አንድ ነው የማትካፈል የማትፋለስ መንግሥትም አንዲት ናት” በማለት የሥላሴን የመለኮት፣ የመንግሥትን የሦስትነት ከቶ የሚያወሳ የለም?

5”…. ለአብ ሲሦ መንግሥት ጐደሎ መንግሥት አንሰጠውም….በተየ አካሉ ምሉዕ መንግሥት ፍጹም መንግሥት እንሰጠዋለን እንጂ…. ለወልድ ሲሦ መንግሥት ጐደሎ መንግሥት አንሰጠውም… ምሉዕ መንግሥት ፍጹም መንግሥት እንሰጠዋለን …ለመንፈስ ቅዱስ ሲሦ መንግሥት ጐደሎ መንግሥት አንሰጠውም፤ ምሉዕ መንግሥት ፍጹም መንግሥት እንሰጠዋለን፡” የሚለውም የስሕተት አገላለጽ ከላይ በተራ ቁጥር 4 ከተገለጸው የተለየ አይደለም ስሕተትነቱ ግን ጐልቶ የሚታይ ነው፡፡ መልሱም በዚያው በተራ ቁጥር ዐራት እንደተገለጸው ነው፡፡

6 “ሥላሴ አካልና መለኮት ከሆኑ ይሚሤለሱ በአካላት ማለቱ ሥላሴን በመለካት መደብ አኑሮ ነውና አንድ መለኮት በአካል ሦስት ይባላል ማለት ነው”?

የሚለው የአንዳድ ሰዎች ልብወለድ አገላለጽ እንጂ ከቤተ ክርስቲያናችን የምሥጢረ ሥላሴ  የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትና ከቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት አገላለጽ ጋር የሚስማማ አይደለም፡፡ አንባቢዎችን የሚያደናግርና ግራ የሚያጋባ፣ የሚለያይም በነገረ መለኮት ትምሕርት ስሕተት ነው፡፡

 1. “መለኮት በአካል ሦስት ማለትም የሦስቱ አካል መለኮት ነው ማለት ነው መለኮት ሰው ሆነ፣ ሥጋ ተዋሕደ፣ ሞተ፣ ተነሣ፣ የሚባለው ግን ከሦስቱ አካላት አንዱ የእግዚብሐር ወልድ መለኮት ነው መለኮት በአካል ሦስት የምንለው ሦስቱን ነው፡፡ መለኮት በሥጋ ሞተ የምንለው አንዱን ነው”? የሚለውም በቤተ ክርስቲናያናችን የምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት አገላለጽ ሥላሴ በስም፣ በአካል፣ በግብር በኩነት ሦስት ይባላል እንጂ መለኮት በአካል ሦስት አይባልም ለዚህም ማስረጃ

የ፮ኛው መልስ

የሚሆነው ሐዋርያዊው ቅዱስ አትናቴዎስ በሃ/አበው ምዕ ፻፮  ቁ ፰ ወሶበሂ ንቤ አሐዱ እግዚአብሔር አሐዱ ህላዌ ወአሐዱ መለኮት አኮ ዘያበጥል እምኔነ ዝንቱ ተሰምዮተ ሠለስቱ አካላት ወብሂለ ሠለስቱሂ አካላት አኮ ዘይፈልጥ መለኮተ ላዕሌነ ኀበ ሠለስቱ መለኮት እስመ ለለአሐዱ አሐዱ እምሠለስቱ አካላት ህልዋን በበአካላቲሆሙ ወመለኮትሂ ህልው በህላዌሁ ወኢይትፈለጥ ለከዊነ ሠለስቱ መለኮት እስመ ቅድስት ሥላሴ አሐዱ እሙንቱ በተዋሕዶ እንበለ ፍልጠት ዘንተ ንቤ በእንተ ተዋሕዶተ አምለክ በአጽእኖ ዘተምህርናሁ እም አበዊነ ቅዱሳን”

 • “አንድ እግዚአብሔር፣ አንድ መለኮት፣ አንድ ባሕርይ ብለን ይህን በአካል ሦስት ማለትን የሚያፈርስብን አይደለም በአካላት ሦስት ማለትም መለኮትን ሦስት መለኮት ወደ መባል የሚከፍለው አይደለም ከሦስቱ አካላት አንዱም አንዱ በየአካላቸው ጸነተው የኖራሉና ሦስት መለኮት ለመሆን አይከፈልምና ቅድስት ሥላሴ መለየት በለለበት አንድነት አንድ ናቸውና ስለ ፈጣሪያችን አንድነት ከቅድሳን አባቶቻችን እንደተማርነው በምስጢር ይህን ተናገርን” ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ም ፳፭ ፥ ፭-፯
 1. “ይረስዮ ሥጋሁ ወደሞ ብለው በባረኩት ጊዜ በአምላካዊ ሥራ በግብረ መንፈስ ቅዱስ ተለውጦ ኀብስቱ በመልዕልተ መስቀል በዕለተ ዓርብ የተሰቀለው ነፍስ የተለየችው መለኮት የተዋሐደው አብ መንፈስ ቅዱስ ህልዋን የሆኑበት ትኩስ ሥጋ ይሆናል ወይኑም ጐድኑን በጦር በወጉት ጊዜ ከጐድኑ የፈሰሰው ነፍስ የተለየችው መለኮት የተዋሐደው አብ መንፈስ ቅዱስ ህልዋን የሆኑበት ትኩስ ደም ይሆናል፡፡

ስለዚህም የምንቀበለው ሥጋና ደም ወልድ በተለየ አካሉ የተዋሐደው አብ በልብነቱ መንፈስ ቅዲስ በእስትንፋስነቱ ህልዋን የሆኑበት ሥጋ መለኮት ነው እንላለን”? አብ በልብነቱ መንፈስ ቅዱስ በእስትን ፋስነቱ ህልዋን የሆኑበት” የሚለው በቤተ ክርስቲያናችን የምስጢረ ቁርባን ትምህርት አገላለጽ በሊቃውንቱም አባባል የተለመደና ተቀባይነት ያለው አይደለም ምክንያቱም የምንቀበለው ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም ነፍስ የተለየችው መለኮት የተዋሐደው ሥጋ ወልደ እግዚአብሔር ደመ ወልደ እግዚአብሔር ነው እንጂ? “ አብ በልብነቱ መንፈስ ቅዱስ በእስትንፋስነቱ ህልዋን የሆኑበት” የሚል አገላለጽ የለም፡፡

 • ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሥጋውና ደሙ እንዲህ ብሏል… እውነት እውነት እላችኋለሁ ሙሴ እንጀራን ከሰማይ እንደልሰጣችሁ ነገር ግን አባቴ እውነተኛ እንጀራን ከሰማይ ይሰጣችኋል የእግዚአብሔር እንጀራ እርሱ ከሰማይ የወረደ ነውና ሕይወት የሚሰጥ ነው፡፡ (ዮሐ. ፮ ፥ ፴፪- ፴፫)፡፡

የ፰ኛው መልስ

እኔ ነኝ የሕይወት እንጀራ ከእርሱ የሚበላ ኹሉ ፤ እንዳይሞት ከሰማይ የወረደ እንጀራ ይህ ነው፤ እኔ ነኝ ሕያው እንጀራ ከሰማይ የወረደ ማንም ከዚህ እንጀራ የበላ ለዘለዓለሙ ይኖራል እኔም የምሰጠው እንጀራ የዘለዓለም ሕይወት እሰጠው ዘንድ ያለኝ ሥጋ ነው፣…. ዮሐ. ፮፥፴፭-፵፰፣፶‐፶፩

 • ጌታችን ይህን ነገር በቃሉ ሲነግራቸው መጀመሪያ ለሰሙት ሰዎች በግብር እስኪያሳያቸው ድረስ ሊታይ የማይቻል ረቂቂ ምስጢር ነበር፡፡ ዮሐ. ፮ ፥ ፷፡፡ በኋላ ግን ለውጦ ባሳያቸው ጊዜ ተረድተው አምነውታል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ መጀመሪያ የሥጋውና የደሙን ምሥጢር ሲያሳይ እንዲህ ነበር፡፡ ዓርብ ሊሰቀል ሐሙስ ማታ ማለት የሐሙስ ቀን አልፎ የዓርብ ማታ ሲገባ አልዓዛር በተባለ ሰው ቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር መጀመሪያ የኦሪትን መሥዋዕት ሠውቶ በልቷል፡፡ ወዲያው የበሉትን የኦሪት መሥዋዕት በተአምራት ከሆዳቸው አጥፍቶ ሰዎች ለእራት ካመጡለት ኀብስት አንዱን አንሥቶ ያዘና ወደ አባቱ ጸለየ ኀብስቱ በሥልጣኑ ለውጦ ሥጋውን አድርጎ ይህ ስለ እናንተ የሚሰጥ ሥጋዬ ነውና እንኩ ብሉ ብሎ ለደቀመዛሙርቱ ሰጣቸው ቀጥሎም ወይን በጽዋ ቀድቶ ጸለየ ወይኑንም ለውጦ ደሙን አድርጎ ይህ ስለ እናንት የሚፈስ ደሜ ነው እንኩ ጠጡ ብሎ ሰጥቷቸዋል፡፡

(ሉቃ. ፳፪ ፥ ፲፱‐ ፳)-፳፮ ፥ ፳፮-፳፰፣ማር.፲፬ ፥ ፳፪‐፳፭)።

ሳይሰቀል አስቀድሞ ምሥጢረ ቁርባንን ያሳየበት ምክንያትም ዓርብ ዕለት በተሰቀለ ጊዜ ከደቀመዛመርቱ ጋር ተገናኝቶ ሥራ ለመሥራት ስለማይቻል ነው፡፡  (ዮሐ. ፲፮ ፥ ፴፪ )፡፡

ሐዋርያትም ይህን አድርጉ ባላቸው ትምህርት መሠረት ኀብስትና ወይን አቅረበው በጸሎት ባርከው በመለወጥ አማናዊ ሥጋውንና አማናዊ ደሙን እያደረጉ ያቆርቡ ነበር፡፡ (፩ቆሮ.፲ ፥ ፲፮)

ከጸሎተ ቅዳሴውም ውስጥ ካህኑ የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋውንና ደሙን በአማን ያደርገው ዘንድ አቤቱ ቅዱስ መንፈስህን ወደዚህ ኅብስትና ወደዚህ ጽዋዕ እንድትልክ እንለምንሀለን፣ የሚለውን ጸሎት ሲጸልይ በግብረ በመንፈስ ቅዱስ ተለውጦ በአማን ኅብስቱ የክርስቶስን ሥጋ ወይኑም የክርስቶስን ደም ይሆናል፡፡ የሐዋርየት ቅዳሴ ቁ.፵፰ ፥ ፵፱

ከዚህ በኋላ ሥጋውን ካህኑ እንደ ሥርዐቱ ለሚገባቸው ያቆርባቸዋል ዲያቆኑ ደሙን በዕርፈ መስቀሉ ያቀብላቸዋል፡፡

ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ሥጋውን ደሙን ተቀብሎ ከኃጢአት ፍርድ ይነጻል የዘለዓለምን ሕይወት ወርሶ በመነግሥተ ሰማይ ለዘለዓለም ይኖራል፡፡

ስለዚህ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ብሏል፣  ሥጋዬን የበላ ደሜንም የጠጣ እርሱ የዘለዓለም ሕይወት አለው እኔም በኋላኛው ቀን አስነሣዋለሁ፡፡ ሥጋዬ የእውነት መብል ነውና ደሜም የእውነት መጠጥ ነውና ሥጋዬን የበላ ደሜንም የጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ የለከኝ አብ ሕያው እንደሆነ እኔም ስለ አብ ሕያው  ነኝ ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ ደግሞ እርሱ ስለእኔ ሕያው ይሆናል፣….. (ዮሐ. ፮ ፥ ፶፬‐ ፶፯)

 1. ወላዲ ባሕርይ ተወላዲ ባሕርይ፣  ሠረጺ ባሕርይ….  ወላዲ  መለኮት ተወላዲ መለኮት  ሠራጺ መለኮት? የሚለው ከቤተክርስቲያናችን የምሥጢረ ስላሴ ትምህርት ያፈነገጠ ነው ምክንያቱም “ወላዲ ባሕርይ ተወላዲ ባሕርይ ሠራ ባሕርይ ወላዲ መለኮት ተወላዲ መለኮት ሠረጺ መለኮት”? የሚል  በብሉይ ኪዳንና በሐዲስ  ኪዳን፣ እንዲሁም በመጻሕፍተ ሊቃውንት በገጸ ንባብም ሆነ በትርጓሜ ፈጽሞ አይገኝምና መለኮትን አካላት በሚለያዩበት ስም  ወላዲ መለኮት ተወላዲ መለኮት  ሠረጺ መለኮት ማለት መለኮትን እንደ አካላት ሶስት ወደ ማለት የሚያደርስ ስሕተት ነው፡፡?

ለዚህም ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ  ዘአንጺኪያ በሃ/ አበው  ምዕ ፻፫ ገጽ ፬፷፬ “ወናወግዝ ዓዲ  እለ ይብሉ ሠለስተ መለኮተ እንተ ዘአብ  ወወልድ  ወመንፈስ ቅዱስ” ትርጉም፡- “ዳግመኛም  የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ መለኮት ሶስት ነው የሚሉትን እናወግዛለን” በማለት አስጠቅቆአል፡፡  

ተጨማሪ የ፱ኛው መልስ

 • እንደ መጽሐፍ ቅዱስም አገላለጽ እግዚአብሔር አምላክ “አንድ እግዚአብሔር በሶስትነት ሥላሴ በአንድነት” ተብሎ ተደንግጓል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን  የእግዚአብሔር ቃል የመጽሐፍ ቅዱሱን ትክክለኛ ትርጉም ወይም ጭብጥ ወይም ጥቅስ የሚገልጸውን ቅድሚያ ማግኘት አለበት፡፡ ስለ አንድነት ከሆነ የአንድነትን ትርጉም  መያዝ፤ ለሶስትነት /ሥላሴ/ ከሆነ የሶስትነትን ትርጉም መያዝ አለበት፡፡ በሌላ አነጋገር አንድነት ስለአድነት ባሕርይ የተጠቀሱትን ጥቅሶች መስማማት፣ ሶስትነት /ሥላሴ/ ስለሥላሴ ከተጠቀሱ ጥቅሶች ጋር መጣጣም አለበት፡፡  ስለዚህ  ስለ ምስጢረ ሥላሴ ትምህርተ ሃይማኖት ስናጠና የአጠናናችን ዘዴ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ላይ ያተኮረ ሆኖ የእግዚአብሔርን አንድነትና ሦስትነት  ምንነትን ለይቶ በማወቅ ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት፡፡ አመለካከታችንንም አንድ ገጽ (አንድ አካል) ወይም ስለ ሶስትነት የተነገረውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ በተሳሳተ መንገድ በመተርጉም  መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ በተሳሳተ  መንገድ በመተርጎም  ሶስት አማልክት ከሚሉ መናፍቃን ፈጽሜ በመራቅ የአንድነትን ምስጢር በሶስትነት ሳልነጣጥል፣ የሶስትነትን ምስጢር በአንድነት ሳልጠቀልል ነው፡፡ አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስን በተመለከተ የመጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ ትንታኔ ዐላማ የቤተ ክርስቲያን ዋነኛ ትምህርት ነው፡፡    
 1. “በመለኮት አንድም ሶስትም ናቸው በባሕርይ አንድም ሶስትም ናቸው በግብር አንድም ሶስትም ናቸው በአምላክነት አንድም ሶስት ናቸው? የሚለውም ከቤተ ክርስቲያናችን የምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት አገላለጽ በፍጹም የተለየ ስሕተት ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን የምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት ከአባቶቻችን ሊቃውንት ሲያያዝ የመጣውና የታወቀው በቅዱሳት መጻሕፍትም የተጻፈው “በስም፣ በአካል፣ በግብር ሶስት፣ በመለኮት በፈቃድ በባሕርይ፣ በጌትነት… አንድ የሚል ነው ” እንጂ እንደዚህ ያለ የተደበላለቀና አንባቢን የሚያደናግር አገላለጽ ነው፡፡

በመሆኑም እነዚህ “ምስጢረ ሥላሴ ከላይ ከ1—10 ለምሳሌ ያህል በተገለጹት ሐሳቦች እንደተገለጸው የምስጢረ ሥላሴን ትምህርት በተዛባና ትክክል ባልሆነ አቀራረብ አደናጋሪ ይዘት ያላቸው ስለሆነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን የአምስቱ አዕማደ ምሥጢር ትምህርትን መሠረት አድርጐ የተዘጋጀ መልስ ስልሆነ ይቅመበት

በእነዚህም የቅዱሳት መጻሕፍት ማስረጃዎች መሠረት የአንድነትንና የሦስትነትን ምሥጢር እንደመኾናቸው ውሱን ያልኾነውን እግዚአብሐርን እና ውስኖች የማወቅ ችሎታችን ዐቅም እንደሌለው ማወቅ ይኖርብናል፡፡

የ፲ኛው እና ማጠቃላያው መልስ

ስለሆነም የቀደምት አበው የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ እና

የሲኖዶሶች ምስክርነት

 • በአራተኛው መቶ ዓመት አካባቢ በመሥጢረ ሥላሴ ላይ ብዙ መናፍቃን በመነሣታቸው ምክንያት ልዩ ልዩ የዓለም ዐቀፍ ሲኖዶሶች ተሰብስበዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል ፫፻፳፭ ዓ.ም በኒቂያ ከተማ የተሰበሰበው ሦስት መቶ ዓሥራ ስምንት (፫፻፲፰) ሊቃውንት የዓለም ኤጲስ ቆጶሳት የተገኙበትና በ፫፻፹፩ዓ.ም ደግሞ በቁስጥንጥንያ አንድ መቶ ኀምሳ የዓለም ኤጲስ ቆጶሳት የተገኙበት ሁለት የዓለም ዐቀፍ ሲኖዶሶች ቀጥሎ ያለውን የእምነት ቀኖና ደንግገዋል፡፡

“ኹሉን በያዘ፣ ሰማይንና ምድርን፣ የሚታይና የማይታየውን በፈጠረ፣ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን፡፡

ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ በተወለደ፣ የአብ አንድያ ልጁ በሚኾን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን፡፡ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ እውነተኛ አምላክ የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ በመለኮቱ ከአብ ጋር የሚተካከል ኹሉ  በእርሱ የኾነ ስለ እኛ ስለ ሰዎች እኛን ለማዳን ከሰማይ ወረደ በመንፈስ ቅዱስ  ከቅድስት ድንግል ማርያም ሰው ኾነ፤ ሰው ኾኖም በጰንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን ስለ እኛ ተሰቀለ፤ ታመመ፤ ሞተ፤ ተቀበረም በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈ በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ፣ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ፤ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ይፈርድ ዘንድ በጌትነት ይመጣል፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም፡፡

ሕይወትን በሚሰጥ ጌታ ከአብ በሠረጸ ከአብና ከወልድ ጋር በሚሰገድለት በነቢያት አድሮ በተናገረ በመንፈስ ቅዲስ አምናለሁ፡፡

ዓለም ዐቀፋዊትና ሐዋርያዊት በኾነች በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን  አምናለሁ፡፡

ኀጢአትን ለማስተስረይ በአንዲት ጥምቀት አምናለሁ፡፡

የሙታንን መነሣትና የሚመጣውን ሕይወት ተስፋ አደርጋለሁ፤ ለዘላለሙ አሜን፡፡

የቅዱሳን አበው ምስክርነት

 • ቅዱስ ጎርጎርዮስ የቂሣርያ ኤጲስ ቆጶስ “ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ እንላለን….. የእግዚአብሐር አቃኒም ስሞች ናቸው፤ ስሞችም አቃኒም ናቸው፡፡ የአቃኒም ትርጓሜው በገጽ በመልክ ፍጹማን የሚኾኑ ባለመለወጥ ጸንተው የሚኖሩ አካላት ማለት ነውና ባሕርዩ አንድ ሲኾን ሦስቱ አካላት ጸንተው በሚኖሩ  በእሊህ ነውና ባሕርዩ አንድ ሲኾን ሦስቱ አካላት ጸንተው በሚኖሩ በእሊህ ስሞች ይጠራሉ፤ ሶስት አካላት አንድ መለኮት ናቸው፡፡” (ሃ. አበ. ገጽ ፴፱ ፥ ፵ )

ቅዱስ አትናቴዎስ “በባሕርይ አንድ እንደኾኑ በሦስቱ አካላት አምናለሁ፤ እሊህም አብ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ናቸው፤ አብ የሚያድን ነው፤ ወልድም የሚያድን ነው፤ መንፈስ ቅዱስም የሚያድን ነው፡፡ አንድ ሲኾኑ ሦስት ናቸው፤ ሶስት ሲኾኑ በባሕርይ በመለኮት በክብር በመመስገን በሥልጣን ፍጡራንንም ኹሉ በመፍጠር በፈቃድ ኀጢአትን ይቅር በማለት በማትለወጥ ዕውቀት በረከትን በመስጠት አንድ ናቸው (ሃ.አበ.ገጽ ፭)

 • ቅዱስ ባስልዮስ የቂሣርያ ኤጲስ ቆጶስ “የሦስቱ አካላት መለኮት ፍጹም አንድነትን ልናውቅ ይገባናል፣ የእነርሱ የሚኾን አንድ መለኮትን አንድ በማድረግ እናዋሕድ፡፡ በአብ ወላዲነት አሥራጺነት መለኮት አንድ እንደኾነ ሃይማኖትን እንመን፤ ወልድ ከአብ ተወልዷልና መንፈስ ቅዱስም ከአብ ተገኝቷልና አብ ከወልድ ወልድም ከመንፈስ ቅዱስ ሳይቀድም ወልድ ከአብ በመወለዱ መንፈስ ቅዱስም ከአብ በመሥረጹ የፈጣሪያችን የሦስትነቱ መለኮት አንድ ይኾናል፡፡” (ሃ. አበ. ገጽ ፻፯)
 • የሮም ሊቀ ጳጳስ አቡሊዲስ “አብ ወልድን የወለደ ነውና ዳግመኛም በማይነገር፣ በሐሳብም በማይመረመር ግብር መንፈስ ቅዱስ ከእርሱ ተገኝቷልና አብ ከወልድ ወልድም ከመንፈስ ቅዱስ ሳይቀድም መንፈስ ቅዱስ ከወልድ ወልድም ከአብ ወደ ኋላ

ሳይኾን ነው፡፡ ወልድም ለአብ ለመንፈስ ቅዱስ ቃላቸው ነው፤ መንፈስ ቅዱስም ለአብ ለወልድ እስትንፋሳቸው ነው፤ የሦስቱ አካላት መለኮት አንድ እንደኾነ በዚሀ ዐውቀን ለእርሱ እንሰግዳለን፡፡ “(ሃ.አበ.ገጽ) ፻፴፯ – ፻፴፷)

 • የኢየሩሳሌም ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ ዮሐንሰ “አንድ አምላክ ብለን የምንሰግድላቸው ሥሉስ ቅዱስ በባሕርይ በመለኮት አንድ እንደኾኑ እናምናለን እሊህም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ እሊህም ሦስቱ አካላት በገጽ ፈጹማን እንደኾኑ በሥልጣን በባሕርይ ከዘመን አስቀድሞ በመኖር በጌትነት በመፍጠር ሳይለወጡ በመኖር አንድ እንደኾኑ እናምናለን፤ ይህን እንዲህ ብሎ የማያምነውን እኛ እናወግዘዋለን፡፡” ብለዋል፡፡ (ሃ.አበ.ገጽ ፻፰፯)
 • ቅዱስ ቄርሎስ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት “ አንድ መለኮት አንድ ባሕርይ አንድ ኀይል አንድ ልዕልና አንድ ጌትነት አንድ ክብር ከጥንት አስቀድሞ የነበረ አንድ ቀዳማዊነት ነው፤ በሦስት አካላት በሦስት ገጻት ፍጹማን ናቸው፤ ግዙፋን አይደሉም፤ ያልተፈጠሩ ናቸው፤ ድካም የማይስማማቸው/ የማይለወጡ ናቸው፤ ለመገኘት ጥንት ለዘመን ፍጻሜ የላቸውም፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በአካል ሦስት በባሕርይ አንድ ነው ብሎ ማመን ይህ ነው የማይመረመር በቅድምና የነበረ” (ሃ አበ. ገጽ ፪፶፮)
 • ቅዱስ ቴዎዶስዮስ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት፡- “በአካል በገጽ ሦስት ነው፤ በመለኮት አንድ ነው፤ ሥሉስ ቅዱስ አንድ ናቸው አንድ አገዛዝ አንድ ጌትነት አንድ መለኮት አንድ መንግሥት ገንዘባቸው ነው፡፡ አብ ከወልድ ተለይቶ የኖረበት ዘመን የለም ወልድን የወለደበት መንፈስ ቅዱስን ያሠረጸበት ተለይቶ የኖረበት ዘመን የለም፤ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በቅድምና የነበሩ ናቸው እንጂ ወልድ ከእግዚአብሐር አብ ተወለደ፤ መንፈስ ቅዱስም ከአብ ተገኘ ሥሉስ ቅዱስ ያልተፈጠሩ ናቸው፡፡ “ (ሃ.አበ ገጽ ፫፵፪)
 • ቅዱስ ሳዊሮስ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት፡- “ ሦስቱ አካላት በመልክ ፍጹማን ናቸው፤ ሦስቱ ገጻት በክብር በብርሃን አንድ ናቸው፤ በባሕርይ አንድ ናቸው፤ በሥልጣን አንድ ናቸው በጌትነት አንድ ናቸው፤ በመለኮት አንድ ናቸው፤ በመሰገድ አንድ ናቸው፣ በመመስገን አንድ ናቸው የታመኑ ሰዎች እንደሚያምኑት፡፡…… በሦስቱ አካላት ውስጥ መገዛዛት መታጠቅ መፍታት የለም፤ በማዕረገ መለኮት አንዱ ካንዱ አይበልጥም፤ አንዱ አንዱን እንደ መልእክተኛ በሥልጣኑ አያዝዘውም፤ በአንድ መለኮተ ክብር በአገዛዝ የኹሉ ፈጣሪ ገንዘብ በሚኾን በባሕርይ ዕውቀት አንድ ናቸው እንጂ፡፡” (ሃ. አበ. ገጽ ፫፻፶፯)

 

 

አባ ሳሙኤል፤

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀጳጳስ 

አዲስ አበባ

 

ኮሚዩኒኬሽን የአንድ ተቋም የደም ስር ነው። በተለያየ ደረጃ ያሉ የተቋሙ አካላት እንደ አንደ አንድ ውህድ አካል ለመንቀሳቀስ የተስተካከለ የመረጃና የኮሚዩኒኬሽን ትስስር ሊኖራቸው ይገባል። ይህ ባልሆነበት ሁኔታ የደም ዝውውር ስርዓቱ ተዛብቶ አደጋ እንደሚወድቅ ሰው ሁሉ ተቋማትም የተስተካከለ የመረጃ  ዝውውር ስርዓት ከሌላቸወ ይሞታሉ።

ይህም ሆኖ መረጃ መኖሩ ብቻ በቂ አይደለም። ሙያዊ የመረጃ ስርጭት ክህሎት ለአመራር ኃላፊነታችን ብቻ ሳይሆን ለእለት ተእለት ሰብአዊ ግንኙነታችን ጭምር ጠቃሚ ነው።  መረጃ  በትክክለኛው  ጊዜ መንግድና አቀራረብ የማይተላለፍ ከሆነ ከመረጃ ተቀባዩ ጋር የተለያ ሓሳብ የምናጸባርቅ እስኪመስል ድረስ ለመግባባት አስቸጋሪ ነው።

በተቋም ውስጥ ይሁን ከተቋም ውጭ ላለው ተደራሽ መረጃ የምናቀርብብት ስርዓትና አግባብ የምንፈልገውን ወጤት በሚያስገኝ መልኩ ሲኬድበት አናይም። ሚስጥራዊነትን እንደ ታላቅ ዕሴት በሚቆጥረው ባህላችን መረጃ እንደ የሥራ መሳሪያ ሳይሆን  እንደ የስልጣን  ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል። ከዚህም በተጨማሪ በስርዓታችን ውስጥ የትኛውን መረጃ ማን ማወቅ አለበት ከማንስ ሚስጥር መሆን አለበት የሚለውን የሚደነግግ የመረጃ ህግ ቢኖርም ፍላጎት የሚወሰንበትን ሁኔታ በስፋት እናስተውላለን መሪዎች።

እንዳንድ መሪዎች  የተቋሙን ራዕይና እቅዱ በግልፅ ከማብራራት ይልቅ ተከታዮቻቸው የሚያስቡት ጭምር እንዲያወቁ ይጠብቃሉ። የተቋሙ ተልዕኮና ግብ በግልዕ እንዲታወቅና መግባባት እንዲደረስበት በመጨረሻም የሚፈልገውን ውጤት ብቻ ሳይሆን የሚኬድበትን አቅጣጫ ፍጥነት የማሳወቀና የማግባባት ኃላፊነትታቸውን ይዘነጋሉ። በዚህ ሁኔታ መረጃ በአመራሩ በስስት የሚጠበቅ የግል ንብረት ይሆንና ተከታዮቹ ሥራቸውን አወቀው በነፃነት የሚሰሩ ሳይሆን አለቅዬውን ለማስደሰትና ታማኝነታቸውን የበለጠ ለመግለፅ የሚራኮቱ ትእዛዝ ጠባቂዎች ይሆናሉ። እያንዳንዱ ሥራ አከጠቃላይ ዓላማው ጋር እንዴት እንደሚያያዝ በማይታወቅበት ሁኔታ የሥራ ሞራልም ቀስ በቀስ ይዘቅጣል።

በመርህ ላይ ተመስርተው እና በቂ መረጃ ይዘው የሚሰሩ ሰዎች መርሁን በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነው ያለምንም አዛዥ ግባራዊ ለማድረግና ችግሮችን ለመፍታት ይችላሉ። በትእዛዝ ላይ ተመስርተው የሚያስቡ ሰዎች ግን ስኬት ማስመዝገብ የሚችሉት በተወሰኑ ሁኔታዎች እና ጉዳዮች ላይ ብቻ ነው። በተነገራቸው ጉዳይና በእርግጠኝነት በሚያውቁት ውጤት ዙሪያ ነው። ቀደም ብሎ ስምምነት በተደረሰባቸው መርሆዎችና በአስፈላጊ መረጃ የታጠቁ ሰዎች በኮምፓስ እንደሚመራ ተጓዥ ናቸው። ኮምፓስ በየትኛውም የማይታወቅ ዱርና በረሃ ላይ ቢኮንም መወጣጫ መንገድንና መዳረሻን ማሳየት ይችላል። የጠራ መረጃና የጉዞ አቀጣጫ የታጠቀ ኃይል በእያንዳንዱ እርምጃ የአለቃውን አይን አይን ማየትሰያስፈልገው ኮምፓሱን ይዞ በዓላማው መንፈስ ላይ ተመስርቶ በሙሉ ልብ ፊት ለፊት የሚገጥመውን ጦርነት የሚያሽንፍ ኃይል  ይሆናል። ለዚህም ውጤታማ የኮሚዩኒኬሽን ስርዓት የማይተካ ሚና አለው።

በአንድ ተቋም ውስጥ ያለው የኮሚዩኒኬሽን ባህል ለብቻው የተነጠለ ሳይሆን የአመራርና የተቋሙ ባህል ነፀብራቅ ነው። የኮሚዩኒኬሽን ስርዓቱና ባህሉ ደግሞ በተራው የአመራርና ተከታይ የጎንዮሽ የአባላት ግንኙነት የአባላቱ  የሥራ ተነሳሽንት ውጤት የተቋሙ የፈጠራ አቅምና የአባላቱ  የባለቤትበት መንፈስ ላይ ሳይቀር ተፅእኖ አለው።

ውጤታማ የኮሚዩኒኬሽን ሥራ የሚጀምረው በተቋሙ ተልዕኮ ላይ ግልዕንትን በመፍጥር ነው። በዚህም መሰረት ለእያንዳንዱ ሠራተኛ የሚጠበቅበትን ማሳወቅ ብቻ ሳይሆን የተቋሙን እቅድ በጋራ ማቀድ በጋራ መገምገምና እያንዳንዱ ሠራተኛ እንደየውጤቱ የሚሽለምበትንና የደከመው ደግሞ የሚደገፍበትን ሁኔታ መፍጠር ለተሳካ የኮሚዩኒኬሽን ስርዓት መሰረት ነው። በሥራ ወቅት ለምንመራቸው ሰዎች በአጠቃላይ ሊደረስበት የሚገባውን ውጤትና  ከእያንዳንዱ ግለሰብ የሚጠበቀውን ሚና ግልፅ ማድረግ ያስፈልጋል። በዚህ ዙሪያ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት ጊዜ ሀብትና ጉልበት መጀመሪያውኑ ተግባብቶ ሥራ  ባልደረሰቦች በውጤቱና በሂደቱ ላይ እስተዋዕኦ ይኖራቸዋል ብሎ ማመን ይጠበቃል።

በተቋሙ ውስጥ ግልዕና የመተማመን ግንኝነት መፍጠር ለውስጥና ለውጭ ኮሚዩኒኬሽን ውጤታማነት ቁልፍ ጉዳይ ነው። ውጤታማ ውስጡ ተቋም የኮሚዩኒኬሽን ስርዓት የተቋሙን የውስጥ አካላት የሚያስተሳስር ክር ብቻ ሳይሆን ለውጭ አካላትም ጠንካራ የግንኙነት ድልድይ  ይሆናል። ጥሩ የመረጃ ስርጭት ስርዓት በሌለበት ሁኔታ ክፍተቱ በሃሜታና በአሉባልታ ይተካል እንደ። ማንኛውም ተፈጥሮዊ ክስተት አአምሯችን ክፍተትን አይፈቅድም መረጃ በውቅቱና በሚፈለግው መጠንና ጥራት ካልተሰራጨ ወይም በአግባቡ ካልተሰራጨ የሰው አእምሮ ከሌላ ምንጭ ወይም በራሱ በሚፈጥረው ነገር ከፈተቱን ይሞላል። ይህ ሁኔታ ብዙውን ጊዜ ተጨማሪ ወጪ ወደሚጠይቅ የእሳት ማጥፋት ሥራ  ያስገባል።

በውስጠ ተቋም ሆነ ከተቋም ውጭ ካሉ ባለጉዳዩች ጋር ባለን የኮሚዩኒኬሽን ግንኙነት በጥሞና አድሞጦ መረጃና ሀሳብን አደራጅቶ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ጠቃሚ ክህሎት ቢሆንም ለተሳካ ኮሚዩኒኬሽን ብቻውን በቂ አይደለም። በመጀመሪያ የምናሰራጨውን መረጃ ማወቅ ብቻም ሳይሆን ያለማመንታት ስርጥቱን ዓላማና የምንጠብቀውን ውጤት ቀድመን ማወቅ ያስፈልጋል። መረጃውን እንዲሁ መበተን ሳይሆን ውጤቱን የምናውቅበት ይግብረ መልስ ስርዓት ሊኖረው ይገባል። ይህ ካልሆን ዒላችንን ሳወቅ ወደ ጨለማ የማቆልቆ ያህል የባከን ጊዜ እና ሥራ  ይሆናል። ግብረ-መልስ ባለወቅንብት ሁኔታ ቀጣይ ሥራዎችን ለማቀድና ጉድለቶችን ለማረም የምናውቅበት መንገድ አይኖርም።

 

ከብፁዕ አቡነ ሳሙኤል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ

አዲስ አበባ

 

 

 

        ልዑል  ባሕርይ  እግዚአብሔር  አምላካችን  ከዘመነ  ሉቃስ  ወንጌላዊ  ወደ ዘመነ  ዮሐንስ               

           ፍስሐ ዜናዊ  በሰላም በሕይወት  በጤና  እንኳን  አደረስዎ!!

                            ወትባርክ አክሊለ ዓመተ መሕረትክ፣

                           ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም

                          ወይረውዩ አድባረ በድው

በቸርነትህ ዓመታትን ታቀናጃለህ፣ዘመናትንም ታበዛዋለህ። ገዳማት ልምላሜውን አግኝተው ደስ ይላቸዋል። በበረኃ ያሉት ተራራዎች ሁሉ ዝናሙን ይረካሉ። ኮረብታዎችም ደስ ብሏቸው ልምላሜውን እንደዝናር ይታጠቃሉ።መዝ.64፥11-12

ርትዕሰ እምድር ሠረጸት፣ ወጽድቅኒ እምሰማይ ሐወጸ፣ወእግዚአብሔርኒ ይሁብ ምሕረቶ።

እውነት ከምድር በቀለች፣ ጽድቅም ከሰማይ ተመለከተች፣ እግዚአብሔርም በጎ ነገርን ይሰጣል። መዝ 84፥10-11

“የዘመናት ባለቤት እግዚአብሔር አምላካችን ዘመናትን ጊዜያትን በሚመጡ ጊዜያት በሚመጡት ዘመናት እግዚአብሔር አምላክ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለጠግነት ይሰጠን ዘንደ ነው።” ኤፌ. 2፥6

ቸሩ አምላካችን ዘመኑን የሰላም፣ የጤና፣ የበረከት፣ የፍቅርና የሕይወት ዘመን ያድርግልን አሜን!!

 

                                           ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን !!

 

አባ ሳሙኤል

በኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ

 አዲስ አበባ

 

ስለ ሰላምና ዕርቅ እንዲሁም ግጭት አፈታ አስመልክቶ ከዚህ በታች የተገለጹትን በዚህ መነሻነት ከዚህ ቀጥሎ የተዘጋጀው ጽሑፍ እውነተኝነት ሃይማኖተኝነት ስለም እና ፍትሓዊነት አፈታትን ጥያቄዎች  ስለሆነ አንባቢ እያንዳንዱን ክፍል ከነበባ በኋላ  ስለዚህ እነዚህ

ጥያቄዎች  በአግባቡ የቤት ሥራዎች ይሠሩበት ከመጽሐፉ የተወሰዱ ጥቃዎች  በአግባብ ይሥሩ

1.     ሰላም በአያንዳንዳችን እጅ ነው ስንል ምን ማልታችን ነው?

2.    ቤተክርስቲያና ስለሰላም አጥብቃ እንድ ታሰተምር በተለይ ሰባኪያን ስለሰላም በአግባቡ እንዲያስተምሩ ምን ዝግጅት ማድረግ አለባት ?

3.    የሃይማኖት አባቶች በንስሐ ልጆቻቸው በኩል ሰላምን እንዲያስተምሩ የሰላም መመሪያ ቢዘጋጅ መልካምነቱን ይግለፁ ?

4.    ሰላም ከእምነት፣ ከመልካም አስተዳደር፣ ከዲሞክራሲ እና ከልማት ጋር እንዴት መጣጣም ይቻላል?

5.    ሰላምንና ግብረገብነትን በየደረጃው በትምህርት ቤቶች እንዴት ማስተማር ይገባል?

6.   ከመጽሐፉ በተገኘው ትምህርት በግልም ሆነ በቡድን ስለሰላም ምን መደረግ አለበት ይላሉ?

7.    የሃይማኖትና የመንግሥት ባለሥልጣናት ስለሰላም ጉዳይ አርአያ ሆነው ይታያሉ ወይ?

8.    መሪዎች ራሳቸውን የሰላም ሐዘዋርያ አድርገው ሌላውን ባገኙት አጋጣሚ ማስተማር ችሏል?

9.   ሰለሰላም ለማስተማር ከሚከተሉት እነማን በበለጠ ይሳተፉ?

                ሀ.  የደብር አስተዳዳሪዎ

                ለ.  ካህናት 

                .  ሰባክያነ ወንጌል

                .  የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች

                ሠ.  የእድር መሪዎች

                ረ. የቀበሌና የወረዳ አመራር አባላት

                ሰ. ሌሎች የመንግሥት አካላት 

10.  ከላይ የተጠቀሱት ሁሉም፣ ስለ ሰላም ጠቃሚነት ከ5 ገጾች ባልበለጠ አስተያየትዎን ያዳበሩ

1.     ሃይማኖቶች ስለ ሰው ተፈጥሮና ምንነት ሲገልጽ የሰው ልጅ ፈጣሪ ልዩ ትኩረት የሰጠውና በከንቱ  ያልተፈጠረ ፍጡር  ነው ስንልምን ማለት ነው?

2.    ሰው ሃይማኖተኛ ፍጡር እንደሆነ የሃይማኖት ሊቃውንተ ይናገራሉ ሃይማኖታዊ ዝንባሌም የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህርይ ነው ስንል ምን ማለት ነው?

3.    ሃይማኖት የሰዎችን አመለካካትና ጠባይ ለመለወጥና ለመቃኘት ጠንካራ መሳሪያ እንደሆነ የተለያዩ መረጃዎች ያመለክታሉእርሱሶስ የሃይማኖት አባቶ ምን ቢያደርጉ የተሻለ ነው ይላሉ?

4.    የሃይማኖት አባቶች ቸርነትና ለጋሽነት የበጎነትና የነፃ አገልገሎት በመስጠት በፍትሕ በሰላምና ዕርቅ ጉዳዮች በመሰማራት ጠንካራ ማኅበራዊ ትሥሥር በመፍጠርና በሰዎች መካካል ድንበር ተሻጋሪ ቤተሰባዊነት በመገንባትም አስተዋጽኦ አላቸው ይላሉ?

5.    የሃይማኖት መሠረታዊ የጋራ ዕሴት ለሰው ልጅ በሙሉ ለመንፈሳዊ ሕይወት ብቻ ሳይሆን  ለምድራዊ ሕይወት ጭምር በጣም አስፈላጊ ነው ታድያ እንዴት ማስተማር ይገባል?

6.   ለሰው ልጅ ሰላማዊ አኗኗር የሚጠቅሙ በርካታ የጋራ ማኅበራዊ  ዕሴቶች ውስጥ የተወሰኑትን የጋራ ዕሴቶች  በተጨባጭ ይጥቀሱ?

7.   ሃይማኖት የጋራ ዕሴት መሆኑን በማጠበቅ የሚገኘውን ግለሰቦዊ በማኀበራዊነት ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ፋይዳ ለትምህርት እንዲውል እነ ማን ይሳተፉ?

8.   ሃይማኖት የጋራ ዕሴት መሆኑን ባለማወቅና ባለመጠበቅ በግለሰቦች በማኅበረሰብ በሀገር እንዲሁም በመላው ዓለም ሰላምና የሰው ልጅ አብሮ የመኖር ባህርይ ላይ የሚያስከትለው ሁከት፣ ኢፍትሐዊነት፣ ጥላቻ ፣ማስገንዘብ መፍታት  እንዴት ይቻላል?

9.   ሃይማኖቶች የሰው ልጅ በመጨው ዓለም ከሚኖረው ዋጋ በተጨማሪ  በዚህ ዓለም   

 ሲኖር በሚኖረው የርስ በርስ ግንኙነት ወሳኝ ሚናዎች ምንና ምን ናቸው ይላል?

10.       ሰው በአምልኮት ከፈጣረው ጋር የሚገናኝባቸው በማኅበራዊ ኑሮው ሰው ከሰው ጋርና   

     ከተፈጥሮ ጋር በሰላም የሚኖርባቸው መሣሪያ  ምድን ናቸው ይጥቀሱ?

§  ከዚህ መሠረታዊ ግንዛቤ በመነሳት በሃይማኖቶች መካከል ያሉ ሃይማኖታዊ የጋራ ዕሴቶን ምንነት በአጭሩ ከላይ የተጠቀሱት  10 መጠይቆች ስለ ሃይማኖት እና

§  ሰላም ማለት በስምምነት፣ በፍቅር፣ በአንድነት፣ በተመሳሰብ፣ በመከባበር፣ የመኖር ውጤት ጠቃሚነቱን ከ5 ገጾች ባልበለጠ አስተያየቶትን ያዳብሩ

1.   እውነት የቃል (የንግግር) ነው?

2.   እውነት የሥራን (ተግባር)፣ የሐቀኝነት ነውን?

3.   እውነት ሐሳብን እና (ዕቅድን ) ይገልጻል?

4.   የእውነት ትክክለኝነት፣ ቀጥተኝነት፣ ሐቀኝነት፣ ታማኝነት፣ ተቀባይነትና እርግጠኝነት  እንዴት ይገለጽ?

5.   ትእውነት በሃይማኖት አስተምህሮ ከፍተኛ ቦታ ይሰጠዋል እርሶ እዴት እውነትን ይገልፁታል?

6.   እንደ ሃይማኖቶች አስተምህሮት እውነት በእራሱ የመጨረሻ ግብ ነው ብለው ያምናሉ እንዴት?

7.   እውነተኝነት በራሱ የመተማመን፣ የአዋቂነት፣ የቅንነት፣ የመልካም ሰውነት፣ የጀግንነት፣ የርኁርኁነት፣ አውንታዊነት፣ ሚዛናዊነትና የነፃነት  መገለጫ ነው ካሉ እንዴት ይገለጻል?

8.   እውነተኛ ሰው  በእውነት ላይ ከፍተኛ አመኔታ ስላላው እውነት ይናገራል፣ እውነትን ይሠራል እንጂ እውነትን በግድ ተቀበሉ አይልም፣ ስለእውነት አያታልልም ወይም አያስመስልም መልካምነቱ እንዴት ይገለጻል?

9.   ወሸተኛ ከንፈር በእግዚአብሔር ዘንድ አጸያፊ ነው፣ እውነትን የሚያደርጉ ግን በርሱ  

    ዘንድ የተወደዱ ናቸው” የሚለው በምን ላይ ነው?

10.       ፍትሕ ከእውነትኛነት ከሰላም ጋር ቁርኝነት እንዳለው የሃይማኖት ሊቃውን ያስረዱናል   

 ከቅዱሳት መጻሕፍት ይጥቀሱ? 

11.       እውነት ከተያዘ ፍትሕ አይጓደልም፣ እወነተኛ ሰውም ቅን ፈራጅ ሚዛናዊ ወይም ፍትሐዊ ነው ብለን ካልን በእነዚህ       ከላይ በተቀመጡ 11 ጥያቄ መሠረት መልሶት ከ5 ገጾች ባልበለጠ ይጻፉ?

1.     ፍትሕ ሲነሣ በአንተ ሊሆን የማትወደውን በሌላው ላይ አታድርግ የሚለው ፍትሐዊ ወርቃማ መመሪያ በሁሉም ቅዱሳት መጻሕፍት መገለጡ ልናስተውል ይገባል በዚህ መሠረት በየትኛው የመሐፍ ቅዱስ ምዕራፍና ቁጥር ነው የተጠቀሰው?

2.    ፍትሕ ከእውነተኛነትና ከሰላም ጋር ቁርኝነት እንዳለው የሃይማኖት ሊቃንት ያስረዱናል እንዴት ሆኖ?  

3.    ፍትሕ ካለ ሰላም አለ ፍትሕ ከሌለ ሰላም የለም ሰላም የፍትሕ ፍሬ ነው ይላሉ እርሶስ ምን ይላሉ?

4.    ይቅር ባይነት ጠባይም የአማኞች እንዲሆን ቅዱሳት መጻሕፍት ያስተምሩናል ይቅርታ ሰላም እንዳይደፈርስና ዕርቅ እንዳሰፍን ፍትሕ እንዳይጎድል ጥላቻና ልዩነተ ንዳይነግሥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ብለው ካሉ እንዴት?

5.    ይቅርታ በይቅርታ ጠያቄና በ-ይቅርታ ባይ መካከል ያለ ትልቅ ክፍተት ነው የሚሉትካለ?

6.   ይቅርታ ባዮች ፍትሐዊ፣ ቅን፣ የፍቅርና የሰላም ሰዎች ናቸው ሰዎች  ብለው ይላሉ ምክንያቱስ?

7.    ይቅርታ ካለ ጠበኝነት፣ ቂም፣ በቀል፣ ቅንዓት፣ የሉም ማለት ነው እንዴት ሆኖ ይግለፁ?

8.    እግዚአብሔር አምላክ ሰዎች የይቅርታ ባለቤቶች እንዲሆኑ ፈቃዱ ነው ግብዞችና ትምክህተኛች እንድንሆን ግን አይፈቅድምየሚለውን ከመጽሐፍ ቅዱ በማገናኘት ይብራሩት?

9.   ለሰዎች ስሕተታቸውን ይቅር ብትሉ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ኃጢአታችሁ ይቅር ይላችኋልና፣ ለሰዎች ግን ስሕተታቸውን ይቅር ባትሉ የሰማይ አባታችሁ ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም ይቅር የምንለው ማነው እንዴትስ ነው?

 

1.  ሃይማኖቶች ተከታዮቻቸው የሆኑ ምእመናንን ለበጎ ነገሮች ታዛዥ እንዲሆኑ ለክፉ ነገሮች ደግሞ እምቢተኛ እንዲሆኑ  ከአማኞች ምን ይጠበቃል ይላሉ?

2.  ከሃይማኖት ተቋማት ሰዎች ለቤተሰብ ታዛዥነት፣ መልካም ለሆኑ ለማኀበራዊ ሕግጋት ተገዥነት እንዲኖራቸው ከትምሕርት ቤቶች ምን ይጠበቃል?

3.  አባትህን እና እናትህን አክብር፣ አታመንዝር፣ አትስረቅ፣ በሐሰት አትመስክር፣ የባልጅራህን? አትመኝ፣ ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ የሚሉት ትእዛዞች ጥቅሱን በማስቀመጥ ይበራሩ?

4.  ሰላም፣ ፍቅር፣ ደስታ ፍትሕና ብልጽግና መከባበር ሰብዓዊነት ነው ብለው ያምናሉ?

5.  የሥነ ምግባር መርሆዎች የሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ዕሴቶች ምንጮች በመሆናቸው ጠቀሜታቸው ለማነው ለአገር ለቤተሰብ ለሁሉም ለተወሰኑ ?

6.  ሃይማኖታዊ የሥነ ምግባር መመሪያዎች በአብዛኛው እንዲተገብሩ የሚጠብቁት በግለሰብ ደረጃ፣ በሃይማኖት አባቶች በቤተ ሰብ፣ በወጣቶች በማህበረ ሰብ?

7.  በሥነ-ምግባር ዝርዝር ውስጥ የተጠቀሱት መመሪያዎች እንዲጠበቁ ምን መደረግ አለበት ይላሉ?

8.  ማንኛውም ግለሰብ ከሌላው ጋር በሚኖረው መልካም ግንኙነት ምክንያት የተሻለች አገር እንድትኖር የሥነ-ምግባር መርኅ ማለትም ሰላማዊነት ሰውን ማክበር፣ ለቤተሰብ ተገቢውን ትኩረትና ድጋፍ መስጠት የሚኖረበት አካባቢ ለሰብዓዊነት በአምላክ ለተፈጠሩ ሁሉ ምቹ ማን ምንመሥራት አለበት ይላሉ?

9.  በግለ ሰብ ወይም በህብረተሰብ ደረጃ መሆን የለባቸውም የሚሏቸውን ጠባዮች፣ እሴቶች፣ ልምዶች ይዘርዝሩ?

10.  በሕይወትዎ የይቅርታ ልምድ ተግባራዊ ለማድረግ ይሞክሩለጉድለታችንና ለችግሮቻቸን መፍትሔዎች ምን ሊሆን እንደሚችል ከ5 ገጽ ባልበለጠ ይጻፉ?

11.    በሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ዕሴቶች ተኮትኰተው ያደጉ ሕፃናት ለኅብረተሰብ ሁለንተና ደኅንነትና እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል በምንና በምን ይጠቅማል ይላሉ?

12.  በሃይማኖት እና የሥነ-ምግባር መርኆዎች ከተጠበቁ፣ ፈጣሪን የሚፈራ፣ ለሀገር የሚጠቅም፣ በማኅበሰቡ ውስጥም ታማኝና  አርአያ የሚሆን ትውልድ መፍጠር ይቻላል ካሉ እንዴት? ያብራሩ?

      ከላይ የተጠቀሱት ሁሉም ስለ መልካም ሥነ -ምግባር እና የግብረ ገብ ትምህርት 

     ጠቃሚነት ከ5 ገጽ ያልበለጠ አስተያየትዎትን ያዳብሩ

 

1.     ሰው ጥሩም ይሁን መጥፎ በነፃነቱ የመረጠው ምርጫ ነው?

2.    የሰው ልጅ የፈለገውን የማድረግ ነፃነት አለው ሲባል ገደብ የለሽ  ማለት  ነው?

3.    የሰው ልጅ ነፃነት በአቅሙ በማንነቱና በልዩ ልዩ ሰብዓዊ ሕግጋት የተወሰ ነው ብለው ያምናሉ እንዴት?

4.    ነፃነት የሚከበረውም የሌሎችን መብትና ነፃነት እስካከበሩ ድረስ ብቻ ነው  ካሉ ምክንያቱን ይግለፁ?

5.    ነፃነት ከተፈጥሮ ሕግ፣ ከማኅበረሰብ ሕግና ከእውቀት ጋር የጠበቀ ግንኙነት አለው ይላሉ ?

6.   ያለሕግና ገደብ የሚሰጥ ነፃነት ያልተገራ ፈረስን ያለልጓም እንደመጋለብ ይቆጠራል የሚለው ብሂላዊ አነጋገር እንዴት ይገለጻል?

7.    በፊታችሁ ሕይወትንና ሞትን በረከትንና መናገርም እንዳስቀመጥሁ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ አስመሰክራለሁ  በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍ ይገኛል?

8.    ከተፈጠሩት ፍጥረታት በሙሉ ሰው እጅግ በጣም የከበረ ነው ማረጋገጫው ምንድ ነው?

9.   የሰው ዘር በሙሉ ከአንድ ምንጭ የተቀዳ መሆኑን ቅዱሳን መጻሕፍት ያረጋግጣሉ በየትኛው የመጽሐፍ ክፍሎች ነው የተጠቀሱት?

10.  ሰው ሁሉ በተፈጥሮ እኩል ነው በቀለም፣ በቋንቋ፣ በፆታ፣ በዕውቀት፣ በእድሜ፣ ወዘተ ቢለያይም የሰው ዘር አንድ ነው ብለው ይምናሉ?

የሰው ልጅ ነፃነት ከሚለው ጽንስ ሐሳብ ያለዎትን ማንነት እንዴ ይመለከቱታል? ስለ ሕይወትዎ ምን ግንዛቤ ከመጽሐፉ ምን  አግኝተዋል? ከሌሎች ጋር ያወያዩበት

ከዚህች ትከክለኛውን  የአለመግባባት የግጭት አፈታት ጥያቄዎችን ይመልከቱ የመጣበትን ምንጭ ማጥናት ያስፈልጋል አንዳንዱ የሥራ አመራር ሊቃውንት ችግሩን ማወቅ ማለት የችግሩን መፍትሔ ለማግኘት ግማሽ መንገድ መሄድ ነው የሚሉት ለዚህ ነው በአብዛኛው አለመግባባትን የማቃለል ሥራ ላይ ሲውሉ የሚታዩት የሚከተሉት በአግባቡ ተረድተው ለመሥራት ይሞክሩ

1.     አመቻችነት ይህ ተግባር የተሰጠው ሦስት ወገን ያልተግባቡ ወገኖቸ እንዲገናኙ  

            አመቺ ሁኔታ ለምሳሌ ጊዜ ቦታ ሌሎች አስፈላጊ ነገሮች ከመፍጠር    

           ውጪ ሌላ ድርሻ አላቸው ይላ እንዴት? ያብሩት?

2.     ማስገደድ ማስገደድ ልዩነት ወይም አለመግባባት በተፈጠረ ጊዜ ያንዱን ወገን   

          ፍላጎት ወይም ውሳኔ በሌላው ላይ በግድ መጫን ይቻላልን?

3.    . የአብላጫ ውሳኔ መፈጸም የዚህ ዓይነት ዘዴ አለመግባባቱን አብዛኞች ድምፅ  

                                በሰጡበት መንገድ መፍታት ችግሩን ይፉቷዋል ብለው

                              ያምናሉ አው ካሉ እንዴት ?

4.    ዕርቅ ይህ ዘዴ ሁሉቱን ወገኖች ሊያግባባ የሚችለውን መፍትሔ ብቻ  

   በመውሰድ  ከሁለቱም ወገን የሚቀረው ቀርቶ ስጥቶ መቀበል በሚል   

    መርሕ ማለት ምን ማልት ነው?

5.    መቀላቀል ይህ ዘዴ የተቃራኒውን ወገን አመለካከት ወይም ዓላማን በመቀበል  

        መተባበር ማት ነው ከተቃራኒው ጋር መተባበር ያለ ምንም መርህ             

          ይቻላል ወይ እንዴት?  

6.   ማለሳለስ ሁሉት ተቃራኒ ወገኖች የልዩነት ነጥቦቻቸውን ሆን ብልው ችላ በማት

       የሚያግባባቸውን ንጥቦ ብቻ እየለዩ አብሮ ለመቀጠል መወሰን ሲባል   

         ምንያታዊነቱ ምድን ነው ይሉ?

7.    መራቅ ይህ ከነገር ጦር እደሩ በተሰኘው አባባል  የሚገለጽ ይመስላል፣ ይህ     

     ዘዴ አለመግባባት ሊፈጥር ከሚችል ሁኔታ ሆን ብሎ መሸሸ ማለት ነውን?

8.    አለመግባባትን ለማቃለል ሶስተኛ ወገን ምን ድርሻ እንደሚኖረው ያውቃሉ?

9.   አለመገባባትን ለማቃለል የሚያስችል ብቃት ምን እንደሆነ ግንዛቤ ወስደዋል ከተረዱት ምን ድን ነው ?

10.   አለመግባባትን ለማቃለል የሶስተኛ ወገን ሚና ምንድን ነው ይላሉ?

11.    አለመግባባትነ ማቃለል ከሁለቱ የማይግባቡ ወገኖች አልፎ የሦስተኛ ወገንን አስፈላጊነት ምንድን ነው

12.  ሁለት ሊግባቡ ያልቻሉ ወገኖች በራሳቸው ጥረት ችግራቸውን ማቃለል ካልቻሉ ወደባሰ ሁኔታ እንዳይሸጋገር በራሳቸው ጋባዥነት ወይም በሌላ ጠያቂነት ሦስተኛ ወገን ሊገባበት ይችላል? እንዴት?

13.  ደራዳሪነት የአደራዳሪነት ተግባር በአብዛኛው ሁለት ወገኖች ተገናኘተው

         እንዲወያዩ መርዳት ብቻ  ነው ወይስ?

14.  ገላጋይነት ገላጋይነት ወይም በእንግሊዝኛው አርቢትሬሽን የምነለው ሦስተኛ  

       ወገን የሁለቱንም ወገኖች የአለመግባባት መነሻ ምክንያቶች መከራከሪያ      

        ነጥቦች ወዘተ ካደመጠ በኃላ ምን ያደርጋልን?

15.  አለመግባባት በማቀለል ተግባር የሦስተኛ ወገን መግባት በሁሉቱ ወገኖች ውሳኔ     

              ወይም ከሁለቱ አንዱ በሚያቀርበው ሃሳብ ያለበለዚያም በሦስተኛ ወገን     

               ሊመጣ የሚችል ነው ለአንድ ያለመግባባት ሁኔታ የትኛው የሦስተኛ   

               ወገን  ዓይነት ነው የሚጠቅመው?

16.  እነዚህና ሌሎችም የሚጠቅሙ ጥያቄዎች በማዳበር አለመግባባትን በጠቃሚ ሁኔታ ማቃለል ይቻላል ለሀገር እድገትም ጠቃሚነቱ ከፍተኛ ነው ስለዚህ ከ5 ገጽ ባልበለጠ ለመመለስ ይሞክሩ

 

 

አባ ሳሙኤል

በኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ

                                                         አዲስ አበባ

ለመላው ኢትዮጵያውያን በሀገር ውስጥና በውጭ ዓለም ለምትገኙ ሁሉ

ልዑለ ባሕርይ ቸሩ እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ከማርቆስ ወንጌላዊ

 ወደ ዘመነ ቅዱስ ሉቃስ ዜናዊ 2011ዓ.ም በሰላም፤ በጤና፤ በሕይወት ሁላችንንም አደረሰን!!

                                                    ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ፤

                                                  ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም፤

                                                  ወይረውዩ አድባረ በድው (መዝ. 64÷11-12)፡፡

በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃዋለህ፣ ምደረበዳውንም ገዳማት ልምላሜውን አግኝተው ደስ ይላቸዋል በበረኃ ያሉት ተራራዎች ሁሉ ዝናሙን ይረካሉ፡፡ ኮረብታዎችም ደስ ብሏቸው ልምላሜውን እንደዝናር ይታጠቃሉ፡፡ ቆላውና ደጋው ስንዴውንና የተለያየውን እህል ይሞላል፡፡

ወወሀብኮሙ ሲሳዮሙ ለሕዝበ ኢትዮጵያ (ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው) ተብሎ በነቢየ  እግዚአብሔር ቃል በተነገረው መሠረት ኢትዮጵያን በረድኤት ጐበኘሀት (ወአብዛኅኮ ለብዕላ) በሚመጡ ዘመናትም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለጠግነት ይሰጠን ዘንድ ነው፡፡ ኤፌ. 2፥6

ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ “አእትቱ እምላዕሌክሙ ግዕዘክሙ ዘትካት በእንተ ብሉይ ብእሲ ዘይማስን በፍትወተ ስሒት፤ ሐድሱ መንፈሰ ልብክሙ፡፡ ወልበስዎ ለሐዲስ ብእሲ ዘሐደሶ እግዚአብሔር በጽድቅ ወበርትዕ ወበንጽሕ” በተሳሳተ ምኞት የተበላሸውን አስቀድሞ ትኖሩበት የነበረውን አሮጌውን ሰውነት ከእናንተ አርቁ፡፡ ልቡናችሁን በእውቀት አድሱ፤ በእውነት፣ በጽድቅና በንጽሕና እግዚአብሔርን ለመምሰል የተፈጠረውን አዲሱን ሰውነት ልበሱ” (ኤፌ. 4÷22-24)፡፡

ይህ ዓመት በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር 2011 ዓ.ም ሲሆን በአውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር 2018 ነው፡፡ ይህ ልዩነት የመጣው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የምዕራብ አብያተ ክርስቲያናት የተለያየ የዘመን አቆጣጠር ስለሚከተሉ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሌላው የክርስትና ዓለም የተለየ የራስዋ ብቻ የሆነ የዘመን አቆጣጠር መንገድ አላት፡፡ ይህም የዘመን አቆጣጠር መጽሐፍ ቅዱስን በተለይም መጽሐፈ ሄኖክንና ኩፋሌን መሠረት ያደረገ ነው፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ታሪክ መረዳት እንደሚቻለው ጥንታዊው የጁሊያን የዘመን አቆጣጠር ከአሁኑ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የዘመን አቆጣጠር ተመሳሳይነት ነበረው፡፡ ሆኖም የምዕራብ ቤተ ክርስቲያን በ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ የጁሊያን የዘመን አቆጣጠር የተባለ ሌላ የዘመን አቆጣጠር ጀመረች፡፡ ይህም የግሪጎርያን የዘመን አቆጣጠር ሲሆን የ4 ዓመት የአቆጣጠር ልዮነት ስሕተት እንዳለው ራሳቸው አውሮፓውያን ያምናሉ፡፡

ያም ሆነ ይህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ በያዝነው እና

በምንጠቀምበት ባሕረ ሀሳብ በተባለው የዘመን አቆጣጠር ስልት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ታላቅ አገልግሎት እያቀረበች ትገኛለች፡፡ አሁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ዝም ቢሉ ለዓመቱ የዘመን መቁጠሪያ (ካሌንደር) ማዘጋጀት የሚችል ሰው ማግኘት ያስቸግራል፡፡ ለሚመጣው ዓመትም የዐቢይ ጾም፣ የሰኔ ጾም መቼ እንደሚገባ እንዲሁም የሆሳዕና፣ የስቅለት፣ የፋሲካና የዕርገት በዓላት መቼ እንደሚውሉ ለመናገር የሚችል ሰው አይኖርም፡፡ የእኛ ኦቶዶክሳዊ የተዋሕዶ ሊቃውንት የመሬትን፣ የፀሐይንና የጨረቃን እንቅስቃሴና ዑደት በልዩ የባሕረ ሀሳብ አቆጣጠር እያሰሉ የዕለታትን፣ የወራትን፣ የዓመታትንና የበዓላትን ቀናት መዋያ ለመናገር ጥልቅና ሰፊ የሆነ እውቀት አላቸው፡፡

‹‹የተመረጠችውን የእግዚአብሔርን ዓመት እሰብክ ዘንድ ላከኝ››

ይህ ቃል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረው ቃለ ወንጌል ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ  ክርስቶስ ለሰው ሲል ሰው የሆነ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደመሆኑ መጠን ይህን ቃል የተናገረው ሰው ሆኖ ወደዚህ ዓለም ለመምጣት የፈቀደበትን ምሥጢር ግልጽ በአደረገበት የትምህርት ክፍል ነው፡፡

በአንድ የሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ሲገባ ያነብ ዘንድ የቅዱስ ኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፡፡ መጽሐፉን ሲገልጥም ‹‹የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፡፡ ስለዚህ ቀብቶ (ማለት ከሥጋ ጋር አዋሕዶ) ለድሆች የምሥራችን እነግራቸው ዘንድ፤ ለተማረኩትም ነጻነትን እሰብከላቸው ዘንድ፤ ያዘኑትን ደስ አሰኛቸው ዘንድ፤ ዕውሮችም ያዩ ዘንድ የተገፉትንም አድናቸው ዘንድ፤ የታሰሩትንም እፈታቸው ዘንድ፤ የቆሰሉትንም እፈውሳቸው ዘንድ የተመረጠችውንም የእግዚብሔርን ዓመት እሰብክ ዘንድ ላከኝ›› የሚል ቃል አገኘ፡፡ ይህን የትንቢት ቃል የተናገረውም ነቢዩ ቅዱስ ኢሳይያስ ነበር፡፡ ኢሳ.61፥1-2፡፡ ጌታችን ይህን ቃል ከአነበበ በኋላም ‹‹የዚህ መጽሐፍ ቃል ዛሬ በጆሮዋችሁ ተፈጸመ›› ሲል እንደ ተናገረ፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት ስለሆነ በእሱ ትምህርትና ተአምራት፤ ስቅለትና ሞት በእርግጥ በኀጢአት ምክንያት ከሥጋዊና መንፈሳዊ በረከት ነዳያን የነበሩ በረከተ ሥጋንና በረከተ ነፍስን አግኝተዋል፡፡ በኀጢአት ምክንያት የዲያብሎስ ምርኮኞች የነበሩ ነጻ ወጥተዋል፡፡ በተፈጥሮ ያገኙትን ክብር አጥተው ኃዘንተኞቸ የነበሩ ያጡትን በማግኘታቸው ለዘለዓለማዊ ደስታ ዕድል ፈንታቸው ሁኗል፡፡ ቀን የጨለመባቸው ዕውራነ ሥጋና ዕውራነ ነፍስ የሆኑ መንፈሳዊና ሥጋዊ ብርሃንን አግኝተዋል፡፡ የዓለማዊና ሥጋዊ ፈቃድ ተቸናፊ የነበሩ አቸናፊ ሁነዋል፡፡ የኃጢአት እሥረኞች የነበሩ በይቅርታ ከእስራት ተፈትተዋል፡፡ በኃጢአት ደዌ የቆሰሉ ፈውስን አግኝተዋል፡፡ ይህ ሁሉ በረከት የተገኘው በክርስቶስ ስለሆነ ነቢዩ ቅዱስ ኢሳይያስ ‹‹የተመረጠችው የእግዚብሔር ዓመት›› ያላት ይህ ሁሉ ጸጋ የተገኝባት የድኅነት ቀን ናት፡፡ ዘመነ ድኅነት ማለት በግልጽ አነጋጋር ዘመነ ክርስትና ማለት ነው፡፡

የዘመን መለወጫን በዓል፣ የአዲሱን ዓመት በዓል የምናከረው

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንቶስ መልእክቱ ‹‹በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ፤ በመዳንም ቀን ረዳሁህ›› የሚለውን የነቢዩ ቅዱስ ኢሳይያስን ቃል ከጠቀሰ በኋላ ‹‹እነሆ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፦ የመዳን ቀን አሁን ነው›› 2. ቆሮ. 6፥2 ይላል፡፡  በቅዱስ መጽሐፍ የተመረጠች የእግዚአብሔር ዓመት፣ የተወደደ ሰዓት፣ የመዳን ቀን›› የሚል የተለያየ ስያሜ የተሰጠው አሁን እኛ ለምንኖርበት የክርስትና ዘመን መሆኑ ግልጽ ከሆነ ዘንድ በዚህ የድኅነት ዘመን ከሞተ ሥጋና ሞተ ነፍስ፣ ከደዌ ሥጋና ከደዌ ነፍስ፣ ከድቀተ ኃጢአትና ከአምላካዊ ፍርድ መዳን ካልተቻለ መኖር ትርጒም የለውም፡፡ ምንተ ይበቊዖ ለሰብእ ለእመ ኵሎ ዓለመ ረብኀ ወነፍሶ ኀጐለ (ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል) ማቴ.16፥26

አሁን ለዚህ ሁሉ ሐተታ መነሻ የሆነው  በዚሁ ጽሑፍ መግቢያ ላይ የተጠቀሰው ቃለ ወንጌል ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ የዘመን መለወጫ በዓልን የምታከብረው ይህን ቃል  በማስተማር  በመተግበር ነው፡፡ ‹‹የተመረጠችው የእግዚብሔርን ዓመት እሰብክ ዘንድ ላከኝ›› የሚለው ቃል ከክርስቶስ ልደት በኋላ ያለው እያንዳንዱ ዓመት የተመረጠ የእግዚአብሔር ዓመት መሆኑን የሚያረጋግጥ ኃይለ ቃል ነው፡፡ ይህም ማለት ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም ከመጣ በኋላ ቀኑም ሆነ ሰዓቱ የድኅነት ሰዓት ሁኗል ማለት ነው፡፡

በመሆኑም አዲስ ዓመት ብዙ ነገሮችን ያስታውሰናል፡፡ በዚህ በአዲሱ ዓመት እና ባለፈው ዓመት  የሠራነውን፤ የፈጸምነውን ነገር ሁሉ እናስታውሳለን፡፡ በአዲሱ ዓመት ባለፈው ዓመት የተሠራው ሥራ ሁሉ ይገመገማል፡፡ በአለፈው ዓመት ስለተሠራው ሥራ ሪፖርት (ዘገባ) ይቀርባል፡፡ እያንዳንዱም ሠራተኛ በአለፈው ዓመት ውስጥ ስለሠራቸው ሥራዎች ሁሉ ሪፖርት (ዘገባ) ለቅርብ አለቃው ያቀርባል፡፡ ይህ የሰለጠነው ዓለም አሠራር ነው፡፡ በዚህ ዓይነት የእያንዳንዱ ሠራተኛ ሥራ በአዲሱ ዓመት ይገመገማል፡፡

ባለፈው ዓመት መልካም ሥራ ከተሠራ፣ ይህ መልካም ሥራ በሚቀጥለውም ዓመት በተሻለና በበለጠ ሁኔታ እንዲቀጥል ይደረጋል፡፡

ባለፈው ዓመት 1ኛ) ስሕተት ከተሠራ፣

2ኛ) እንዲሠራ በታቀደው መሠረት ሥራው ካልተከናወነ፣

3ኛ) ሥራው ግቡን ካልመታ በአጠቃላይ ያለፈው ዓመት ስሕተትና ያለፈው ዓመት ድክመት በሚመጣው ዓመት እንዳይደገም ትኩረት ይሰጠዋል፡፡ ባለፈው ዓመት ስሕተት ወይም ጉድለት የሠሩ ሁሉ ያ ስሕተት፣ ያድክመት፣ ያጉድለት በአዲሱ ዓመት እንዳይደገም የሚመለከታቸው ሁሉ ታላቅ ጥንቃቄ ያደርጋሉ፤ ቃልም ይገባሉ፡፡ ሠራተኞች ሁሉ፣ አለቆችም ሆኑ የበታች ሠራተኞች እንደገና በአዲሱ ዓመት መልካምና የተሻለ ሥራ ለመሥራት አዲስ የሥራ ዕቅድና አዲስ የሥራ ፕሮግራም ያወጣሉ፡፡ እንዲሁም ለሥራ ማስኬጃ፣ ለወጭ መሸፈኛ የሚሆን በጀት ይዘጋጃል፡፡ ይህ እንግዲህ በሥጋዊ ሕይወታችን፣ በሥጋዊ ሥራችን የምንፈጽመው ተግባር ነው፡፡

በመንፈሳዊ ሕይወታችንስ ምንድን ነው የምናደርገው? መጀመሪያ ባለፈው ዓመት ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ምን ሠርተናል? ምን አከናውነናል? እያንዳንዳችን ባለፈው ዓመት ስለሠጠነው መንፈሳዊ አገልግሎት ለፈጣሪያችን ወይንም ለሕሊናችን ሪፖርት (ዘገባ) ማቅረብ አለብን፡፡ ለሚመጣውም ዓመት ዕቅድ ማውጣት አለብን፡፡ ምናልባት ባለፈው ዓመት በመንፈሳዊ ሕይወታችን ተገቢ አገልግሎት አልሰጠን ይሆናል፡፡ በእግዚአብሔር ሕግና ትእዛዝ አልሄድን (አልተጓዝን) ይሆናል፡፡ ይህንን ሁሉ ገምግመንና መርምረን ያለፈውን ዓመት መጥፎ ሥራዎቻችንን ሠርተንበት ከሆነ በአዲሱ ዓመት ደግመን እንዳንሠራ መጠንቀቅና ለእግዚአብሔር ቃል መግባት አለብን፤ ጥንቃቄም ማድረግ አለብን፡፡ በአዲሱ ዓመት መልካም ሥራና የጽድቅ ሥራ እንድንሠራና እግዚአብሔርን እንድናስደስት ዕቅድ ማውጣት አለብን፡፡ ከምናገኘውም ገቢ ሁሉ ለእግዚአብሔር አሥራት ለመክፈል እና ለተቸገረውም ለመርዳት ላዘነው ለማጽናናት ዕቅድ ማውጣት አለብን፡፡ ይህንንም ለማድረግ ለአምላካችን ቃል መግባት ይኖርብናል፡፡

ዘመኑ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፤ እድፈትም፤ ለሌለበት፤ ለማያልፍም ርስት እንደምሕረቱ ብዛት የመንፈሳዊ እውነተኛውን ሃይማኖት ለመጠበቅና ለማገልገል  ለሀገርና ለሕዝብ የሚጠቅም ሥራ እንሠራበት ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡

ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ቅዱስት ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ካህናት ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ “ኃረየ ፲ወ፪ተ ሐዋርያተ ሤሞሙ ኖለተ ወወሀቦሙ ሀብታተ ይስብኩ ቃለተ ሠለስተ አስማተ አሐደ መንግሥተ (አሥራ ሁለት ሐዋርያትን መረጠ፤ ለሕዝብ ጠባቂ አድርጐ ሾማቸው፤አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ (ሦስት ስሞችን) አንድ የእግዚአብሔርን መንግሥት ዐሠርቱ ቃላትን፤ ያስተምሩ ዘንድ እግዚአብሔር አምላክ አዘዘ በማለት በገለፀው መሠረት የተጣለብንን እና የተሰጠንን ሐላፊነት በሚገባ ተወጥተን የመንግሥቱ ወራሾች እንሆን ዘንድ ቅዱስ አምላክ ይርዳን፡፡

በየመሥራያ ቤቱ ሐላፊነት የተጣለባችሁና የተሰጣችሁ ክርስቲያኖች በሙሉ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ኢትኰንኑ ከመ ኢትትኰነኑ፡፡ እስመ በኵነኔ ዘኰነንክሙ ትትኴነኑ አንትሙ፡፡ ወበመስፈርት ዘሰፈርክሙ ይሰፍሩ ለክሙ፡፡ (እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈርድባችኃልና በምትሰፍሩበትም መስፈርያ ይሰፈርባቸኃል ማቴ.7፥1 በማለት አዟልና ፍርድ እንዳይጔል ደሀ እንዳይበደል በፍትሐዊነትና በቅንነት በታማኝነትና በትህትና በእኩልነት ሕዝብ እንድታስተዳድሩ በጐ ሕሊና ብሩህ አእምሮ ቀና አመለካከቱን እግዚአብሔር አምላክ ያድላችሁ፡፡

በመማርና በማስተማር ላይ የምትገኙ ሁሉ፦ ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ፡ በዮሐንስ ድጓው ጥበብ ትይኄስ እምብዘኅ መዛግብት፣ ኢወርቅ ሤጡ፣ ወኢብሩር ተውላጡ፣ ጥበብ ክቡራት ዕንቊ መሠረታ፣ አልቦ ለጥበብ ዘይመስላ (በዚህ ዓለም ዕውቀትን የሚስተካከላት የሚወዳደራት የለም፡፡ ስለዚህ ከብዙ ሀብት ዕውቀት ትበልጣለቸ፡፡ ወርቅም፣ ብርም፣ አልማዝም፣ቢሆኑ አይስተካከሏትም፡፡ የጥበብ መሠረቷ የከበረ ነው፡፡ ጥበብን የሚመስላት የሚስተካከላት የሚያክላት የለም እያለ በገለጸውና በአስተማረው መሠረት ለምታስተምሩትና ለምትማሩትም ቁሞ ነገር ትኩረት ሰጥታችሁ ተገቢውን የምርምር ውጤት በማስገኘት ሀገራችንና ሕዝባችን በተሻለ የኑሮ ደረጃ እንዲኖር እንድታደርጉ የፈጣሪያችን ትዕዛዘ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

በግብርና ሙያ ላይ ላላችሁ ገበሬዎች “እግዚኦ ባርክ ፍሬሃ ለምድር፡፡ መሐሪ ወጻድቅ መኑ ከማከ ዘታርኁ ክረምተ በጸጋከ፡፡ ነፍስ ድኅንት ወነፍስ ርህብት እንተ ጸግበት ተአኩተከ፡፡” አቤቱ የምድርን ፍሬ ባርክ፡፡ በስጦታህ ክረምትን መልሰህ የምታመጣው ሆይ! እንደ አንተ ያለ ጻድቅና ርኅሩኅ አምላክ ማን ነው? የታመመች ሰውነት በተፈወሰች ጊዜ የተራበች ሰውነት በጠገበች ጊዜ ታመሰግንሃለች እያላችሁ አመስግኑ፡፡

የዘመነ ኦሪት መጨረሻ የዘመነ ሐዲስ መነሻ፤ ነቢይም፣ ሰማዕትም፣ ሐዋርያም በአጥማቂነቱ ካህን፤ የዓለምን ኃጢአት ይቅር የሚል ከእኔ በኋላ ይመጣል በማለቱ ነቢይ፤ ስለ ክርስቶስ ሕይወቱን በመስጠቱ ሰማዕት ከሆነው ከቅዱስ ዮሐንስ በረከት ረድኤት እግዚአብሔር አምላካችን ሁላችንም ያድለን አሜን!!

ስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘአብጽሐነ እስከ ዛቲ ዕለት፤ ከዚህ ዘመን፣ ከዚህ ዕለትና ከዚህ ሰዓት ያደረሰን ልዑል እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን፡፡

ቸሩ ፈጣሪያችን መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዘመኑን የሰላም፣ የዕድገት፣ የጤናና የብልጽግና ዘመን ያድርግልን፡፡ ለሀገራችንና ለቤተ ክርስቲያናችን እንዲሁም ለመላው ዓለም በሙሉ እውነተኛውን ሰላምና ፍቅርን ያድልልን፡፡

 

 

አባ ሳሙኤል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀጳጳስ

አዲስ አበባ

 

 

 

“መኑ ይከልአነ ፍቅሮ ለክርስቶስ„ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል?
1. መከራ ወይስ ጭንቀት፣ ወይስ ስደት፣ ወይስ ረሃብ፣ ወይስ ራቁትነት፣ ወይስ ፍርሃት፣ ወይስ ሞት ነው። ሮሜ 8፥35

2. “ኢትፍርህዎሙ ለአለ ይቅትሉ ሥጋክሙ”
“ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል
የማይቻላቸውን አትፍሩ ፣ ይልቅስ ነፍስንም
ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ„ ማቴ 10፥28
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ ስንኖርና የምንቀበለው መከራ ሁሉ ቢበዛ ከሥጋ ያለፈ እንዳልሆነ ነገር ግን በነፍሳችን ላይ ጠላታችንን አንዳች ማድረግ እንደማይችል አረጋግጦልና።
3. ቅዱስ ጴጥሮስም “ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኳን መከራን ብትቀበሉ ብፁዓን ናችሁ። ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ አትናወጡም ብሏል። 1ጴጥ. 3-14 ከዚም የተነሣ ሰማዕታት ለሥጋቸው ሳይሳሱ “እስም በእንቲ አሁ ይቅትሉነ ኩሎ አሚረ ወኮነ ከመ አባግዕ ዘይጠብሁ።„ ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፣ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን እያሉ ስለ ክርስቶስ ፍቅር እራሳቸውን ለሞት አሳልፈው ሰጥተዋል። ሮሜ 8፥35
ሐዋርያትና አብዛኛው በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩት ጳጳሳት ሊቃውንት በሰማዕትነት አልፈዋል።
በድንጋይ ተወግረው ተፈተኑ ሞቱ፣ በመጋዝ ተሰነጠቁ፣ በሰይፍ ተገድለው በሰማእትነት ሞቱ፣ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፣ ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፣ በዋሻና በምድር ጉዳጓድ ተቅበዘበዙ። እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ ዕብ.11፥37
4. ጸርሑ ጻድቃን ወእግዚአብሔር ስምዖሙ። ጢሞ. 3፥11 ጻድቃን ወደ እግዚአብሔር ለመኑ እሱም ልመናቸውን ሰማ ካገኛቸውም መከራ ሁሉ ያድናቸው ዘንድ መልአኩ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ እሳቱን አጠፋው። የሚፍለቀለቀውም ውኃ እንደ በረዶ ቀዘቀዘ። ይህንን ተአምር ከተመለከቱት ብዙዎቹ ኢ አማንያን በክርስቶስ አመኑ። ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት
5. “ይትአየነ መልአከ እግዚአብሔር አውዶሙ፤ ለእለ ይፈርህዎ„
ወያድኅኖሙ። የእግዚአብሔር መልአክ እግዚአብሔር በሚፈሩት ዙሪያ ይሰፍራል፤ ያድናቸውማል መዝ. 33፥7
6. ቅዱስ ጳውሎስም ሲገልጽው፣ “እነርሱ በእምነት ሁሉንም ድል ነሡ፣
ጽድቅን አደረጉ፣ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ የአናብስትን አፍ ዙጉ የእሳትን ኃይል አጠፉ ከሰይፍ ስልት አመለጡ ከድካማቸው በረቱ
ዕብ.11፥33 ሠለስቱ ደቂቅን፣ ቅዱስ ቂርቆስን፣ እነ ቅዱስ አግናጤዎስ ሐዋርያ ቅዱስ እስጢፋኖስ ማለት መሆኑን ግድ ይላል።
7. “እሰመ ለመላእክቲሁ ይኤዝዞሙ በእንቲአክ„
በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስላንተ ያዛቸዋልና እግርህም
በድንጋይ እንዳትሰናክል በእጆቻቸው ያነሡሃል “መዝ. 90፥1
8. “ከመ ይዕቀቡከ በኵሉ ፍናዊክ„
በመንገድ ይጠብቅህ ወዳዘጋጀሁትም ሥፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ
መልአኬን በፊትህ እሰዳለሁ በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ስሜም
በርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት። ማቴ.
4፥7
9. “ብዙኅ ሕማሞሙ ለጻድቃን። የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው„ ሐሥ13፥50
የአባቶቻቸውን ርስት አሳልፈን ለባዕድ አንሰጥም በማለት የተገደሉትን መጽሐፍ ቅዱስ ክብር ሰጥቶ መዝግቧቸዋል። እስራኤላዊው ናቡቴ 1ኛ ነገ. 20፥1-15 ስለዚህ ቅዱስት ቤተ ክርስቲያን በሰማያት ያለውን ርስት በሚያሰጥ እምነትን መስክረው መሥዋዕት ለሆኑ ተከታዮቿ የቅዱስት ቤተ ክርስቲያን ሰማእታት ናቸው።
1.0 “ወእምኵሉ ያድኅኖሙ„ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ግን ካገኛቸው
መከራ ሁሉ ያድናቸዋል። 2ቆሮ. 1፥5
በዘመነ ሰማዕታት እንደ ወርቅ በእሳት፣ በመከራ ተፈትነው በሃይማኖት ነጥረው ከወጡ ሰማዕታት አንዱ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ነው። የዚህን ሰማዕት ገድልና ታሪክ ከሌሎች ለየት አድርጎ በአስደናቂ ደረጃ ላይ የሚያስቀምጠው የዕድሜው ሁኔታ ነው። ቅዱስ ቂርቆስ የሦስት ዓመት ሕፃን ነበር። ለነገሩ እነ ቅዱስ ጊዮርጊስም ስማቸውን ከፍ ከፍ አድርጎ የሚያስተጋባው ገድላቸውና የሰማዕትነት ታሪካቸው እንደሚገልጸው ተጋድሎውን የፈጸሙት በሃያ ዓመት የወጣትነት ዕድሜአቸው ነው።
ከእነ ቅዱስ ቂርቆስ ባነስ የዕድሜ ደረጃ ባሉ ሕፃናትም የተፈጸመ ብዙ የምስክርነትና የምስጋና ታሪክ በቅዱሳት መጻሕፍት ተጽፎዋል።
11. መጥምቁ ዮሐንስ ለልዑል እግዚአብሔር አምልኮትና ስግደት ያቀረበው ገና በእናቱ ማህፀን ሳለ ነው (ሉቃ.1፥40)። እንዲሁም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ በገባ ጊዜ ዝማሬና ምስጋና ያቀረቡለት ከሁለት እስከ አምስት ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የነበሩት ሕፃናት ነበር። ሆሣእና ለወልደ ዳዊት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለመንግሥተ ሰማያት ወራሽነት ምሳሌ አድርጎ ያስተማረባቸው ሕፃናትን ነበር (መዝ. 60፥61-2 ማቴ. 19፥14) እንደ ሕፃና ካልሆናች
12. “ቅሩብ እግዚአብሔር ለየዋሃነ ልብ„ እግዚአብሔር አምላክ ቅን ልቡና እና ሃይማኖት ላላቸው ሰዎች ቅርብ ነው ልመናቸውን፣ ጸሎታቸውን፣ ስዕለታቸውን፣ ፈጥኖ ያሰማል።

ይቆየን

ከብፁዕ አቡነ ሳሙኤል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀጳጳስ
አዲስ አበባ

 

 

 

 

 

 

በተሰጠኝ የቀጠሮ ሰዓት  መሠረት ከቢሮአቸው ተገኘሁና እንድገባ ተፈቀደልኝ፡፡

ቢሮአቸውን ከፍቸ ስገባ ትሕትና እና ፍቅር በተሞላበት መልካም አባታዊ አቀባበል ከወንበራቸው ተነሥተው በያዙት መስቀል ባረኩኝና እንድቀመጥ ፈቀዱልኝ፡፡

በተደረገልኝ መልካም አቀባበል ፈጣሪ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በጸሎተ ሐሙስ የሐዋርያትን እግር ያጠበበትንና እናንተም  ለሌሎች ወንድሞቻችሁ እንዲሁ አድርጉ በማለት  በተግባር የፈጸመውንና የሠራውን ሥርዐት እንዳስታውስ አደረገኝ፡፡ ምንአለ ሌሎችም የሀገር፤ የሕዝብና የሃይማኖት መሪዎች እንደ ብፁዕነታቸው እንዲያገለግሉት ለሾማቸውና ሐላፊነት  ለሰጣቸው፤ ለሚያከብራቸውና ለሚታዘዛቸው ሕዝብ  መልካም ፊትና ጥሩ ቃል መስጠትን ከአቡነ ሳሙኤል ቢማሩ አልኩኝ፡፡ አንድ ሊቀ ጳጳስ ከተቀመጠበት ወንበር ተነሥቶ ባለጉዳይን ሲቀበል ማየቴና ለእኔም በተደረገልኝ የክብር አቀባበል ከምጠብቀው በላይ ሆኖ ስላገኘሁት በጣም ተደሰትኩ፡፡

እኒህ አባት ሚዲያዎች ብዙ ያሉላቸውና መጻሕፍቶቻቸው በአስገራሚ መረጃዎች የተሞሉ ስለመሆናቸው የሚነገርላቸው በብዙ ለመረጃ ቅርብ በሆኑ አማንያን ዘንድ ከሚታወቁትና ከፍተኛ የከበሬታ ማዕረግ ካላቸው አበው ሊቃነ ጳጳሳት መካከል አንዱ ከሆኑት የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ ጋር እነሆ እላለሁ፡፡

ሊቀ ጳጳሱ የዋዛ እንዳልሆኑ የነገሩኝ ወዳጆቸና ጓደኞቸ ልክ እንደሆኑ ተረዳሁ፤ አረጋገጥኩ፡፡ ምክንያቱም ከመጀመሪያው አነጋገራቸው ሁሉ በቁም ነገር የተሞላ፤ የሚገርም አገላለጽና አቀራረብ ነበር፡፡

ስለ ቤተ ክርስቲያን ማንነት የገለጹልኝን እነሆ፤

ቤተ ክርስቲያን የሥጋና የነፍስ ሀኪም ቤት፤ የእውቀት፤ የፍትሕና የሕግ መገኛ መሠረተ ሕይወት ነች፡፡ የታመሙ የሚፈወሱባት፤ያዘኑ የሚጽናኑባት፤በእየዕለቱ ብዙ ሕሙማነ ሥጋና ሕሙማነ ነፍስ ለህክምና የሚመላለሱባትና ደጅ የሚጠኑባት የኢየሩሳሌም ሰማያዊት ተምሳሌት ነች፡፡

ምእመናንና ምእመናት ከሊቅ እስከ ደቂቅ ጸበሉን ጠጥተውና ተጠምቀው፤ እምነቱን ተቀብተው፤ በመስቀሉና በገድሉ ታሽተው፤ ሱባኤ ይዘው፤ ንስሓ ተቀብለው፤ ክቡር ሥጋውንና ቅዱስ ደሙን ተቀብለው ምድራዊና ሰማያዊ ክብር የሚያገኙባት፤ በሥጋ በነፍስ በአእምሮ ከሚያስጨንቃቸው ነገር የሚላቀቁባት፤ ሁሉም ሰው እኩል እንዲገለገሉባት የተሰጠች በምድር ያለች ሰማያዊት የእግዚአብሔር ቤት ነች፡፡

በመሆኑም ሰዎች በዚህ ዓለም ያለውን ውጣ ውረድ፤ የደረሰባቸውን፤ ያጋጠማቸውን ችግርና መከራ፤ ስቃይኛ ፈተና፤ለሰው መንገር የከበዳቸውን ከባድና አስጨናቂ ነገር ሁሉ ለፈጣሪ ነግረውና ተማኅጽነው አምላክም ሰዎችን  የሃይማኖታቸውን ጽናትና የልባቸውን ቅንነት አይቶ ከመከራ ሥጋና ከመከራ ነፍስ የሚያድናባት ፍትሐ-አምላክ የሚገኝባት በከበረ ደሙ የመሠረታት ዘለዓለማዊ ሕይወትን የምታሰጥ እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕፁቂሃ የሆነች ምስአል ወምስጋድ ወምስትራየ ኀጢአት ማኅደረ መለኮት ደብተራ ቅድስት የመድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ቤት፤ ታቦተ ሕጉ ያለባት፤ ጉልላቷ ደሙን ያፈሰሰባት መስቀል የተተከለባት የክርስቲያኖች ቤት ነች፡፡

ጥንታዊት፤ ታሪካዊት፤ ሐዋርያዊት፤ ብሔራዊትና ርትዕት የሆነች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ውለታ ሳስብ ውስጤ ይረበሻል፡፡ ምክንያቱም ብዕር ቀርጻ፤ብራና ዳምጣ፤ ቀለም በጥብጣ፤ ለኢትዮጵያ ሀገራቸን ታሪክን፤ ቅርስን፤ ፍትሕን፤ መልካም አስተዳደግንና አስተዳደርን፤ ጥሩ ባህልንና ሥርዓትን፤ ርኅራኄ የተሞላበት መፋቀርንና መረዳዳትን፤ መከባበርንና ሰላምን፤ ነጻነትንና ክብርን  ጠብቃና አስጠብቃ ለትውልድ ያቆየች ቤተ ክርስቲያን ይህ ሁሉ ውለታዋ መገንዘብ ያስፈልጋል። ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን የሚጠሉ ሁሉ እርሷን ለመጉዳት በጠላትነት ሲረባረቡባት ማየት ቀና ልቡና እና ንጹሕ ኅሊና ላለው ሰው ምን ያህል ያሳዝናል!!

የወጣቶችን መልካም ሥነ ምግባር በተመለከተ የሠጡኝ ምክር

ወጣትነት አስቸጋሪ የሆነና ሊታሰብበት የሚገባ የእድሜ ክልል ነው፡፡ በመሆኑም የወጣትነት ዘመን በሃይማኖት ትምህርት፤ በመልካም ሥነ ምግባርና በእውቀት ካልተገራና ካልተገነባ እጅግ በጣም አስፈሪና አስጨናቂ፤ አደጋ ያዘለና የከበበው የእድሜ ክልል ነው፡፡ ወጣቶችን በዚህ የእድሜ ክልል ውስጥ በሥጋዊና በመንፈሳዊ እውቀት ካልገነባናቸው ብቻቸውን አይጎዱም፤ ብቻቸውን አያዝኑም፤ ብቻቸውን አይከስሩም፤ብቻቸውን አያነቡም፡፡ ኪሳራው ጉዳቱ ኀዘኑ ለቅሶው ውድቀቱ የቤተሰብ፤ የማኅበረሰብ ፤የቤተ ክርስቲያን፤ የመንግሥትና የሀገር በአጠቃላይ የሁላችንም ፈተና ነው፡፡ወጣቶችን ማገዝ ማለት ደግሞ ቤተሰብን፤ ማኅበረሰብን፤ ቤተ ክርስቲያንን፤ ሀገርን በአጠቃላይ ሁላችንንም መርዳት ነው፡፡

በዘመናችን ከዘመኑ ስልጣኔ ጋር በተያያዘ መልኩ የወጣቶችን በጎ ሐሳብና ተግባር የሚሰርቁ እጅግ በጣም ብዙ የሆኑ ዘመኑ የወለዳቸውና ያመጣቸው ጎጂ መጥፎና ዘግናኝ ክስተቶችና ነገሮች እየታዩ ነው፡፡ ሰው ዘመናዊነት በሚል ሰበብ በመታለል ከአምላኩ በመራቅና በመለየት ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ሞተ ሥጋና ሞተ ነፍስ አደጋ ወዳለበት የመጓዝ ተግባር በአንድ ሌሊት የተፈጠረ አይደለም፡፡ ክፉ አሳቢዎችና አድራጊዎች ይህችን ቅድስት የክርስቲያን ሀገር ቅዱስ የሆነ ባህሏን ለማጥፋት፤ እምነቷንም ለመሸርሸር ፕሮጀክት ቀርጸው  ለረጅም ዘመናት በሚያደርጉት ተንኮል ነው፡፡

ስለዚህ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ ማስተዋልን፤ ክብርንና ሞራልን ጠብቆ መኖርን፤በሃይማኖትና በመልካም ሥነ ምግባር መጽናትን፤ ወደ ተረጋጋ አእምሮ መመለስንና መታመንን፤ ፍቅርን ገንዘብ ካላደረግን በዓለም ላይ የምናያቸው አደጋዎችና ሁኔታዎች በእኛም ላይ ይደርሳሉ፡፡ የእግዚአብሔርን ሕግ አለመጠበቅ ታላቅ ቅጣት ያስከትላል፡፡ ሰው ሰውን ቢበድል ከፈጣሪ ዘንድ ይለምኑለታል፤ሰው ከእግዚአብሔር ሕግ ቢለይና ፈጣሪውን ቢያሳዝን ግን ከማን ዘንድ ያማልዱታል፡፡ ከባድ አደጋ ነው፡፡

በዘመናችን እጅግ ጎጂና መጥፎ ልማዶች ከምንላቸው ውስጥ ለምሳሌ ያህል፤

ለአንደዛዥ ዕፀዋት ሱስ ተገዥ መሆን፤

የሰዶምና የገሞራ ሰዎች የጠፉበትን ግብረ ሰዶማዊነት ዝንባሌ፤

ሠርተውና ደክመው ያላገኙትን ገንዘብ በሙስና ለማግኘት መመኘትና መሞከር፤

የቤተሰብ፤የወገን፤ የሀገር እና የሃይማኖት ፍቅር ማጣት፤

ለአዩት ብልጭልጭ ነገር ሁሉ መጓጓትና ተገዥ መሆን፤

የወደፊት ራእይና እቅድ አለመኖር፤ለዕለቱ ብቻ ልደሰት ማለት፤

ከዘመኑ ስልጣኔ አንጻር በአእምሮአቸው ለሚነሱ ጥያቄዎች ትክክለኛ የመልስ አሰጣጥ ችግር፤

ግለኝነት ማለትም እኔ ብቻ ከተጠቀምኩ ለሌላው ምን አገባኝ ማለት፤፤

እናትን፤ አባትን፤ ታላቅን፤ የሕዝብንና የሃይማኖት መሪን ያለማክብር ዝንባሌ፤

የእንተርኔትና የሶሻል ሚዲያ ሱሰኛ መሆን፤

በተግባር ላላዩትና ተጨባጭ ላልሆነ ነገር በሐሜትና በአሉባልታ መነዳት፤

ለትምህርት፤ለምርምርና ለሥራ መነሣሣት ያለው ፍላጎትና ጥረት ደካማ መሆን

ሰይጣን በገሀድ ሲመለክ ማየትና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

በመሆኑም ወጣቱ ትውልድ እነዚህን ችግሮችና መሰናክሎች እንዴት ማለፍ እንዳለበት ቤተሰብ፤ ማኅበረሰብ፤ ቤተ ክርስቲያን፤ መንግሥትና መምህራን   በአጠቃላይ ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን ካልተረዳዳን ሀገር እንዲረከብ ተስፋ የተጣለበት ወጣት መንገድ ላይ ወድቆ ይቀራል፡፡ ሀገር ተረካቢ ታጣለች፡፡ ይህ የጋራ ኪሳራ ደግሞ በምድርም በሰማይም ያስጠይቃል፡፡ ጥሩ ዜጋ ካለ  ሀገር፤ ሃይማኖት፤ ልማት፤ ክብር፤ ነፃነት፤ ሞራል፤ ጤና አለ፡፡

ከላይ እንደገለጽኩት ጥሩ ሥነ ምግባርን የምታስተምር ማለትም ዐሥርቱ ቃላትንና ስድስቱ ሕገ ወንጌልን መሠረት ያደረገች እናት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ተመርኩዘን ትውልዱ ከቅጽረ ቤተ ክርስቲያን እንዳይርቅ ከእጃችን እንዳይወጣ ተግተን መሥራት ይጠበቅብናል፡፡ የዘመኑን ወጣት ትውልድ ካጣነው ትልቅ አደጋ ላይ ስለምንወድቅ ቆም ብለን ማሰብና ማሰላሰል ያለብን አሁን ነው፡፡

የዘመናዊነት ጥቅም

ዘመናዊነት እንደ ስሙ ችግር ያለበት አይመሰልም፤ የለውምም፡፡ ነገር ግን ሰው በከፊል የተረዳውና እየሆነም ያለው በተቃራኒ መልኩ እጅግ ዘግናኝና አስከፊ በሆነ መንገድ ነው፡፡ ዘመናዊነት ማለት እኮ የራስን ማንነት መጣል፤ ከእምነትና ከመልካም ባህል መለየት መውጣት ማለት አይደለም፡፡ ብርሃነ ዓለም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “አርአያ ኩንዎሙ ለመርዔቱ/ ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ::” 1ጴ. 5፡-3 በማለት እናዳስተማረን የዘመናዊ መረጃ መረብ ለሁሉም እኩል መዳረስ፤ የዘመናዊ ትራንስፖርት ሲስተም ሁሉም ተጠቃሚ መሆን፤ የዘመናዊ መገናኛ መረብ ለሁሉም መድረስ፤ የዘመናዊ ጤና አገልግሎት፤ዘመናዊ የአመራረት ስልት፤ ዘመናዊና ቀልጣፋ የሆነ ፍትሕ የማግኘት፤ ዘመናዊ የመማርና የማስተመር መስፋፋት፤ ዓለም የደረሰበትን ሁሉ ጥብብ ማወቅና መጠቀም፤ አዳዲስና ጠቃሚ ግኝቶችን መፍጠር፤ መንፈሳዊና ሥጋዊ ሕይወትን በሰላምና በጤና ማኖር፤ ለሰማያዊው ዓለም ምድራዊውን የሠመረ ማድረግ ናቸው፡፡ ስለዚህ እኒህ ዓለም ከመሰልጠኑ የተነሣ ያገኘናቸው ትሩፋቶች ሊናቁና ሊጠሉ አይገባም፡፡ ምክንያቱም ለመንፈሳዊው ዓለም እድገትም እጅግ ብዙ አስተወጽኦ አድርገዋል፡፡

በመሆኑም ዓለማችን የሳይንስና የመገናኛ ቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም ዕድገትን  በፍጥነት በሁሉም ዘመናዊ የመገናኛ አውታሮች የፈጠሩት ትስስር ከፍተኛ ነው።

ለምሳሌ ዘመናዊ ዘዴዎች መካካል የሳይተለይት የስልክና የኢንተርት የድርጅታል ስርጭት የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነው።

ለማኅበራዊ ትስስር እንዲሁም ለጋራ ብልፅግናና የተፈጥሮ ሀብት በአግባብ እንዲያዝና ጥቅም ላይ እንዲውል።

ዓለም በአንድ ምህዋር ውስጥ አንዲት መንግድር ናት ሲባል የነፃ ንግድና የፋይናንስ ዝውውር ሀገራት በእድገት ጎዳና እንዲጔዙ አድርጎዋቸል ይህ ጥሩ ጎኑ ነው ነገር ግን የዚህን ያክል ደግሞ መጥፎ አስተዋጽኦ እያደረገም ይገኛል ስለዚህ ምግብ ሲባል የተገኘውን ሁሉ መመገብ ሳይሆን መርጦ ከሃይማኖትና ከባህል ስለዚህም ምግብ ሲባል የተገኘውን ሁሉ መመገብ ሳይሆን መርጦ ከሃይማነትና ከባህል አንፃር የሚያስማማውንና የተፈቀደውን መመገብ ግድ ነው። ስለጣኔ እንዲሁ ነው። ያገኘህውን አይበላም።

ለምሳሌ በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ፡-

ሀ. የሕትመት መሳሪያዎች ግኝት መበራከትና መስፋፋት ቅዱሳት መጻሕፍት በብዛትና  በፍጥነት ታትመው ለተጠቃሚው ሁሉ  በቀላሉ እንዲዳረስ መሆኑ፤

ለ. ጧፍና ሻማ በማብራት ብቻ ይሠጥ የነበረው መንፈሳዊ አገልግሎት በኤሌክትሪክ ኃይል መብራት መታገዙ፤

ሐ. ማይክራፎን በመጠቀም በውስጥም በውጭም በሩቅም ያለው ሕዝብ በሙለ ሊገለገል ቻሉ፤

መ. የሊቃውንቱን አስተምህሮ ማስ ሚዲያ በመጠቀም በዓለም ላሉ የእምነቱ ተከታዮች ማዳረስ  መቻሉ፤

ሠ. የኢንተርኔት፤ የፋከስና የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚ መሆን፤

ረ. በፕሮጀክተር በመታገዝ ማስተማርና መልእክት ማስተላለፍ መቻሉ፤

ሰ. በሞንተርቦ በመታገዝ ድምጽን ከፍ አድርጎ ሁሉም ሰው እንዲሰማው  መደረጉና የመሳሰሉት ዘመናዊነትን የተላበሱ ግልጋሎት ሰጭ መሳሪዎች የሚወደዱና

የሚመረጡ ናቸው፡፡

ሕገ እግዚአብሔርን አለመጠበቅ ደግሞ ዋጋ ያስከፍላል፡፡ 

ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክ በነፃ አእምሯችን ተጠቅመን  መልካም ነገርን ሁሉ እንድንሠራና እንድንጠቀም ፈቅዶልናል፡፡ ከክፉና ከጎጂ ድርጊትም እንድንጠበቅ አዝዞናል፡፡ለማጠቃለል ያህልም ነቢየ እግዚአብሔር ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት “ሚጦን ለአዕይንትየ ከመ ኢይርአያ ከንቶ፡፡” “ወአሕይወኒ በፍኖትከ”/ከንቱ ነገርን እንዳያዩ ዓይኖቸን መልስ፡፡ በመንገድህ ሕያው አድርገኝ፡፡ መዝ. 118/119. 37 ይላል፡፡ በሀገራችንና በሕዝባችን ላይ እየታየ ያለውን መጥፎ ተግባር ለመከላከል የሁላችንም ሐላፊነት አለብን፡፡ ምክንያቱም በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔር መንጋ ጠብቁ ተብለን ታዝዘናል፡፡ 1ጴ. 5፡- 2

 

ብፁዕነታቸው ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን አሉኝ

እኔም አሜን ይሁንልን  አልኩኝ፡፡

በመጨረሻ የብፁዕነትዎ ቡራኬ ይድረሰኝ ብዬ ተሰናበትኩ

 

ከአባ ሳሙኤል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን

ሊቀ ጳጳስ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ገጽ

ማውጫ

መቅድም………………………………………………………………   1

መግቢያ……………………………………………………………….   4

ምዕራፍ አንድ  ሥነ ፍጥረት…………………………………..   8

ሀ. የሰው ተፈጥሮ………………………………………………. 10

ለ. የሰው ነፍስ ተፈጥሮ………………………………………… 11

ሐ. እግዚአብሔርና ሥነ ፍጥረቱ………………………………. 11

መ. ዴይዝም……………………………………………………… 18

ምዕራፍ ሁለት ስለ ሕዝብ ብዙኅነት የፈላስፋዎች

አስተያየት……………………………………….. 20

ሀ. የሕዝብን ብዛት አስተሳሰብ……………………………….. 21

ለ. ጥንታዊ (Classical) ዘመን……………………………….. 23

ሐ. ጥንታዊ (Early) የሥልጣኔ ዘመን………………………. 25

ምዕራፍ ሦስት የሥነ ሕዝብን መመጠን ተጽዕኖዎች……….. 46

ምዕራፍ ዐራት ሳይንስና ውጤቱ! ……………………………..  56

ምዕራፍ አምስት የሕዝብ ብዝኀነት እድገት…………………… 81

ምዕራፍ ስድስት ሰውና ላብራቶሪ (DNA) ……………………  93

ሀ. ስለ ሕዝብ ብዙኀነት የቤተ ክርስቲያን መልእክት………. 106

ለ. ረሀብና እርዛት በሽታና ሞት……………………………… 107

ሐ. ችግር ፈጣሪ ራሱ ሰው……………………………………. 108

መ. የችግሩስ መፍትሔ……………………………………….. 110

ምዕራፍ ሰባት የሰው ሥነ ምግባር በፈላስፎች አስተያየት……. 116

ሀ. ሂዶኒዝም…………………………………………………….. 120

ለ. ዩቲሊቴሪያኒዝም……………………………………………… 126

ሐ. ፔርፌክሽኒዝም……………………………………………… 130

መ. ኃጢአትና ተንኮል…………………………………………… 135

ሠ.  ሰውና ጤናው……………………………………………… 153

ረ. ጠንካራ ሕዝብና እውነተኛ እምነት…………………………. 159

ሰ. ዘመናዊ ሰው…………………………………………………. 165

ሸ. ዩቲሊቴሪያኒዝም ……………………………………………. 171

ቀ. ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር…………………………………… 178

ምዕራፍ ስምንት ፅንስ ማቋረጥ ቤተ ክርስቲያን አይፈቀድም.. 187

ሀ. የሰው ነፍስ እና ሞት……………………………………….. 203

ለ. ሞት ምንድን ነው??………………………………………… 204

ሐ. የሰው ነፍስና ከሥጋ ጋር መዋሐድ………………………. 206

መ. ሳይንስ እና ሥነ ሕዝብ……………………………………. 209

ምዕራፍ ዘጠኝ የኢትዮጵያውያን ጥንታዊ ሥልጣኔ………….. 219

ሀ.  ሳይንስና ሐኪሞቹ………………………………………… 225

ለ. ስለ ሕክምና አገልግሎት የቤተ ክርስቲያን መልእክት….. 232

ሐ. የቤተ ክርስቲያን መልእክት………………………………. 241

ዋቢ መጻሕፍት……………………………………………………… 245

ከአሁን በፊት በአዘጋጁ የታተሙ መጻሕፍት……………………. 247

መቅድም

መቅድም ማለት መጀመሪያ በቅድሚያ የሚገኝ በር ወይም መግቢያ (መቅድም) ማለት ነው፤ ለቤት በር አለው ለመጽሐፍም መግቢያ እንደሚያስፈልገው ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህ  ይህ የመጽሐፉ በር ነው፡፡

 • ፍጡር ፈጣሪውን ለማወቅ ባሰበ ጊዜ እንደ መላእክት በአእምሮ ጠባይአዊ አብርሃም በሥነ ፍጥረት ተመራምሮ እንደ ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ፊቱን አይቶ ቃል በቃል ተነጋግሮ እንደ ቅዱስ ጳውሎስም በተአምራት ተገልጾለት ተመልሶም በመጽሐፍ አእምሮአዊና በተስፋ አረጋግጦ አምላክ እንደአለ የሚያምኑበት ትምህርት ነው እንጂ እንደ ዕቃ የሚገዙት፣ በእጅ የሚጨበጥ የሚዳሰስ እንደ መብልና መጠጥ የሚቀምሱት እንደ ልብስ የሚለብሱት አይደለም፡፡
 • ሃይማኖት እግዚአብሔር ከሁሉ በፊት የነበረ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር ማንኛውንም ነገር ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣ ያስገኘ ፍጥረታትን ሁሉ የፈጠረ ያስገኘ፤ ለእርሱ አስገኝ፤ አሳላፊ፤ አምጭ የሌለው በአንድነት፤ በሦስትነት ያለ፤ ሁሉን ቻይ፤ የማይለወጥ አንድ አምላክ መኖሩን ማመን ነው፡፡

“ሃይማኖት የአምልኮትን ሥርዓት ከእምነትም የተነሣ የሰውን አካሔድ ያጠቃልላል፡፡ የክርስትና ሃይማኖት መሠረት የሰው ምርምር ሳይሆን የእግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ መገለጥ ነው፡፡ ለዚህም መገለጥ ሰው የሚሰጠው ተገቢ የሆነ የአጸፋ ምላሽ ማመንና መታዘዝ ነው”፡፡ 2ኛ ጢሞ. 4÷7፣ ይሁዳ 3÷20፣ 1ኛ ቆሮ. 2÷11፡፡

 • ሃይማኖት፡- አርአያ ፈጣሪ አምሳለ ፈጣሪ የሆነ ሰው ፈጣሪው እግዚአብሔርን የሚያውቅበት መሣሪያ ነው፡፡ “ነአምር ከመ ተፈጥረ ዓለም በቃለ እግዚአብሔር ወአስተርአየ ዘኢያስተርኢ ምንትኒ ዘኮነ እምኀበ ኢሀሎ”፡፡ ዓለም በእግዚአብሔር ቃል እንደተፈጠረ፡፡ የሚታየውም ነገር ከማይታየው እንደሆነ በእምነት እናውቃለን፡፡ ዕብ. 11÷3
 • ሃይማኖት፡- ሰው ከፈጣሪው ጋር የሚገናኝበት የጽድቅ መንገድ ነው፡፡ “አስመ እንተ ውስጡ ለሰብእ የኀድር ክርስቶስ በሃይማኖት ውስተ ልብክሙ” በልባችሁ ውስጥ በፍቅር ሥር መሠረታችሁ የጸና ሲሆን ክርስቶስ በሃይማኖት በሰው ውስጥ ያድራልና፡፡ ኤፌ. 3÷17፣ ዘሌ. 26÷12፡፡
 • “ወኢትኩኑ ኑፉቃነ ወኢትሑር ውስተ አርዑተ ቅኔ እለ ኢየአምኑ፡ መኑ ዘያስተዔርያ ለጽድቅ ምስለ ኃጢአት፣ ወመኑ ዘየኀብሮ ለብርሃን ምስለ ጽልመት፡፡ ወመኑ ዘየኀብሮ ለክርስቶስ ምስለ ቤልሆር፣ ወመኑ ዘይከፍሎሙ ለመሃይምናን ምስለ ኑፉቃን፡፡” ትርጉም
 • የእግዚአብሔር ታቦትስ በጣዖት ቤት ውስጥ የሚያኖር ማን ነው? የሕያው እግዚአብሔር ማደርያዎች እኛ አይደለምን? እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረ “እኔ በእነርሱ አድራለሁ በመካከላቸውም እኖራለሁ አምላካቸውም እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆኑኛል፡፡” 2 ቆሮ. 6÷16
 • ሃይማኖት፡- ሰው ተፈጥሮውንና ምንነቱን የሚረዳበት የሕይወት መመሪያ ነው፡፡ ንግበር ሰብአ በአርያነ ወበአምሳሊነ ዘፍ. 1÷26
 • ሃይማኖት፡- አእምሩ ከመ እግዚአብሔር ውእቱ አምላክነ፡፡ ወውእቱ ፈጠረነ ወአኮ ንሕነ፡፡ ንሕነሰ ሕዝቡ ወአባግዐ መርዔቱ፡፡ እግዚአብሔር እርሱ አምላካችን እንደሆነ ዕወቁ፣ እርሱ ፈጠረን እኛም አይደለም እኛስ ሕዝቡ የመሰማርያውም በጎች ነን፡፡ መዝ. 99÷3

መግቢያ

ይህን ስለ ሕዝብ ብዙኅነት የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮና ሳይንስ የተሰኘውን መጽሐፍ የጻፍንበት ምክንያት በተለያዩ ሀገሮች የነበሩ የሥነ ሕዝብ ጸሐፊዎችና ፈላስፋዎች ያደረጉትን የሥነ ሕዝብ አወዛጋቢ ጉዳይ በግልጽ ለማሳየት የነበረውን የፍልስፍና ዘይቤ እና ሃይማኖታውያን ሥርዓቶችን፣ ለወጣቱ ትውልድ ለማሳወቅና የፈላስፎችን አስተሳሰብና አስተያየት በሥነ ሕዝብ ጥናት ላይ ምርምር ለሚያደርጉ ጸሐፊዎች በር ለመክፈት ነው፡፡

በሀገራችን አከራካሪው የሥነ ሕዝብ ጉዳይ አዲስ ነገር መስሎ ይታይ ይሆናል፡፡ በዘመናችን በዚህ ላይ ትኩረት ሰጥተው የጻፉ ሰዎች ባይኖሩም ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስና በሌሎችም ቀኖናዊ የሃይማኖት መጻሕፍት ተጽፎ እናገኛለን፡፡

“ፍትሐ ነገሥት ንባብና ትርጓሜ” የተባለው መጽሐፍ ቅዱስ የነበረውንና ያለውን የጋብቻ ሁኔታ ሲገልጽ በውስጡ እምነትን፣ ሥርዓትን፣ ግብረ ገብነትን፣ ፍርድንና ሕግጋትን በአጠቃላይ የመንፈሳዊንና ሥጋዊውን አስተዳደርና ሥነ ሥርዓት አጠቃሎ የያዘ መጽሐፍ ነው፡፡

በብሉይ ኪዳን “ልጅ ለመውለድ ዘር ለመተካት፣ ለቀደምት ፍጥረታት ብዙ ተባዙ ምድርን ሙሏት ያላቸው የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን እንረዳለን፡፡ ዘፍ.1÷28 በሐዲስ ኪዳንም አባትና እናቱን ትቶ ከሚስቱ ጋር ይተባበራል፡፡ ሁለቱም አንድ አካል ይሆናሉ፡፡ እግዚአብሔር አንድ ያደረገውን ሰው ሊለየው አይገባም ይላል፡፡ ማቴ.19÷6 ቅዱስ ጳውሎስ ሚስት የሌላቸው ወንዶችና ባል የሌላቸው ሴቶች እንደኔ ሆነው ቢኖሩ ይሻላቸዋል፡፡ መታገስ ባይችሉ ግን ያግቡ በፍትወት ፃር ከመቃጠል ማግባት ይሻላል” ይላል፡፡

በሕገ ወንጌል ሥርዓት መሠረት ጋብቻ የሚፈቀደው ለአንድ ወንድ አንዲት ሴት፣ ለአንዲት ሴት አንድ ወንድ ብቻ ነው፡፡ በዝሙት ምክንያት ካልሆነ በስተቀር መፋታት አይፈቀድም፡፡

በመጽሐፈ ሥነ ፍጥረት ስለ ሥነ ፍጥረት፣ ሊቀ ነቢያት ሙሴ አስፋፍቶ ጽፏል፡፡ ከርሱም በኋላ የተነሱ ነቢያት የእሱን ፈለግ በመከተል ጽፈዋል፡፡ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖት ሊቃውንት ብዙ በሥነ ሕዝብና ክርስትናን በማንሳት ጉዳዮችን ግልጽ በሆነ ሐተታ ያብራራሉ፡፡

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ግን ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት ያለውን አምላካዊ ትዕዛዝ ታስተምራለች፡፡ መፍጠር የቻለ አምላክ መመገብ አይሳነውምና፡፡ 318ቱ ሊቃውንት የጻፉት ፍትሐ ነገሥት የተሰኘው መጽሐፍ ስለ ሥርዓተ ጋብቻ በስፋት ያብራራልና  አንቀጽ 24 ላይ መመልከት ይቻላል፡፡

ለመግቢያ ያህል ስለአገራችን ይህን ካልን፣ የውጭውን ዓለም በተመለከተ በእንግሊዝ፣ በፈረንሳይ፣ በስዊድን፣ በጀርመንና በአሜሪካ ተነስቶ የነበረውን የሥነ ሕዝብ ፅንሰ ሐሳብ አወዛጋቢ ጉዳይ እንደየሀገሩ አመለካከትና አስተሳሰብ በመጽሐፉ ውስጥ በዝርዝር ተጽፏል፡፡ ለአብነት ያህል አንዳንዶቹን እንመልከት፤

 • ማክ አቨሊ፤ “ሕዝብ እንዲጨምር ከተፈለገ፣ በተፈጥሮ በታደለች ሀገር ላይ የተለያዩ ኢኮኖሚ ግንባታ መመሥረት አለብን፡፡ ሁሉም ነገር በተፈጥሮ የተሟላ ነው፡፡ አለበለዚያ ግን ሕዝብ ብቻውን በድህነትና በበሽታ ያልቃል፡፡ ሃብትና የሕዝብ ብዛት ለአንድ ሀገር መሪ የኃይል ምንጭ ነው፣ መሪው ብልህ ከሆነ በሕዝብ ብዛት ምክንያት የፖለቲካ ችግር አይኖርም” ይላል፡፡
 • በአንፃሩ ሰር ቶማስ ሙር የተባለ፣ “የሕዝብ ችግር ሊፈታ የሚችለው ሀገር በዕቅድ ሲመራ ነው በማለት የዜጎችንም ቤተሰብ መወሰንና መመጠን ይደግፋል፡፡ በዛን ጊዜ አንድ ቤተሰብ ከ16 ያልበለጠ፣ ከ10 ያላነሰ መሆን አለበት” ይላል፡፡
 • ቦርኒትዝ፣ “በ17ኛው ክፍለ ዘመን የነበረው የጀርመን ጸሐፊ፣ የሕዝብ ዕድገት አስፈላጊ ነው፣ አንድ ሀገር እንዲያድግ ከተፈለገ፣ ዜጎች መጨመር አለባቸው፡፡ ያላገቡና ልጅ የሌላቸው ሊቀጡ፣ ብዙ ልጆች ያሏቸው ደግሞ ሊሸለሙ” ይገባል በማለት ጽፏል፡፡

ስለዚህ የሕዝብ እድገት አስፈላጊ ነው የሚል አመለካከት እና የሕዝብ እድገት አስፈላጊ አይደለም ለድህነት ትልቁ ምክንያት ይህ ነው የሚሉ አስተሳሰቦች፣ እንዲሁም ከሕገ እግዚአብሔር መሠረት አንጻር ጽንስን ማስወረድ  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ቀኖና  ሲታይ  በወንጀል የሚያስጠይቅ እንደሆነና እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉትን ነጥቦች አካቷልና በተለይ የሰው ልጅ ሥነ ምግባር በባሕላችንና በእምነታችን አንፃር ሲታይ ይህ ይገባል ይህ አይገባም የሚለውን ሁሉ የጣሰውን አዲሱ የሳይንስ ፈጠራ መጽሐፉን በማንበብ ይጠቀሙበት፡፡

 

መልካም ንባብ

ከአባ ሳሙኤል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን

ሊቀ ጳጳስ

 

 

ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ እጅ እንደተጠመቀ አልዋለም አላደረም ዕለቱን ገዳመ ቆሮንቶስ ወደሚባል ሥፍራ ወይም በረሀ ገባ፡፡

 • በዚያም ፵ ቀን ፵ ሌሊት ጾመ፣ ጾሙም እኛ እንደምንጾመው በቀንና በሌሊት ባለው ክፍለ ጊዜ በመብላትና በመጠጣት ሳይሆን ፵ውን ቀን ምንም ሳይበላና ሳይጠጣ እንደ አንድ ቀን አድርጎ ከቆመ ሳያርፍ፣ ከዘረጋ ሳያጥፍ እንደጾመ መጻሕፍት ይነግሩናል፡፡
 • ሆኖም ጾሙን በመጾም ላይ እንዳለ ሰይጣን መጥቶ በሦስት አርእስተ ኃጣውእ ፈተና አቀረበበት፤ የፈተናዎቹም ዓይነቶች ስስት፣ ትዕቢት እና ፍቅረ ንዋይ (ገንዘብን መውደድ) ነበሩ፡፡
 • ዲያበሎስ (ሰይጣን) ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በእነዚህ አርእስተ ኃጣውእ ለመፈተን ኀይለ ቃሉን ከመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ያደርግ ነበር፡፡ ነገር ግን ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥቅሱን በጥቅስ እየመለሰ በመለኮታዊ ኀይሉ እየደመሰሰ ድል አድርጎታል፡፡
 • ሰይጣን በመጀመሪያ ጌታችንን የእግዚአብሔርስ ልጅ ከሆንህ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ እዘዝ እና አንተም እኔም ርቦናል እንብላ አለው፡፡ እርሱ ጌታ ግን “ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም፣ ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ ተብሎ ተጽፎአል ሲል ገሠጸው”፡፡

ሰይጣን ስሙ እንደ ኃጢአቱ ብዙ ነው፡፡ ይኸውም የወደቁት መላእክት አለቃ፣ የመልካም ነገር ተቃራኒ ዲያብሎስ ብዔል ዜቡል፣ ቤልሆር አብዩን አጶልዮን፣ ወንድሞች ከሳሽ ባለጋራ፣ የዓለም ሁሉ ከሳሽ ታላቁ ዘንዶ፣ የቀድሞው እባብ፣ ክፉው ነፍሰ ገዳይ የሐሰት አባት እየተባለ ይነገርለታል፡፡ ጌታችን ሰይጣን በጠየቀው ጥያቄ አሳፍሮ ከመለሰው በኋላ እንደገና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ቅድስት ከተማ ሔደ፡፡ ሰይጣንም ደግሞ መጥቶ በአጠገቡ ቆሞ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል፡፡ እግርህንም እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔርስ ልጅ ከሆንክ ራስህን ወደታች ወርውር አለው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሰይጣንን ጌታ አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ተጽፎአል ሲል አዋርዶና አሳፍሮ ሰደደው፡፡ ከዚህ በኋላም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደረጅም ተራራ ሔደ፡፡ ሰይጣንም ተከትሎት ሔደ፡፡ በለመደው ትዕቢቱና ትምክህቱ ተሞልቶ ምትሐቱን አዘጋጅቶ የዓለምን መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውን፣ ከተማቸውን በወርቅ፣ በአልማዝ በዕንቁ ለብጦ አስገጦ አስውቦ አሳምሮ አሳየው፡፡

ጌታችንንም እንዲህ አለው ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ ክብር በወርቅና በአልማዝ በዕንቁና በከበረ ድንጋይ የተጌጠውን የተዋበውን ከተማ እሰጥሃለሁ ሲል በአምላክነቱ ሊፈትነው ሞከረ፡፡ ጌታችን ግን ሰይጣንን ሒድ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና ብሎ በማያዳግም በትረ ግሣጼው ቀጣው፤ አሳፈረው፣ አባረረው፡፡ ከዚህ በኋላ ሰይጣን እንደጢስ ተኖ እንደ ትቢያ በኖ ከፊቱ ጠፋ፡፡ (ማቴ. ፬÷፩-፲፩)

የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ፈተናዎች ማለት ሰይጣን በስስት ሲመጣበት በትዕግሥት፣ በትዕቢት ሲመጣበት በትሕትና በአፍቅሮ ንዋይ ቢመጣበት በጸሊአ ንዋይ ዲያብሎስንና ሠራዊቱን በሙሉ ድል እንዳደረጋቸው ሁሉ እኛም በሕይወታችን ዘመን በጾማችንና በጸሎታችን፣ ጊዜ ትዕግሥትን፣ ትሕትናን ጸሊአ ንዋይን ገንዘብ አድርገን ብንጸና ፈቃደ ሥጋችንና ፈቃደ ሰይጣንን ድል ለማድረግ እንደምንችል ይታመናል፡፡ በነዚህ መንፈሳውያን መሣሪያዎች እንድንጠቀምም አስተምሮናል፡፡

ፈተና ቢደርስብን እንኳ የእግዚአብሔር መላእክት መጥተው እንደሚቆሙልንና እንደሚረዱን፣ እንደሚያጽናኑንና እንደሚያ- በረታቱንም አንጠራጠርም፡፡ ድል ለመንሣት ኀይል፣ ጽንዕ እንደምናገኝም በሙሉ ልብ እናምናለን፡፡ እንተማመናለን፡፡ ይኸውም “ይትዐየን መልአከ እግዚአብሔር ዐውዶሙ፤ ለእለ ይፈርሕዎ ወያድኅኖሙ፤ ጠዐሙ ወታእምሩ ከመኄረ እግዚአብሔር” ተብሎ ተጽፎአልና ይህም ማለት እግዚአብሔርን በሚፈሩና በሚያከብሩ ምእመናን ዙሪያ መላእክት ይከትማሉ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ደግ ቸር መሆኑን በአዳኝነቱ፣ በደግነቱ ልትተማመኑ እንድትችሉ በእርሱ ወደ እርሱ ተጠጉ ተብሎ ተጽፎአል፡፡ ተናጋሪውም ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ነው፡፡ “ወሰቦ ትጸውሙ ኢትኩኑ ከመ መደልዋን” በምትጾሙበት ጊዜ እንደ ግብዞች አትሁኑ “አንትሙሰ ሶበ ትጸውሙ ቅብኡ ርዕሰክሙ” እናንተስ ስትጾሙ ራሳችሁን ተቀቡ፡፡ ማለትም ጾመኛ ጸሎተኛ ተብላችሁ በውዳሴ ከንቱ ምክንያት ዋጋችሁን እንዳታጡ፡፡ ማቴ. ፮÷፲፮

በጊዜውም ያለ ጊዜውም አካሔዳቸውን ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ያደረጉ ሰዎች ከጥንት ጠላታቸው ከዲያብሎስ የኃጢአት ቀምበር ነፃ ናቸው፡፡ በተለይም በጾም በጸሎት ቅኑት እንደገበሬ፣ ጽሙድ እንደ በሬ ሆነው ሌት ተቀን የሚተጉ አማንያን ሁሉ ጠላትን ድል ነሥተውት ይኖራሉ፡፡ ከሕፃንነት ዘመኑ አንሥቶ፣ በአምልኮተ እግዚአብሔር ጸንቶ ከመኖሩም በላይ በጾም በጸሎት ተወስኖ ይኖር የነበረው ነቢዩ ዳንኤል ከወገኖቹ ጋር ተማርኮ ወደ ባቢሎን ከተወሰደ በኋላ በአምልኮቱና በበጎ ምግባሩ ጸንቶ በመገኘቱ ከመጣበት ፈተና ሁሉ እንደዳነ ከመጽሐፈ ትንቢቱ እንረዳለን፡፡ ት.ዳን. ፱÷፫-፲፡፡

ነቢየ ልዑል ዳንኤል የነገሥታት ዘር ነበር፡፡ ዐዋቂ፣ ነገር አርቃቂ በዐራቱ ነገሥታተ ባቢሎን ነበረ፡፡ በእምነተ ጽኑዕነቱና በአምልኮቱ፣ በጸሎቱና በጾሙ በነገሥታቱም በሕዝቡም ዘንድ ታዋቂ ነበር፡፡ በዚሁም ምክንያት መኳንንቱና የንጉሡ አማካሪዎቹ ሁሉ የዳንኤልን በንጉሡ ዘንድ መወደድ አይተው ያልፈጸመውን ኃጢአትና ወንጀል ተብትበው ንጉሡ ከዳንኤል ጋር የሚጋጭበትንና የሚለያይበትን፣ የሚጣላበትንና ከፊቱ የሚርቅበትን እንዲያውም በተራቡ አናብስት ተበልቶ የሚጠፋበትን መንገድ አዘጋጁ፡፡ ይህም ፈተና በአምልኮተ እግዚአብሔር ምክንያት የመጣበት ነበር፡፡

 • ንጉሡ ናቡከደነጾርም ለጊዜው መስሎት በዳንአል ላይ ተቈጣ፡፡ ዳንኤል ግን ንጉሡን አንተ ብትቈጣ ንጉሥ ሆይ እኔ ከሕፃንነቴ ጊዜ ጀምሮ የማመልከው የአባቶቼን አምላክ እግዚአብሔርን ስለማመልክ የተለመደውን የዘወትር ጸሎቴን ከመጸለይ ፈጽሞ አላቋርጥም ብሎ ነገረው፡፡
 • ንጉሡም እጅግ ከመናደዱና ከመበሳጨቱ የተነሣ ከእጄ የሚያድንህ ሰው ከኔ የበለጠ ኃያል ፈጣሪም ሆነ ፍጡር ካለ አያለሁ ብሎ አማካሪዎቹ በጥላቻ መልኩ ያዘጋጁትን የውሳኔ ሀሳብ ጽሑፍ ወይም ቃለ ጉባኤ አጽድቆ ወዳጁ ዳንኤልን ወደተራቡት አናብስት ጉድጓድ ውስጥ ይዞ ወረወረው፡፡ ነገር ግን ንጉሡ ዳንኤል ይወደው ስለነበረ ሌሊቱን ሙሉ እህል ሳይቀምስ ሳይተኛና ሳያርፍ፣ ሲበሳጭና ሲያዝን አደረ፤ ዳንኤል እነዚህ ሁለት ቀን ሳይበሉ የሰነበቱት አናብስት ጅራታቸውን እንደለማዳ የቤት እንስሣ እየወዘወዙ ከእግሩ በታች ወድቀው የእግሩን ትቢያ እየላሱ ተቀበሉት እንጂ ምንም አልነኩትም፡፡
 • ዳንኤልም በአናብስት ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ፣ ከአናብስት መካከል ቆሞ “ኢትመጥወነ ለግሙራ በእንተ ስምከ፣ ወኢትሚጥ ኪዳነከ፣ ወኢታርሕቅ ምሕረተከ እምኔነ፣ በእንተ አብርሃም ፍቁርከ፤ ወበእንተ ይስሐቅ ቁልዔከ ወበእንተ እስራኤል ቅዱስከ”፡፡
 • ስለስምህ ብለህ ለጥፋት አሳልፈህ አትስጠን ከእኛ ዘንድ ምሕረትን አታርቅብን፣ ኪዳንህንም አትመልስብን፣ አትርሳንም ስለወዳጆችህ፣ ስለአብርሃም፣ ስለይስሐቅና ስለያዕቆብ ብለህ አስበን እያለ ጸለየ፡፡ (ዳን. ፮÷፲፱-፳፯)

ንጉሡ ዳርዮስም ዳንአል ወደ አናብስት ጉድጓድ ውስጥ በመጣሉ አዝኖአልና፤ በነጋታው ከተቀመጠበት ተነሣ፤ ወደአናብስት ጉድጓድ ለመሄድ ዝግጅት አድርጎ ማልዶ ተነሣ፡፡ መኳንንቱን፣ መሣፍንቱን ራስ ቤትወደዶቹን አማካሪዎቹንና ባለሟሎቹን አስከትሎ ነቢዩ ዳንኤል ወደተወረወረበት የአናብስት ጉድጓድ ሄደ፡፡ ጉድጓዱ የታሸገበትን ማኅተም ቀደደ፡፡ በሩን ከፈተ ወደ ጉድጓዱም ተመለከተ እነሆ ዳንኤልም በጉድጓዱ ውስጥ በአናብስት መካከል በሕይወት ቆሞ ሲጸልይ አገኘው፡፡ በዚሁ ጊዜ ንጉሡ ዳርዮስ “የሕያው አምላክ አገልጋይ ዳንኤል ሆይ ሁልጊዜ የምታመልከው አምላክ እግዚአብሔር ከአናብስት አፍ ያድንህ ዘንድ ችሎአልን? አለው”፡፡

 • ዳንኤልም ንጉሡ ዳርዮስን “ንጉሥ ሆይ ሺህ ዓመት ንገሥ ቅንነት ተገኝቶብኛልና አንተንም ደግሞ ንጉሥ ሆይ አልበደልሁህምና አምላኬ መልአኩን ልኮ የአናብስትን አፍ ዘጋ፤ እነርሱም አልነኩኝም ብሎ መለሰለት”፡፡
 • ንጉሡም ዳንኤልን ከጉድጓድ አውጥቶ የዳንኤልን ጠላቶች የእርሱን አማካሪዎች አምጥቶ አናብስት ለእናንተ ደግሞ እንደ ዳንኤል ይሰግዱላችሁ እንደሆን ወደ ጉድጓዱ ውረዱ ብሎ ቢወረውሯቸው ገና ሳይወርዱ አናብስቱ እየዘለሉ ይዘው ቀለጣጥመው ሰባብረው ዋጡአቸው፡፡ በሠፈሩት ቁና መሠፈር አይቀርምና የሥራቸውን አገኙ፡፡
 • ከዚህ በኋላም ንጉሡና ቤተሰቡ፣ እንዲሁም በግዛቱ ውስጥ ያሉ ያገሩ ሕዝብ ሁሉ በዳንኤል አምላክ በእግዚአብሔር እንዲያምኑ አዋጅ አስተላለፈ፡፡ ሕዝቡም የእግዚአብሔርን ፈጣሪነት አምኖ፣ ተቀብሎ በአምልኮቱ ጸና፡፡ (ዳን. ፮÷፲፮-፳፰)
 • ስለዚህ እኛም ሰማይንና ምድርን ጥቃቅኑንና ግዙፋን ፍጥረታትን የፈጠረ እውተኛ ፈጣሪ አምላክ የሆነው እግዚአብሔርን በእውነት ማምለክና የተቀደሰ ሥራን መሥራት በጾም፣ በጸሎት መትጋት፣ በትእዛዛቱ መጽናት፣ በፍቅር፣ በአንድነት፣ በሰላም በትህትና አብሮ መኖር ይገባናል፡፡ መንገዳችንና አካሄዳችን እንዲሁ የቀና ከሆነ እግዚአብሔር አምላካችን ከመጣብን አስደንጋጭና ክፉ ፈተና ሁሉ እንደሚያድነን የታመነ ነው፡፡ ይህኑም ተረድተን ከከንቱ አምልኮ ተጠብቀን በጾም በጸሎት ተወስነን በሥጋው ወደሙ ጸንተን ከቈየነው ለተስፋ መንግሥተ ሰማያት እንደሚያበቃን አንጠራጠርም፡፡ ለዚሁም እንድንበቃ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡ (የሐ.ሥ. ፲÷፫-፬፣ ፲÷፴-፴፩) ይቆየን

                                                               ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከወርኀ ጾሙ በኋላ

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመዋዕለ ጾሙ በኋላ የማስተማር መርሐ ግብሩን ለመጀመር ከቆሮንቶስ ተራራ ወርዶ በቃና ዘገሊላ አጠገብ በባሕሩ ዳር ሁለት ወንድማማቾችን ጴጥሮስ የሚሉት ስምዖንንና ወንድሙ እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አይቶ (በኋላዬ) ኑና ተከተሉኝ ሰዎችን የምታጠምዱ አደርጋችኋለሁ ብሎ አስከተላቸው፤

 • ይህም ሰዎችን በትምህርት፣ በተአምራት ታሳምናላችሁ፣ ከድንቁርና ወደ እውቀት፣ ከክሕደት ወደ እምነት ከገቢረ ኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ ትመልሳላችሁ፡፡ ከአጋንንት ቁራኝነት አላቅቃችሁ፣ በንስሓ አጥባችሁ ከእግዚአብሔር ጋር ለማገናኘት የሚያስችል ሥልጣን ታገኛላችሁ፡፡ ወደ ገሃነመ እሳት የሚወስደውን መንገድ በቅዱስ ወንጌል አጥራችሁ፣ የመንግሥተ ሰማያትን በር ከፍታችሁ ለማስገባት ትችሉ ዘንድ ቁልፍ ይሰጣችኋል፤ በምድር ያሠራችሁት በሰማይም እንደታሠረ እንዲሆን የምትችሉበትን ሥልጣን እሰጣችኋለሁ፤ በምድር የፈታችሁትም በሰማይ የተፈታ ይሆናል፡፡ ሰው ሁሉ በተድላ በደስታ በመንግሥተ ሰማይ ለመመላለስ እንዲበቃ ታደርጉታላችሁ አላቸው፡፡ እነርሱም ያለ አንዳች ጥርጥርና ማመንታት በሌለበት መረባቸውን፣ ጀልባቸውንና ቤታቸውን ትተው ከቤታቸው ተለይተው ሁሉን ትተው በቀና በጸና እምነት፣ በንጹሕ ልብ ተከተሉት፡፡ (ማቴ. ፬÷፲፰-፳፣ ማር. ፩÷፲፮-፳)

ከዚህ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገሊላና አካባቢዋ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር እያበሰረ ማስተማሩን ቀጠለ፡፡ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሓ ግቡ እያለ አስተማረ፡፡ ይገሥጻቸው፣ ይመክራቸውና ያርማቸው ነበር፡፡ ይልቁንም በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ የተያዙትን ይፈውሳቸው ነበር፡፡

ማለትም ሀ – ለምጻሞችን ያነፃቸው፣

ለ – የሞቱትን ያስነሣቸው፣

ሐ – ልምሾዎችንና ሽባዎቹን ያረታቸው፣

መ – አጋንንት ያደሩባቸውን ያወጣላቸው፣

ሠ  – ዲዳዎቹንና ደንቆሮዎቹን አንደበታቸውን

የከፈተላቸው፣

ረ –  ደም የሚፈሳቸውና የተቅማጥ በሽታ የያዛቸውን፣

የፈወሳቸው፣

ሰ – የራስ ፍልጠት፣ የሆድ ቁርጠት፣ የእግር ቁርጥማት፣  የቆዳ ምልጠት፣ የልብ ጥመት የያዛቸውንና ያደረባቸውን ከደዌያቸው ሁሉ የፈወሳቸው፣ ያላቅቃቸው ነበር፡፡

 • ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋና በነፍስ ደዌያትን በሚያመጡ ርኲሳን አጋንንት ላይ ሥልጣኑን በማሳየት በብዙ ሺህ የሚቈጠሩ ሰዎች ይከተሉት ነበር፡፡ በተለይም ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ ከዋለበት የሚውሉ፣ ካደረበት የሚያድሩ ፻፳ ቤተሰብ ነበሩት፡፡

ክፍላቸውም፡- ፩ – አሥራ ሁለት ሐዋርያት፣

፪ – ሰባ ሁለት አርድእት፣

፫ – ሠላሳ ስድስት ቅዱሳት አንስት ተብለው የሚጠሩ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሲከተሉ፣ መንፈሳዊ አገልግሎትን ሲያሟሉ የኖሩ ናቸው፡፡

 • አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌሉን ሲያስተምር እየተከታተሉ ሕዝቡን የሚያገለግሉ፣ ሰው ሁሉ ከኃጢአት፣ ከፍዳና ከዘለዓለማዊ ኲነኔ ወጥቶ፣ በክርስቶስ ክርስቲያን፣ በጥምቀቱ ውሉደ እግዚአብሔር አሰኝተው በዚሁ ስም እንዲጠሩ በማድረግ በዓለም ሁሉ ተሠማርተው፣ ሕይወታቸውን ወደ ቅድስና ለውጠው፣ የወንጌሉ ቃል ተግባራዊ እንዲሆን ያደረጉና አሁንም በተሰጣቸው ቃል ኪዳን መሠረት ሰው ዘለዓለማዊ ሕይወት እንዲኖረው የሚያደርጉ አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ናቸው፡፡
 • ስለሆነም ጌታችን በቅዱስ ቃሉ ያስተማረውን ሐዋርያት ተቀብለው ለዓለሙ ሁሉ ያደረሱት ትምህርተ ወንጌል ተባለ፤ ወንጌል ማለትም የደስታና የሰላም የፍሥሓና የምሥራች ነጋሪ አብሳሪ ማለት ነው፡፡ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሓ ግቡ” የምትል በመሆንዋ የምስራች ተባለች፡፡ (ማቴ. ፫÷፪፣ ማቴ. ፬÷፲፯)
 • ፯ኛ/ አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “የማስተማር ተግባሩን ሲጀምር መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሓ ግቡ” የሚል ነበር፡፡ በቀዳማይ አባታችን አዳም በደል ምክንያት አጥተናት የነበረችውን ገነት መንግሥተ ሰማያትን በዳግማይ አዳም ጌታ ፭ ሺህ ከ፭ መቶ ዘመን ሲፈጸም ተመልሳልናለችና ይህችው የከበረችን ሥፍራ ለማግኘት በጸጸትና በአንብዓ ንስሓ መታጠብ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ባለቤቱ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነግሮናል አስተምሮናል፡፡

ስለዚህ በክርስቶስ ክርስቲያን፣ በወልድ ውሉድ ተብለው የሚጠሩት ወገኖች በሙሉ ሥርዓተ አምልኮታቸውን ጠብቀው፣ የሚሠሩትንና ሊፈጽሙት የሚገባቸውን ተግባር ሁሉ አከናውነው ተዘጋጅተው መቀመጥ፣ መጠበቅ አለባቸው፡፡

                                                                                     ሥርዓተ ጾምወ ጸሎት

ጾምና ጸሎት እንደ ሰምና ፈትል የተስማሙ ናቸው፤ ጸሎት ዘወትር ከክርስቲያኖች አንደበት ሊለይ የማይገባ ተግባር ነው፤ በመሠረቱ ምእመናን ሁሉ ዘወትር መጸለይ እንደሚገባቸው መዘንጋት የለባቸውም፡፡

 • ከጸሎት የተለየ ክርስቲያን የአጋንንት በረት ነው ወይም ነፍስ የተለየው በድን ነው፡፡ ምክንያቱም ጸሎት የሕይወት እስትንፋስ ነው ተብሎ ተጽፏልና፡፡
 • ጾም ምንም እንኳ የተለየ ጊዜና ወራት ቢኖረውም ሁለቱ ትሩፋት ለክርስቲያን ሁሉ አስፈላጊዎች ናቸው፡፡ ክርስቲያን ነኝ የሚል ሁሉ በጽኑዕ እምነት፣ በንጹሕ ልቡና በቅንነት ከጸለየና ከጾመ ከእግዚአብሔር ዘንድ የለመነውንና የጠየቀውን ፈጣን መልስ እንደሚያገኝ የታመነ ነው፡፡ እግዚአብሔር ቅዱስና ንጹሐ ባሕርይ አምላክ ስለሆነ የሚቀርብለት ልመና፣ ጾምና መሥዋዕት ሁሉ በንጽሕና ከቅን ልቡና የመነጨ መሆን አለበት፡፡
 • ጾምና ጸሎት ለታይታና ለይስሙላ የሚደረግ ለግብር ይውጣ የሚቀርብ አይደለም፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር አምላክን በትሕትና በንጽሕናና በቅድስና ሆነው ቢለምኑት፣ ቢጠሩት መልስ ይዞ የሚመለስ ፈጣን መሣሪያ ስለሆነ ነው፡፡
 • እውነትና ፍቅር ትሕትናና ይውህና ሳይዙ፣ ልቡናን ንጹሕ ሳያደርጉ እምነትንም ሳያጸኑ እነዕገሌ እንዲህ ያደርጋሉ ብለው ሃያ አራት ሰዓት ከእህልና ከውሃ ተለይተው እንደቶራ ተገትረው ቢለፈልፉና ቢጮኹ፣ ቢወድቁ ቢነሡ ጸሎቱ ከቅድመ እግዚአብሔር ደርሶ መልስ ይዞ ሊመለስ እንደማይችል መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡
 • እግዚአብሔር ከልብ ባልመነጨ ረጅም ጸሎትና፣ እውነትን ባልያዘ ጾም ቢለምኑት አያስደስተውም፡፡ በትምክህት፣ በምቀኝነት፣ በክፋትና በተንኰል፣ የተተበተበ ልቡና ይዞ መላ ዘመናትን ቢወድቁ፣ ቢነሡ፣ ቢጾሙ እና ቢጸልዩ እግዚአብሔር ጆሮውን ወደዚሁ ጾምና ጸሎት አያዘነብልም፡፡ (ሉቃ. ፲፰÷፲፩፣ ኢሳ. ፶፰÷፫-፲፪፣ ማቴ. ፳፫÷፳፱-፴፯፣ ማቴ. ፳፫÷፲፬)
 • ለአብነት ያህል በንጽሕናና በቅድስና ፣ በመንፈሳዊ ቅንዓትና በቅን ልቡና፣ በጽኑዕ እምነትና በንጹሕ ኅሊና፣ በትዕግሥትና በትሕትና፣ በተስፋና በፍቅር የሚጸለይ ጸሎትን ሁሉ ከነቢይ ኤልያስ ጸሎት ጋር ብናገናዝበው ስለጸሎት ጠቃሚነትና ጎጂነት በቀላሉ ለመረዳትና ለመገንዘብ ያስችለናል፡፡
 • ኤልያስ “አቤቱ የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ ሆይ አንተ በእስራኤል ላይ አምላክ እንደሆንህ፣ እኔም ባሪያህ እንደሆንሁ፣ ይህን ሁሉ በቃል እንዳደረግሁ ዛሬ ይገለጽ፤ አቤቱ አንተ አምላክ እንደሆንኸ፣ ልባቸውንም ደግሞ እንደመለስህ ይህ ሕዝብ ያውቅ ዘንድ ስማኝ አቤቱ ስማኝ” ብሎ ባቀረበው አጭርና ልባዊ ጸሎት የተገኘው መልስ ፈጣን እንደነበረ እንመለከታለን፡፡ ኤልያስ በዚህ አጭር ጸሎቱ ያቀረበውን መሥዋዕት ከሰማይ እሳት ወርዶ እንደበላለት፣ እግዚአብሔርም እንደተቀበለለት በግልጽ ተረጋግጧል፡፡ (፩ኛ/ነገ. ፲፰÷፴፮)
 • ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘወትር ሳንታክት እንድንጸልይና የምንጸልየውንም ጸሎት በንጹሕ ልቡና ከተንኰልና ከምቀኝነት፣ ከክፋትና ከጥመት ከስርቆትና ከአምልኮ ጣዖት የጸዳን ሆነን አጭርና ልባዊ ጸሎት ለአምላካችን እግዚአብሔር እንድናቀርብ አዞናል፡፡
 • ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለአንዲት ነዝናዛ ሴት (መበለት)ና እግዚአብሔርን ስለማይፈራ አንድ ዐመጸኛ ዳኛ የሰጠን ምሳሌያዊ ትምህርትም በቂ ማስረጃችን ነው፡፡ የእነዚህንም ልመና ስናስተውል፡-

፩ኛ/ ከላይ እንደተገለጸው የኤልያስ ጸሎት አጭር እንደነበረ ነው፡፡ እንዲሁም ከንጹሕ ልብ የመነጨና ከሁሉም ነገር የጸዳ መሆኑን ተመልክተናል፡፡ ከዚህም አብነት የተነሣ የሁሉም ሰው ጸሎት አጭር ልባዊና ከዓለም አስተሳሰብ የራቀ መሆን እንዳለበት ቅዱስ መጽሐፍ ያዝዘናል፤ እንዲህ ሲል እናንተስ እንዲህ ጸልዩ፣ አባታችን ሆይ፣ በሰማይ የምትኖር ስምህ ይቀደስ… ይህን ጸሎት ያለ ማቋረጥ ዘወትር መጸለይ የሚገባን መሆኑን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዞናል፡፡ (ማቴ. ፮÷፲፣ ሉቃ. ፲፰÷፩-፰)

፪ኛ/ ጸሎታችን ለታይታና ለውዳሴ ከንቱ ሳይሆን ቂምንና በቀልን፣ ክፋትንና ተንኰልን፣ ትምክህትንና ትዕቢትን አስወግደን ፍቅርንና ትሕትናን የዋህነትንና ርኅራኄን ገንዘብ አድርገን እንድንጸልይ የሚገባን መሆኑን በየክፍሉ ተነግሮናል ተረድተናል፡፡ ይኸውም አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናንተ ልበ ደንዳኖች ጻፍቶችና ፈሪሳውያን በጸሎት ርዝማኔ እያመካኛችሁ የመበለቶችን ቤት ስለምትበሉ ወዮላችሁ፣ ስለዚህ የባሰ ፍርድ ትቀበላላችሁ ብሎአል፡፡

የፈሪሳውያንን ግብዝነትና ስውር ደባ፣ ስለጾማቸውና ጸሎታቸው ውስጣዊ ሕይወትም በእብነ በረድ እንዳሸበረቀ መቃብር ሆኖ ስለታየው ነቀፌታን አስከትሎባቸዋል፡፡ ይህም በእርሱ ዘንድ ምንም የተሠወረና የተደበቀ ምሥጢር እንደሌለ የሚያስረዳ ነው፡፡ (ማቴ. ፳፫÷፲፬፣ ሉቃ. ፲፰÷፩-፲፬)

፫ኛ/ ክርስቲያን ከመጸለዩ በፊት እንዴት መጸለይ እንደሚገባው ማወቅና መጠንቀቅ አለበት፡፡ ሲጸልዩ አይቶ ሳይማር ሳያውቅና ሳይጠነቀቅ እኔም ልጸልይ ቢል ምንም እንኳ ሀሳቡ መንፈሳዊ ቅንዓት እንዳደረበት ቢያመለክትም ከላይ እንደተገለጸው ሊያሟላው የሚገባውን ደረጃ በደረጃ ማጥናት ተገቢ መሆኑን ማወቅ ግዴታ ይሆናል፡፡

 • በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ጸሎት መሠረት አንድ ክርስቲያን ሲጸልይ
 • ለማን ነው የምጸልየው?
 • ምንድን ነው የምጸልየው?
 • ለምን ነው የምጸልየው?
 • መቼ ነው የምጸልየው?
 • እንዴት ነው የምጸልየው?
 • የት ነው የምጸልየው? የሚሉ ሥርዓተ ጸሎት መመሪያዎችን በሙሉ ማወቅ ይጠበቅበታል፡፡

፬ኛ/ ከአንዳንድ በስም ክርስቲያን ነን ባዮች የሚሰማው ጸሎት እንኳንስ በእግዚአብሔር ፊት ቀርቦ ግዳጅ ሊፈጽም ይቅርና በሰው ጆሮ ሲሰማም እንኳ እጅግ የሚቀፍና የሚያስጸይፍ ነው፡፡ ወደ ቤተክርስቲያን ሄደው በዐጸዱ ሥር ቆመው የዕገሌን፣ የዕገሊትን ነገር ካላሳየኸኝ ዳግም ከደጀ ሰላምህ አልደርስም፤ የሚሉና የመሳሰሉ የአረማውያን ባሕርይ የሚከተሉ ብዙ ናቸው፡፡ (ማቴ. ፳÷፳፪)

፭ኛ/ ጾም ማለት ምን ማለት እንደሆነና ምን እንደሚመስል፣ እንዴትስ መጾም እንደሚገባ፣ በጾም ወራት ከምን ከምን መከልከልና መራቅ እንደሚያስፈልግ አስቀድሞ ሊቃውንትን፣ መጠየቅ፣ መጻሕፍትን ማንበብና ማወቅ ግዴታ ይሆናል፡፡ ከጥሉላተ መባልዕት ብቻ መገለሉ በልዩ ልዩ ሥርወ ኃጢአት መንከባለሉና መበከሉ ጾመኛ ነኝ ሊያሰኝ እንደማይቻል መታወቅ አለበት፡፡

፮ኛ/ አንድ ሰው ስለጾምና ስለጸሎት አጠቃቀም በተገቢው መንገድ ሳይገነዘብ ለመጾም ቢሞክር ጥፋትን እንጂ ልማትን፣ መርገምን እንጂ በረከትን አያስገኝም፤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጾም ጊዜ እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን መመልከት እንደማይገባን አስተምሮናል፡፡ ለመጾምና ለመጸለይ የሚዘጋጅ ሰው በቅድሚያ ፍቅርን፣ ትሕትናን፣ ትዕግሥትን፣ ንስሓን፣ ጸጸትን፣ ቸርነትን፣ ይቅር ባይነትን ገንዘብ ማድረግ ይገባል፡፡ ከዚህም ጋር ከልዩ ልዩ የአልኮል መጠጦች፣ ከክፋት ከተንኰል፣ ከቂም ከበቀል፣ ከዝሙት ከሐሜት፣ መንጻት ከክርስቲያን ወገን ሁሉ የሚጠበቅ ግዴታ ነው፡፡ እነዚህን ሁሉ አውቀን፣ ጠንቅቀን፣ የምንጸልይና የምንጾም ከሆነ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልመናችንን ሁሉ ተቀብሎ ይፈጽምልናል፡፡ ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ስለጾም ሲያስተምር ይጹም ዐይን ይጹም ልሳን እዝንኒ ይጹም እሚሰሚዓ ሕሡም (ዐይን ይጹም አንደበትም ክፉ ከመናገር ይጹም ጆሮም የማይገባ የከፋ ነገርን ከመስማት ይጹም) ብሎ በዝማሬው አዝዞናል፡፡ ጾምና ጸሎት ማለት ይህን ይመስላል፡፡

፯ኛ/ የመለመንን ሥርዓት የማያውቅ ሰው እንኳንስ እግዚአብሔርን ሥጋውያን፣ ዓለማውያን/ ምድራውያን ባለሥልጣናትና ባለጸጎችንም ቢሆን አያስደስትም፡፡ በእውነትና ከልብ በመነጨ ጸሎት ሆኖ የተለማኞችን ልብ የሚነካና የሚቀሰቅስ ካልሆነ ለማኙ ከተለማኙ ሰው ሊያገኘው የፈለገውን ሊያገኝ አይችልም፡፡

፰ኛ/ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልጅ አባቱን ዓሣ ቢለምነው እባብ፣ ጊንጥ ይሰጠዋልን? እን ኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ፣ ለልጆቻችሁም መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ በሰማያት ያለው አባታችሁ በእውነት ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸዋል? ካለ በኋላ “ለምኑ ይሰጣችሁማል” ፈልጉ ታገኙማላችሁ፣ መዝጊያን አንኳኩ ይከፈትላችሁማል፤ የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና፣ የፈለገውንም ያገኛል ብሎአል፡፡ (ማቴ. ፯÷፯)

፱ኛ/ ሐና የፈለገችውን ለማግኘት ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሔደች፡፡ ልቧን ከክፉ ነገረ ሁሉ አጽድታም ወደ እግዚአብሔር ጸለየች፡፡ እግዚአብሔርም ጸሎትዋን ፈጥኖ ሰማት ምክንያቱም ጸሎትዋ አጭርና ልባዊ ስለነበረ ነው፡፡ የጸሎትዋ አቀራረብም አቤቱ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! የባሪያህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፣ እኔንም ባትረሳኝ ለባርያህም ወንድ ልጅ ብትሰጥ ዕድሜውን ሙሉ ለእግዚአብሔር እሰጠዋለሁ ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም የሚል ነበር፡፡

፲ኛ/ ሐና በዚህ አጭር ጸሎትዋ ርኅሩኅ አምላክ ውርደትዋንና ስድቧን ሁሉ አይቶ አስወገደላት፣ የልቧንም ምኞት ፈጸመላት ወንድ ልጅም ሰጣት፡፡ ከዚህም በኋላ ከልብ ለለመነችውና ልመናዋንም ሰምቶ የፈለገችውን ሰጣት፡፡ ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋናዋን ስታቀርብ “ጽጉባነ እክል ርኅቡ፣ ወርኁባን ጸግቡ፣ እስመ መካን ወለደት ሰብአተ፣ ወወላድሰ ስእነት ወሊደ” አለች፡፡ የቃሉ ትርጉም እህል በልተው የጠገቡ ተራቡ፣ የተራቡትም ጠገቡ፣ መካንዋ ሰባት ወለደች፤ ወላድዋ ደግሞ መከነች ማለትም ሕልቃና አንደኛዋ ሐና፣ ሁለተኛዋ ፍናና የሚባሉ ሁለት ሚስቶች ነበሩት፡፡ ነገር ግን ፍናና ልጆች ሲኖሩአት ሐና ስላልወለደች ፍናና በሐና ላይ ታላግጥ ነበረችና ልዑል እግዚአብሔር የሐናን ግፍ አይቶ ሦስት ወንዶችና ሁለት ሴቶች ልጆችን ስትወልድ ፍናና ደግሞ መውለድን በማቆምዋ ከዚህ በላይ የተጠቀሰውን ኀይለ ቃል ተናገረች፡፡ (፩ኛ/ ሳሙ. ፩÷፬-፯፣ ፪÷፳-፳፩)

፲፩ኛ/ በዚህም መሠረት ወደ እግዚአብሔር የሚቀርበው ጸሎት እግዚአብሔር አምላክ የማይፈልገውን በደል ለመፈጸምና ይህም በእግዚአብሔር ስጦታ የማጥቃያ መሣሪያ ለማግኘት ማለት ሀብት አግኝቶ ሰውን ለመበደል ሳይሆን ሰጥቶ፣ መጽውቶ ለመጽደቅ መሆን እንዳለበት፣ እንዲሁም ባለጸጋ ሆኖ በሰው ወይም በድሆች ላይ ለመታበይ፣ ለመመካት፣ ለመኩራራትና ለመመጻደቅ እንዳልሆነ መገንዘብ እንደሚገባ ቅዱሳት መጻሕፍት ያዝዙናል፡፡

፲፪ኛ/ ጾምና ጸሎት ከዘመነ ብሉይ ጀምሮ በሥርዓተ አምልኮት እና በሥርዓተ እምነታችን መሠረት ሲፈጸም የኖረ፣ ያለና የሚኖር ነው፡፡ ሆኖም ጾምና ጸሎት ሰዎች የሠሩትና የደነገጉት ሳይሆን የእግዚአብሔርን ፈቃድና ትእዛዝ መሠረት በማድረግ በየዐረፍተ ዘመኑ የነበሩት አባቶች ሲጠቀሙበትና ሲጠቅሙበት፣ እስካሁንም በተግባር ሲፈጽሙት የሚታይ ቅዱስ ተግባር ነው፡፡

፲፫ኛ/ ጸሎት የሕይወታችን እስትንፋስ ስለሆነ ያለ ጾምም ዘወትር ሊደረግ የሚገባው ልመና ነው፡፡ ጾም ግን ምንም እንኳ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ የሚፈጽመው ትሩፋት የሆነ ሁሉ መሆኑ ቢያመለክትም ከጥሉላተ መባልዕት የምንከለክልበት ብቻ ቢመስልም ይኸው ሥርዓትም ከጸሎት ጋር የማይለያይ መሆን እንዳለበት ማንም ሊዘነጋው የማይገባ መንፈሳዊ ግዴታ ነው፡፡

 •    ጠግበው የነበሩ እንጀራ አጡ፡፡

ተርበው የነበሩ ከራብ ዐርፈዋል

መካኒቱ ሰባት ወልዳለችና

ብዙም የወለደችው ደክማለች፡፡

ምክንያቱም ጸሎት የተለየው ጾም የማጣትና የችግር ጾም ተብሎ ከሚነገረው አባባል የተለየ አይደለምና ነው፡፡

፲፬ኛ/ አንዳንድ በስም ክርስቲያን ነን ባዮች ጾምን ከእምነት ትሩፋት ለይተው ይመለከቱታል፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ትሩፋት የሆኑትን ሁሉም አያስፈልጉም ይላሉ፤ በዚህም አመለካከታቸው እምነታቸውን ከሁሉ በላይና ከማንም እምነትም የተለየ አድርገው ሲናገሩ ይሰማሉ፣ በተጋድሎአቸውና በገቢረ ተአምራትነታቸው ቅዱሳን የሚል ቅጽል ከተሰጣቸው ጋር ራሳቸውን ያስተካክላሉ እንዲህ አይነቱ አመለካከትም ቅዱሳት መጻሕፍትን ካለማንበብና ካለመመርመር የተነሣ ሊሆን እንደሚችል በምሁራን ዓይን ታይቷል፡፡

፲፭ኛ/ ጾምን ከጸሎት ለይቶ መጾም ጸሎትን ከጾም ነጥሎ መጸለይ ቢቻልም ሁለቱን ለየብቻ መፈጸም እንደማይገባ ግን ለሁሉ ግልጽ መሆን አለበት፡፡ ይልቁንም ጸሎተኛና ጾመኛ ሰው በማንኛውም ጊዜና ቀን፣ ወራትና ዓመታት ቢሆን ሰውን የሚያስቀይምና እግዚአብሔርን የሚያሳዝን መሆን የለበትም፡፡ ቀደም ብለን እንደአተትነው ምእመናን በኅብረተሰቡ መካከል ሆነው እንዴት መጸለይና መጾም እንደሚገባቸው ለማወቅ እንደሚችሉ አስቀድመው ሕጉንና ትእዛዙን መመርመርና ማጥናት፣ ማወቅና መረዳት ይገባቸዋል፡፡

፲፮ኛ/ የጾምና የጸሎት አጀማመርና አፈጻጸምን ሳያውቁ በመላምት ወይም ሰዎች ያደርጋሉ በማለት ለመጾምና ለመጸለይ በድፍረት ተነሣሥቶ መሞከሩ ከላይ እንደተጠቀሰው ውጤት አልባና ዋጋቢስ እንደሚሆን አያጠራጥርም፡፡ እዚህ ላይ አንድ ታሪክ ብንጠቅስ አንድ ኀይለኛ ሽፍታ ነበረ ዳዊት ሳይደግም ውዳሴ ማርያም ሳያደርስ እህል የሚባል ነገር ፈጽሞ አይቀምስም ነበር፡፡ ነገር ግን እሱባለበት አካባቢ የሚያልፍን ሰው ገንዘቡን ልብሱን እየገፈፈ ይወስድ ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ሰው በድንገት እሱ ካለበት ቦታ ደረሰና ሽፍታ መሆኑን አውቆ ሩጫውን ቀጠለ፡፡ አሽከሮቹን ብዙ ገንዘብ ሳይዝ አይቀርም ብሎ ተከተሉት አላቸው፡፡ ሰውየው ሲሮጥ እነርሱም ሲሮጡ ብዙ ደክመው ያዙትና ፈተሹት አምስት ሳንቲም አልነበረውም፡፡ ወደ አለቃቸው ወደ ሽፍታው አምጥተው ምንም እንደሌለው ነገሩት፡፡ እርሱም ዳዊት እየደገመ ነበርና በእጁ ምልክት እየሰጠ እረዱት ቢል አረዱት፡፡ አንባብያን አስተውሉ እንዲህ ዐይነት ጸሎተኞችና ጾሞኞች እንዳሉ ልብ በሉ፡፡ ጸሎታችሁና ጾማችሁ በእንዲህ ዐይነቱ እንዳይሆን ተጠንቀቁ፤ ዕወቁ፤ አስተውሎ፤ ልባችሁን ሰብስባችሁ ማየት አለባችሁ፡፡

                                                                              የጾም ሥነ ሥርዓት

ጽድቃችሁ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን ጽድቅ ካልበለጠ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት አትገቡም ተብሎ የተነገረውን አምላካዊ ቃል ማስተዋል ይጠቅማል፡፡ የጾምና የጸሎት አንድነትን በተመለከተ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ የጾምን ሥነ ሥርዓት መግለጽም እንደሚያስፈልግ በማመን እንደሚከተለው ለማስረዳት እንፈልጋለን፡፡

 • ጾም ማለት መሠረታዊ አሳቡ ምንም አለመብላትና አለመጠጣትን የሚያመለክት ነው፡፡ በእምነት መሠረትነት የሚፈጸመው ጾም ግን ከዚህ አባባል ፈጽሞ የተለየ ነው፡፡ ክርስቲያኖች ስንቀ ነፍስ ይሆናቸው ዘንድ የሚበላ የሚጠጣ ሳያጡ ፍትወተ ሥጋን ለማድከም ሲሉ ስለ ጽድቅ ይራባሉ፡፡ ይጠማሉ ለጽድቅ የሚራቡ ብፁዓን ናቸው ተብሎ ተነግሮላቸዋልና፤ (ማቴ. ፭÷፮)
 • ክርስቲያኖች በጾም ወራት ያላቸው ከሌላቸው ተካፍለው ይበላሉ፤ ለቁርሳቸው የታሰበውን አጠራቅመው ለነዳያን ይመጸውታሉ፤ (ማቴ. ፳፭÷፴፯፣ ምሳ. ፲፱)
 • ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጾምን ስንጾም ከቅባት ነክ ብቻ በመታቀብ ሳይሆን የኃጢአት ምንጮች ከሆኑ ነገሮች ሁሉ መራቅ፣ ሰውነትን ከሚያፈዙና ከሚያደነዝዙ፣ ከአልኮል መጠጦች ከጫትና ከሲጋራ ከዝሙትና ከስርቆት ከተንኰልና ከቂም በቀል በአጠቃላይ የኃጢአት አመንጪ ከሆኑ ነገሮች ሁሉ እንድንሸሽ ያስጠነቅቀናል፣ ይመክረናል፣ ያስተምረናል፣ ይመራናል፡፡
 • ልዑል እግዚአብሔር በነቢያቱ አድሮ ስለጾም ያናገረውንና ያጻፈውን ማንበቡና ማስተዋሉ ይጠቅማል፡፡ በነቢዩ በኢሳይያስ ያደረው መንፈስ ቅዱስ ለምን ጾምን አንተም አልተመለከትኸንም ሰውነታችንንስ ስለምን አዋረድን አንተም አላወቅኸንም ይላሉ ሲል የሰዎችን እምነት ልብና ሀሳብ ምን እንደሚመስል ከገለጸ በኋላ ጾመኞች ስላላቸው አመለካከት ሲገልጽ ደግሞ ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ ሠራተኛችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ እነሆ ለጥልና ለክርክር ትጾማላችሁ በግፍ ጡጫም ትማታላችሁ የሚል ሆኖ ይነበባለ፡፡ (ኢሳ. ፶፰÷፬-፱)
 • ከዚህም አያይዞ እኔ የምፈልገው ጾም ይህ ነውን? ጾማችሁንም ወደላይ ታሰሙ ዘንድ፣ የተገፉትንስ አርነት ትሰዱ ዘንድ፣ ቀንበሩንስ ትሠብሩ ዘንድ አይደለምን? እንጀራንስ ለተራበ ትቈርሱ ዘንድ፣ የተራቈተውንስ ታለብሰው ዘንድ ከሥጋ ዘመድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን? በማለት ስለ አጿጿም መልክና ይዘት፣ ሕግና ሥርዓት አብራርቶ አስረድቶአል፡፡ (ኢሳ. ፶፰÷፭-፲፫)
 • ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስም ስለጾም ሲያስረዳና የጾምን ትርጉም ሲያብራራ ግብዝነት የተመላበትን የፈሪሳውያንን እምነትና የጾማቸውን ሥርዓት ተመልክቶ የጾምን አፈጻጸም ከሥርዓቱና ከሕግጋቱ የራቀ መሆኑን በቅዱስ ወንጌሉ እንደነቀፋቸው ተጽፎአል፡፡ (ማቴ. ፲፰÷፲፪፣ ማቴ. ፯÷፲፯-፲፰)
 • ከሁሉ የበለጠ እምነት አለን የሚሉ ሐሳውያን ደግሞ በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ የተመሰከረለትና ጸንቶ የሚኖረውን ሥርዓተ ጾምን ሲነቅፉና ሲያናንቁ ይታያሉ፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለጾመልን እኛ መጾም አያስፈልገንም እያሉም ሲመጻደቁ ይሰማሉ፡፡ እነዚህ በጥቅም የታወሩ፣ በክህደት ሰንሰለት የታሠሩ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ከግራ እጃቸው፣ የማይለዩና የማታለያ ሠይፍን በቀኝ እጃቸው ጨብጠው በየመንደሩ እየዞሩ የሚያሳስቱ ተኩላዎች ሕገ እግዚአብሔርን የሚያፈርሱ ናቸው፡፡ በላይ ስለጾም ማስረጃ አድርገው የሚጠቅሱት ኃይለ ቃልም “ከሆድ የሚወጣውን እንጂ ወደ ሆድ የሚገባውን ሰውን አያረክሰውም” ብለው ነው፡፡ (ማቴ. ፲፭÷፲-፲፩)

 • ጌታችን ከሆድ የሚወጣ እንጂ ወደ ሆድ የሚገባው ሰውን

አያረክሰውም ያለው ስለምን እንደሆነ ሳይገነዘቡ ወይም የዋሆችን ለማደናገር ሲሉ፣ አለዚያም ራሳቸው አስተው ሌላውን በተሳሳተ መንገድ እየመሩ ወደ ዘለዓለም ጥፋት ለማስገባት የዘረጉት ወጥመድ እንጂ ጥቅሱ ስለጾም ፈጽሞ መሰል እንደሌለው ግልጽ ነው፡፡ ይህ ጥቅስ በእውነተኛ በትምህርተ ክርስትና ለጎለመሱ በተዋሕዶ ትምህርት ለተራቀቁና ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ ለላቁ፣ እጅግ አስቂኝና አስገራሚ ነው፡፡ በመሆኑም ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ቃል ለመናገርና ለማስረዳት የፈለገው ስለእጅ መታጠብና አለመታጠብ እንጂ ስለጾም አልነበረም፡፡

 • ፈሪሳውያን የጌታችን ደቀመዛሙርት እጃቸውን ሳይታጠቡ እንጀራ ሲበሉ አይተው እንደጥፋትና እንደኃጢአት አስቈጠሩባቸው ለአጭር አስተሳሰባቸው ሲመልስ ታጥበውም ሳይታጠቡም ቢበሉ ኃጢአት አለመሆኑን ያስረዳበት ታሪክ እንጂ ስለጾም እንዳልሆነ ለማስገንዘብ ነው፡፡ በተጨማሪም ሰው በቃሉ ተናግሮ በልብ ክፉ ሀሳብና ተንኰል አስቦ ፈጣሪን፣ ወገንን፣ ሰውን ተናግሮ ማስቀየም የማይገባ መሆኑን የተጠቀመበት አገላለጽ ነው፡፡
 • ጾም በዘመነ ብሉይም ሆነ በዘመነ ሐዲስ አባቶች ሲጠቀሙበት ከመኖራቸውም በላይ ለሁላችንም የነፍሳችን ፍቱን መድኃኒት መሆኑን ከፈጣሪያችንና ከአባቶቻችን አብነት ወስደናል፡፡ የጾማችን ፍቱንነትና ጠቃሚነትም ቅዱሳት መጻሕፍት በየክፍሉና በየምዕራፉ ይነግሩናል፡፡
 • ጾም ፍቅረ እግዚአብሔርን የሚገልጽ መሆኑን ያመለክታል፡፡ የሃይማኖት ፍሬም ነው፡፡ ለምእመናንም የእምነታቸው መመዘኛ ነው፡፡ የፍቅር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አርአያና ምሳሌ ሆኖ በገዳመ ቆሮንቶስ ፵ ቀን ፵ ሌሊት የጾመልን ጠቀሜታው ምን ያህል የላቀ መሆኑን በሚገባ እንድንረዳ ያደርገናል፡፡
 • ጾም ለእውነተኛ ክርስቲያን አጥርና ቅጥር ነው፡፡ ጽኑም መዝጊያ ነው፡፡ አጥር፣ ቅጥር ጠባቂ የሌለው ቤት ለቀጣፊና ለዘራፊ የተጋለጠ የመሆኑን ያህል ከጾምና ከጸሎት የራቀ ክርስቲያንም ለዲያብሎስና ለሠራዊቱ የተጋለጠ፣ የተመቻቸ ነው፡፡
 • ጾምና ጸሎት የእያንዳንዱ ክርስቲያን መንፈሳዊ ግዴታዎች፣ የመንፈስም ፍሬዎች ናቸው፤ ከነዚህ መንፈሳውያን መሣሪያዎች የተለየ ክርስቲያን እምነት አለኝ ቢል ውሸተኛ ነው፤ በነፍሱም የሞተ እንጂ ሕይወት አለኝ ለማለት አይችልም፡፡ (ያዕ. ፪÷፲፬-፳፣ ኢሳ. ፶፰÷፯-፲፪)
 • ክርስቲያኖች የእምነታቸው መገለጫ ከሆኑ ምግባራት መካከል ጾምና  ጸሎት  ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡  ስለሆነም

ጾማችንን በደስታና በተሰበረ ልብ ሆነን መጾም ይገባናል፡፡

 • ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናንተ እኔን አብነት አድርጋችሁ ከእምነትና ከትሩፋት ጋር ከጾማችሁ፣ ከጸለያችሁ አጋንንትን ድል ታደርጋላችሁ ብሎ ነው በምሳሌነት ጾሞ ያሳየን፣
 • በዚህም መሠረት ቤተ ክርስቲያናችን ሰባት አጽዋማት አሏት፡፡ እነርሱም፡-

፩ኛ/ ዐቢይ ጾም (ሁዳዴ ወይም ጾመ ኢየሱስ)

፪ኛ/ ጾመ ሐዋርያት (የጌታችን ደቀ መዛሙርት የጾሙት)

፫ኛ/ ጾመ ፍልሰታ (የእመቤታችን ፍልሰተ ሥጋ ሐዋርያት የጾሙት)

፬ኛ/ ጾመ ነቢያት (ጌታችንን ይወርዳል፣ ይወለዳል ሲሉ ነቢያት የጾሙት)

፭ኛ/ ጾመ ገሃድ (የጌታችን መገለጽ በማስታወስ የሚጾም)

፮ኛ/ ጾመ ነነዌ (የነነዌ ሰዎች ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት የጾሙት)

፯ኛ/ ጾመ ዐርብ፣ ሮብ ይህ ጾም መድኃኔዓለም ከዘመነ ብሉይ ጀምሮ ሲጾም የነበረ ብዙ አባቶች ብዙ ወገኖች ሲጠቅም የነበረ ጾም ነው፡፡

 • እስራኤላውያን ሲጾሙአቸው ከነበሩ አጽዋማት መካከል ዐርብና ሮብን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ከጌታ ልደት ጀምሮ ስታስፈጽመው ትገኛለች፡፡ (ሉቃ. ፲፰÷፲፪)
 • ሮብ፡- መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ተገርፎ፣ ተሰቅሎ እንዲሞት የተፈረደበት የተወሰነበት ቀን በመሆኑ ጌታ ለእኛ ሲል የተፈጸመበትን በደል እያስታወስን እንደሚለን፡፡
 • ዓርብ፡- የዓለም መድኃኒት ጌታ በግፍ መታሰሩን መገረፉን ረቀቱን በወንበዴዎች መሀል እንደሌባ መሰቀሉን መሞቱን መቀበሩን እና ሳይበድል የተበደለ ሳይገድል የተገደለ አምልክ መሆኑን በጾም የምናስብበት ቀን ነው፡፡ በአጠቃላይ ስለ ጾም ሕግጋት አፈጻጸም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሯል፡፡ እውነተኛውን ፍርዱ ፍረዱ ቸርነትንና ምሕረትን ሁላችሁ ለወንድሞቻችሁ አድርጉ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን መጻተኛውንና ችግረኛውን አትበድሉ ከእናንተም ማንም በወንድሙ ላይ ክፉውን ነገር አያስብ፡፡ ዘካ. ፯÷፭

“ቦኑ ጾመ ዘጾምክሙ ሊተ ጾምሰ አኮ ጸዊም እምኅብስት ወማይ ባሕቲቱ ይጹም ልሳንክሙ እምነገረ ውዴት ለእመ ኮንከ ዘኢትኪል ትጹም እመባልዕት ጹም እንከ እምኅሊናት እኩይ” (ከመብል ከመጠጥ መጾም ቢያቅትህ በሰዎች ላይ ክፉ ከማሰብ ጹም)

     ለብፁዕ አቡነ ሳሙኤል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን 

ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀጳጳስ

       አዲስ  አበባ